አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ጥቅምት 16–22 (እ.አ.አ) 1 እና 2 ተሰሎንቄ፦ “በእምነታችሁ የጎደለውን [ሙሉ]”


“ጥቅምት 16–22 (እ.አ.አ) 1 እና 2 ተሰሎንቄ፦ ‘በእምነታችሁ የጎደለውን [ሙሉ] የተባበራችሁ እንድትሆኑ’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ጥቅምት 16–22 (እ.አ.አ) 1 እና 2 ተሰሎንቄ፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
እህት ሚስዮናውያን ከወጣት ወንድ ጋር እያወሩ

ጥቅምት 16–22 (እ.አ.አ)

1 እና 2 ተሰሎንቄ

“በእምነታችሁ የጎደለውን [ሙሉ]”

ከመንፈስ የተቀበልናቸውን ግንዛቤዎች ካልመዘገብን ልንረሳቸው እንችላለን። 1 እና 2 ተሰሎንቄን ስታነቡ መንፈስ እንድትመዘግቡ የሚገፋፋችሁ ምንድን ነው?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በተሰሎንቄ ጳውሎስና ሲላስ “ዓለምን ያወኩ” (የሐዋርያት ሥራ 17፥6) በመባል ተከሰዋል። ስብከታቸው በአይሁዶች መካከል የተወሰኑ መሪዎችን አስቆጣ፣ እናም እነዚህ መሪዎች ሕዝቡን ወደ ሁከት አነሳሱ (የሐዋርያት ሥራ 17፥1–10ን ተመልከቱ)። በዚህ ምክንያት ጳውሎስና ሲላስ ተሰሎንቄን ለቀው እንዲወጡ ተመከሩ። ጳውሎስ ስለ ተሰሎንቄ አዲስ ተከታዮች እና ስለሚደርስባቸው መከራ ቢጨነቅም ተመልሶ ሊጠይቃቸው አልቻለም። “ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ … እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ” ብሎ ጻፈ። በምላሹ፣ በተሰሎንቄ ሲያገለግል የነበረው የጳውሎስ ረዳት ጢሞቴዎስ፣ “ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምስራች” አምጥቶልናል (1 ተሰሎንቄ 3፥5–6)። በእርግጥ፣ የተሰሎንቄ ቅዱሳን “[ለሚያምኑ] ሁሉ” (1 ተሰሎንቄ 1፥7) ምሳሌ በመባል ይታወቁ ነበር፣ እናም የእምነታቸው ዜና ወደ ውጭ ከተሞች ተሰራጨ። በመካከላቸው ያለው ሥራ “ከንቱ እንዳልሆነ” (1 ተሰሎንቄ 2፥1) በመስማቱ የጳውሎስን ደስታ እና እፎይታ አስቡ። ነገር ግን ጳውሎስ ቀደም ሲል ታማኝነት ለወደፊት መንፈሳዊ ሕልውና በቂ አለመሆኑን ያውቅ ነበር፣ እናም በቅዱሳን መካከል ስላሉ የሐሰት መምህራንን ተጽዕኖ ይጠነቀቅ ነበር (2 ተሰሎንቄ 2፥2–3ን ተመልከቱ)። ለእነሱ እና ለእኛ ያለው መልእክት “በእምነታችን የጎደለውን [መሙላት]” እንድንቀጥል እና በፍቅር “[እንድንበዛ]” ነው (1 ተሰሎንቄ 3፥104፥10ን ይመልከቱ)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

1 ተሰሎንቄ 1–2

የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሌሎችን በቅንነትና በፍቅር ያገለግላሉ።

1 ተሰሎንቄ፣ ውስጥ የጳውሎስ ቃላት የእግዚአብሄርን ልጆች ለማገልገል ራሱን ሙሉ በሙሉ የሰጠን ሰው አሳቢነት እና ደስታ ያሳያል። በተለይ በ1 ተሰሎንቄ፣ የመጀመሪያ ሁለት ምዕራፎች ውስጥ የጌታን ደቀ መዝሙር ዝንባሌ እና ድርጊት የሚገልጹ ቃላትን እና ሀረጎችን ታገኛላችሁ። ለምሳሌ ከ 1 ተሰሎንቄ 1፥5–82፥1–13 ጌታን ስለማገልገል ምን ትማራላችሁ?

እግዚአብሔርን እና ልጆቹን ለማገልገል ያላችሁን እድሎች አስቡ። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ አገልግሎታችሁን እንድታሻሽሉ የሚያነሳሷችሁን ምን ታገኛላችሁ? ባገኛችሁት ነገር ላይ በመመስረት እራሳችሁን ለመጠየቅ አስቡ፤ ለምሳሌ “እኔ ለማውቃቸው ነገሮች ምሳሌ ነኝን?” (1 ተሰሎንቄ 1፥7ን ተመልከቱ)።

1 ተሰሎንቄ 3፥7–134፥1–12

“ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም”

ጳውሎስ በተሰሎንቄ ቅዱሳን ታማኝነት ተደሰተ (1 ተሰሎንቄ 3፥7–9ን ተመልከቱ)። ነገር ግን እርሱ ደግሞ በዚያ ታማኝነት “[ይበዙ] ዘንድ” (1 ተሰሎንቄ 4፥1) ይፈልጋል። 1 ተሰሎንቄ 3፥7–134፥1–12ን ስታነቡ በመንፈሳዊነት “[መብዛት]” የምትችሉባቸውን መንገዶች አሰላስሉ (1 ተሰሎንቄ 4፥10)። ለምሳሌ፣ ጳውሎስ እንደ “ቅድስና” እና “መቀደስ” ያሉ ቃላትን እንደተጠቀመ ልብ በሉ። ስለ እነዚህ ቃላት ትርጉም ከጳውሎስ ጽሑፎች ምን ትማራላችሁ? የበለጠ ቅዱስ እና የተቀደሳችሁ እንድትሆኑ አዳኙ እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል?

በተጨማሪም የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ፣ “ቅዱስ፣” “መቀደስ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

1 ተሰሎንቄ 4፥16–185፥1–102 ተሰሎንቄ 1፥4–10

ታማኝ እና ንቁ ከሆንኩ ለአዳኙ ዳግም ምጽአት እዘጋጃለሁ።

1 ተሰሎንቄ 5፥1–10፣ ውስጥ፣ ጳውሎስ ኢየሱስ ወደ ምድር ስለሚመለስበት ጊዜ ለማስተማር በርካታ ዘይቤዎችን ተጠቅሟል። እነዚህን ዘይቤዎች በምታጠኑበት ጊዜ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት የሚመጡትን ግንዛቤዎች ለመፃፍ አስቡ።

  • “በሌሊት [የሚመጣ] ሌባ”፦

  • “ምጥ [የያዛት] እርጉዝ”፦

  • ሌሎች ያገኛችሁት ዘይቤዎች፦

1 ተሰሎንቄ 4፥16–185፥1–102 ተሰሎንቄ 1፥4–10ምን ተጨማሪ እውነቶች ትማራላችሁ? ለአዳኙ መምጣት ለመንቃት እና ለመዘጋጀት ምን እንድታደርጉ ተነሳስታችኋል?

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን “ለጌታ መመለስ መዘጋጀት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 81–84።

2 ተሰሎንቄ 2።

ክህደት፣ ወይም ከእውነት መራቅ፣ ከሁለተኛው ምጽዓት አስቀድሞ እንደሚመጣ ተነግሯል።

እየጨመረ በሄደ መከራ መሃል ብዙ የተሰሎንቄ ቅዱሳን የአዳኙ ዳግም ምጽዓት መቅረብ አለበት ብለው ያምኑ ነበር። ነገር ግን ጳውሎስ ኢየሱስ ወደ ምድር ከመመለሱ በፊት ክህደት— አመፅ ወይም ከእውነት “መራቅ” እንደሚከሰት ያውቅ ነበር(2 ተሰሎንቄ 2፥1–4ን ተመልከቱ)። ከሚከተሉት ውስጥ አንዳንዶቹን በማሰላሰል ስለ ታላቁ ክህደት ያላችሁን ግንዛቤ እና ስለ ዳግም መመለስ ያላችሁን አድናቆት በጥልቀት ማሳደግ ትችላላችሁ።

  • ስለ ክህደት አስቀድሞ የተናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍት፤፦ ኢሳይያስ 24፥5አሞጽ 8፥11–12ማቴዎስ 24፥4–142 ጢሞቴዎስ 4፥3–4

  • በጳውሎስ ዘመን ክህደትን ተጀምሮ እንደነበር የሚያሳዩ ቅዱሳት መጻሕፍት፦ የሐዋርያት ሥራ 20፥28–30ገላትያ 1፥6–71 ጢሞቴዎስ 1፥5–7

  • ስለ ታላቁ ክህደት በክርስቲያናዊ ተሃድሶዎች ላይ የተደረጉ ምልከታዎች

    ማርቲን ሉተር፦ “ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር በሚስማማ መልኩ ቤተክርስቲያንን ከማሻሻል ውጭ ምንም አልፈለግሁም። … በቀላሉ እኔ የምለው ክርስትና ሊጠብቁት ከሚገቡት መካከል እንደሌለ ነው” (በኢ. ጂ. ሽዌበርት ሉተር እና የእሱ ጊዜያት፦ ተሃድሶ ከአዲስ እይታ (1950 [እ.አ.አ]፣ 590)።

    ሮጀር ዊሊያምስ፦ “ክህደቱ … ክርስቶስ እንደገና አዲስ አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል አዲስ ሐዋርያትን እስከሚልክ ድረስ ከዚያ ክህደት ማገገም እንዳይቻል ሁሉንም አበላሽቷል” (በፊሊፕ ሻፍ የሕዝበ ክርስትና የሃይማኖት መግለጫዎች 1877 [እ.አ.አ]፣ 851)።

በተጨማሪም 2 ኔፊ 28፤ የወንጌል ርዕሶች፣ “ክህደት፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgን ተመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

1 ተሰሎንቄ 3፥9–13ጳውሎስ ለወዳጆቹ ስለነበረው ስሜት ምን ያስደንቃችኋል? “እርስ በእርሳችን ያለንን … ፍቅር ማብዛት እና መጨመር” የምንችለው እንዴት ነው? (ቁጥር 12)።

1 ተሰሎንቄ 4፥13–18በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለ ትንሣኤ የትኞቹ ሐረጎች መጽናናት ይሰጧችኋል?

1 ተሰሎንቄ 5፥14–251 ተሰሎንቄ 5፥14–25፣ ያለውን የጳውሎስን ምክር ስትቃኙ፣ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ቤተሰቡ ሊያተኩርበት የሚችል ሐረግ እንዲያገኝ ጋብዙ። እነዚህን ሐረጎች እንደ ማስታወሻ በቤታችሁ ውስጥ ለማሳየት የፈጠራ መንገዶችን አግኙ። ለምሳሌ፣ እያንዳንዱ ሰው እሱ ወይም እሷ የመረጠውን ሐረግ የሚያሳዩ ወይም የሚያጠናክሩ ስዕሎችን ሊያገኝ ወይም ሊስል ይችላል።

2 ተሰሎንቄ 3፥13በደቀመዝሙርነት ከሚጠይቀው የተነሳ “መልካም ሥራን መሥራት [አታካች]” መስሎ ተሰምቶን ያውቃል? እንዲህ ሲሰማን ምን ይረዳናል? (ገላትያ 6፥9ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥33ን ተመልከቱ።) ይህ በሚሆንበት ጊዜ እርስ በእርስ መደጋገፍ የምንችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “እንደ ኢየሱስ ለመሆን እየሞከርኩ ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 78–79።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በየቀኑ መገለጥን ይፈልጉ። “ራዕይ ብዙውን ጊዜ ‘ትዕዛዝ ላይ ትዕዛዝ’ይመጣል (2 ኔፊ 28፥30)፣ ሁሉም በአንድ ጊዜ አይደለም። … የወንጌል ጥናት ጊዜ የምትመድቡለት ነገር ሳይሆን ሁሌም የምታደርጉት ነገር እንደሆነ አድርጋችሁ አስቡ (በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 12)።

ምስል
ክርስቶስ በደመና ውስጥ

ትንሳኤ ያደረገው ክርስቶስ፣ በሮበርት ቲ ባሬት

አትም