አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ)
ነሐሴ 7፟–13 (እ.አ.አ)። ሮሜ 1–6፦ “የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን”


“ነሐሴ 7–13 (እ.አ.አ)። ሮሜ 1–6፦ ‘የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን’” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ አዲስ ኪዳን 2023 (እ.አ.አ) [2022 (እ.አ.አ)]

“ነሐሴ 7–13 (እ.አ.አ)። ሮሜ 1–6፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2023 (እ.አ.አ)

ምስል
ጳውሎስ ደብዳቤ እየጻፈ

ነሐሴ 7–13 (እ.አ.አ)

ሮሜ 1–6

“የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን”

ያደረባችሁን መነሳሳት መመዝገብ መንፈስ የሚያስተምረውን እንድታስታውሱ ይረዳችኋል። እንዲሁም ስለእነዚህ ማበረታቻዎች ምን እንደሚሰማችሁም ለመመዝገብ አስቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ጳውሎስ የተለያዩ የአይሁዶች እና የአህዛብ ቡድን ለሆኑት ለሮሜ ቤተክርስቲያን አባላት መልእክቱን በጻፈበት ጊዜ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ከገሊላ ከትንሽ አማኞች ቡድን በላይ አድጋ ነበር። ከአዳኙ ትንሣኤ በኋላ ወደ 20 ዓመታት ገደማ፣ የሃያሏ ግዛት ዋና ከተማ ሮምን ጨምሮ፣ ሐዋርያቱ ሊጓዙባቸው በሚችሉባቸው ቦታዎች ሁሉ የክርስቲያኖች ጉባኤዎች ነበሩ። አሁንም፣ ከሮሜ ግዛት ስፋት ጋር ሲነፃፀር፣ ቤተክርስቲያኗ ትንሽ ነበረች እና ብዙውን ጊዜ መከራ ይደርስባት ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ አንዳንዶች “[በክርስቶስ] ወንጌል [እፍረት]” ሊሰማቸው ይችላል፣ ነገር ግን ጳውሎስ አይደለም። እውነተኛ ኃይል “ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን” (ሮሜ 1፥16) በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ውስጥ እንደሚገኝ ያውቅና ይመሰክር ነበር።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

መልእክቶች ምንድን ናቸው፣ እና እንዴት ተደራጁ?

መልእክቶቹ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሚገኙ ቅዱሳን በቤተክርስቲያን መሪዎች የተጻፉ ደብዳቤዎች ናቸው። ሐዋርያው ጳውሎስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ አብዛኞቹን መልእክቶች ጽፏል—ከሮሜ ጀምሮ እስከ ዕብራውያን ድረስ። የእሱ መልእክቶች በዕብራይስጥ ካልሆነ በቀር በርዝመታቸው የተደራጁ ናቸው (በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት “የጳውሎሳዊ መልዕክቶች”ን ተመልከቱ)። ሮሜ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የመጀመሪያው መልእክት ቢሆንም፣ በእርግጥ የተጻፈው የጳውሎስ ሚስዮናዊ ጉዞዎች መጨረሻ አካባቢ ነው።

ሮሜ 1–6

“ጻድቅ በእምነት ይኖራል”

የሚከተሉት ትርጓሜዎች የሮሜ መልእክትን በተሻለ ለመረዳት ይረዳችኋል፦

ሕጉ።ጳውሎስ ስለ “ሕጉ” ሲጽፍ ስለ ሙሴ ሕግ ማለቱ ነበር። በጳውሎስ ጽሑፎች ውስጥ “ስራ” የሚለው ቃል ከሙሴ ሕግ ጋር የተያያዙ ውጫዊ ድርጊቶችን ያመለክታል። በሮሜ 3፥23–31፣ ከተገለጸው “የእምነት ህግ” ከሙሴ ሕግ እና በእሱ ሥር የሚፈለጉ ሥራዎች እንዴት እንደሚለዩ አስቡ።

መገረዝ፣ አለመገረዝ።በጥንት ጊዜ መገረዝ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን ምልክት ነበር። ጳውሎስ “መገረዝ” የሚለውን ቃል አይሁዶችን (የቃል ኪዳኑን ሕዝብ) እና “አለመገረዝን” የተጠቀመው ደግሞ አሕዛብን ለማመልከት ነው። ሮሜ 2፥25–29 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕዝብ መሆን የእውነት ምን ማለት እንደሆነ የሚያስተምረውን አሰላስሉ። መገረዝ ከእንግዲህ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባው ቃል ኪዳን አለመሆኑን ልብ በሉ (የሐዋርያት ሥራ 15፥23–29ን ተመልከቱ)።

መጽደቅ፣ ማፅደቅ፣ የጸደቀ።እነዚህ ቃላት የሚያመለክቱት የኃጢአትን ስርየት ወይም ይቅርታን ነው። ስንጸድቅ ይቅር እንባላለን፣ ጥፋተኛ አንሆንም፣ እናም ለኃጢአቶቻችን ከዘላለም ቅጣት ነፃ እንወጣለን። እነዚህን ቃላት ስታዩ፣ ማጽደቅ ስለማስቻል ጳውሎስ ያስተማረውን አስተውሉ (በተጨማሪ የቅዱሳት መጻሕፍት መመሪያን፣ “መጽደቅ፣ ማጽደቅ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ዲ. ቶድ ክርስቶፈርሰን፣ “መጽደቅ እና መንጻት፣” ኢንዛይን፣ ሰኔ 2001 (እ.አ.አ) 18–25ን ተመልከቱ)። በሮሜ ውስጥ እንደ “ጻድቅ” እና “ጽድቅ” ያሉ ቃላት እንደ “ትክክለኛ” እና “መጽደቅ” ለሚሉት ተመሳሳይ ቃላት ሆነው ሊታዩ ይችላሉ።

ጸጋ።ጸጋ “በኢየሱስ ክርስቶስ የተትረፈረፈ ምሕረት እና ፍቅር የተሰጠ መለኮታዊ … እርዳታ ወይም ጥንካሬ” ነው። በጸጋ፣ ሁሉም ሰዎች ከሞት ተነስተው ያለመሞትን ይቀበላሉ። በተጨማሪም፣ “ፀጋ ወንዶች እና ሴቶች የራሳቸውን ጥረት ሁሉ ካደረጉ በኋላ የዘላለም ሕይወትን እና ከፍ ከፍ መደረግን እንዲያገኙ የሚያስችል ኃይል ነው።” በእኛ ጥረት ጸጋን አናገኝም፤ ይልቁንም “[እኛ] በራሳችን ልንተገብራቸው የማንችላቸውን መልካም ሥራዎች ለመሥራት ጥንካሬ እና እርዳታ” የሚሰጠን ጸጋ ነው (የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “ጸጋ”፤ በተጨማሪም 2 ኔፊ 25፥23፤ ዲተር ኤፍ. ኡክዲርፍ “የጸጋ ስጦታ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ) 107–10፤ ብራድ ዊልኮክስ “ጸጋው በቂ ነው፣” ሊያሆና፣ መስከረም፣ 2013 (እ.አ.አ)፣ 43–45ን ተመልከቱ)። ሮሜን በምታነቡበት ጊዜ፣ ስለ አዳኙ ጸጋ የተማራችሁትን መዝግቡ።

ሮሜ 2፥17–29

የእኔ ተግባሮች የእኔን መለወጥ ማንፀባረቅ እና ማሳደግ አለባቸው።

በሮም የሚኖሩ አንዳንድ የአይሁድ ክርስቲያኖች አሁንም የሙሴ ሕግ ሥርዓቶች መዳንን ያመጣሉ ብለው ያምኑ ነበር። እኛ በሙሴ ሕግ ስለማንኖር ይህ ከእንግዲህ የማይተገበር ችግር ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የጳውሎስን ጽሑፎች ስታነቡ፣ በተለይም ሮሜ 2፥17–29፣ ወንጌልን ለመኖር የራሳችሁን ጥረት አስቡ። ቅዱስ ቁርባንን እንደመውሰድ ወይም ቤተመቅደስ እንደመሄድ ያሉ ውጫዊ ተግባሮች መለወጣችሁን ጥልቅ የሚያደርጉ እና በክርስቶስ ላይ ያላችሁን እምነት የሚያጠነክሩ ናቸው? (አልማ 25፥15–16ን ተመልከቱ)። ውጫዊ ድርጊቶቻችሁ ወደ ልብ ለውጥ እንዲመሩ መቀየር ያለባችሁ ነገር አለ?

በተጨማሪም ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “ለመሆን ተግዳሮቶች፣” ኢንዛይን፣ ህዳር 2000 (እ.አ.አ)፣ 32–34ን ተመልከቱ።

ሮሜ 3፥10–31፤ 5

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፣ ለኃጢአቴ ይቅርታን አገኛለሁ።

ጳውሎስ “ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ” (ሮሜ 3፥10) በማለት በድፍረት በተናገረው ቃል አንዳንድ ሰዎች ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። ነገር ግን በሮሜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ መልእክቶችም አሉ። ምእራፍ 3 እና 5፣ ላይ ፈልጓቸው እናም “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል” (ሮሜ 3፥23) የሚለውን ማስታወስ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ባለው “ተስፋ [መመካት]” (ሮሜ 5፥2) ለመማር አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን አስቡ።

ሮሜ 6

ኢየሱስ ክርስቶስ “በአዲስ ሕይወት እንድመላለስ” ጋብዞኛል።

ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አኗኗራችንን መለወጥ እንዳለበት አስተምሯል። በሮሜ 6 ላይ ያሉት ዓረፍተ ነገሮች አዳኙን መከተል “በአዲስ ሕይወት [እንድትመላለሱ]” (ቁጥር 4) እንዴት እንደሚረዳችሁ የሚገልጹት የትኞቹ ናቸው?

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳት መጻህፍት ጥናትና ለቤተሰብ የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሮሜ 1፥16–17“በክርስቶስ ወንጌል [እንደማናፍር]” እንዴት ማሳየት እንችላለን?

ሮሜ 3፥23–28እነዚህን ጥቅሶች በምታነቡበት ጊዜ፣ እኛ የእግዚአብሔርን ጸጋ “በብቃት ማግኘት” ፈጽሞ ልናደርገው የማንችለውን እና በመቀበል መካከል ያለውን ልዩነት ልትወያዩ ትችላላሁ። የእግዚአብሔር ጸጋ መቼ ተሰማን? ይበልጥ በሙላት እንዴት ልንቀበለው እንችላለን?

ሮሜ 5፥3–5ምን ዓይነት መከራዎች ደርሰውብናል? እነዚህ መከራዎች ትዕግሥትን፣ ልምድን እና ተስፋን እንድናዳብር የረዱን እንዴት ነው?

ሮሜ 6፥3–6በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ጳውሎስ ስለ ጥምቀት ምሳሌነት ምን አለ? ምናልባት ቤተሰባችሁ በሚመጣ ጥምቀት ላይ ለመገኘት አቅዶ ይሆናል። ወይም የቤተሰብ አባላት የጥምቀታቸው እለት ፎቶን ወይም ትውስታዎች ማካፈል ይችላሉ። የጥምቀት ቃል ኪዳኖቻችንን መፈጸምና መጠበቅ “በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ” የሚረዳን እንዴት ነው?

ምስል
አንድ ሰው ሌላውን በሐይቅ ሲያጠምቅ

ጥምቀት እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙርነት አዲስ ሕይወት መጀመርን ያመለክታል።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት ዝርዝርኑ፣ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍል ተመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “እኔ ስጠመቅ፣” የልጆች የመዝሙር መጻፍ፣ 103።

የግል ጥናትን ማሻሻል

በምታጠኑበት ጊዜ ጥያቄዎችን ጠይቁ። ቅዱሳት መጻህፍትን ስታጠኑ ጥያቄዎች ወደ አዕምሯችሁ ሊመጡ ይችላሉ። እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና መልሶችን ፈልጉ። ለምሳሌ በሮሜ 1–6 “ጸጋ ምንድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልሶችን መፈለግ ትችላላችሁ።

ምስል
ክርስቶስ ሴት ልጅን ከጅረት ከፍ ሲያደርግ

አትፍራ፣ በግሬግ ኬ. ኦልሰን

አትም