ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፦ ቃል ኪዳን


”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፦ ቃል ኪዳን፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) 2021 (እ.አ.አ)

”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች ፦ ቃል ኪዳን፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

የሃሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች

ቃል ኪዳን

በመላው ብሉይ ኪዳን ቃል ኪዳንየሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ታነባላችሁ። ዛሬ አብዛኛውን ጊዜ ቃልኪዳኖችን ከእግዚያብሄር ጋር እንደተደረጉ የተቀደሱ የተስፋ ቃላት እናስባቸዋለን፤ ነገር ግን በጥንት አለም ቃልኪዳኖች የሰዎች የእርስ በርስ መስተጋብር አስፈላጊ ክፍሎች ነበሩ። ለደህንነታቸው እና ለመኖር ሰዎች እርስ በርስ መተማመን አስፈለጋቸው እናም ቃልኪዳኖች ያንን እምነት የሚያረጋግጡባቸው መንገዶች ነበሩ።

ስለዚህ እግዚያብሄር ከኖህ ፣ከአብርሃም ወይም ከሙሴ ጋር ስለ ቃልኪዳን በተነጋገረ ጊዜ ከእርሱ ጋር መተማመን ያለበት ወዳጅነት ውስጥ እንዲገቡ እየጋበዛቸው ነበር። በብሉይ ኪዳን ውስጥ ካሉ የቃልኪዳን ምሳሌዎች በጣም የታወቀው እግዚያብሄር ከአብርሃም እና ከሳራ ጋር ያደረገው ነው—አናም ከዚያ ከዘሮቻቸው ከይስሃቅ እና (እስራኤልም ተብሎ ከሚጠራው) ከያዕቆብ ጋር አደሰው። አብዛኛውን ጊዜ ይህንን የአብርሃም ቃል ኪዳን ብለን እንጠራዋለን፤ ምንም እንኳን በብሉይ ኪዳን በቀላሉ “ቃልኪዳን” ተብሎ ይታወቅ የነበረ ቢሆንም፡፡ ብሉይ ኪዳን በመሰረቱ ራሳቸውን የዚህ ቃል ኪዳን ወራሾች—የቃልኪዳን ህዝቦች አድርገው የሚያዩ ህዝቦች ታሪክ እንደሆነ ታያላችሁ።

የአብርሃም ቃል ኪዳን ዛሬም አስፈላጊ እንደሆነ ቀጥሏል፤በተለይ ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን። ለምን? ምክንያቱም በቀጥታ የአብርሃም፣የይስሃቅ እና የያዕቆብ ዘሮች ብንሆንም ባንሆንም እኛም የቃል ኪዳኑ ህዝቦች ነን።( ገላትያ 3፥27–29ን ይመልከቱ) በዚህ ምክንያት የአብርሃም ቃል ኪዳን ምን እንደሆነ እና ለእኛም ዛሬ እንዴት እንደሚሆን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።

የአብርሃም ቃል ኪዳን ምንድን ነው?

አብርሃም “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ ለመሆን“ ፈለገ።(አብርሃም 1፥2) አብርሃም ይህ ፍላጎት ሲያድርበት የመጀመሪያው አልነበረም ፤ እንዲሁም ቃልኪዳን ለመቀበልም የመጀመሪያው አልነበረም። “የአባቶችን በረከቶች“ (አብርሃም 1፥2)—ለአዳም እና ለሄዋን እንዲሁም ከዚያ በኋላ እነዚህን በረከቶች በትጋት ለፈለጉ በቃል ኪዳን የተሰጡ በረከቶችን ፈለገ።።

እግዚያብሄር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን የአስደናቂ በረከቶችን ተስፋ ይሰጣል: የመሬት ውርስ፣ታላቅ ህዝብ፣የክህነት ስርዐቶችን መቀበለል እና በመጪው ትውልድ ሁሉ ክብር የሚሰጠው ስም። ነገር ግን የዚህ ቃል ኪዳን ትኩረት አብርሃም እና ቤተሰቡ በሚቀበሏቸው በረከቶች ላይ ብቻ አልነበረም ፤ነገር ግን ለተቀሩት የእግዚያብሄር ልጆች በሚሆኑት በረከት ላይም እንጂ። “ለበረከት ትሆናለህ “ አለ እግዚያብሄር “ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ“(ኦሪት ዘፍጥረት 12፥2–3)።

እነዚህ ቃል ኪዳኖች ለአብርሃም፣ለሳራ እና ለትውልዳቸው ከእግዚያብሄር ልጆች መካከል ልዩ የመብት ደረጃ ሰጥቷቸው ነበር? ሌሎችን የመባረክ መብት ከመሆኑ አንጻር ብቻ ነው፡፡ የአብርሃም ቤተሰብ “በደህንነት በረከቶች እንዲሁም ለዘላለም ህይወት በሆኑት የወንጌል በረከቶችን “ በማካፈል “ይህንን አገልግሎት እና ክህነት ለሁሉም ህዝቦች ይዘው መሄድ“ ነበረባቸው(አብርሃም 2፥9፣ 11)፡፡

ይህ ቃል ኪዳን አብርሃም ሲጠብቀው የኖረው በረከት ነበር፡፡ ከተቀበለው በኋላ አብርሃም በልቡ “ አገልጋይህ በትኩረት ፈልጎህ ነበር አሁን አገኘሁህ“ አለ፡፡(አብርሃም 2፥12)

ያ ከሺህ አመታት በፊት ነበር፤ነገር ግን ይህ ቃልኪዳን በእኛ ዘመን ዳግም ተመልሷል( 1 ነኔፊ 22፥8–12ይመልከቱ፡፡) እናም በአሁኑ ጊዜ በእግዚያብሄር ህዝቦች ህይወት እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ የእግዚያብሄር ስራ በአለም ዙሪያ ያሉ ቤተሰቦችን እየባረከ እያደገ ሲሄድ በርግጥ የቃል ኪዳኑ ፍጻሜ በኋለኞቹ ቀናት እየተፋጠነ ነው፡፡ እናም ማንም እንደአብርሃም ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን ቢፈልግ፣ማንም ጌታን በትጋት ቢፈልግ የእርሱ አካል ሊሆን ይችላል፡፡

ቤተሰብ በቤተመቅደስ ፊት ለፊት

የአብርሃም ቃል ኪዳን ለእኔ ምን ማለት ነው?

እናንተ የቃል ኪዳኑ ልጆች ናችሁ። በተጠመቃችሁ ጊዜ ከእግዚያብሄር ጋር ቃል ኪዳን ገብታችኋል፡፡ ከቅዱስ ቁርባኑ በምትካፈሉበት ጊዜ ሁሉ ያንን ቃል ኪዳን ታድሳላችሁ፡፡ በቤተመቅደስ ውስጥም የተቀደሰ ቃልኪዳን ታደርጋላችሁ፡፡ በአንድ ላይ እነዚህ ቃል ኪዳኖች በሙላት በቤተመቅደስ ስርአቶች በሚገኘው በአብርሃም ቃል ኪዳን ተሳታፊ ያደርጓችኋል፡፡ ፕሬዚዳንት ራሰል ኤም. ኔልሰን እንደተናገሩት “በመጨረሻም በቅዱስ ቤተመቅደስ ለአብርሃም፣ለይስሃቅ እና ለዘሮቻቸው ቃል እንደተገባው የዘላለም ቤተሰብ በረከቶች ጣምራ ወራሽ ልንሆን እንችላለን፡፡”1

በእነዚህ ቃል ኪዳኖች እና ስርአቶች አማካኝነት የእግዚያብሄር ህዝቦች እንሆናለን፡፡( ኦሪት ዘጸአትኦሪት ዘዳግም 7፥626፥18ትንቢተ ህዝቅኤል 11፥20ይመልከቱ)፡፡ በዙሪያችን ካለው አለም የተለየን እንሆናለን፡፡ ቃል ኪዳኖቻችን እውነተኛ፣ቁርጠኛ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንድንሆን ያስችሉናል፡፡ ፕሬዚዳንት ኔልሰን “ቃል ኪዳኖቻችን ከእርሱ ጋር ያስተሳስሩናል እንዲሁም አምላካዊ ሃይል ይሰጡናል“ ሲሉ አብራርተዋል፡፡ 2 እናም እግዚያብሄር ህዝቦቹን በሃይሉ ሲባርክ ሌሎችን እንዲባርኩ በመጋበዝ እና በመጠበቅ ነው—ለ“ሁሉም የምድር ቤተሰቦች“ “በረከቶች“ ይሆናሉ፡፡(አብርሃም 2፥9, 11)፡፡

ይህ የአብርሃም ቃል ኪዳን በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ዳግም በመመለሱ ሳቢያ ለእኛ የተሰጠን ውድ እውቀት ነው። ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስለቃል ኪዳን ስታነቡ እግዚያብሄር ከአብርሃም፣ከይስሃቅ እና ከያዕቆብ ጋር ብቻ ስለነበረው ግንኙነት አታስቡ፡፡ ከናንተ ጋር ስላለውም ግንኙነት አስቡ፡፡ እንደምድር አሸዋ ስለሚሆኑት ዘሮች ( ኦሪት ዘፍጥረት 28፥14ይመልከቱ) ስታነቡ ዛሬ አብርሃምን አባታችን ስለሚሉት ስለሚልዮኖቹ ብቻ አታስቡ፡፡ በተጨማሪም እግዚያብሄር ለእናንተ የገባውን የዘላለማዊ ቤተሰብ እና የዘላለማዊ እድገት ቃልኪዳንን አስቡ( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 131፥1–4132፥20–24ይመልከቱ)፡፡ ስለውርስ ምድር ቃል ኪዳን ስታነቡ ለአብርሃም ቃል ኪዳን ስለተገባለት ምድር ብቻ አታስቡ፡፡ የመሬትን የራሷን የሰለስቲያል ፍጻሜም አስቡ— ”ጌታን ለሚጠብቁ” ”የዋሆች” የተገባ የውርስ ቃል ኪዳን(ማቴዎስ 5፥5መዝሙር 37፥9, 11፤ በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 88፥17–20ን ይመልከቱ)፡፡ እናም የእግዚያብሄር የቃል ኪዳን ህዝቦች “የምድርን ቤተሰቦች ሁሉ“ (አብርሃም 2፥11)ይባርካሉ ስለሚለው ስታነቡ ስለአብርሃም አገልግሎት ወይም ከእርሱ የዘር ሃረግ ስለመጡት ነቢያት ብቻ አታስቡ፡፡ እንደኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተከታዮች—በዙሪያችሁ ላሉ ቤተሰቦች በረከት ለመሆን—ምን ልታደርጉ እንደምትችሉም አስቡ፡፡

ማስታወሻዎች

  1. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ቃል ኪዳኖች፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2011(እ.አ.አ)፣ 88፡፡

  2. ራስል ኤም. ኔልሰን፣“Drawing the Power of Jesus Christ into Our Lives”ሊያሆና፣ ግንቦት 2017 (እ.አ.አ)፣ 41። ፕሬዚዳንት ሊንዳ ኬ.በርተን እንዲህ ብለዋል “ቃል ኪዳኖችን መግባት እና መጠበቅ ማለት ራሳችንን ከሰማይ አባታችን እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለማጣመር መምረጥ ማለት ነው፡፡ አዳኙን ለመከተል ቁርጠኛ መሆን ማለት ነው“ (“The Power, Joy, and Love of Covenant Keeping፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013(እ.አ.አ)፣ 111)፡፡