ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የካቲት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 24–27፦ ቃል ኪዳኑ ታድሷል


“የካቲት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 24-27፤ ቃል ኪዳኑ ታድሷል፣“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“የካቲት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 24-27፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦2022 (እ.አ.አ)

ርብቃ

የርብቃ ምስል በዳይሊን ማርሽ

የካቲት 21–27 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 24–27

ቃል ኪዳኑ ታድሷል

ኦሪት ዘፍጥረት 24–27ን ስታነቡ ለምትቀበሏቸው መንፈሳዊ ግንዛቤዎች ትኩረት ስጡ፡፡ የምታገኟቸው መርሆች ከህይወታችሁ ጋር እንደሚገናኙ ለማወቅ ጸልዩ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እግዚያብሄር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃልኪዳን በአብርሃም እና በዘሮቹ አማካኝነት “ ሁሉም የምድር ቤተሰቦች ይባረካሉ“(አብርሃም 2፥ 11) የሚለውን ተስፋ ይጨምር ነበር። ያ በአንድ ትውልድ ሊፈጸም የሚችል ተስፋ አይደለም፦ በብዙ መንገዶች፣ መጽሃፍ ቅዱስ በመካሄድ ላይ ያሉ የእግዚያብሄር የተስፋዎች አፈጸጸም ታሪክ ነው። እናም ከይስሃቅ እና ከርብቃ ቤተሰብ ጋር ቃል ኪዳኑን በማደስ ጀመረ። በእነሱ ተሞክሮዎች አማካኝነት የቃል ኪዳኑ አካል ስለመሆን የተወሰነ ነገር እንማራለን። ምሳሌነታቸው ስለደግነት፣ስለትዕግሰት እና እግዚያብሄር ተስፋ በሰጣቸው በረከቶች ላይ እምነት ስለመጣል ያስተምረናል። እናም የእግዚያብሄርን በረከቶች ለራሳችን እና ለልጆቻችን እስከሚመጣው ትውልድ ለማረጋገጥ አለማዊ “ብልጭልጭ ነገርን“ኦሪት ዘፍጥረት 25፥30መተው የሚያዋጣ እንደሆነ እንማራለን።

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 24

ጋብቻ ለእግዚያብሄር ዘላለማዊ እቅድ አስፈላጊ ነው።

ዛሬ ዛሬ ብዙ ሰዎች ትዳርን አነስተኛ ቅድሚያ ያለው አልፎ ተርፎም ሸክም ያደርጉታል። አብርሃም የተለየ እይታ ነበረው—ለእሱ የልጁ የይስሃቅ ጋብቻ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነበር። ለእሱ በጣም አስፈላጊ የነበረው ለምን ይመስላችኋል? ክፍል 24ን ስታነቡ በእግዚያብሄር የደህንነት እቅድ ውስጥ የጋብቻን አስፈላጊነት አስቡ፡፡ የሽማግሌ ዲ.ቶድ ክሪስቶፈርሰንን “ጋብቻ ለምን፣ቤተሰብ ለምን” (ሊያሆና ግንቦት 2015(እ.አ.አ)፣ 50–53) መልዕክት ልታነቡ እና ”በወንድ እና በሴት መካለል የተመሰረተ ጋብቻ ለእግዚያብሄር እቅድ መስፋፋት ለምን ከሁሉም የበለጠ አመቺ ሁኔታን እንደሚያቀርብ” ልትገምቱ ትችላላችሁ(ገጽ 52)፡፡

እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ያሉ ሌሎች አስፈላጊ መርሆችን እንድትገምቱ ሊረዷችሁ ይችሉ ይሆናል:

ኦሪት ዘፍጥረት 24፧1–14፡፡ አብርሃም እና አገልጋዩ ለይስሃቅ ሚስት ለማግኘት በሚያደርጉት ጥረት ጌታን ለማካተት ምን አደረጉ?

ኦሪት ዘፍጥረት 24፧15–28፣ 55–60፡፡ ከርብቃ ለመቅዳት የምትወዱት ምን ብቃቶች ታገኛላችሁ?

ሌሎች ምን ግንዛቤዎች ታገኛላችሁ?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 131፧1–4፤ “ቤተሰብ:ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 25፥29–34

በአፋጣኝ እርካታ እና የላቀ አሴት ባላቸው ነገሮች መካከል መምረጥ እችላለሁ፡፡

በአብርሃም ባህል ውስጥ፣በተለይ የቤተሰቡ ታላቅ ወንድ ልጅ ብኩርና የተባለ የአመራር እና የመብት ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ይህ ልጅ ቀሪውን ቤተሰብ ከመንከባከብ ትልቅ ሃላፊነቶቸ ጋር ከወላጆቹ በዛ ያለ ውርስ ይቀበላል፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 25፥29–34ን ስታነቡ ኤሳው ለምን ለምግብ ሲል ብኩርናውን ለመተው ፈቃደኛ እንደነበረ አስቡ፡፡ በዚህ ዘገባ ውስጥ ለራሳችሁ ምን ትምህርት አገኛችሁ? ለምሳሌ፦እናንተ ትልቅ ዋጋ ከምትሰጧቸው በረከቶች ላይ ትኩረታችሁን የሚያዛባ “ብልጭልጭ ነገር“ አለ? በእነዚህ በረከቶች ላይ ለማተኮር እና አድናቆታችሁን ለመግለጽ ምን እያደረጋችሁ ነው?

በተጨማሪም ማቴዎስ 6፥19–332 ኔፊ 9፥51፣ ኤም. ረስል ባላርድ ፣ “What Matters Most Is What Lasts Longest፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2005(እ.አ.አ) 41–44፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 26፥1–5

የአብርሃም ቃል ኪዳን በይስሃቅ በኩል ታድሷል።

እግዚያብሄር ከአብርሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን በብዙ ትውልዶች መካከል እንዲቀጥል የታሰበ ነበር፤ ስለዚህ የአብርሃም እና የሳራ የቃል ኪዳን ውርስ ጥበቃ ወደ ይስሃቅ፣ያዕቆብ እና በልጅ ልጆቻቸው ውስጥ ወዳሉ ወደሌሎች ታማኝ ሴቶች እና ወንዶች መተላለፍ ያስፈልገዋል፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 26፥1–5ን ስታነቡ፣ እግዚያብሄር የጠቀሳቸውን አንዳንድ የቃል ኪዳን በረከቶች ፈልጉ? ከእነዚህ ጥቅሶች ስለ እግዚያብሄር ምን ትማራላችሁ?

ኦሪት ዘፍጥረት 26፧18-25፣ 32-33፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የህያው ውሃ ምንጭ ነው።

የውሃ ጉድጓዶች እና ምንጮች እንዲሁም ሌሎች የውሃ አካላት በብዙ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ውስጥ ጠቃሚ ሚና እንደተጫወቱ ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ይህ የሚያስደንቅ አይደለም፤ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ እነዚህ ታሪኮች የተከናወኑት እጅግ ደረቅ በሆኑ ቦታዎች ነው። በ ኦሪት ዘፍጥረት 26 ውስጥ ስለይስሃቅ የውሃ ጉድጓዶች ስታነቡ፣በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ ውሃ ምን ሊወክል እንደሚችል አሰላስሉ። ስለ መንፈሳዊ “ህያው ውሃ“ ምንጭ ምን ግንዛቤ ታገኛላችሁ?( ዮሃንስ 4፧10–15ይመልከቱ)። በህይወታችሁ መንፈሳዊ ኩሬ የምትቆፍሩት እንዴት ነው? አዳኙ እንደ ህያው ውሃ የሆነላችሁ እንዴት ነው? ፍልስጥኤማውያን ኩሬውን “አቁመውት“ እንደነበር( ኦሪት ዘፍጥረት 26፧18) ልብ በሉ። በህይወታችሁ ውስጥ ህያው የውሃ ኩሬያችሁን እያቆመ ያለ የሆነ ነገር አለ?

የጥንት የውሃ ጉድጓድ

አብርሃም እና ይስሃቅ የውሃ ጉድጓዶች የቆፈሩበት በጥንት ቤርሳቤህ የሚገኝ የውሃ ጉድጓድ።

ኦሪት ዘፍጥረት 27

ርብቃ እና ያዕቆብ ይስሃቅን በማታለላቸው ስህተተኞች ነበሩ?

ርብቃ እና ያዕቆብ በረከትን ለያዕቆብ ለማስገኘት ስለተጠቀሙበት አቀራረብ ምክንያቶች አናውቅም። አሁን በእጃችን ያለን ብሉይ ኪዳን ሙሉ እንዳልሆነ ማስታወስ ይጠቅማል።( ሙሴ 1፧23፣ 41ይመልከቱ)። ለእኛ አስቸጋሪ ሊመስሉ የሚችሉትን ማብራራት የሚችሉ ከዋና መዝገቦች ውስጥ የጠፉ መረጃዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ነገር ግን ያዕቆብ ከይስሃቅ በረከቱን እንዲቀበል የእግዚብሄር ፈቃድ መሆኑን እናውቃለን፤ ምክንያቱም ያዕቆብ ኤሳውን እንደሚመራው ርብቃ ራዕይ አይታ ነበር።( ኦሪት ዘፍጥረት 25፧23)። ይስሃቅ በኤሳው ፋንታ ያዕቆብን መባረኩን ካወቀ በኋላ—የእግዚያብሄር ፈቃድ ተፈጽሞ እንደነበር በመጠቆም ያዕቆብ “እንደሚባረክ“ አረጋገጠ።ኦሪት ዘፍጥረት 27፧33)።

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 24፧2-4፣ 32-48፡፡አብርሃም አንዱን የታመነ አገልጋይ ለይስሃቅ ሚስት እንዲፈልግለት ጠየቀው፤ እናም አገልጋዩ ያንን ለመፈጸም ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፡፡ የአብርሃም አገልጋይ ቃሉን በመጠበቅ ታማኝነት ያሳየው እንዴት ነበር? ምሳሌውን እንዴት መከተል እንችላለን?

ኦሪት ዘፍጥረት 24፧15–28፣ 55–60፡፡ቤተሰባችሁ ርብቃን ለይስሃቅ ብቁ ዘላለማዊ አጋር ያደረጓትን ባህርያት በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ሊፈልግ ይችላል፡፡ ከነዚህ ባህርያት ውስጥ ሊያዳብሩት እንደሚገባቸው የሚሰማቸውን አንዱን እንዲመርጡ የቤተሰቡን አባላት አበረታቷቸው፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 25፧19–34፤ 27፡፡የኤሳው ብኩርና እና በረከቶች እንዴት ወደ ያዕቆብ እንደመጡ የሚናገሩትን ታሪኮች ለመከለስ “ያዕቆብ እና ኤሳው“ የሚለውን (ከ ብሉይ ኪዳን ታሪኮች) ውስጥ በማውጣት በተለየ ቁራጭ ወረቀት ልትጽፉ ትችላላችሁ፡፡ የቤተሰቡ አባላት አረፍተ ነገሮቹን በትክክለኛ ቅደም ተከተል ለማስቀመጥ አብረው ሊሰሩ ይችላሉ፡፡

ስለኤሳው ብኩርና መሸጥ ስትወያዩ ከሰማያዊ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ስላላችሁ ግንኙቶች የመሰለ ለቤተሰባችሁ ይበልጥ ትርጉም ስላለው ነገርም ልትነጋገሩ ትችላላችሁ፡፡ ምናልባት የቤተሰብ አባላት ዘላለማዊ ዋጋ እንዳላቸው የሚገምቷቸውን እቃዎች እና ስዕሎች ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ እነዚያን ነገሮች ለምን እንደመረጡ ያብራሩ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 26፥3–5፡፡ቤተሰቦቻችሁ ስለአብርሃም ቃል ኪዳን እንዲገነዘቡ ለመርዳት በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የተገለጹትን ተስፋዎች እንዲፈልጉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፡፡ ዛሬ ስለነዚህ ተስፋዎች ማወቃችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?( ”ልታስታውሷቸው የሚገቡ ሃሳቦች:ቃል ኪዳን፣ ”የሚለውን በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ይመልከቱ)፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 26፧18–25፣ 32–33፡፡የውሃ ጉድጓዶች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ውሃ ጉድጓድ የሆነው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናት ይመልከቱ፡፡

የሚመከር መዝሙር፦ትክክለኛውን ምረጥ፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 239 ፡፡

የግል ጥናትን ማሻሻል

የቅዱሳን ጽሁፎች ጥቅሶችን በቃል መያዝ፡፡ ሽማግሌ ሪቻርድ ዲ.ስኮት “በቃል የተያዘ ቅዱስ ጽሁፍ በጊዜ ሂደት የማይደበዝዝ ዘላቂ ጓደኛ ይሆናል“ (“The Power of Scripture፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2011(እ.አ.አ)፣6)፡፡

ኤሳው እና ያዕቆብ

ኤሳው ብኩርናውን ለያዕቆብ ሲሸጥ፣ በግሌን ኤስ. ሆፕኪንሰን