ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የካቲት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 18–23፦ “በውኑ ለእግዚያብሄር የሚሳነው ነገር አለን?“


“የካቲት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 18–23፦ ’በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን?’” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“የካቲት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 18–23፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ሳራ ህጻኑን ይስሃቅን ታቅፋ

ሳራ እና ይስሃቅ በስኮት ስኖው

የካቲት 14–20 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 18–23

“በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን?“

ሙሴ–23ን አንብቡ እና አሰላስሉ ከዚያም የምትቀበሉትን ግንዛቤዎች መዝግቡ፡፡ እነዚህን ምዕራፎች ለማጥናት እንዲረዷችሁ በዚህ መዘርዝር ውስጥ ያሉትን ሃሳቦች መጠቀም ትችላላችሁ። እንዲሁም በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ ጌታ በተለይ ለናንተ ያለውን ሌሎች መልዕክቶች ለመፈለግ ልትነሳሱም ትችላላችሁ፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እጅግ በሚያሳዝን እና እጅግ በሚያስደስት ኩነቶች የተሞላው የአብርሃም ህይወት በራዕይ ለተማረው እውነት ምስክር ነው—ይሄውም፣ ” [የእኛ]ጌታ እግዚአብሄር የሚያዘንን ነገሮች በሙሉ እንደ[ምንፈጽም] ለማየት ነው፡፡” (አብርሃም 3፧25)፡፡ አብርሃም እራሱ ታማኝ መሆኑን ያረጋግጥ ይሆን? እርሱ እና ሳራ እድሜያቸው ገፍቶ ልጅ በሌላቸው ሰዐት እንኳን ታላቅ ትውልድ ለመስጠት እግዚያብሄር በሰጠው ተስፋ ማመኑን ይቀጥል ይሆን? እናም ይስሃቅ ከተወለደ በኋላ በእርሱ አማካኝነት ቃሉን እንደሚፈጽም እግዚያብሄር ቃል ገብቶ የነበረውን ያንኑ ልጅ እንዲሰዋ ሲታዘዝ የአብርሃም እምነት ሊታሰብ በማይችለው ሊጸና ይችል ይሆን? አብርሃም ታማኝ መሆኑን አረጋገጠ፡፡ አብርሃም እግዚያብሄርን አመነ እንዲሁም እግዚያብሄር አብርሃምን አመነ፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 18–23ውስጥ የራሳችንን በእግዚያብሄር ተስፋዎች የማመን ችሎታ እንድናስብ ሊያነሳሱን የሚችሉ፣ከክፋት ለመሸሽ እና ደግሞም ላለመመለስ እንዲሁም መስዋእትነቱ ምንም ይሁን ምን በእግዚያብሄር ለመታመን ከአብርሃም እና ከሌሎች ህይወት የተወሰዱ ታሪኮችን እናገኛለን፡፡

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 18፧9-1421–7

ጌታ ተስፋዎቹን በራሱ ጊዜ ይፈጽማል፡፡

ጌታ ለሚታመኑት ታላቅ ተስፋዎችን ሰጥቷል፣ ነገረ ግን አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች እነዚያ ተስፋዎች እንዴት ሊፈጸሙ እንደሚችሉ እንድንጠይቅ ሊያደርጉን ይችላሉ፡፡ አብርሃም እና ሳራ አንዳንዴ እንደዚያ ተሰምቷቸው የነበረ ሊሆን ይችላል፡፡ ከእነሱ ተሞክሮዎች ምን ትማራላችሁ? ጥናታችሁን ጌታ ለአብርሃም ገብቶ የነበረውን ቃል ኪዳን በ ኦሪት ዘፍጥረት 17፥ 4፣15–22ውስጥ በመከለሰስ መጀመር የሚጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ኦሪት ዘፍጥረት 17፥23 [በ ኦሪት ዘፍጥረት17፥ 17ውስጥ፣ የግርጌ ማስታወሻ b]፤ ኦሪት ዘፍጥረት18፥ 9–12ን ይመልከቱ)፡፡ ጌታ በተስፋዎቹ የበለጠ እምነት እንዲኖራቸው ሊረዳቸው ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር? ኦሪት ዘፍጥረት 18፥ 14ን ይመልከቱ)፡፡

በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ እምነታችሁን የሚገነባ ምን ነገር ታገኛላችሁ? በራሳችሁ ወይንም በሌሎች ህይወት ውስጥ—ሌሎች ምን ተሞክሮዎች—ጌታ የሰጣችሁን ተስፋዎች በራሱ ጊዜ እና መንገድ እንደሚያሟላ እምነታችሁን አጠናክረዋል?

በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥68ን ይመልከቱ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 19፥12–29

ጌታ ከክፋት እንድንሸሽ አዞናል።

ስለ ሎጥ እና ስለ ቤተሰቡ ስታነቡ ከክፋት ስለመሸሽ ምን ትምህርት ትማራላችሁ? ለምሳሌ ሎጥ እና ቤተሰቡ ጥፋትን እንዲያመልጡ ለመርዳት መላዕክቱ ከተናገሩት እና ካደረጉት ምን ነገር ያስገርማችኋል?( ኦሪት ዘፍጥረት 19፥12–17ን ይመልከቱ)፡፡ እናንተ እና ቤተሰባችሁ በዚህ አለም ካሉ ክፉ ተጽዕኖዎች እንድትሸሹ ወይም ከለላ እንድታገኙ ጌታ እንዴት ይረዳችኋል?

ስለሰዶም እና ገሞራ ሃጢያቶች ተጨማሪ ለማግኘት ህዝቅኤል 16፥49–50 ን እና ይሁዳ 1፥7–8ን ይመልከቱ፡፡

በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 19፥9–15 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ይመልከቱ፡፡

ምስል
ሎጥ እና ቤተሰቡ ከሰዶም እና ገሞራ ሲሸሹ የሚያሳይ ምስል

ከሰዶም እና ገሞራ መሸሽ፣ በጁሊየስ ቮን ካሮልስፌልድ

ዘፍጥረት 19፥26

የሎጥ ሚስት ምን ጥፋት አጠፋች?

ሽማግሌ ጀፍሪ አር. ሆላንድ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል፦

“በግልጽ እንደሚታየው የሎጥ ሚስት ያጠፋችው ጥፋት ወደኋላ መመልከቷ ብቻ አልነበረም፤በልቧ ወደኋላ ለመመለስ ፈልጋ ነበር፡፡ የከተማውን ድንበር እንኳን ለቃ ሳትወጣ ሰዶም እና ገሞራ ሲያቀርቡላት የነበረውን ነገር አስቀድማ እየናፈቀች የነበረ ይመስላል፡፡… እምነት አልነበራትም፡፡ የጌታን ከነበራት የተሻለ ነገር የመስጠት ችሎታ ተጠራጠረች፡፡ …

“ለእያንዳንዱ ትውልድ ሁሉም [ህዝብ] እጣራለሁ፣‘የሎጥን ሚስት አስቧት‘[ሉቃስ 17፥32]፡፡ እምነት ለወደፊት ነው፡፡ እምነት የሚገነባው ባለፈው ነገር ላይ ነው ነገር ግን በዚያ ለመቆየት በፍጹም አይፈልግም፡፡ እምነት እግዚያብሄር ለእያንዳንዳችን ታላቅ ነገሮች እንዳሉት እንዲሁም ክርስቶስ በእውነት ‘ለሚመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህን ነው‘ ብሎ ያምናል (ዕብራውያን 9፥11)” (“The Best Is Yet to Be፣” ኢንዛይን፣ ጥር 2010(እ.አ.አ)፣ 24፣ 27).

ኦሪት ዘፍጥረት 22፥1–19

አብርሃም ይስሃቅን ለመስዋዕት ለማቅረብ የነበረው ፈቃደኝነት ከእግዚያብሄር እና ከልጁ ጋር አምሳልነት ያለው ነው፡፡

አብርሃም ይስሀቅን እንደመስዋዕት እንዲያቀርብ እግዚያብሄር የጠየቀበትን ሁሉንም ምክንያቶች አናውቅም፤በእግዚያብሄር ላይ ያለውን እምነት መፈተኛ እንደነበረ እናውቃለን ( ኦሪት ዘፍጥረት 22፥1–19ይመልከቱ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 22፥1–19ን ስታነቡ ከአብርሃም ተሞክሮ ምን ትማራላችሁ?

የአብርሃም ልጁን ለመስዋዕት ለማቅረብ የነበረው ፈቃደኝነት “ከእግዚያብሄር እና ከአንድያ ልጁ ጋር አምሳልነት ያለው“ ነበር (ያዕቆብ 4:5)፡፡ በአብርሃም ፈተና እና እግዚያብሄር አብ ልጁን ለእኛ እንደመስዋዕት አድርጎ በማበርከት መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ስታሰላስሉ ስለ ሰማያዊ አባታችሁ ምን ይሰማችኋል?

በይስሃቅ እና በአዳኙ መካከልም ተመሳሳይነቶች አሉ፡፡ እነዚህን ተመሳሳይነቶች እየፈለጋችሁ ኦሪት ዘፍጥረት 22፥1–19 ን እንደገና ማንበብን አስቡ፡፡

በተጨማሪም “Akedah (The Binding)” የሚለውን ቪዲዮ ይመልከቱ፣ ChurchofJesusChrist.org

ምስል
family study icon

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 18፥24፡፡ከቅዱሳን ጽሁፎች፣ከቤተሰብ ታሪክ ወይም ከራሳችሁ ህይወት ለጌታ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ያስተማሯችሁ ሌሎች ታሪኮች አሉ?

ኦሪት ዘፍጥረት 18፥16–33ከነዚህ ቁጥሮች ስለአብርሃም ባህርይ ምን እንማራለን? የእርሱን ምሳሌ እንዴት መከተል እንችላለን? በተጨማሪም አልማ 10፥22–23ንይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 19፥15–17፡፡እነዚህ ጥቅሶች የቤተሰባችሁ አባላት ክፋት ካለባቸው ሁኔታዎች ለመሸሽ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ለመዘጋጀት ሊረዳቸው ይችላል፡፡ እነዚህ አንዳንድ ሁኔታዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ለምሳሌ፦ተገቢ ስላልሆነ ሚዲያ ወይም በሃሜት ስለመፈተን ውይይት ልታደርጉ ትችላላችሁ። ከነዚህ ሁኔታዎች እንዴት መሸሽ እንችላለን?

ኦሪት ዘፍጥረት 21፥9–20፡፡ሳራ እና አብርሃም ካስወጧቸው በኋላ እግዚያብሄር አጋርን እና እስማኤልን ስለያዘበት ሁኔታ ቤተሰባችሁን ምን ያስገርመዋል?

ኦሪት ዘፍጥረት 22፧1–14፡፡አብርሃም ይስሃቅን እንዲሰዋ እግዚያብሄር ባዘዘው ትዕዛዝ እና በአዳኙ የሃጢያት መስዋዕት ክፍያ ታሪክ መካከል ያለውን ግንኙነት ቤተሰባችሁ እንዲያይ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? የቤተሰብ አባላት በእነዚህ ሁለት ክንውኖች መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ሲወያዩ የአብርሃምን እና የይስሃቅን እንዲሁም የስቅለትን ምስሎች ልታሳዩ ትችላላችሁ(”አብርሃም እና ይስሃቅ፣” በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮችውስጥ ይመልከቱ)፡፡ እንደ “ልጁን ልኮታል” (የልጆች የመዝሙር መጽሃፍ፣ 34-35) አይነት ስለአዳኙ የሚናገሩ መዝሙሮችን መዘመር እና ስአዳኙ መስዋዕት የሚገልጹ ሃረጎችን መፈለግ ትችላላችሁ።

እንደ ቤተሰብ ምን መስዋዕት እንድናደርግ ተጠይቀናል? እነዚህ መስዋዕቶች ወደ እግዚያብሄር እንድንቀርብ ያደረጉን እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “God Loved Us, So He Sent His Son፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 187።

የግል ጥናትን ማሻሻል

መንፈሱን ስሙ በምታነቡበት ጊዜ ከምታነቡት ጋር የማይዛመዱ ቢመስሉም ለሀሳባችሁ እና ለስሜታችሁ ትኩረት ስጡ። ምናልባት እነዚያ ግንዛቤዎች ራሳቸው እግዚያብሄር እንድትማሩ የፈለጋቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ምስል
አብርሃም እና ይስሃቅ እየተራመዱ

አብርሃም እና ሳራ ምስል በጄፍ ዎርድ

አትም