ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የካቲት 7–13 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 12-17፤ አብርሃም 1–2፦ “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን “


“የካቲት 7–13 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 12-17፤ አብርሃም 1-2 ፦‘ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን፣‘“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“የካቲት 7–13 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 12-17፤ አብርሃም 1-2፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
አብርሃም እና ሳራ

አብርሃም እና ሳራ ምስል በዳይሊን ማርሽ

የካቲት 7–13 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 12-17አብርሃም 1–2

“ታላቅ የጽድቅ ተከታይ መሆን “

ስለአብራም እና ስለሶራ (በኋላ አብርሃም እና ሳራ ተብለው ተጠርተዋል) እና ስለቤተሰባቸው ስታነቡ ምሳሌነታቸው እንዴት እንደሚያነሳሳችሁ አሰላስሉ፡፡ “ታላቅ የጽድቅ ተከታይ ለመሆን“ ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ ያላችሁን ስሜት መዝግቡ (አብርሃም 1፥2)፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

እግዚያብሄር ከእርሱ ጋር በገባው ቃል ኪዳን ምክንያት አብርሃም “የታማኞች አባት“ (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 138፥41) እና “የእግዚያብሄር ወዳጅ” (ያዕቆብ 2:23) ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ዛሬ ሚልዮኖች እንደ ቀጥተኛ የዘር ሃረጋቸው ይቀበሉታል፣እንዲሁም ሌሎች ወደኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመለወጥ እንደቤተሰቡ ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም አብርሃም ራሱ ቸግር ካለበት ቤተሰብ ነው የመጣው—እውነተኛውን የእግዚያብሄር አምልኮ ትቶ የነበረው አባቱ አብርሃምን ለሃሰት አማልክት ሊሰዋው ሞክሮ ነበር፡፡ ያም ቢሆን የአብርሃም ፍላጎት“ታላቅ የጽድቅ ተከታይ ለመሆን“ ነበር፤(አብርሃም 1፥2) እናም የህይወት ታሪክ ዘገባው እግዚያብሄር ፍላጎቱን እንዳከበረለት ያሳያል፡፡ የአንድ ሰው የቤተሰብ ታሪክ ምንም ይሁን ምን ወደፊቱ በተስፋ ሊሞላ እንደሚችል የአብርሃም ህይወት እንደምስክር ጎልቶ ይታያል፡፡

ምስል
Learn More image
ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

አብርሀም 1፥1–19.

እግዚያብሄር ስለእምነቴ እና ስለጽድቅ ፍላጎቴ ይባርከኛል፡፡

እንደብዙዎቻችን አብርሃም ክፋት ባለበት አካባቢ ኖሯል ሆኖም ፃድቅ መሆንን ፈልጎ ነበረ፡፡ ፕሬዚዳንት ዳልን ኤች.ኦክስ የፅድቅ ፍላጎት የመኖርን አስፈላጊነት አስተምረዋል፦ሁሉንም ሃጢያት የማድረግ ፍላጎት ማጥፋት እንደሚፈልግ ሁሉ፤ “ዘላለማዊ ህይወት ተጨማሪ ማድረግንም ይጠይቃል፡፡ ዘላለማዊ ግባችን ላይ ለመድረስ፣ዘላለማዊ ፍጡር ለመሆን …የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ለማግኘት እንፈልጋለን እንዲሁም እነሱን ለመፈጸም እንጥራለን፡፡ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ የሚሰማን ከሆነ—በርግጠኝነት ለማንኛችንም ቀላል አይደለም—ከዚያም እነዚህን ብቃቶች ለማግኘት በመፈለግ መጀመር እና ስለሚሰሙን ስሜቶች እርዳታ ለማግኘት አፍቃሪ ሰማያዊ አባታችንን መጥራት አለብን[ ሞሮኒ 7፥48ይመልከቱ]” (“ፍላጎት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2011(እ.አ.አ)፣ 44–45)፡፡ አብርሃም 1፥1–19ን ስታነቡ እነዚህ ጥቅሶች ፕሬዚዳንት ኦክስ ያስተማሩንን እንዴት እንደሚያብራሩ አስቡ። እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ፦

  • አብርሃም ምን ፈልጎ እና ሽቶ ነበር? እምነቱን ለማሳየት ምን አደረገ?

  • ፍላጎቶቻችሁ ምን ምን ናቸው? ፍላጎቶቻችሁን ለማጥራት ማድረግ እንደሚያስፈልጋችሁ የሚሰማችሁ ነገር አለ?

  • በጽድቅ ፍላጎቶቹ ምክንያት አብርሃም ምን ምን ፈተናዎች አጋጠሙት? እግዚያብሄርስ እንዴት ረዳው?

  • የቤተሰብ አባላቶቻቸው ጽድቅን ለማይፈልጉ እነዚህ ቁጥሮች ምን መልዕክት አላቸው?

በተጨማሪም ማቴዎስ 7፥7፤ “Deliverance of Abraham” (video)፣ ChurchofJesusChrist.org፤ “Educate Your Desires, Elder Andersen Counsels” (ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ።

አብርሃም 2፥10–11

በአብርሃም ቃል ኪዳን ውስጥ የተካተተው ማን ነው?

ጌታ ቃልኪዳኑን ከአብርሃም ጋር ሲያደርግ ይህ ቃልኪዳን በአብርሃም ትውልድ ወይም “ዘር“ ውስጥ እንደሚቀጥል እና “ ይህን ወንጌል የተቀበሉት ሁሉ…እንዳንተ ዘር ይቆጠራሉ“ ሲል ቃል ገብቷል(አብርሃም 2፥10–11)። ይህ ማለት ቃል በቃል የአብርሃም ዘሮችም ሆኑ በመጠመቅ እና ወደኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመቀየር እንደቤተሰቡ የሆኑ የአብርሃም ቃል ኪዳን ተስፋ የሚሆነው ለሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት ነው ማለት ነው ( ገላትያ 3፥26–29ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 132፥30–32ን ይመልከቱ)። እንደ አብርሃም ዘር ለመቆጠር አንድ ግለሰብ የወንጌልን ህጎች እና ስርዐቶች ማክበር አለበት።

ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1–313፥15–1615፥1–617፥1–8, 15–22አብርሃም 2፥8–11

የአብርሃም ቃል ኪዳን እኔን እና ቤተሰቦቼን ይባርካል።

ሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት በአብርሃም ቃል ኪዳን በመካተታቸው ምክንያት ይህ ቃል ኪዳን በህይወታችሁ ውስጥ ለምን ትርጉም ያለው እንደሆነ የተወሰነ ጊዜ በማሰላሰል ልታሳልፉ ትችላላችሁ። ስለሚቀጥሉት ጥያቄዎች ያሏችሁን ሃሳቦች መዝግቡ:

አብርሃም 2፥8–11 ውስጥ የሰፈሩት ተስፋዎች እኔን እና ቤተሰቤን መባረክ የሚችሉት እንዴት ነው?(በተጨማሪም ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1–313፥15–16ን ይመልከቱ)።

ኦሪት ዘፍጥረት15፥1-617፥1–8፣ 15–22ስለ አብርሃም ቃል ኪዳን ምን እማራለሁ?

“ሁሉም የምድር ቤተሰቦች ይባረካሉ“ የሚለው ተስፋ እንዲፈጸም ለመርዳት ምን ለማድረግ እነሳሳለሁ? (አብርሃም 2፥11)።

የተስፋ ምድርን እንደመውረስ እና የታላቅ ህዝብ ወላጅ እንደመሆን ያሉ ለአብርሃም እና ለሳራ የተሰጡትን አንዳንድ ምድራዊ በረከቶች ዘላለማዊ ትይዩዎች እንዳሏቸው ልታስቡ ትችላላችሁ። እነዚህ በሰለስቲያል መንግስት ያለውን ውርስ ( ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 132፥29)እና ዘላለማዊ ጋብቻ ከዘላለማዊ ትውልድ ጋር ይጨምራሉ። ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 131፥1–4132፥20–24፣28–32ን ይመልከቱ)፡፡ “እንደ አብርሃም፣ይስሃቅ እና ያዕቆብ ዘሮች የመጨረሸውን በረከቶች የምንቀበለው በቤተመቅደስ“ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ራስል ኤም.ኔልሰን አስተምረዋል ፡፡ (“The Gathering of Scattered Israel፣” ሊያሆና ህዳር 2006(እ.አ.አ)፣ 80).

በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ኦሪት ዘፍጥረት 15፥9–1217፥3–12 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጾች)፤ በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት፣ “የአብርሃም ቃልኪዳን”፤ “ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፦ ቃል ኪዳን፣” በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ይመልከቱ፡፡

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 13፥5–12በቤተሰቡ ውስጥ ሰላም ለመፍጠር አብርሃም ምን አደረገ? ምናልባት የቤተሰባችሁ አባላት በቤተሰብ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አለመግባባቶች እንዴት እንደሚፈቱ በመተወን እንደ አብርሃም ሰላም ወዳድ መሆንን ሊለማመዱ ይችላሉ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 13፥1615፥2–617፥15–19፡፡ቤተሰባችሁ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ያሉትን —ምንም እንኳን አብርሃም እና ሳራ ገና ልጆች ያልነበሯቸው ቢሆንም ዘሮቻቸው እንደ ምድር አፈር ፣እንደ ሰማይ ከዋክብት ወይም እንደባህርዳር አሸዋ እንደሚሆኑ የሚናገሩትን ተስፋዎች እንዲገነዘብ እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ?( ኦሪት ዘፍጥረት 22፥17ን ይመልከቱ)፡፡ ምናልባት ለቤተሰባችሁ አባላት የአሸዋ መያዣ ሳጥን ልታሳዩ፣ ከዋክብትን ልትመለከቱ ወይም ከዚህ መዘርዝር ጋር ያለውን ስዕል ልትጠቀሙ ትችላላችሁ? ሊሆኑ የማይችሉ በሚመስሉ ጊዜም እንኳን የእግዚያብሄርን ተስፋዎች ልናምን የምንችለው እንዴት ነው ?

ኦሪት ዘፍጥረት 14፥18–20፡፡የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 14፥25-40ስለመልከ ጼዴቅ ምን እንማራለን? (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጾች፤ በተጨማሪም አልማ 13፥3–19ይመልከቱ)፡፡ እንደ መልከ ጼዴቅ እንዴት“ጽድቅን [መመስረት]“ እንችላለን?ቁጥር 36)፡፡ ከመልከ ጼዴቅ አገልግሎት ሌላ ምን ነገር ያነሳሳናል?

ምስል
መልከ ጼዴቅ አብርሃምን ሲባርክ።

መልከ ጼዴቅ አብርሃምን ሲባርክ፣ በዋልተር ሬን

ኦሪት ዘፍጥረት 16ስለአጋር ማንበብ በተበደልን ጊዜ ጌታ እንዴት እንደሚረዳን ለመወያየት አጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል። “እስማኤል“ ማለት “እግዚያብሄር ይሰማል“ ማለት መሆኑንም ልትጠቁሙ ትችላላችሁ። የመበደል ስሜት በተሰማን ጊዜ ጌታ እንደሰማን አና እንደረዳን የተሰማን መቼ ነው?( ኦሪት ዘፍጥረት 16፥11ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “I Want to Live the Gospel፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 148።

የማስተማር ዘዴያችንን ማሻሻል

የምትገኙ እና ተደራሽ ሁኑ፡፡ አንዳንድ አመቺ የማስተማሪያ ጊዜዎች በቤተሰብ አባላት ልብ ውስጥ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ሲጸነሱ ይጀምራሉ፡፡ የቤተሰባችሁን አባላት ልትሰሟቸው ፍላጎት እንዳላችሁ በአንደበታችሁ እና በተግባራችሁ አማካኝነት አሳውቋቸው፡፡ ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 16ን ይመልከቱ፡፡)

ምስል
ሳራ በከዋክብት የተሞላውን ሰማይ ስትመለከት

የአብርሃም እና የሳራ ትውልድ “እንደሰማይ ክዋክብት“ እንደሚበዛ እግዚያብሄር ተስፋ ሰጠ(ኦሪት ዘፍጥረት 22፥17)፡፡ የእግዚያብሄርን ተስፋ ማሰላሰል፣ በከርትኒ ማትዝ

አትም