ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፭፥፱–፲፪። ከዘፍጥረት ፲፭፥፩–፮ ጋር አነጻፅሩ
አብርሐም ስለትንሳኤ ተማረ እናም የኢየሱስን ስጋዊ አገልግሎት ተመለከተ።
፱ እና አብራም አለ፣ ጌታ አምላክ ሆይ፣ ለዘለአለም ውርስ ይህን መሬት ለእኔ እንዴት ትሰጠኛለህ?
፲ እና ጌታ እንዲህ አለ፣ ብትሞትም እንኳን፣ ይህን ለአንተ ለመስጠት አልችልም?
፲፩ እና ከሞትክ፣ ይህን የእራስህ ልታደርገው ትችላለህ፣ የሰው ልጅ የሚኖርበት ቀን ይመጣልና፤ ነገር ግን ካልሞተ እንዴት ለመኖር ይችላል? መጀመሪያ ህይወት መሰጠት አለበት።
፲፪ እና እንዲህ ሆኖ፣ አብራም ተመለከተ እና የሰው ልጅ ቀናትን አየ፣ እና ተደሰተ፣ እና ነፍሱም እረፍትን አገኘች፣ እና በጌታ አመነ፤ ጌታም ይህን ለእርሱ እንደ ጻድቅነት ቆጠረለት።