ጆ.ስ.ት.፣ ፩ ሳሙኤል ፲፮፥፲፬–፲፮፣ ፳፫። ከ፩ ሳሙኤል ፲፮፥፲፬–፲፮፣ ፳፫ ጋር አነጻፅሩ፤ በ፩ ሳሙኤል ፲፰፥፲ እና ፲፱፥፱ ላይም አንድ አይነት ቅያሬዎች ተደርገዋል
በሳኦል ላይ የመጣው የክፉ መንፈስ ከጌታ አልነበረም።
፲፬ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልመጣው ክፉም መንፈስ አሠቃየው።
፲፭ የሳኦልም ባሪያዎችም አሉት፣ እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልሆነው ክፉ መንፈስ ያሠቃይሃል።
፲፮ በገና መልካም አድርጎ የሚመታ ሰው ይሹ ዘንድ ጌታችን በፊቱ የሚቆሙትን ባሪያዎቹን ይዘዝ፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያልመጣው ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ በእጁ ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህ።
፳፫ እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልመጣው ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፣ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር።