ከጆሴፍ ስሚዝ የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምርጫዎች
የሚቀጥሉት ከንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ቅጅ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.) የተመረጡ ክፍሎች ናቸው። ጌታ የመጀመሪያዎቹ ቃላቶች ከተጻፉ በኋላ የተቀየሩትን ወይም የጠፉትን የመፅሐፍ ቅዱስ እውነቶች ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ዳግሞ እንዲመልሳቸው አነሳስቶት ነበር። እነዚህ ደግመው የተመለሱ እውነቶች ትምህርቶችን አብራርተዋል እና የቅዱስ መጻህፍት መረዳትን አሻሽለዋል።
ጌታ የመጀመሪያ ጸሀፊዎች የጻፉትን አንዳንድ እውነቶችን ለጆሴፍ ስለገለጠለት፣ የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም በአለም ውስጥ ካሉት ማናቸውም ሌሎች የመፅሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የተለየ ነው። በዚህም አስተያየት፣ ትርጉም የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው ሰፋ ባለና ከልምድ በተለየ መንገድ ነው የሚጠቀምበት፣ ምክንያቱም የጆሴፍ ትርጉም ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ የተተረጎመ ሳይሆን በራዕይ የመጣ ነበር።
የጆሴፍ ስሚዝ የንጉስ ጄምስ መፅሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከተለያዩ የትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ክፍሎች ጋር የተገናኘ ወይም በእነዚህ ውስጥ የተጠቀሰ ነው (ክፍሎች ፴፯፣ ፵፭፣ ፸፫፣ ፸፮፣ ፸፯፣ ፹፮፣ ፺፩፣ ና ፻፴፪ ተመልከቱ)። ደግሞም፣ መፅሐፈ ሙሴ እና ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተወሰዱ ምንባቦች ናቸው።
ለጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ተጨማሪ መረጃ፣ የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ውስጥ “የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም (ጆ.ስ.ት.)”ን ተመልከቱ።
የሚቀጥሉት ምሳሌዎች ከጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም የተመረጡ ናሙናዎችን ያሳያሉ።
© 2018 by Intellectual Reserve, Inc. All rights reserved. Source: 2015/03/24