ጆ.ስ.ት.፣ ቁላስይስ ፪፥፳፩–፳፪። ከቁላስይስ ፪፥፳–፳፫ ጋር አነጻፅሩ
የሰዎች ትእዛዛት ራስን በመቆጣጠር አይነት ነገር ላይ ጥቅም ይኖረዋል፣ ግን እነርሱ እግዚአብሔርን አያከብሩም ወይም ሰውን አያድኑም።
፳፩ እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ የተወሰኑት፣ አትያዝ፣ አትቅመስ፣ አትንካ ብለው ከሚያስተምሩት ሰዎች የመጡ ትምህርቶች እና ትእዛዛት የትኞቹ ናቸው?
፳፪ ይህ እንደ ምንም የእግዚአብሔር ክብር ሳይሆን፣ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ማድረግ፣ ጥበብ ያለው ይመስላል።