ጆ.ስ.ት.፣ ገላትያ ፫፥፲፱–፳። ከገላትያ ፫፥፲፱–፳ ጋር አነጻፅሩ
የሙሴ የመጀመሪያው ቃል ኪዳን፣ ወይም የህግ፣ መካከለኛ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።
፲፱ እንግዲህ በዚህ በመጀመሪያው ቃል ኪዳን (በህግ) መካከለኛ እንዲሆን በመላእክት እጅ ለተሾመው ሙሴ በተሰጠው ህግ ውስጥ ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ ህግ የተጨመረው በመተላለፍ ምክንያት ነበር።
፳ አሁን ይህ መካከለኛ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ አልነበረም፤ ነገር ግን አንድ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ አለ፣ ለአብርሐም እና ለዘሩ ስለተሰጠው ቃል ኪዳን በሚመለከት በህግ ውስጥ እንደተጻፈው፣ ይህም ክርስቶስ ነው። አሁን ክርስቶስ የህይወት መካከለኛ ነው፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሐም የገባው ቃል ኪዳን ነውና።