የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፵፰


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት፵፰፥፭–፲፩።ዘፍጥረት ፵፰፥፭–፮ ጋር አነጻፅሩ

ኤፍሬም እና ምናሴ የእስራኤል ጎሳዎች ሆኑ። በጥንት ይኖር የነበረው ዮሴፍ ቤተሰቦቹን በጊዜው እንዳዳናቸው፣ የእርሱ ትውልዶችም በኋለኛው ቀናት እስራኤልን በመንፈስ ያድናሉ።

አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር ስለተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ኤፍሬምና ምናሴ፣ እነሆ እነርሱ የእኔ ናቸው፣ እና የአባቶቼ አምላክ ይባርካቸዋል፤ እንዲሁም እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይባረካሉ፣ እነርሱ የእኔ ናቸውና፤ ስለዚህ በስሜም ይጠራሉ። (ስለዚህ እነርሱም እስራኤል ተብለው ተጠርተው ነበር።)

እና ከእነርሱ በኋላ የወለድካቸው ልጆችህም የአንተ ይሆናሉ፣ እና በውርሳቸው፣ በጎሳዎቻቸውም፣ በወንድሞቻቸው ስም ይጠራሉ፤ ስለዚህ የምናሴና የኤፍሬም ጎሳ ተብለው ይጠራሉ።

እና ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፣ የአባቶቼ አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ሲገለጥልኝ፣ ይህን መሬት ለዘለአለም ንብረት ለእኔ እና ለዘሬ እንደሚሰጠኝ ማለልኝ።

ስለዚህ፣ ልጄ ሆይ፣ አንተ ቤቴን ከሞት በማዳን ለእኔ አገልጋይ እንደትሆን በማስነሳቱ ባርኮኛል።

ህዝቦቼን፣ ወንድሞችህን፣ በምድሩ በሀይል ከነበረው ራብ ጊዜ በማዳን፤ ስለዚህ የአባቶችን አምላክ ይባርክሀል፣ እና የወገብህ ፍሬዎች፣ ከወንድሞችህ በላይ፣ እና ከአባትህ ቤት በላይ ይባረካሉ።

አንተ አሸንፈሀልና፣ እና የአባትህም ቤት፣ ወደ ግብፅ በወንድሞችህ እጆች ከመሸጥህ በፊትአንተ ታይተውህ እንደነበረም፣ ለአንተ ሰገዱ፤ ስለዚህ ወንድሞችህ ለአንተ ከትውልድ ወደ ትውልድ፣ ለወገቦችህ ፍሬዎች ለዘለአለም ይሰግዳሉ፤

፲፩ ለህዝቦቼም፣ በባርነታቸው ቀን ከአገልጋይነት እንድታድናቸው፣ ብርሀን ትሆናለህ፤ እና በኀጥያት ስርም አብረው ታጥፈው በነበረ ጊዜምደህንነትን እንድታመጣላቸው።