ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፶፥፳፬–፴፰። ከዘፍጥረት ፶፥፳፬–፳፮፤ ከ፪ ኔፊ ፫፥፬–፳፪ ጋር አነጻፅሩ
ጆሴፍ በግብፅ ውስጥ ሙሴ እስራኤልን ከግብጻዊ ባርነት ነጻ እንደሚያደርግ፤ የጆሴፍ ትውልዶች ቅርንጫፍ በጌታ ቃል ኪዳኖች ወደሚታወሱበት ወደ ሩቅ አገር እንደሚመሩ፤ እግዚአብሔር የይሁዳንና የዮሴፍን መዝገቦች እንዲያዋህድ ዮሴፍ የሚባል ነቢይ በኋለኛው ቀናት እንደሚጠራ፤ እና አሮን እንደ ሙሴ ተናጋሪ እንደሚያገለግል ተነበየ።
፳፬ እና ዮሴፍ ለወንድሞቹ አለ፣ እሞታለሁ፣ እና ወደ አባቶቻችንም እሄዳለሁ፤ እና ወደ መቃብሬም በደስታ እሄዳለሁ። በባርነታችሁ ቀናት ከስቃያችሁ ያድናችሁ ዘንድ የአባቴ ያዕቆብ አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ጌታ ጎብኝቶኛል፣ እና ከወገቤ ፍሬዎች፣ ጌታ አምላክ ከወገቤ ጻድቃዊ ቅርንጫፍ ያስነሳ ዘንድ የጌታን ቃል ኪዳን አግኝቻለሁ፤ እና ለእናንተም፣ አባቴ ያዕቆብ እስራኤል ብሎ የጠራችሁ፣ ነቢይ፤ (ሻይሎ የሚባለው መሲህ አይደለም)፤ እና ይህም ነቢይ በባርነታችሁ ቀናት ህዝቦቼን ከግብፅ ያድናቸዋል።
፳፭ እናም እንዲህ ሆኖ አለፈ እንደገናም ይበተናሉ፤ እና ቅርንጫፍም ይሰበራል፣ እና ወደ ሩቅ አገርም ይወሰዳሉ፤ ይሁን እንጂ መሲህ ሲመጣ፣ በጌታ ቃል ኪዳን ይታወሳሉ፤ በኋለኛው ቀናት እርሱ በመንፈስ ኃይል ይገለጥላቸዋልና፣ እና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከተደበቀው ጨለማና ምርኮም ወደ ነፃነት ያወጣቸዋል።
፳፮ ጌታ አምላኬ፣ ለወገቤ ፍሬ ተመራጭ ባለራዕይ የሆነ ባለራዕይ ያስነሳል።
፳፯ እንደዚህም የአባቶቼ ጌታ አምላክ አለኝ፣ ከወገብህ ፍሬ ምርጥ ባለራዕይ አስነሳለሁ፣ እርሱ ከወገብህ ፍሬ መካከል የተከበረ ይሆናል። ለእነርሱ፣ ለወንድሞችህ፣ ታላቅ ስራን ይሰራ ዘንድ ትዕዛዝን እሰጠዋለሁ።
፳፰ ከአባቶችህ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እንዲያውቁት ያደርጋል፤ እና እንዲሰራ ያዘዝኩትን ማንኛቸውን ነገሮችን ያደርጋል።
፳፱ በፊቴ ትልቅ አደርገዋለሁ፣ የእኔን ስራ ይሰራልና፤ እና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ህዝቦቼን ከግብፅ ምድር ነፃ ያወጣቸው ዘንድ አስነሳዋለሁ ብዬ ለእናንተ የተናገርኩለት ታላቅ ይሆናል፣ ከግብፅ ምድር ህዝቦችህን እንዲያወጣ ባለራዕይ አስነሳለሁና፤ እና እርሱም ሙሴ ተብሎ ይጠራል። እና በስሙም እርሱ ከእናንተ ቤት እንደሆነም ታውቁታላችሁ፤ በንጉስ ሴት ልጅ ይጠባል፣ እና ልጇም ተብሎ ይጠራልና።
፴ እንደገናም ባለራዕይ ከወገብህ ፍሬ አስነሳለሁ፤ እናም ለእርሱም ለወገብ ዘርህ ቃሌን ያመጣ ዘንድ ኃይልን እሰጠዋለሁ፤ እናም ጌታ እንዲህ አለ፥ ቃሌን ብቻ ለማምጣት ሳይሆን፣ ነገር ግን በመጨረሻው ቀናት በመካከላቸው የሄዱትን ቃሌን እንዲያሳምን ነው።
፴፩ ስለሆነም፣ የወገብህ ፍሬዎች ይፅፋሉ፤ እናም የአይሁዳ የወገቡም ፍሬ ይፅፋሉ፤ እናም ይህ በወገብህ ፍሬ የሚጻፈው፣ ደግሞም በአይሁዳ ፍሬ የሚጻፈው፣ የውሸት ትምህርቶች ሀሰት መሆናቸውን ለማስረዳት፣ እና ፀብን እማቆም፣ እና በወገብህ ፍሬ መካከል ሰላምን ለመመስረት፣ እና በኋለኛው ቀናት ወደ አባቶቻቸው ግንዛቤ፣ እናም ደግሞ ለቃል ኪዳናቴ ግንዛቤ ለማምጣት በአንድ ላይ ያድጋሉ ይላል ጌታ።
፴፪ እናም በመጨረሻው ቀናት የሚመልሳቸው ስራዬ የእስራኤል ቤት በሆኑት በሁሉም ህዝቦቼ መካከል በሚሄድበት ጊዜ፣ እርሱ ከድካም ይበረታል።
፴፫ ባለራዕዩን ጌታ ይባርከዋል፣ እናም እርሱን ለማጥፋት የሚሞክሩ ይሸነፋሉ፣ ይህን ቃል ኪዳን እሰጥሀለሁና፤ ከትውልድ እስከትውልድ አስታውስሀለሁ፣ እና ስሙም ዮሴፍ ተብሎ ይጠራል፣ ስሙም ከአባቱም ጋር አንድ ይሆናል፣ እናም እርሱ ልክ እንደአንተ ይሆናል፣ ጌታ በእርሱ እጅ የሚያመጣው ነገር ህዝቦቼን ወደ ደህንነት የሚያመጣ ይሆናልና።
፴፬ እና ጌታ ዮሴፍን ለዘለአለም ፍሬውን እንደሚጠብቅ ቃል ገብቶለት አለ፣ ሙሴን አስነሳለሁ፣ እና በእጁም በትር ይኖራል፣ እና እርሱም ህዝቦቼን ይሰበስባል፣ እና እንደ መንጋዎችም ይመራቸዋል፣ እና የቀይ ባህር ውሀንም በበትሩ ይመታል።
፴፭ እና ፍርድም ይኖረዋል፣ እና የጌታን ቃል ይፅፋል። እና ብዙ ቃላቶችንም አይናገርም፣ በራሴ እጅ ጣት ህጌን እፅፍለታለሁና። እናም ተናጋሪ እሰጠዋለሁ፣ እና ስሙም አሮን ተብሎ ይጠራል።
፴፮ እና ደግሞም መሀላ እንደገባሁትም በመጨረሻው ቀናት ይህ ለአንተ ይሆንልሀል። ስለዚህ፣ ዮሴፍ ለወንድሞቹ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔርም በእርግጥም ይጎበኛችኋል፥ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል፤ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኋል።
፴፯ እና ዮሴፍ ለወንድሞቹ ብዙ ሌላ ነገሮች አረጋገጠ፣ እና እግዚአብሔር በእርግጥም ሲጎበኛችሁ አጥንቴን ከዚህ አንሥታችሁ ከእናንተ ጋር ትወስዳላችሁ ብሎ የእስራኤልን ልጆች መሀላ ገባ።
፴፰ ዮሴፍም በመቶ አሥር ዓመት ዕድሜው ሞተ፤ በሽቶም አሹት፥ በግብፅ ምድር በሣጥን ውስጥ አኖሩት፤ እና እንዲወሰድ እና በአባቱ መቃብር ውስጥ እንዲቀበር ዘንድ፣ የእስራኤል ልጆችም እርሱን ከመቀበር አስቀሩት። እና እንደዚህም ለእርሱ የማሉትን መሀላ አስታወሱ።