የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፬


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፬፥፳፩።ዘፀአት ፬፥፳፩፯፥፫፣ ፲፫፱፥፲፪፲፥፩፣ ፳፣ ፳፯፲፩፥፲፲፬፥፬፣ ፰፣ ፲፯፤ ከዘዳግም ፪፥፴ ጋር አነጻፅሩ

ጌታ ለፈርዖን ልብ መፅናት ሀላፊ አይደለም። ደግሞም ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፯፥፫፣ ፲፫፱፥፲፪፲፥፩፣ ፳፣ ፳፯፲፩፥፲፲፬፥፬፣ ፰፣ ፲፯ን ተመልከቱ፤ እያንዳንዱ ማጣቀሻዎች፣ በትክክል ሲተረጎሙ፣ ፈርዖን የራሱን ልብ እንዳጸና ያሳያሉ።

፳፩ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፣ ወደ ግብፅ ስትመለስ በእጅህ ያደረግሁትን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት ታደርገው ዘንድ ተመልከት፣ እና እኔም ውጤታማ እንድትሆን አደርግሀለሁ፤ ፈርዖን ግን ልቡን ያጸናዋል፣ እና ሕዝብንም አይለቅም።

ጆ.ስ.ት.፣ ኦሪት ዘፀአት ፬፥፳፬–፳፯።ዘፀአት ፬፥፳፬–፳፯ ጋር አነጻፅሩ

ሙሴ ወንድ ልጁን ባለመግረዙ ምክንያት ጌታ ሊገድለውም ሲያስፈራራ፣ ሲፓራም ይህን ስርዓት እራሷ በማከናወን ህይወቱን አዳነች። ሙሴም ኃጢያቱን ተናዘዘ።

፳፬ እንዲህም ሆነ፤ በመንገድ ላይ ባደረበት ስፍራ እግዚአብሔር ተገናኘው። የጌታ ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ፣ እናም ሊገድለውም እጁ ሊያሳርፍበት ነበር፤ ምክንያቱም ወንድ ልጁን አልገረዘምና።

፳፭ ከዚያም ሲፓራም ባልጩት ወሰደች፥ የልጅዋንም ሸለፈት ገረዘች፥ እናም ባልጩትን ወደ እግሩም ጣለችው፣ እና በእርግጥም አንተ ለእኔ የደም ሙሽራ ነህ አለች።

፳፮ እናም ጌታ ሙሴን አዳነው እናም ለቀቀው፣ ምክንያቱም ሲፓራም ሚስቱ ልጅን ስለገረዘች። ስለ ግርዛቱ አንተ የደም ሙሽራ ነህ አለች። እና ሙሴ አፈረ፣ እና ፊቱን ከጌታ ሸሸገ፣ እናም አለ፣ በጌታ ፊት ኃጢያት ሰርቻለሁ።

፳፯ እግዚአብሔርም አሮንን፣ ሄደህ በምድረ በዳ ሙሴን ተገናኘው አለው፤ ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፤ እግዚአብሔር ለእርሱ በታየበት ተራራም ላይ፤ እና አሮን ሳመውም።