የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፬


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአት ፴፬፥፩–፪፣ ፲፬።ዘፀአት ፴፬፥፩–፪፣ ፲፬ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹፬፥፳፩–፳፮ ጋር አነጻፅሩ

እግዚአብሔር እንደገና ህግን በሙሴ በተዘጋጀ ድንጋይ ላይ ጻፈ እናም የመልከ ጼዴቅ ክህነትና ስርዓቶችን ከእስራኤል ህዝብ ወሰደ። በዚህ ምትክም የስጋዊ ትእዛዛት ህግን ሰጣቸው።

እና ጌታ ሙሴን አለ፣ እንደመጀመሪያው አይነት ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጥረብ፣ እና በእነርሱም ላይ ደግሜ የህግን ቃላቶች አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያው ጽላቶች ላይ በተጻፉበት መሰረት እፅፍባቸዋለሁ፤ ነገር ግን በመጀመሪያው መሰረት አይሆኑም፣ ከመካከላቸው ክህነትን እወስዳለሁና፤ ስለዚህ ቅዱስ ስርዓት፣ እና የዚህ ስነ ስርዓት፣ በፊታቸው አይሄድምና፤ እኔም በመካከላቸው አልሄድምና፣ አለበለዚያ አጠፋቸዋለሁ።

ነገር ግን እንደ መጀመሪያውም ህግን እሰጣቸዋለሁ፣ ነገር ግን ይህም የስጋዊ ትእዛዝ ህግ ይሆናል፤ በቁጣዬ በእንግድነታቸው ዘመን ወዳለሁበት፣ ወደ እረፍቴ እንዳይገቡ መሀላ ገብቼአለሁ። ስለዚህ እንዳዘዝኩህ አድርግ፣ እና በጠዋትም ተዘጋጅ፣ እና በጠዋት ወደ ሲና ተራራ ውጣ፣ እና በፊቴም በተራራው ጫፍ ላይ ራስህን አቅርብ።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የብሉይ ኪዳን ህዝቦች የሚያውቁበት አንድ ስም ያህዌህ ነው።

፲፬ ስሙ ያህዌህ፣ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ።