የጥናት እርዳታዎች
ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፱


ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፱፥፬–፮።ዘፍጥረት ፰፥፳–፳፪ ጋር አነጻፅሩ

ከጎርፍ በኋላ፣ ኖህ ምድርን እንደገና እንዳይረግም ጌታን ጠየቀ።

ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያውን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ ከንጹሐን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፥ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ፤ እናም ለጌታ ምስጋና አቀረበ፣ እና በልቡ ተደሰተ።

እና ጌታም ለኖህ ተናገረ፣ እናም ባረከው። እናም ኖህ መልካሙን መዓዛ አሸተተ፣ እና በልቡ አለ፤

ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው እንዳይረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ምድር እስካለች ድረስ፣ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረገው ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና እንዳይመታም በጸሎት የጌታን ስም እጠራለሁ፤

ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፱፥፲–፲፭።ዘፍጥረት ፱፥፬–፱ ጋር አነጻፅሩ

ሰው የእንሰሳትንም ሆነ የሰዎችን ደም በማፍሰስ ተጠያቂ ነው። እግዚአብሔር ከኖህ እና ከወንድ ልጆቹ ጋር ከሔኖክ ጋር እንደገባው አይነት ቃል ኪዳን መሰረተ።

ነገር ግን፣ እንደመብል የምሰጥህን ስጋዎች ሁሉ ደም በምድር ላይ ይፈሳል፣ ይህም የዚህን ህይወት ይወስዳል፣ እና ደሙን አትብላ።

፲፩ በእርግጥም፣ ለመብል፣ ህይወትህን ለማዳን ካልሆነ በስተቀር ደም አይፍሰስ፤ እና የእያንዳንዱን አራዊት ደም ከእጅህ እሻዋለሁ።

፲፪ እና የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ፣ በሰው ደሙ ይፈስሳል፤ ሰው የሰውን ደም ማፍሰስ አይገባውምና።

፲፫ እያንዳንዱ የሰው ወንድም የሰውን ህይወት እንዲያድን ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ሰውን በመልኬ ፈጥሬአለሁና።

፲፬ እና ትእዛዝም እሰጣችኋለሁ፣ እናንተም ብዙ፥ ተባዙ፤ በምድር ላይ ተዋለዱ፥ እርቡባትም።

፲፭ እግዚአብሔርም ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ እኔም እነሆ፣ ከአባታችሁ ሔኖክ ጋር ከእናንተና በኋላ ስለሚመጣው ዘራችሁ በሚለከት ያደረኩትን ቃል ኪዳኔን እመሰርታለሁ።

ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፱፥፳፩–፳፭።ዘፍጥረት ፱፥፲፮–፲፯ ጋር አነጻፅሩ

እግዚአብሔር ቀስተ ዳመና በሰማይ የሰራው ከሔኖክ እና ከኖኀ ጋር እርሱ የገባውን ቃል ኪዳን ለማስታወስ ነው። በመጨረሻዎቹ ቀናት የበኩራቱ ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ ከምድር ጻድቅ ጋር ይቀናጃሉ።

፳፩ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ እና ሰዎች ትእዛዛቴን ሁሉ ሲያከብሩ፣ ወደ እኔ የወሰድኳት የሔኖክ ከተማ ፅዮን እንደገና ወደ ምድር ስትመጣ፣ እኔ ለአባታችሁ ሔኖክ የገባሁትን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማስታወስ አያታለሁ።

፳፪ እና ይህም የዘላለም ቃል ኪዳኔ ነው፣ ትውልዶችህ እውነትን ሲያቅፉ፣ እና ወደላይ ሲመለከቱ፣ ከእዚያም ፅዮን ወደታች ትመለከታለች፣ እና ሰማያት ሁሉ በደስታ ይነቃነቃሉ፣ እና መሬትም በደስታ ትንቀጠቀጣለች፤

፳፫ እና የበኩራት ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ ከሰማይ ይወርዳሉ፣ እና ምድርን የራሳቸው ያደርጓታል፣ እና መጨረሻው እስከሚመጣ ድረስ ቦታ ይኖራቸዋል። እና ይህም፣ ከአባታችሁ ሄኖክ ጋር የገባሁት የዘላለም ቃል ኪዳኔ ነው።

፳፬ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ እና በእናንተም በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል የገባሁትን ቃል ኪዳኔን እመሰርታለሁ።

፳፭ እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፣ በእኔና በአንተ መካከል የመሰረትኩት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው፤ ምክንያቱም ሥጋ ሁሉ በምድር ላይ ይገኛሉና።