ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥረት ፲፱፥፱–፲፭። ከዘፍጥረት ፲፱፥፰–፲ ጋር አነጻፅሩ
ሎጥ የሰዶምን ክፋት ተቋቋመ፣ እናም መላዕክት ጠበቁት።
፱ እነርሱም ወዲያ ሂድ አሉት። እና ተናደውበትም ነበር።
፲ እና እርስ በራሳቸውም እንዲህ አሉ፣ ይህ ሰው በመካከላችን በእንግድነት ለመኖር መጣ፣ አሁን እራሱን ዳኛ ያደርግ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በእርሱ ላይ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግበታለን።
፲፩ ስለዚህ ለሰውየውም እንዲህ አሉት፣ ወንዶቹን፣ እና ደግሞ ሴት ልጆችህንም እንወስዳለን፤ እና መልካም እንደሚመስለን እናደርግባቸዋለን።
፲፪ አሁን ይህም በሰዶም ክፉነት በኩል ነበር።
፲፫ እና ሎጥም አለ፣ አሁን እነሆ፣ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እባካችሁ፣ እነርሱን ወደ እናንተ ወደ ወንድሞቼ እንዳላወጣላችሁ እለምናችኋለሁ፣ እና በአይኖቻችሁ መልካም እንደመሰላችሁም አታደርጉባቸውም፤
፲፬ እግዚአብሔር አገልጋዩ በዚህ ነገር ተገቢ አያደርገውምና፤ ስለዚህ፣ ለዚህ አንድ ጊዜ፣ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፣ በቤቴም ሰላም እንዲኖራቸው ዘንድ እናንተን ወንድሞቼን እለምናችኋለሁ፤ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር የገቡበት ምክንያት ነውና።
፲፭ እና እነርሱም በሎጥ ተናድደው ነበር እና የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ፣ ነገር ግን ቅዱስ ሰዎች የነበሩት የእግዚአብሔር መላእክቶች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።