ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥር 31–የካቲት 6 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 6–11፤ሙሴ 8 ፦“ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ፀጋን አገኘ“


ጥር 31–የካቲት 6 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 6-11፤ ሙሴ 8፦‘ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ፀጋን አገኘ፣‘“ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

ጥር 31–የካቲት 6 (እ.እ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 6–11፤ሙሴ 8፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ኖህ፣ ቤተሰቡ፣ እንስሳት፣መርከብ እና ቀስተዳመና

ኖህ ከመርከቡ ሲወጣ ፣ ምስል በሳም ሎውሎር

ጥር 31–የካቲት 6 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 6–11ሙሴ 8

”ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ፀጋን አገኘ”

በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ ያሉ ታሪኮች አብዛኛውን ጊዜ ብዙ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያስተምሩናል፡፡ ስለጥፋት ውሃ እና ስለባቢሎን ግንብ ስታነቡ እነዚህ ዘገባዎች በናንተ ህይወት እንዴት እንደሚተገበሩ ለማወቅ መነሳሳትን ፈልጉ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ብዙ የመጽሃፍ ቅዱስ አንባቢ ትውልዶች በኖህ እና በጥፋት ውሃ ታሪክ ተነሳስተዋል፡፡ ነገር ግን እኛ በኋለኛው ቀን የምንኖረው ለእርሱ ትኩረት ለመስጠት የተለየ ምክንያት አለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጽአቱን እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ባስተማረ ጊዜ ”በኖህ ዘመን እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል” (ጆሴፍ ስሚዝ—ማቴዎስ 1፥ 41) ብሏል፡፡ በተጨማሪም እንደ “ሃቀኝነት የጎደላቸው” እና “በብጥብጥ የተሞሉ“ የሚሉ የኖህን ቀናት የሚገልጹ ሃረጎች በቀላሉ የኛን ጊዜ ሊገልጹ ይችላሉ(ኦሪት ዘፍጥረት 6፥12–13ሙሴ 8፥28)። በተጨማሪም የባበቢሎን ግንብ ታሪክ ኩራትን ተከትሎት ከሚመጣው ግራ መጋባት እና በእግዚያብሄር ልጆች መካከል ከተፈጠረው ክፍፍል ገለጻ አንጻር ለኛ ዘመን የሚሰራ ይመስላል፡፡

እነዚህ ጥንታዊ ገለጻዎች ውድ የሆኑት ክፋት በመላው ታሪክ ውስጥ እራሱን እንደሚደግም ስለሚያሳዩን ብቻ አይደለም፡፡ ከሁሉም ይበልጥ እነሱን በተመለከተ ምን ማድረግ እንደሚገባን ያስተምሩናል፡፡ ዙሪያው በክፋት የተሞላ ቢሆንም “ኖህ በጌታ አይኖች ውስጥ ፀጋን አገኘ“(ሙሴ 8፥27)፡፡ እናም የያሬድ እና የወንድሙ ቤተሰቦች ወደጌታ ተመለሱ ከዚያም በባቢሎን ከነበረው ክፋት ወጡ ( ኤተር 1፥33–43ን ይመልከቱ)፡፡ በዚህ ሃቀኘነት በጎደለው እና በብጥብጥ በተሞላ የኛ ጊዜ ራሳችንን እና ቤተሰባችንን እንዴት እንጠብቃለን ብለን ከተጨነቅን በነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ያሉት ታዋቂ ታሪኮች ብዙ የሚያስተምሩን አለ፡፡

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 6ሙሴ 8

የጌታን ነቢይ በመከተል መንፈሳዊ ጥበቃ ይገኛል፡፡

ዳግም ለተመለሰው ወንጌል ምስጋና ይግባውና ስለኖህ በብሉይ ኪዳን ከሰፈረው የበለጠ እጅግ ብዙ እናውቃለን፡፡ የ ኦሪት ዘፍጥረት 6የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም በ ሙሴ 8የሚገኝ ሲሆን ኖህ ከእግዚያብሄር ታላላቅ ነቢያት አንዱ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ተሹሞ እና ተልኮ ነበር ፣ከእግዚያብሄር ጋርም ተራምዶ እና ተነጋግሮ ነበር፣ እናም ከጥፋት ውሃ በኋላ የእግዚያብሄርን ልጆች በምድር እንደገና ለማቋቋም ተመርጦ ነበር(በተጨማሪም የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶችትምህርቶች፦ ጆሴፍ ስሚዝ [2007]፣ 104201ይመልከቱ)፡፡ ከኖህ ተሞክሮዎች ስለነቢያት ምን ትማራላችሁ?

ስለኖህ ጊዜ ስታነቡ ከኛ ጊዜ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ልታስተውሉ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፥

ነቢያት በዛሬው አለም ውስጥ ደህንነታችሁ እንደተጠበቀ ሊያቆያችሁ ስለሚችለው ስለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ምን እያስተማሩ ነው? ስለኖህ ተሞክሮዎች ስታነቡ ዛሬ የጌታን ነቢያት እንድትከተሉ የሚያነሳሳችሁ ምንድን ነው?

በተጨማሪም ሞዛያ 13፥33ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 21፥4–7።ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 9፥8–17

መታሰቢያዎች ወይም ምልክቶች ከጌታ ጋር የገባነውን ቃልኪዳኖች ለማስታወስ ይረዱናል።

የወንጌል ቃልኪዳኖች በጠቋሚ፣ በምልክት ወይም “በመታሰቢያ” ሊወከሉ ይችላሉ(ኦሪት ዘፍጥረት 9፥12)። ለምሳሌ የቅዱስ ቁርባን ዳቦ እና ውሃ ወይም የጥምቀት ውሃ ወደ አዕምሯችሁ የሚያመጡትን ከቃልኪዳናችሁ ጋር የተያያዙ የተቀደሱ እውነቶች አስቡ። በ ዘፍጥረት 9፥8–17መሰረት፣ ቀስተ ደመና ምን እንድታስታውሱ ሊያደርጋችሁ ይችላል? የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 9፥21–25 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ምን ግንዛቤ ይጨምርላችኋል? ጌታ እርሱን እና የገባችኋቸውን ቃልኪዳኖች እንድታስታውሱ የሚፈልገው ለምንድነው?

በተጨማሪም ጌሪት ደብልዩ.ጎንግ፣ “ሁልጊዜ አስታውሱት፣” ሊያሆና ግንቦት 2016(እ.አ.አ)፣ 108-11 ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 11፥1–9

ወደ ሰማይ የመድረሻ ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስን መከተል ነው።

የጥንት ባቤል ወይም ባቢሎን ለረዥም ዘመናት የክፋት እና የአለማዊነት ምልክት በመሆን ስታገለግል ቆይታለች ።( ራዕይ 18፥1–10ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 133፥14ይመልከቱ)። ኦሪት ዘፍጥረት 11፥1–9ን ስታጠኑ “ ረዥም ግንብ ገንብተው ሰማይ መድረስን በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ያደረገው“ ሰይጣን እንደሆነ በጻፈው በነቢዩ ሞርሞን የተሰጠውን ማስተዋል አሰላስሉ። (ሄለማን 6፥28፤ በተጨማሪም ቁጥር 26–27ይመልከቱ)። የባቢሎን ግንብ ታሪክ ለናንተ ምን ማስጠንቀቂያዎችን ይዟል?

በተጨማሪም ራዕይ 127፥1ን ይመልከቱ።

ምስል
የባቢሎን ግንብ

የባቢሎን ግንብ ምስል በዴቪድ ግሪን

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና ለቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 6–8.የኖህ መርከብ ታሪክ ነቢያትን መከተል መንፈሳዊ ደህንነት ሊሰጠን እንደሚችል ቤተሰባችሁን ለማስተማር እንዴት ልትጠቀሙ ትችላላችሁ? (“ኖህ እና ቤተሰቡ“ን በ ብሉይ ኪዳን ታሪኮችውስጥ ይመልከቱ)። ከወረቀት ወይም ከግንድ የአሻንጉሊት መርከብ ለመገንባት አብራችሁ መስራት ትችላላችሁ። ኦሪት ዘፍጥረት 6–7ን ስታነቡ መርከቡ ያስገኘውን ጥበቃ ነቢያትን በመከተል ከሚገኘው ጥበቃ ጋር ልታወዳድሩ ትችላላችሁ። ከነቢዩ የቅርብ ጊዜ ምክር ለመወያየት እና በመርከባችሁ የእርሱን የምክር ቃላት ለመጻፍ ልትፈልጉ ትችላላችሁ።

አግዚያብሄር የኖህን ቤተሰብ ካዳነው መርከብ ጋር ሊነጻጸር የሚችል ሌላ ምን ሰጥቶናል? ሌሎች ብዙ ቢኖሩም እነዚህ መረጃዎች አንዳንድ መልሶችን ይጠቁማሉ 2 ኔፊ 9፥7–13ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 115፥5–6፤ እና የፕሬዚዳንት ረሰል ኤም. ኔልሰን መልዕክት “አርአያ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን መሆን” (ሊያሆና ህዳር 2018(እ.አ.አ)፣ 113–14).

ሙሴ 7፥35የጌታ መንፈስ ከእኛ ጋር “መሆን“ ማለት ምን ማለት ነው?( 1 ኔፊ 7፥14ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥33ን ይመልከቱ)። መንፈሱ ከእኛ ጋር መሆኑን ተለማምደን የነበረው መቼ ነበር?

ኦሪት ዘፍጥረት 9፥8–17እናንተ ምን እንደሚወክል ስትነጋገሩ ትንንሽ ልጆች ቀስተ ደመና መሳል ወይም ማቅለም ሊያስደስታቸው ይችላል (በተጨማሪም የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ኦሪት ዘፍጥረት 9፥21–25 [የመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ]ይመልከቱ)። እንደ ቅዱስ ቁርባን ያሉ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል የገባነውን የጥምቀት ቃል ኪዳን የመሳሰሉ ቃል ኪዳናችንን ለማስታወስ የሚረዱንን ነገሮች ልትወያዩም ትችላላችሁ( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 20፥75–79ይመልከቱ፡፡)

ኦሪት ዘፍጥረት 11፥1–9፡፡ ኤተር 1:33–43 ን ማንበብ ቤተሰባችሁ ኦሪት ዘፍጥረት 11 ን ሲያጠና እና ስለባቢሎን ግንብ ሲማር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ከያሬድ ቤተሰቦች እና ከወንድሙ አለም በክፋት ውስጥ ቢሆንም ቤተሰባችን መንፈሳዊ ጥበቃ እንዲያገኝ የሚጠቅም ምን እንማራለን? ተመሳሳይ ችግር አጋጥሟቸው ስለነበረ ከኖህ እና ከቤተሰቦቹ ምን ተጨማሪ ትምህርቶች እንማራለን( ሙሴ 8፥13፣ 16–30ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “ነብዩን ተከተሉ፣” የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ፣ 110–11፣(ቁጥር 3) ፡፡

የግል ጥናትን ማሻሻል

ግንዛቤያችሁን አካፍሉ። ከቅዱሳን ጽሁፎች የተማራችሁትን ነገር ስታካፍሉ ሌሎችን ብቻ አይደለም የምትባርኩት የራሳችሁን ግንዛቤም ጥልቅ ታደርጋላችሁ። ከቅዱሳን ጽሁፎች ለቤተሰባችሁ፣ለጓደኞቻችሁ ወይም ለአጥቢያ አባላት ምን ለማካፈል ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

ምስል
የኖህ መርከብ

የኖህ መርከብ ምስል በአዳም ክሊንት ዴይ

አትም