ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥር 24–30 (እ.አ.አ) ሙሴ 7፦”ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው”


“ጥር 24–30 (እ.አ.አ)፡፡ ሙሴ 7፦ ‘ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው፣‘” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“ጥር 24–30 (እ.አ.አ)፡፡ ሙሴ 7፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ብዙ ሰዎች ፍቅር በተሞላበት ሁኔታ ሲነጋገሩ

እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፣ በኤማ ዶናልድሰን ቴይለር

ጥር 24–30 (እ.አ.አ)

ሙሴ 7

”ጌታ ህዝቡን ፅዮን ብሎ ጠራቸው”

ሙሴ 7ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ የምትቀበሉትን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች መዝግቡ፡፡ ይህንን በማድረግ ከጌታ ለሚሰጣችሁ መመሪያ ዋጋ እንደምትሰጡ እና የእርሱን ተጨማሪ መመሪያ እንደምትፈልጉ ታሳያላችሁ፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በመላው ታሪክ ውስጥ ሰዎች ሄኖክ እና ህዝቡ የደረሱበት ላይ ለመድረስ ሞክረዋል፦ ችግር እና ብጥብጥ የሌለበት በጣም ጥሩ ማህበረሰብ፡፡ እንደ እግዚያብሄር ህዝብ ይህንን ፍላጎት እንጋራለን፡፡ እርሱን ጽዮንን መገንባት ብለን እንጠራዋለን፤እናም ድሆችን ከመንከባከብ እና ሰላምን ከማራመድ በተጨማሪ—ቃልኪዳን መግባትን፣በጽድቅ አብሮ መኖርን እና እርስ በርሳችን እና “ከጽዮን ንጉስ” ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ መሆንን ያካትታል(ሙሴ 7፥53)፡፡ ጽዮንን የመገንባት ስራ በእኛ ጊዜም የቀጠለ በመሆኑ እንዲህ ብሎ መጠየቅ ይረዳል ፣ሄኖክ እና ህዝቡ እንዴት አደረጉት? ዙሪያቸው በክፋት የተሞላ ቢሆንም “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ“ እንዴት ሆኑ?(ሙሴ 7፥18) ሙሴ 7 ስለጽዮን ከሚሰጠን ብዙ ዝርዝሮች መካከል ለኋለኛው ቀን ቅዱሳን በተለይ ጠቃሚ የሆነው ይህ ሊሆን ይችላል፦ ጽዮን ከተማ ብቻ አይደለችም—የልብ እና የአዕምሮ ሁኔታ ነች፡፡ ጌታ እንዳስተማረው ጽዮን “ልበ ንጹህ“ ናት (ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 97፥21)፡፡ ስለዚህ ምናልባት ጽዮንን ለመገንባት ከሁሉም የተሻለው መንገድ በራሳችን ልብ እና ቤት ውስጥ መጀመር ነው፡፡

የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሙሴ 7፥16–21፣ 27፣ 53፣ 62–69

የሄኖክ ጥረቶች በራሳችን ህይወት ውስጥ ጽዮንን ለመገንባት ሞዴል ናቸው፡፡

ሙሴ 7 የእግዚያብሄር ተከታዮች ጽዮንን እንዴት እንደገነቡ የሚናገር መዝገብ ስለሆነ፣ ዛሬም ይህንኑ ለማድረግ ስንጥር ሊመራን እና ሊያነሳሳን ይችላል፡፡ ከ ሙሴ 7፥16–21፣ 27፣ 53፣ 62–69ስለጽዮን የተማራችሁትን ለመመዝገብ ይህን የመሰለ ሰንጠረዥ መጠቀምን አስቡ፡፡

ቁጥር

ስለጽዮን ምን ትማራላችሁ?

ይህ ጽዮንን ለመገንባት ስለምታደርጉት ጥረት ምን ይጠቁማል?

ቁጥር

7፥18

ስለጽዮን ምን ትማራላችሁ?

የጽዮን ህዝቦች “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ “ ነበሩ፡፡

ይህ ጽዮንን ለመገንባት ስለምታደርጉት ጥረት ምን ይጠቁማል?

እንደቤተሰብ እና እንደቤተክርስቲያን አንድ መሆን ያስፈልገናል፡፡

ቁጥር

7፥21

ስለጽዮን ምን ትማራላችሁ?

“[ጽዮን] ከጊዜ በኋላ ወደ ሰማይ ተወስዳለች፡፡ “

ይህ ጽዮንን ለመገንባት ስለምታደርጉት ጥረት ምን ይጠቁማል?

ጽዮንን መገንባት የቀስ በቀስ ሂደት ነው፡፡

ቁጥር

ስለጽዮን ምን ትማራላችሁ?

ይህ ጽዮንን ለመገንባት ስለምታደርጉት ጥረት ምን ይጠቁማል?

ቁጥር

ስለጽዮን ምን ትማራላችሁ?

ይህ ጽዮንን ለመገንባት ስለምታደርጉት ጥረት ምን ይጠቁማል?

ሙሴ 7፥18–19 ፣53

የእግዚያብሄር ህዝቦች “አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ “ ለመሆን መጣር አለባቸው፡፡

ሙሴ 7፥18–19 ጌታ ጽዮን ብሎ ስለጠራቸው ሰዎች አስፈላጊ ባህርያትን ይዘረዝራል፡፡ እነዚህ ባህርያት ጽዮንን ለመገንባት አስፈላጊ የሆኑት ለምን ይመስላችኋል? በዚህ ምዕራፍ እንደተገለጸችው ጽዮን ከሌሎች በአለም ካሉ የተጣመሩ ቡድኖች ወይም ድርጅቶች የምትለየው እንዴት ነው? ይህንን ጥያቄ ስታሰላስሉ በ ቁጥር 53ውስጥ ያሉትን “እኔ የጽዮን ንጉስ መሲህ ነኝ“ ስለሚሉት የኢየሱስ ክርስቶስ ቃላት ልታስቡ ትችላላችሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደንጉሳችን አለን ማለት ምን ማለት ነው? የጽዮንን ባህርያት እንድናዳብር እንዴት ይረዳናል?

በተጨማሪም ፊልጵስዩስ 2፥1–54 ኔፊ 1፥15–18ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥21105፥5ን ይመልከቱ።

ሰዎች ሰላምታ ሲለዋወጡ

“አንድ ልብ እና አንድ አዕምሮ “ ለመሆን መጣር አለብን (ሙሴ 7፥18).፡፡

ሙሴ 7፥21፣23–24፣ 27፣ 69

የሄኖክ ከተማ ምን ሆነች፡፡

“ተወሰደች” (ሙሴ 7፥21, 23)፣ “ከፍ አለች” (ሙሴ 7፥24)፣ “አረገች” (ሙሴ 7፥27)፣እና “ጠፋች” (ሙሴ 7፥69) የሚሉት ሃረጎች የጽዮንን እና የሄኖክን ህዝቦች በስጋ መነጠቅ እና ወደሰማይ መወሰድ ያመለክታሉ፡፡ የተቀየሩ ሰዎች እንደሟች “ህመምን ወይም ሞትን እንዳይቀምሱ የተለወጡ ናቸው (የቅዱሳን ጽሁፎች መመሪያ “የተቀየሩ አካላት፣” “ጽዮን፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ በተጨማሪም 3 ኔፊ 28፥4–9, 15–18, 39–40ን ይመልከቱ)፡፡

ሙሴ 7፥19–69

እግዚያብሄር ለልጆቹ ያነባል፡፡

አንዳንድ ሰዎች እግዚያብሄር በእኛ ላይ የሚሆነው ነገር ስሜታዊ ተጽዕኖ የማያሳድርበት እንደ እሩቅ አካል አድርገው ያዩታል፡፡ ነገር ግን ሄኖክ እግዚያብሄር ለልጆቹ ሲያለቅስ ራዕይ አይቷል፡፡ ሙሴ 7፥28-40ን ስታነቡ፣ እግዚያብሄር ያለቀሰበትን ምክንያቶች ፈልጉ? በ ሙሴ 7፥41-69ውስጥ በተገለጸው በቀሪው የሄኖክ ራዕይ ውስጥ እግዚያብሄር “ለዘላለም ሩህሩህ እና ደግ“ ስለመሆኑ ምን ማስረጃ ታገኛላችሁ?((ለምሳሌዎችሙሴ 7፥30ቁጥር 43፣47እና62 ይመልከቱ)፡፡

ሙሴ 7፥62

በመጨረሻው ቀናት፣ እግዚያብሄር የእርሱን ምርጦች ይሰበስባል።

ቁጥር 62 የመጨረሻዎቹን ቀናት ኩነቶች ይገልጻል። “ፅድቅን ከሰማያት እሰዳለሁ፤ እና ስለ አንድያ ልጄ፣ ከሙታን ትንሳኤውን፣ አዎን፣ እና ስለሁሉም ሰዎች ከሞት ስለመነሳት እንዲመሰክርም እውነትን ከምድር እልካለሁ” የሚሉት ሃረጎች ምን ማለት ሊሆኑ እንደሚችሉ አስቡ። እነዚህ ሃረጎች ስለኋለኛው ቀናት የእግዚአብሔር ሥራ ምን ያስተምሯችኋል?

የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ሙሴ 7፥18–19ቤተሰባችሁ “አንድ ልብ“ መሆን ምን ማለት እንደሆነ በምናባቸው ማየት እንዲችሉ ለመርዳት፣ምናልባት የወረቀት ልብ ልትሰሩ እና ለእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል አንድ ቁራጭ አንዲደርስ አድርጋችሁ ለመገጣጠም ጨዋታ መቆራረጥ ትችላላችሁ። የቤተሰብ አባላት በደረሳቸው ቁራጭ ላይ ስማቸውን ሊጽፉ እና ከዚያም ልቡን ለመገጣጠም አብረው መስራት ይችላሉ። የመገጣጠም ጨዋታውን እየሰራችሁ ስለያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የምትወዷቸውን ነገሮች ልታወሩ ትችላላችሁ።

ሙሴ 7፥28–31፣ 35ከእነዚህ ቁጥሮች ስለእግዚያብሄር ምን እንማራለን?

ሙሴ 7፥32እግዚያብሄር የመምረጥ ነጻነት ለምን ሰጠን? የእግዚያብሄር ትዕዛዛት የመምረጥ ነጻነታችንን እንደሚገድቡ ለሚሰማው ሰው ምን ልንል እንችላለን? 2 ኔፊ 2፥25–27 ን ማንበብ ለዚህ ውይይት ግብአት ሊሆን ይችላል።

ሙሴ 7፥59–67ቤተሰባችሁ ሙሴ 7፥59–67ን ሲያነብ ጌታ ስለመጨረሻው ቀን ለሄኖክ የነገረውን ምልክት አድርጉ ወይም ማስታወሻ ያዙ—ለምሳሌ እግዚያብሄር “የእርሱ ተመራጮችን እንዲሰባሰቡ ያደርጋል“ (ቁጥር 62)እንዲም “ከመጥፎዎቹ መካከል ታላቅ ስቃይ“ ይሆናል(ቁጥር 66)። በመጨረሻው ቀናት ክፋት ቢንሰራፋም እምነት እና ተስፋ እንዴት ሊኖረን ይችላል? እንደዚህ ውይይት አካል የሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራስባንድን አነዚህን ቃላት ማንበብን አስቡ ፦ “ወንድሞች እና እህቶች ደፋር ሁኑ። አዎ፣የምንኖረው በአስቸጋሪ ወቅት ውስጥ ነው ነገር ግን በቃልኪዳን መንገዱ ውስጥ ሆነን መፍራት አይገባንም። ይህንን ስታደርጉ በምንኖርበት ጊዜ ምክንያት ወይም በመንገዳችሁ ላይ በሚመጡት ችግሮች እንዳትሸበሩ እባርካችኋለሁ። በተቀደሱ ስፍራዎች ላይ መቆምን፣ እናም አለመነቃነቅን እንድትመርጡ እባርካችኋለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለ እና ከላይ እንደሚመለከተን፣ እንደሚጠነቀቅልን እና ከጎናችን እንደሚቆም በገባቸው ቃልኪዳኖች እንድታምኑ እባርካችኋለሁ።”(“አትሸበሩ፣” ሊያሆና፣ ህዳር. 2018(እ.አ.አ)፣ 21)።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፦ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦“ፍቅር በቤት፣“ መዝሙሮች፣ ቁጥር. 294

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ንቁ አስተዋይ ሁኑ። በልጆቻችሁ ህይወት ውስጥ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ትኩረት ስታደርጉ እጅግ በጣም ጥሩ የማስተማር እድሎችን ታገኛላችሁ። ቀኑን ሙሉ የሚቀርቡት የልጆቻችሁ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የማስተማሪያ ፍንጭ ሊሰጡ ይችላሉ። ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 16ን ይመልከቱ፡፡)

ሄኖክ እና ህዝቡ ወደላይ ወደ ብርሃን ሲመለከቱ የሚያሳይ ምስል

የጽዮን ከተማ ተለውጣ በዴል ፓርሰን