ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥር 3–9 (እ.ኤ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 2–3፤ አብርሃም 4–5፦“በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“


“ጥር 3–9 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1–2፤ ሙሴ 2–3፤ አብርሃም 4–5:“በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“ጥር 3–9 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 1–2፤ሙሴ2–3፤ አብርሃም 4–5፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦቸና ለቤተሰቦቸ፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የመሬት እና የጨረቃ ምስል

ጥር 3–9 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 1–2ሙሴ 2–3አብርሃም 4–5

“በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“

ስለፍጥረት ከዚህ በፊት አንብባችሁ የነበረ ቢሆንም ሁልጊዜ ከቅዱሳን መጻህፍት ተጨማሪ የምንማረው ነገር አለ፡፡ አዲስ ግንዛቤ እንድታገኙ እንዲረዳችሁ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት ለማግኘት ጸልዩ፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በዙሪያችን ያለው አለም በጣም ያማረ እና ባለሞገስ ስለሆነ ምድር “ባዶ እና አንዳችም ያልነበረባት“ “ባዶ እና ባድማ“ የነበረችበትን ጊዜ ለመገመት ያስቸግራል (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥2አብርሃም 4፥2)፡፡ የፍጥረት ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ነገር እግዚያብሄር ከአንድ ያልተደራጀ ነገር አንድ ታላቅ ነገር መስራት እንደሚችል ነው፡፡ ህይወት ምስቅልቅል በሚመስልበት ጊዜ ያንን ማስታወሱ ይጠቅማል፡፡ ሰማያዊ አባት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪዎች ናቸው፣ በእኛ ላይ ያላቸው የፈጠራ ስራ አላለቀም፡፡ በህይወታችን የጨለማ ጊዚያት ብርሃን እንዲፈነጥቅ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በህይወት ማዕበል አዘል ባህሮች መካከል ጠንካራ መሬት ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ነገሮቹን ማዘዝ ይችላሉ እናም ነገሮቹ እንደታዘዙት ብንታዘዝ ቃላቶቻቸው እንድንሆን ወደታሰብነው ወደ ቆንጆ ፍጥረታት ሊለውጡን ይችላሉ፡፡ ያ በእግዚያብሄር መልክ እና አምሳያ የመፈጠር ትርጉም ክፍል ነው( ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)፡፡ እንደእርሱ የመሆን አቅም አለን ፦ከፍ ከፍ ያልን፣የከበርን የሰለስቲያል አካላት።

ስለኦሪት ዘፍጥረት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘፍጥረት“ የሚለውን ይመልከቱ፡፡

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥1–25ሙሴ 2፥1–25አብርሃም 4፥1–25

በሰማያዊ አባት ትዕዛዝ ኢየሱስ ክርስቶስ መሬትን ፈጠረ፡፡

ሽማግሌ ዲ.ቶድ ክሪስቶፈርሰን “የፍጥረት ሂደቱ ዝርዝር የቱንም ያህል ቢሆን ድንገተኛ እንዳልሆነ ነገር ግን በእግዚያብሄር አብ የተመራ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የተከናወነ እንደሆነ እናውቃለን“ ብለዋል(“Why Marriage, Why Familyሊያሆና፣ ግንቦት 2015(እ.አ.አ) 51)፡፡ አለም እንዴት እንደተፈጠረ በትክክል የማናውቀው ብዙ ነገር ቢኖርም እግዚያብሄር በ ኦሪት ዘፍጥረት 1፥1–25ሙሴ 2፥1–25፤ እና አብርሃም 4፥1–25ውስጥ ከገለጸው በመነሳት ስለፍጥረት ምን እንደምትማሩ አሰላስሉ፡፡ በነዚህ ዘገባዎች ውስጥ ተመሳሳይ የሆነ ምን ነገር ታስተውላላችሁ? ምን የተለየ ነገር ታስተውላላችሁ? ስለፍጥረት ስታነቡ ስለሰማይ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ሃሳቦች አሏችሁ?

ደግሞም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 101፥32–34።ይመልከቱ።

ምስል
የፍጥረትን የተለያዩ ደረጃዎች የሚያሳይ የጨርቅ ሽፋን

ፍጥረት፣ በ ጆአን ሂበርት ዱርሺ

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥27–282፥18–25ሙሴ 3፥18, 21–25አብርሃም 5፥14–19

በወንድ እና በሴት መካከል የሚደረግ ጋብቻ በእግዚያብሄር የታዘዘ ነው፡፡

አዳም እና ሄዋን በትዳር የተጣመሩት በዘላለማዊ የክህነት ስልጣን ሃይል ለዚህ ህይወት እና ለዘላለም ነው፡፡“Lessons from Eveኢንዛይን፣ ህዳር 1987(እ.አ.አ)፣ 87)፡፡ ይህን እውነት ማወቅ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? ኦሪት ዘፍጥረት 1፥27–282፥18–25ሙሴ 3፥18, 21–25፤ እና አብርሃም 5፥14–19ን ስታነቡ ይህንን አሰላስሉ፡፡ በእግዚያብሄር እቅድ ውስጥ ስላለ ጋብቻ ተጨማሪ ለመማር የምትወዱ ከሆነ ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች አንብቡ እና አሰላስሉ፡፡ እነዚህ መረጃዎች ትዳራችሁን ለማሻሻል ወይም ወደፊት ለምትፈጽሙት ትዳር ለመዘጋጀት ምን እንድታደርጉ ያነሳሷችኋል?

በተጨማሪም ማቴዎስ 19፥4-61 ቆሮንቶስ 11፥11፤ሊንዳ ኬ.በርተን፣“We’ll Ascend Together፣“ ሊያሆና፣ ግንቦት 2015 (እ.አ.አ)29–32፣“ቤተሰብ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣“ ChurchofJesusChrist.org“ይመልከቱ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 2፥2-3ሙሴ 3፥2-3አብርሃም 5፥2-3

እግዚያብሄር የሰንበትን ቀን ባረከው እና ቀደሰው፡፡

እግዚያብሄር የሰንበትን ቀን ቅዱስ አደረገው እናም እንቀድሰው ዘንድ ይጠይቀናል። ሽማግሌ ዴቪድ ኤ.ቤድናር “ሰንበት የእግዚያብሄር ቀን ነው። በተለይ እርሱን ለማምለክ እና የእርሱን ታላቅ እና ውድ ቃልኪዳን ለመቀበል እና ለማስታወስ የተለየ ቅዱስ ጊዜ ነው” ሲል አሰተምሯል (“Exceeding Great and Precious Promises፣“ ሊያሆና ህዳር 2017(እ.አ.አ)፣ 92)፡፡ ይህንን አረፍተ ነገር እና ኦሪት ዘፍጥረት 2፥2-3ሙሴ 3፥2-3፤ ወይም አብርሃም 5፥2-3 ን የሰንበትን ቀን ለማክበር ለምን እንደምትመርጡ ለአንድ ሰው ለማብራራት እንዴት ልትጠቀሙ ትችላላችሁ? የእርሱን ቀን በመቀደሳችሁ ጌታ እንዴት ነው የባረካችሁ?

በተጨማሪም ኢሳይያስ 58፥13–14ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 59፥9-13፤ “The Sabbath Is a Delight” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org.ን ይመልከቱ፥።

ምስል
family study icon

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥1–25ሙሴ 2፥1–25አብርሃም 4፥1–25ስለፍጥረት መማርን ለቤተሰባችሁ የሚያዝናና ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? በእያንዳንዱ የፍጥረት ታሪክ ክፍለ-፟ጊዜ የተሰሩትን እንደ ከዋክብት፣ዛፎች ወይም እንስሶች አይነት ነገሮችን ለመፈለግ ቤተሰባችሁን ከቤት ውጪ መውሰድ ትችላላችሁ። በያንዳንዱ ክፍለ-ጊዜ የተፈጠሩ ነገሮችን ምስሎች ልታሳዩ እና ከፍጥረት ዘገባዎች መካከል አንዱን በጋራ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰብ አባላት መስሎቹን በቅደም ተከተል እንደያስቀምጡ መጋበዝ ትችላላችሁ። እነዚህ ፍጥረታት ስለሰማያዊ አባት እና ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሩናል?

ኦሪት ዘፍጥረት 1ሙሴ 2አብርሃም 4የፍጥረት ታሪክ አቀራረብ አንዱ መንገድ በ ኦሪት ዘፍጥረት 1 ወይም በ ሙሴ 2 ውስጥ እግዚያብሄር የሰራቸውን ስራዎች ምን ያህል ጊዜ “መልካም“ እንዳለ ቤተሰባችሁ እንዲፈልግ መጋበዝ ነው። ራሳችንን ጨምሮ—የእግዚያብሄርን ፍጥረታት እንዴት መንከባከብ እንደሚገባን ምን ይጠቁመናል? እነዚህ ኩነቶቸ በ አብርሃም 4ውስጥ ከተገለጹባቸው ቃላት ሁኔታ ምን እንማራለን?

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26-27ሙሴ 2፥26–27አብርሃም 4፥26–27በእግዚአብሔር አምሳል እንደተፈጠርን ማወቃችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ስለራሳችን፣ስለሌሎች እና ስለእግዚያብሄር በሚሰማን መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

ትንንሽ ልጆች ካሏችሁ ሙሴ 2፥27 ን አብራችሁ ልታነቡ እና አንድ ቀላል ጨዋታ ልትጫወቱ ትችላላችሁ፦እንደ ስዕል 90 የመሰለ በ Gospel Art Book (2009(እ.አ.አ))ውስጥ የሚገኘውን የሰማይ አባትን እና የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል አሳዩ፣ ከዚያም የቤተሰብ አባላት ተራ በተራ የሰማይ አባትን ወይም የኢየሱስን የአካል ክፍል እንዲጠቁሙ ጠይቁ። ከዚያም ሌሎቹ የቤተሰብ አባላት ያንኑ የአካል ክፍል በራሳቸው ሰውነት ላይ ሊያሳዩ ይችላሉ።

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥28ሙሴ 2፥28አብርሃም 4፥28”እንዲባዙ እና ምድርን ይሞሉ ዘንድ እግዚአብሔር ለልጆቹ የሰጠው ትእዛዝ አሁንም በተግባር የሚውል ነው ” (“ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ፣” ChurchofJesusChrist.org)። የቤተሰብ አባላት ይህንን እውነት ለማያውቁ ወይም በተለየ መንገድ ለሚያምኑ ስለዚህ ትዕዛዝ ያለንን እምነት እንዴት ለማስረዳት እንደሚቻል መተወን ይችላሉ።

ኦሪት ዘፍጥረት 1፥28ሙሴ 2፥28አብርሃም 4፥28“ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ …ግዟቸው“ ምን ማለት ነው? (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 59፥16-21ን ይመልከቱ)፡፡ ምድርን ለመንከባከብ ያለብንን ሃላፊነት ቤተሰባችን እንዴት ሊወጣው ይችላል?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ፡፡

የሚመከር መዝሙር፦ “የሰማይ አባቴ ይወደኛል፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 228-29።

የማስተማር ዘዴያችንን ማሻሻል

ቅዱሳን ጽሁፎችን በህይወታችን መተግበር፡፡ ከቅዱስ ጽሁፍ አንድ ምንባብ ካነበባችሁ በኋላ የቤተሰበብ አባላት በህይወታቸው እንዲተገብሩት ጋብዟቸው፡፡ ለምሳሌ፦ ሙሴ 3፥1–3 በየሳምንቱ በምናደርገው የሰንበት ቀን አከባበራችን እንዴት ተግባራዊ ይሆናል? ( በአዳኙ መንገድ ማስተማር፣ 21ን ይመልከቱ፡፡)

ምስል
ኢየሱስ ክርስቶስ በደመናዎች መካከል ቆሞ።

ፍጥረት፣ ምስል በአኒ ሄንሪ ናደር

አትም