ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥር 10–16 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 3-4፤ ሙሴ 4-5፦ የአዳም እና የሄዋን ውድቀት


“ጥር 10–16 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 3-4፤ ሙሴ 4–5 ፦የአዳም እና የሄዋን ውድቀት፣“ ኑ፤ ተከተሉኝ—-ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፡ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“ጥር 10–16 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 3-4፤ ሙሴ 4–5፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
አዳም እና ሔዋን አብረው ሲራመዱ

አዳም እና ሔዋን፣ በዳግላስ ኤም. ፍራየር

ጥር 10–16 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 3-4ሙሴ 4–5

የአዳምና ሔዋን ውድቀት

ኦሪት ዘፍጥረት 3-4 እና ሙሴ 4–5ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ጌታ ምን ሊያስተምራችሁ እየሞከረ እንደሆነ አስቡ። አነዚህን እውነቶች እና መንፈሳዊ ግንዛቤያችሁን መዝግቡ እንዲሁም በሳምንቱ ቀናቶች ሁሉ አጢኗቸው።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በመጀመሪያ የአዳም እና ሄዋን የውድቀት ታሪክ አሳዛኝ ሊመስል ይችላል፡፡ አዳም እና ሄዋን ከሚያምረው የኤደን የአትክልት ስፍራ ተባርረው ነበር፡፡ ህመም፣ሃዘን እና ሞት ወዳለበት አለም ተወረወሩ( ኦሪት ዘፍጥረት 3፥16–19ይመልከቱ)። እንዲሁም ከሰማያዊ አባታቸው ተለይተው ነበር። ነገር ግን በሙሴ መጽሃፍ ውስጥ በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት በተመለሱት እውነቶች ምክንያት የአዳም እና የሄዋን ታሪክ በርግጥ ተስፋ እንደሆነ እናውቃለን—እንዲሁም እግዚያብሄር ለልጆቹ ያለው እቅድ አስፈላጊ ክፍል እንደሆነም።

የኤደን የአትክልት ስፍራ ያማረ ነበር። ነገር ግን አዳም እና ሄዋን ካማረ አካባቢ የበለጠ ነገር ያስፈልጋቸው ነበር። የማደግ እድል—ያስፈልጋቸው ነበር —እኛም ሁላችን እንደሚያስፈልገን። የኤደንን የአትክልት ስፍራ ለቆ መውጣት ወደ እግዚያብሄር ለመመለስ እና በመጨረሻም እንደ እርሱ ለመሆን አስፈላጊው የመጀመሪያ እርምጃ ነበር። ያም ማለት ተቃውሞን መጋፈጥ፣ስህተትን መስራት፣ንስሃ መግባትን መማር እና እድገትን እና “የመዳናቸችንን ደስታ “ የሚቻል የሚያደርገውን የአዳኙን የሃጥያት ክፍያ ማመን ማለት ነበር(ሙሴ 5፥11)። ስለዚህ ስለአዳም እና ሄዋን ውድቀት በምታስቡበት ጊዜ አሳዛኝ በሚመስለው ኩነት ላይ ሳይሆን በከፈታቸው እድሎች ላይ አተኩሩ—ትኩረታችሁን አዳም እና ሄዋን ባጡት ገነት ላይ ሳይሆን ምርጫቸው እንድንቀበል በፈቀደልን ክብር ላይ አድርጉ።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 3፥1-7ሙሴ 45፥4-12

ውድቀት እግዚያብሄር ልጆቹን ለማዳን የሚያስፈልግ የእቅዱ አካል ነበር።

የአዳም እና ሄዋን ውድቀት አካላዊ እና መንፈሳዊ ሞትን ወደ ምድር አመጣ። በተጨማሪም መከራን፣ሃዘንን እና ሃጥያትንም አምጥቷል። እነዚህ ሁሉ በውድቀቱ ለመፀፀት ምክንያቶች ይመስላሉ። ነገር ግን ውድቀት በ “አብ አንድያ ልጅ መስዋእት “ አማካኝነት ልጆቹን ለማዳን እና ከፍ ለማድረግ የታለመ የሰማይ አባት እቅድ አካል ነበር(ሙሴ 5፥7)። ኦሪት ዘፍጥረት 3፥1-7ሙሴ 45፥4-12ን ስታጠኑ ውድቀትን እንዲሁም የክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ውድቀትን እንዴት እንደሚቋቋመው እንድትገነዘቡ የሚረዳችሁን ምን እውነት ታገኛላችሁ? እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ሊረዱ ይችላሉ፦

  • ውድቀቱ አዳም እና ሔዋን ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነበር? እኔ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

  • አዳም እና ሄዋን መስዋዕቶች ያቀረቡት ለምን ነበር? እነዚያ መስዋዕቶች ምንን ያመላክቱ ነበር? በነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ከሰፈሩት ከመልአኩ ቃላት ምን መማር እችላለሁ?

  • አዳም እና ሄዋን ከውድቀቱ በኋላ “ደስተኛ “የሆኑት ለምን ነበር? በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኔን ለማዳን ስላዘጋጀው ስለእግዚያብሄር እቅድ ከዚህ ዘገባ ምን እማራለሁ?

በመጽሃፈ ሞርሞን እና በሌሎች የኋለኛው ቀን ራዕዮች ምክንያት በውድቀት ላይ የተለየ እይታ አለን። ለምሳሌ፣ ነቢዩ ሌሂ በ 2 ኔፊ 2 ፥15–27ውስጥ ስለአዳም እና ሄዋን ቤተሰቦቹን ምን እንዳስተማረ አስቡ። የሌሂ ትምህርቶች በኤደን የአትክልት ስፍራ ምን እንደተከሰተ ለማብራራት እና ለምን አስፈላጊ እንደነበረ እንድንገነዘብ የሚረዱን እንዴት ነው ?

በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ 15፥20–22ሞዛያ 3፥19አልማ 12፥21–37ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 29፥39–43የእምነት አንቀጾች 1፥3፤ ዳሊን ኤች. ኦክስ፣“ታላቁ እቅድ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2020(እ.አ.አ)፣ 93–96፤ ዳሊን ኤች. ኦክስ፣ “ለሁሉም ነገሮች ተቃራኒ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2016(እ.አ.አ)፣ 114–17፤ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “Where Justice, Love, and Mercy Meet፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2015(እ.አ.አ)፣ 104–6.ይመልከቱ።

ምስል
ሄዋን ፍሬ ይዛ

ኤደንን መልቀቅ፣ በአኒ ሄንሪ ናደር

ኦሪት ዘፍጥረት 3፥16; ሙሴ 4፥22

አዳም በሄዋን ላይ “ገዥ“ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?

ይህ የቅዱስ ጽሁፍ ምንባብ አንዳንድ ጊዜ አንድ ባል ሚስቱን ደግነት በጎደለው ሁኔታ ቢይዝ ተገቢ ነው የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ሲወሰድበት ቆይቷል። በእኛ ጊዜ የጌታ ነቢያት ባል በቤት ውስጥ በጽድቅ መምራት ሲኖርበት ሚስቱንም እንደ አቻ ጓደኛ ማየት እንዳለበት አስተምረዋል (ቤተሰብ፦ ለአለም የተላለፈ አዋጅ[ChurchofJesusChrist.org] ይመልከቱ)። ሽማግሌ ዴል ጂ. ረንላንድ እና እህት ሩት ላይበርት ረንላንድ ጻድቅ ባል “ማገልገል ይሻል፤፤ስህተቶችን ይቀበላል እንዲሁም ይቅርታን ይሻል፤ምስጋና ለማቅረብ ፈጣን ነው፤የቤተሰብ አባላት ምርጫዎችን ከግምት የሚያስገባ ይሆናል፤ለህይወት አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማቅረብ እና ቤተሰቡን ለመጠበቅ ታላቅ የሃላፊነት ሸክም ይሰማዋል፤ሚስቱን በከፍተኛ ክብር እና ትህትና ይይዛታል። … ቤተሰቡን ይባርካል”(የመልከጼዴቅ የክህነት ስልጣን፦ ትምህርቱን መገንዘብ፣ መርሆዎቹን መኖር [2018(እ.አ.አ)]፣ 23)።

ሙሴ 5፥4–9፣ 16–26

እግዚያብሄር መስዋዕቶቼን በፈቃደኛ እና ታዛዥ ልብ ካቀረብኳቸው ይቀበላል።

አዳም እና ሄዋን የእንስሳ መስዋዕቶች የኢየሱስ የሃጢያት ክፍያ ምልክቶች እንደነበሩ ተምረዋል፣ አንዲሁም ይህንኑ ”ለወንድ እና ለሴት ልጆቻቸው አሳውቀዋል”(ሙሴ 5፥12) ሙሴ 5፥4–9፣ 16–26ን ስታጠኑ ሁለቱ ወንዶች ልጆቻቸው ቃኤል እና አቤል በእነዚህ መስዋዕቶች ላይ ያላቸውን የተለያዩ ዝንባሌዎች አጢኑ። ጌታ የአቤልን መስዋዕት ተቀብሎ የቃኤልን ሳይቀበል የቀረው ለምንድን ነው?

ጌታ ምን አይነት መዋዕቶችን ይጠይቃችኋል? በ ሙሴ 5፥4–9፣ 16–26 ውስጥ ስለነዚያ መስዋዕቶች የምታስቡበትን መንገድ የቀየረ አንድ ነገር አለ?

በተጨማሪም መዝሙር 4፥52 ቆሮንቶስ 9፥7ኦምኒ 1፥263 ኔፊ 9፥19–20ሞሮኒ7፥6–11ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 97፥8፤ ጀፍሪ አር. ሆላንድ፣ “የእግዚያብሄርን በግ ተመልከቱ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019፣ 44–46 ይመልከቱ።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 3ሙሴ 4ቤተሰባችሁ የአዳም እና የሄዋንን ውድቀት በተሻለ መንገድ እንዲገነዘብ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? የ ”አዳም እና ሄዋን” ምስሎችን (ከ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች) መገልበጥ እና ቆርጣችሁ ማውጣት ትችላላችሁ። ከዚያም የአዳም እና የሄዋንን ተሞክሮዎች ስትወያዩ ምስሎቹን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ አብራችሁ መስራት ትችላላችሁ። ለሰማይ አባት የደህንነት ዕቅድ ውድቀት አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው? “The Fall” የሚለውን ቪዲዮ (ChurchofJesusChrist.org) መመልከት ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሊረዳ ይችላል።

ሙሴ 4፥1–4ከነዚህ ጥቅሶች ሰለ እግዚያብሄር፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለሰይጣን ምን እንማራለን? ሰይጣን ሊያጠፋው ፈልጎት የነበረው የመምረጥ ነጻነት ለእግዚያብሄር እቅድ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ሙሴ 5፥5–9አዳኙን ለማስታወስ እንዲረዳቸው እግዚያብሄር አዳም እና ሄዋንን ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው? ስለአዳኙ ለማሰብ እንዲረዳን እግዚያብሄር ምን ሰጥቶናል?

ሙሴ 5፥16–34“የወንድማችን ጠባቂ” መሆን ማለት ምን ማለት ነው? እንደቤተሰብ አንዳችን ሌላችንን በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ የምንችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፥ “ትክክለኛውን መንገድ ምረጡ፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 160–61።

የግል ጥናትን ማሻሻል

የቅዱሳን መጻህፍት ጥናት መርጃን ይጠቀሙ ቅዱሳን ጽሁፎችን በምታጠኑበት ጊዜ የግርጌ ማስታዎሻዎቹን፣ የአርዕስት መምሪያን፣ የመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ-ቃላትን፣ እና የቅዱሳት ጽሁፎች መመሪያን እንዲሁም ተጨማሪ ማስተዋልን ለማግኘት ሌሎች የጥናት እርዳታዎችን ተጠቀሙ።

ምስል
መልአክ አዳምን እና ሔዋንን እየጎበኘ

ምስስል፣ በዋልተር ሬን

አትም