ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ብሉይ ኪዳንን ማንበብ ፦ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች


”ብሉይ ከዳንን ማንበብ፦ ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፣” .ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]

”ብሉይ ኪዳንን ማንበብ፦ ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)

የሃሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች

ብሉይ ኪዳንን ማንበብ

የግል ትርጉም ፈልጉ

በዚህ አመት ብሉይ ኪዳንን ለማጥናት ያገኛችሁትን እድል ስታስቡ እንዴት ይሰማችኋል? ጉጉት? ጥርጣሬ? ፍርሃት? እነዚህን ሁሉ ስሜቶች መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ብሉይ ኪዳን በአለም እጅግ በጣም ጥንታዊ ከሆኑ የጽሁፍ ስብስቦች አንዱ ነው፤እናም ያ አስደሳችም አስፈሪም ያደርገዋል። እነዚህ ጽሁፎች ባይተዋር እና አንዳንድ ጊዜ ያልተለመደ ብሎም የማይመች ሊመስል ከሚችል ከአንድ ጥንታዊ ባህል ነው የመጡት። ሆኖም በነዚህ ጽሁፎች ውስጥ ሰዎች የተለመዱ የሚመስሉ ልምምዶችን ሲያከናውኑ እናያለን ፤እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን መለኮታዊ ባህርይ እና ወንጌሉን የሚመሰክሩትን የወንጌል ጭብጦች እናውቃለን፡፡

አዎን፣ እንደ አብርሃም፣ ሳራ፣ሃና እና ዳንኤል ያሉ ሰዎች የኖሩት ኑሮ በተወሰኑ መንገዶች ከእኛ በጣም የተለየ ነበር፡፡ ነገር ግን፣በተጨማሪም የቤተሰብን ደስታና እና አለመግባባት፣የእምነት እና የጥርጣሬ ጊዜያትን እንዲሁም ስኬትን እና ውድቀትን አሳልፈዋል—ልክ እንደ እኛ እንደሁላችን፡፡ ከሁሉ በላይ እምነትን ተለማምደዋል፣ ንስሃ ገብተዋል፣ቃልኪዳኖችን ገብተዋል፣መንፈሳዊ ልምምዶችም ነበሯቸው እንዲሁም እግዚያብሄርን ለመታዘዝ ሲያደርጉ የነበረውን ጥረት አላቋረጡም ነበር፡፡

እናንተ እና ቤተሰባችሁ በዚህ አመት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የግል ትርጉም ይገኝ ይሆን ብላችሁ ካሰባችሁ ሌሂ እና የሳርያ ቤተሰብ እንዳገኘ አስታውሱ፡፡ ኔፊ፣ወንድሞቹ ማበረታቻ ወይም ማስተካከያ ወይም እይታ ባስፈለጋቸው ጊዜ ከኢሳያስ መጽሃፍ ስለሙሴ እና ስለትምህርቶቹ ታሪኮችን አጋርቷል፡፡ ኔፊ “ነፍሴ በቅዱሳን መጻህፍት ትደሰታለች“(2 ኔፊ 4፥15)ባለበት ጊዜ ዛሬ የብሉይ ኪዳን አካል ስለሆኑት ቅዱሳን መጻህፍት እየተናገረ ነበር፡፡

አዳኙን እሹ

እናንተ እና ቤተሰባችሁ ብሉይ ኪዳንን በማጥናት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መቅረብ ይቻል ይሆን ብላችሁ ካሰባችሁ አዳኙ እራሱ እንደዚያ እንድናደርግ እንደጋበዘን አስታውሱ፡፡ “ቅዱሳን መጻህፍት …ስለእኔ የሚሰክሩ ናቸው“ዮሃንስ 5፥39ብሎ ለአይሁድ መሪዎች ሲነግራቸው ብሉይ ኪዳን ብለን ስለምንጠራቸው ጽሁፎች እየተናገረ ነበር፡፡ በምታነቡት ነገር ውስጥ አዳኙን ለማግኘት በትዕግስት ማሰላሰል እና የመንፈስን ምሪት መሻት ሊያስፈልጋችሁ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ስለእርሱ የሚናገሩት ጥቅሶች በኢሳይያስ ገለጻ ውስጥ እንዳለው ግልጽ ይመስላሉ፣ “ህጻን ተወልዷልና፣ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና: …ስሙም የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“(ኢሳይያስ 9፥6)። በሌሎች ቦታዎች አዳኙ የተወከለው ቀጥታ ባልሆኑ ምልክቶች እና ምስስሎች ነው—ለምሳሌ፣በእንስሳት መስዋዕት ገለጻ በኩል( ኦሪት ዘሌዋውያን 1፥3–4ይመልከቱ)ወይንም ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር በሚልበት እና ከረሃብ በሚታደጋቸው ዘገባ አማካኝነት።

በአዳኙ ላይ ታላቅ እምነት አንዲኖራችሁ ከፈለጋችሁ ብሉይ ኪዳንን በምታነቡበት ጊዜ ታገኙታላችሁ። ምናልባት በዚህ አመት የጥናታችሁ አላማ ይህ ሊሆን ይችላል። ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርቧችሁን ምንባቦች፣ታሪኮች እና ትንቢቶች እንድታገኙ እና በእነሱም ላይ እንድታተኩሩ መንፈሱ እንዲመራችሁ ጸልዩ።

የጥንት ነቢይ ጽሁፍ

የብሉይ ኪዳን ነቢይ ጁዲት ኤ. መህር

በአምላክ ተጠብቆ የቆየ

ብሉይ ኪዳን የሰው ልጆችን የተሟላ እና ትክክለኛ ታሪክ እንዲያቀርብላችሁ አትጠብቁ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ጸሃፊዎች እና አጠናቃሪዎች ሊፈጥሩ የሞከሩት ያንን አይደለም። የእነሱ ትልቅ ጉዳይ ስለእግዚያብሄር—ለልጆቹ ስላለው እቅድ፣የእርሱ የቃል ኪዳን ህዝብ መሆን ማለት ምን ማለት ስለመሆኑ እንዲሁም በቃል ኪዳናችን መኖር ሳንችል ስንቀር ቤዛ እንዴት እንደምናገኝ አንድ ነገር ማስተማር ነበር። አንዳንድ ጊዜ ታሪካዊ ኩነቶችን እነሱ እንደገባቸው በመግለጽ አዘጋጅተውታል—ከታላላቅ ነቢያት ህይወት የተገኙ ታሪኮችን ጨምሮ። ኦሪት ዘፍጥረት የዚህ አንድ ምሳሌ ነው ልክ መጽሃፈ ኢያሱ ፣መጽሀፈ መሳፍንት እና መጽሃፈ ነገስት ቀዳማዊ እና ካልዕ እንደሆኑት ሁሉ። ነገር ግን ሌሎች የብሉይ ኪዳን ጸሃፊዎች ታሪክ-ነክ ለመሆን በጭራሽ አላለሙም። ከዚያ ይልቅ እንደ ግጥም እና ስነጽሁፍ ባሉ የስነ-ጥበብ ስራዎች አማካኝነት አስተምረዋል። መዝሙረ ዳዊት እና መጽሃፈ ምሳሌ በዚህ ክፍል ውስጥ ይገባሉ። እንዲሁም ከኢሳይያስ ጀምሮ እስከ ሚልክያስ ለጥንት እስራኤላውያን የእግዚያብሄርን ቃል የተናገሩ—እንዲሁም በመጽሃፍ ቅዱስ ተዐምራት አማካኝነት ዛሬም የሚያነጋግሩን የነቢያት ውድ ቃላት አሉ።

እነዚህ ሁሉ ነቢያት፣ገጣሚያን እና አቀናባሪዎች ቃላቶቻቸው ከሺዎች አመታት በኋላ በአለም ዙሪያ በሚገኙ ሰዎች ይነበቡ እንደሆን ያውቁ ነበር? አናውቅም። ነገር ግን የሆነው በትክክል ይህ ስለሆነ እንደነቃለን። መንግስታት ተነስተዋል ወድቀዋል፣ከተሞች ድል ተነስተዋል ፣ነገስታት ኖረዋል ሞተዋል ነገር ግን ብሉይ ኪዳን ከትውልድ እስከ ትውልድ ፣ከጸሃፊ እስከ ጸሃፊ ከትርጉም እሰከ ትርጉም ሁሉንም አልፎ ዘልቋል። በርግጥ አንዳንድ ነገሮች ጠፍተዋል ወይም ተቀይረዋል ሆኖም ብዙዎቹ በተዐምራዊ መንገድ ተጠብቀዋል።1

በዚህ አመት ብሉይ ኪዳንን ስታነቡ እነዚህ ማስታወስ የሚገቧችሁ ጥቂቶች ነገሮች ናቸው። ምናልባት እግዚያብሄር እነዚህን የጥንት ጽሁፎች የጠበቃቸው እናንተን እና በምን አይነት ሁኔታዎች ውስጥ እያለፋችሁ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው። ምናልባት አናንተን ወደእርሱ የሚያቀርብ አንድ ነገር እንዲሁም በእቅዱ እና በተወዳጅ ልጁ ላይ ያላችሁን እምነት ለመገንባት በነዚህ ቃላት ውስጥ ለናንተ መንፈሳዊ መልእክት አዘጋጅቶ ይሆናል። ምናልባት አንድ የምታውቁትን ሰው ወደሚባርክ ወደ አንድ ምንባብ ወይም ማስተዋል ይመራችኋል—ለጓደኛችሁ፣ ለቤተሰባችሁ አባል ወይም ከቅዱሳን ለአንዱ ልታጋሩት ወደምትችሉት አንድ መልዕክት። ብዙ አማራጮች አሉ። ስለዚያ ማሰብ አያስደስትም?

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ መጻህፍት

በብዙዎቹ የብሉይ ኪዳን የክርስቲያን እትሞች ውስጥ መጽሃፎቹ የተደራጁት መጀመሪያ ወደ አንድ ስብስብ ሲቀናበሩ ከተስተካከሉበት በተለየ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ የዕብራይስጡ መጽሃፍ ቅዱስ መጽሃፎቹን በሶስት ምድቦች ሲመድብ—ህግ፣ነቢያት፣እና ጽሁፎች—አብዛኛዎቹ የክርስቲያን መጽሃፍ ቅዱሶች መጽሃፎቹን በአራት ምድቦች ይመድባሉ: ህግ(ኦሪት ዘፍጥረት እና ኦሪት ዘዳግም)፣ታሪክ(መጽሃፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ–መጽሃፈ አስቴር)፣የግጥም መጻህፍት(መጽሃፈ ኢዮብ–መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን) እና ነቢያት(ትንቢተ ኢሳይያስ–ትንቢተ ሚልክያስ)።

እነዚህ ምድቦች አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? ምክንያቱም የምታጠኑትን የመጽሃፍ አይነት ማወቃቹሁ እንዴት እንደምታጠኑት እንድታውቁ ሊረዳችሁ ስለሚችል ነው፡፡

“ህግን“ ወይም የብሉይ ኪዳንን የመጀመሪያ አምስት መጽሃፎች ስታነቡ ልታስታውሱ የሚገባችሁ ነገር እነሆ። ከሙሴ ጋር የሚያያዙት እነዚህ መጽሃፎች በጊዜ ሂደት ምናልባት በብዙ ጸሃፍት እና አጠናቃሪዎች እጆች ተላልፈዋል። አሁንም የሙሴ መጻህፍት በተነሳሽነት የተጻፉ የእግዚያብሄር ቃላት ናቸው፤ምንም እንኳን—እንደማንኛውም በሟቾች አማካኝነት የተላለፉ ሌሎች የእግዚያብሄር ስራዎች—ለሰብአዊ እንከኖች የተጋለጡ ቢሆኑም።( ሙሴ 1፥41የእምነት አንቀጾች 1፥8ይመልከቱ)። በማዘጋጀት ስለረዳበት ስለተቀደሰው የመጽሃፈ ሞርሞን መዝገብ “ስህተቶቸ ካሉ ስህተቶቹ የሰዎች ስህተቶች ናቸው ፤ስለዚህ የእግዚያብሄር የሆኑትን አትኮንኑ“ ሲል የተናገራቸው የሞሮኒ ቃላት እዚህ ይረዳሉ። (የመጽሃፈ ሞርሞን የርዕስ ገጽ)። በሌላ አነጋገር አንድ የቅዱስ ጽሁፍ መድብል የእግዚያብሄር ቃል ለመሆን ከሰብአዊ ስህተት ነጻ መሆን አይጠበቅበትም።

ማስታወሻ

  1. ፕሬዚዳንት ኤም.ረስል ባላርድ፦“ዛሬ መጽሃፍ ቅዱስ ያለን በእድል ወይም በአጋጣሚ አይደለም ብለዋል። ጻድቅ ግለሰቦች ያዩዋቸውን ቅዱስ ነገሮች እንዲሁም የሰሟቸውንና የተናገሯቸውን በመንፈስ የተመሩ ቃላት ለመጻፍ በመንፈስ ተነሳስተው ነበር። ሌሎች ታማኝ ሰዎች እነዚህን መዝገቦች ለመጠበቅ እና ለማቆየት በመንፈስ ተመርተው ነበር”።(“The Miracle of the Holy Bible፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2007(እ.አ.አ)፣ 80)