ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ጥር 17–23 (እ.ኤ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6፦ “እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር“


“ጥር 17–23 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6፤‘እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር፣’” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“ጥር 17–23 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 5፤ ሙሴ 6” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
አዳም እና ሄዋን ከኤደን የአትክልት ስፍራ ውጪ

ከገነት የተሻለ፣ በ ኬንዳል ሬይ ጆንሰን

ጥር 17–23 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 5ሙሴ 6

“እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር“

ኦሪት ዘፍጥረት 5ሙሴ 6ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ የምትቀበሉትን መንፈሳዊ ግንዛቤዎች መዝግቡ፡፡ ለእናንተና ለቤተሰባችሁ ጠቃሚ የሆነ ምን መልዕክት አገኘኛችሁ?

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አብዛኛው ኦሪት ዘፍጥረት 5 በአዳም እና ሄዋን እና በኖህ መካከል ያለው የትውልዶች ዝርዝር ነው፡፡ ብዙ ስሞችን እናነባለን ነገር ግን ስለእነርሱ ብዙ አንማርም፡፡ ከዚያም በዚህ አስደሳች ነገር ግን ባልተብራራ መስመር የተገለጸውን ከአዳም ስድስተኛ ትውልድ ስለሆነው ስለሄኖክ እናነባለን “ ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚያብሄር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤እግዚያብሄር ወስዶታልና“(ኦሪት ዘፍጥረት 5፥24)፡፡ በርግጠኝነት ከዚያ ጀርባ አንድ ታሪክ አለ፡፡ ነገር ግን ያለምንም ማብራሪያ የትውልዶች ዝርዝሩ ካቆመበት ይቀጥላል፡፡

በሚያስደስት ሁኔታ፣ ሙሴ 6 የሄኖክን ታሪክ በዝርዝር ይገልጻል—እናም ትልቅ ታሪክ ነው፡፡ ስለሄኖክ ትህትና፣የስጋት ስሜቶች፣ እግዚያብሄር በውስጡ ስላየው አቅም እና እንደ እግዚያብሄር ነብይ ስለሰራው ታላቅ ስራ እንማራለን፡፡ በትውልዶች እያደገ ሲሄድም ስለአዳም እና ሄዋን ቤተሰብ ጠራ ያለ ምስል እናገኛለን፡፡ ስለሰይጣን “ታላቅ ስልጣን” ነገር ግን በተቃራኒው ደግሞ “የእግዚያብሄርን መንገዶች“ ስላስተማሩ ወላጆች እና “ስለሚናገሩ እና ስለሚተነብዩ“ “ስለጽድቅ ሰባኪያን“ እናነባለን(ሙሴ 6፥15፣ 21፣ 23)፡፡ በተለይ እነዚህ ወላጆች እና ሰባኪያን ስላስተማሩት ትምህርት የምንማረው ትምህርት ድንቅ ነው: እምነት፣ንስሃ፣ጥምቀት እና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ( ሙሴ 6፥50–52ን ይመልከቱ)፡፡ ያ ትምህርት አብሮት እንደሚሄደው ክህነት “በመጀመሪያ ነበረ [እናም] እስከ አለም መጨረሻም ይኖራል“ (ሙሴ 6:7)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ሙሴ 6፥26–36

ነቢይ ገላጭ ነው።

ሙሴ 6፥26–36ን ስታጠኑ፣ ስለአይኖች፣ስለጨለማ እና እይታ ምን ትማራላችሁ? በሄኖክ ዘመን “አይኖቻቸው አርቀው መመልከት“ ያልቻሉት እነማን ናቸው? እነዚህ ሰዎች እውነትን ማየት ያልቻሉት ለምን ነበር? ሄኖክ ምን ለማየት ችሎ ነበር? የዘመናችን ነቢያት ገላጮች እንደሆኑ እምነታችሁን የገነባው ምንድን ነው? ( ቁጥር 36፤ የቅዱሳን ጽሁፎች መምሪያ፣“ገላጭ፣” scriptures.ChurchofJesusChrist.orgን ይመልከቱ)።

ሙሴ 8፥26–47

ጉድለቶች ቢኖሩብንም እግዚያብሄር ስራውን እንድንሰራ ይጠራናል።

እግዚያብሄር እንድንሰራው በጠራን ስራ የመጨነቅ ስሜት መሰማት ያልተለመደ ነገር አይደለም። ጌታ ነቢይ እንዲሆን በጠራው ጊዜ ሄኖክም እንደዛ ተሰምቶት ነበር። ሙሴ 6፥26–36፣ ን ስታነቡ ኢዮብ ለምን የመጨነቅ ስሜት እንደተሰማው እና ጉብዝና እንዲሰማው ጌታ ምን እንዳለው ፈልጉ። በ ቁጥር 37–47፣ ውስጥ ጌታ ሄኖክን የረዳበትን እና ስራውን እንዲሰራ ሃይል የሰጠበትን መንገዶች ፈልጉ (በተጨማሪም ሙሴ 7፥13ን ይመልከቱ)። የሄኖክን ተሞክሮዎች እንደሙሴ ( ዘጸአት 4፥10–16ን ይመልከቱ)፣ ኤርሚያስ ( ትንቢተ ኤርሚያስ 1፥4–10ን ይመልከቱ)፣ ኔፊ ( 2 ኔፊ 33፥1–4ን ይመልከቱ)፣ እና ሞሮኒ ( ኤተር 12፥23–29ን ይመልከቱ)ካሉ ብቃት እንደሌላቸው ከተሰማቸው ከሌሎች ነቢያት ጋር ልታነጻጽሩ ትችላላችሁ። ከነዚህ ቅዱሳን ጽሁፎች እግዚያብሄር እንድትሰሩት ስለሰጣችሁ ስራ ምን እንድትማሩ የሚፈልግ ሆኖ ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ያዕቆብ 4፥6–8ን ይመልከቱ፡፡

ሙሴ 6፥48–68

የክርስቶስ ትምህርት የእግዚአብሔር የደህንነት እቅድ ዋና ክፍል ነው።

የሙሴ መጽሃፍ ስላለን እግዚያብሄር ልጆቹን ከመጀመሪያው ጀምሮ ይቅርታን እና ቤዛን እንዴት እንደሚያገኙ ሲያስተምር እንደነበረ እናውቃለን። በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ እነዚህ አስተምህሮዎች አንዳንድ ጊዜ የክርስቶስ ትምህርት ተብለው ይጠራሉ( 2 ኔፊ 31፥13–21ን ይመልከቱ)። ሙሴ 6፥48–68ን ስታጠኑ፣ ለመቤዠት ምን ማወቅ እና ማድረግ እንዳለብን ፈልጉ? ሄኖክ ያስተማረውን የራሳችሁን ማጠቃለያ መጻፍ ጠቃሚ ሆኖ ልታገኙት ትችላላችሁ። እነዚህ እውነቶች ከአዳም እና ሄዋን ጊዜ ጀምሮ ሲሰጡ እንደነበር ማወቁ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህን ትምህርቶች በማጥናታችሁ ሳቢያ ምን ለማድረግ የተነሳሽነት ስሜት ይሰማችኋል ?

ሙሴ 6፥51–62

“እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር።“

አዳም እና ሄዋን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ውድ እውነቶች ተምረዋል። ነገር ግን በ ሙሴ 6፥27–28 ውስጥ ያሉት የጌታ ቃላት ከሄኖክ ትውልድ በፊት የነበሩ ብዙ ሰዎች እነዚያን እውነቶች እየኖሯቸው እንዳልነበር ግልጽ ያደርጋሉ። ጌታ ጠፍተው የነበሩትን እውነቶች —በመጀመሪያ ለአዳም ከተሰጠው ፦“እነዚህን ነገሮች በነጻ ለልጆችህ አስተምር“ ከሚለው ትዕዛዝ ጋር ሄኖክ ዳግም እንዲመልስ ፈለገ(ሙሴ 6:58)። ሙሴ 6፥51-62ን ስታነቡ፣ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ትማራላችሁ? በተለይ ለመጪው ትውልድ ጠቃሚ የሚሆን ምን ታገኛላችሁ? እነዚህን እውነቶች ለወደፊቱ ትውልዶች ለማስተላለፍ ለመርዳት ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ምስል
ቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍትን ሲያነብ

ወላጆች ወንጌልን ለልጆቻቸው ማስተማር አለባቸው።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 5ሙሴ 6፥5–25፣ 46የአዳም እና ሄዋን ቤተሰብ ያዘጋጀውን “የመታሰቢያ መጽሃፍ“ ማንበብ የራሳችሁን የመታሰቢያ መጽሃፍ እንድታዘጋጁ ቤተሰባችሁን ሊያነሳሳ ይችላል። ምን ልታካትቱ እንደምትችሉ እንደ ቤተሰብ ተወያዩ። ምናልባት በቤተሰብ ታሪካችሁ ፎቶዎች ፣ታሪኮች ወይም ሰነዶች አሏችሁ። አሁን በቤተሰባችሁ እየሆኑ ካሉ ነገሮች ለማካተት ልትመርጡም ትችላላችሁ። የወደፊቱ ትውልዶች ምን ጠቃሚ ነገር ያገኛሉ? በተጨማሪም “በመነሳሳት መንፈስ“ሙሴ 6፥5እና “በእግዚያብሄር ጣት በተሰጠን ምሳሌ መሰረት“ሙሴ 6፥46የሚሉት ሃረጎች ጥረታችሁን እንዴት ሊመሩ እንደሚችሉ ልትወያዩ ትችላላችሁ። ከመታሰቢያ መጽሃፋችሁ መረጃዎችን ወደ FamilySearch.orgማከልን አስቡ።

ሙሴ 6፥53–62ሙሴ 6፥53ውስጥ ያለውን የአዳም ጥያቄ እንዴት እንመልሳለን? በ ቁጥሮች 57–62ውስጥ ምን ምላሾችን እናገኛለን?

ሙሴ 6፥59“ወደ መንግስተ ሰማያት በድጋሚ መወለድ” ማለት ምን ማለት ነው? በህይወታችን ሙሉ በድጋሚ መወለዳችንን እንድንቀጥል ምን ማድረግ እንችላለን? እርዳታ ለማግኘት፣ አልማ 5፥7–14፣ 26፤ የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያ “ዳግመኛ መወለድ፣ከእግዚያብሄር መወለድscriptures.ChurchofJesusChrist.org፤ ዴቪድ ኤ.ቤድናር፣ “Always Retain a Remission of Your Sins” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2016(እ.አ.አ)፣ 59–62) ይመልከቱ።

ሙሴ 6፥61ከዚህ ጥቅስ ስለመንፈስ ቅዱስ ምን እንማራለን?

ሙሴ 6፥63“ ስለ[ክርስቶስ] የሚመሰክሩ“ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው?(በተጨማሪም 2 ኔፊ 11፥4ን ይመልከቱ)። የቤተሰብ አባላት ”ከላይ በሰማይ” እና ”በምድር ላይ” ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለመማር የሚረዳቸውን ያዩትን ነገር እንዲያጋሩ መጋበዝን አስቡ። ለምሳሌ ዛፎች፣ድንጋዮች ወይም ጸሃይ አዳኙን እንዴት ያስታውሱናል? “የህይወት ውሃ“ እና “የህይወት እንጀራ“ የሚሉት መጠሪያዎች ስለእርሱ ምን ያስተምሩናል?? (ዮሃንስ 4፥10–146፥35)።

ልጆችን ለማስተማር ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናት ይመልከቱ፡፡

የሚመከር መዝሙር፦ “አንተ ወደ ፈለግከው ቦታ እሄዳለሁ፣” መዝሙር፣ ቁጥር 270፡፡

የግል ጥናትን ማሻሻል

ምልክቶችን ፈልጉ። በቅዱሳን መጻህፍት ውስጥ ነገሮች ወይም ኩነቶች አብዛኛውን ጊዜ መንፈሳዊ እውነታን የሚወክሉ ወይም እነሱን የሚያመላክቱ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ምልክቶች የትምህርትን ግንዛቤያችሁን ሊያሳድጉ ይችላሉ። ለምሳሌ በ ሙሴ 6፥35ውስጥ ካሉት የአይኖች እና የሸክላ ምልክቶች ምን ትማራላችሁ?

ምስል
አዳም እና ሔዋን ከልጆች ጋር

አዳም እና ሔዋን ልጆቻቸውን ሲያስተምሩ፣ በዴል ፓርሰን

አትም