ታህሳስ 27፟–ጥር 2 (እ.ኤ.አ)፡፡ ሙሴ 1፤ አብርሃም 3፦ ”ይህ ስራዬ እና ክብሬ ነው”፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) [2021 (እ.አ.አ)]
ታህሳስ 27፟–ጥር 2 (እ.ኤ.አ)፡፡ ሙሴ 1፤ አብርሃም 3፣” ኑ፣ ተከተሉኝ—ለግለሰቦቸ እና ለቤተሰቦቸ፦ 2022 (እ.አ.አ)
ታህሳስ 27፟–ጥር 2 (እ.አ.አ)
ሙሴ 1፤ አብርሃም 3
”ይህ ስራዬ እና ክብሬ ነው”
እግዚያብሄር ለሙሴ እና ለአብርሃም የተናገረውን ስታነቡ እናንተንም ምን እያላችሁ እንደሆነ አሰላስሉ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
መጽሃፍ ቅዱስ “በመጀመሪያ እግዚያብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ“ በሚሉት ቃላት ይጀምራል።(ኦሪት ዘፍጥረት 1፥ 1) ነገር ግን ከዚህ “መጀመሪያ“ በፊት እዚያ ምን ነበር? እናም እግዚያብሄር ይህን ሁሉ ለምን ፈጠረ? በነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ጌታ ለእነዚህ ጥያቄዎች ብርሃን ፈንጥቋል።
ለምሳሌ፦ አብርሃም ያየውን “አለም ከመፈጠሩ በፊት“ በመንፈስ ህልውና እንደነበረን የሚያሳይ ራዕይን መዝገብ ሰጥቶናል ( አብርሃም 3፥22–28ይመልከቱ።) በተጨማሪም ጌታ በመንፈስ ተነሳሽነት የተተረጎሙትን ወይም የተከለሱትን የሙሴ መጽሃፎች የሚባሉትን የዘፍጥረት የመጀመሪያ ስድስት ምዕራፎች ሰጥቶናል—ያ “በመጀመሪያ “ ብሎ አይጀምርም። ከዚያ ይልቅ ታዋቂ ለሆነው የዘፍጥረት ታሪክ የተወሰነ ትርጉም ከሚሰጥ ሙሴ ከነበረው ተሞክሮ ይጀምራል። በአንድ ላይ፣ እነዚህ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጽሁፎች የብሉይ ኪዳን ጥናታችንን ለመጀመር ጥሩ ቦታዎች ናቸው፤ ምክንያቱም ንባባችንን መስመር ሊያሲዙ የሚችሉ አንዳንድ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ይመልሳሉ፦ እግዚያብሄር ማን ነው? እኛ ማን ነን? የእግዚያብሄር ስራ ምንድን ነው፣በዚያ ውስጥ የእኛ ቦታ ምንድን ነው? የኦሪት ዘፍጥረት የመክፈቻ ምእራፎች ለሙሴ ጥያቄ የጌታ መልሶች ሆነው ሊታዩ ይችላሉ ፦ ”እግዚአብሔር ሆይ፣ ለአገልጋይህ ርህራሄ ይሰማህ፣ እና ስለዚህ ምድርና ኗሪዎቿ እናም ስለሰማያት ንገረኝ፣ ከዚያም አገልጋይህ ይረካል”(ሙሴ 1፥36)።
ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
እንደ እግዚያብሄር ልጅነቴ መለኮታዊ ፍጻሜ አለኝ።
ፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ.ኡክዶርፍ “በዚህ ህይወት የሚያጋጥመን አብዛኛው ግራ መጋባት የሚመጣው በቀላሉ ማን እንደሆንን ካለማወቅ ነው “ ብሎ አስተምሯል። (“The Reflection in the Water” [Church Educational System fireside for young adults፣ ህዳር 1፣ 2009(እ.አ.አ)]፣ ChurchofJesusChrist.org ሰማያዊ አባት ይህንን ያውቃል፣ሰይጣንም እንደዚሁ። እግዚያብሄር ለሙሴ የሰጠው የመጀመሪያ መልእክት“አንተ ልጄ ነህ“ እና “በአንድያ ልጄ አምሳል ነህ“ (ሙሴ 1፥4፣6).የሚሉትን እውነቶች ያካትታል። በተቃራኒው ፣ሰይጣን ሙሴን “የሰው ልጅ“ ብቻ ሲል ጠርቶታል(ሙሴ 1፥12)። ሰይጣን እንድታደርጉ እንደሚፈልገው ራሳችሁን እንደ “ የሰው ወንድ[ወይም ሴት]ልጅ“ ብቻ አድርጋችሁ ብታስቡት ህይወታችሁ እና ውሳኔያችሁ እንዴት የተለየ ይሆን ነበር? የእግዚያብሄር ልጅ መሆናችሁን ማወቃችሁ እና ያንን ማስታወሳችሁ ህይወታችሁን የሚባርከው እንዴት ነው?
በ ሙሴ 1 ውስጥ የትኞቹ ጥቅሶች ወይም ሃረጎች ናቸው ያሏችሁን መለኮታዊ ዋጋ ስሜት የሚሰጧችሁ?
የሰይጣንን ተጽዕኖዎች መቋቋም እችላለሁ።
ሙሴ 1 በግልጽ እንደሚያሳየው ጠንካራ መንፈሳዊ ተሞክሮዎች ከፈተና ውጪ አያደርጉንም። በርግጥ ከሰይጣን ዘዴዎች አንዱ እነዚያን ተሞክሮዎች ወይም ከእነርሱ የተማርነውን ነገር እንድንጠራጠር መፈተን ነው። በ ቁጥሮች 12–26ውሰጥ ሙሴ ለሰይጣን የሰጠውን መልስ ስታነቡ ለተቀበላችሁት ምስክርነት ታማኝ ሆናችሁ እንድትቆዩ እንዲረዳችሁ ምን ትማራላችሁ? የሰይጣንን ሌሎች ፈተናዎች ለመቋቋም ምን ይረዳችኋል? (ለምሳሌ ቁጥር 15 እና18)ን ይመልከቱ)፡፡
በተማራችሁት መሰረት ፈተናን ለመቋቋም እቅድ ማውጣት ትችላላችሁ፡፡ ለምሳሌ ፦“ እንዳደርግ በምፈተንበት ጊዜ አደርጋለሁ “ የሚለውን አረፍተ-ነገር ልታሟሉ ትችላላችሁ፡፡
በተጨማሪም ማቴዎስ 4፥1–11፣ ሄለማን 5፥12፤ ጋሪ ኢ.ስቲቨንሰን፣“Deceive Me Not፣“ ሊያሆና ህዳር 2019 (እ.አ.አ)93–96፤“የእግዚያብሄር ልጅ ነኝ (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ፡፡
የእግዚያብሄር ስራ እና ክብር ዘላማዊ ህይወት እንዳገኝ መርዳት ነው፡፡
የእግዚያብሄርን ፍጥረቶች በራእይ ከተመለከተ በኋላ ሙሴ “እባክህ ንገረኝ እንዴት እነዚህ ነገሮች እንዲህ ሆኑ“ ሲል ለጌታ ጥያቄ አቀረበ (ሙሴ 1፥30) በ ሙሴ 1፥31–39ውስጥ ስላለው የጌታ ምላሽ ያስገረማችሁ ምንድነው?
አብርሃምም በ አብርሃም 3ውስጥ የተመዘገበ የራእይ ተሞክሮ ነበረው፡፡ ከ ቁጥሮች 22-26 ውስጥ የሙሴን ጥያቄ ለመመለስ መርዳት የሚችል ምን ታገኛላችሁ?
ሙሴ እና አብርሃም ከራዕዮቻቸው የተማሩትን ሌሎች እውነቶች ለመዘርዘር አስቡ:ስለእግዚያብሄር፣ስለራሳቸው እና ስለእግዚያብሄር ፍጥረት አላማ የተማሩትን እውነቶች፡፡ እነዚህ እውነቶች ራሳችሁን እና በዙሪያችሁ ያለውን አለም በምትመለከቱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩት እንዴት ነው?
በተጨማሪም ዲየተር ኤፍ. ኡክዶርፍ፣ “You Matter to Him፣” ሊያሆና ህዳር 2011(እ.አ.አ)፣ 19-22 ፣ የወንጌል አርዕስቶች፣“ቅድመ ምለድራዊ ህይወት፣” topics.ChurchofJesusChrist.org.ይመልከቱ፡፡
ከአብርሃም በተጨማሪ ሌሎች “ከመወለዳቸው በፊት የተመረጡ“ ነበሩ?
“በቅድመ ህይወት የመንፈስ አለም የተወሰኑ መንፈሶች በምድራዊ ኑሯቸው ወቅት የተለዩ ተልዕኮዎችን እንዲፈጽሙ እግዚያብሄር ሹሟል፡፡ ይህ ቀድሞ መመረጥ ይባላል፡፡ … የአስቀድሞ መሾም ትምህርት ለአዳኙ እና ለነቢያት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም የቤተክርስቲያኗ አባላት ይሰራል” (የወንጌል አርዕስቶች ”ቀድሞ መመረጥ፣” topics.ChurchofJesusChrist.org)፡፡
የአብርሃምን እና የሙሴን መጻህፍት ያገኘናቸው እንዴት ነው?
የሙሴ መጽሃፍ የጆሴፍ ስሚዝ በመንፈስ የተነሳሳ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም የመጀመሪያው ክፍል ነው፡፡ የአብርሃም መጽሃፍ ለጆሴፍ ስሚዝ የተገለጸው በግብጽ ፓፒረስ ላይ በሚሰራበት ወቅት ነበር፡፡ ዛሬ በታላቅ ዋጋ እንቁ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ መጻህፍት ስለሙሴ፣ስለአብርሃም እና ስለሌሎች ነቢያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ የማይገኙ ብዙ መረጃዎችን ይሰጣሉ፡፡ እነዚህን መጻህፍት እንዴት እንዳገኘናቸው ይበልጥ ለመማር “የጆሴፍ ስሚዝ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም“ (የቤተክርስቲያን ታሪክ ርዕሶች ፣ ChurchofJesusChrist.org/study/history/topics) እና ”Translation and Historicity of the Book of Abraham” (የወንጌል አርእስቶች፣ topics.ChurchofJesusChrist.org) ይመልከቱ፡፡
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ሙሴ 1፥2–6፤ አብርሃም3፥11–12፡፡የቤተሰብ አባላት “የእግዚያብሄር ልጅ ነኝ“ (የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ 2–3) በሚለው መዝሙር ውስጥ እነዚህ ቅዱሳን መጻህፍት ከሚያስተምሯቸው እውነቶች ጋር የሚዛመዱ ሀረጎችን እንዲፈልጉ ልትጋብዟቸው ትችላላችሁ፡፡
-
ሙሴ 1፥4፣ 30–39ቤተሰባችሁ አንዳንድ “የ[እግዚያብሄርን] የእጅ ስራ“ በመመልከት ይደሰታል?(ቁጥር 4) ምናልባት እነዚህን ጥቅሶች በመናፈሻ ውስጥ ወይም ኮከቦች ባሉበት ምሽት ልታነቡ ትችላላችሁ፡፡ ከዚያም እግዚያብሄር ለምን አለምን እንደፈጠረ እና ሰለ“ስራው እና ክብሩ“ መነጋገር ትችላላችሁ(ቁጥር 39)።
-
ሙሴ 1፥18።በእግዚያብሄር እና በሰይጣን “መካከል ፍርድ ለመስጠት“ እርስ በርሳችን እንድንረዳዳ ምን ምክር ማጋራት እንችላለን? (ደግሞም ሞሮኒ 7፥12–18፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥23–24ይመልከቱ።)
-
አብርሃም 3፥24–26መመሪያዎችን መከተል እንደሚችሉ ለማሳየት የሚያስችላቸውን እንደ የወረቀት አውሮፕላን ማጣጠፍ ወይም የምግብ አሰራር አይነት መከተልን የመሰለ የሚያዝናና ነገር ግን ፈታኝ ስራ ለቤተሰባችሁ ልትሰጡ ትችላላችሁ። ይህ ተግባር በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ከተገለጸው የምድራዊ ህይወታችን አላማ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝር ከ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፦ “እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፣” የልጆች መዝሙር መፅሐፍ፣ 2–3።