ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፦ የእስራኤል ቤት


”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች፦ የእስራኤል ቤት፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) 2021 (እ.አ.አ)

”ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች ፦ የእስራኤል ቤት፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የሃሳቦች ምልክት

ልናስታውሳቸው የሚገቡን ሃሳቦች

የእስራኤል ቤት

በምስራቃዊ ከነዓን ምድረ በዳ አንድ ቦታ ያዕቆብ ከመንታ ወንድሙ ከኤሳው ጋር ለመገናኘት በጭንቀት ጠበቀው፡፡ ከሃያ አመታት ቀደም ብሎ ያዕቆብ ለመጨረሻ ጊዜ ኤሳውን ባየው ጊዜ ኤሳው ሊገድለው እያስፈራራው ነበር፡፡ የእግዚያበብሄርን በረከት እየጠየቀ ያዕቆብ ለሊቱን ሙሉ በምድረ በዳ ሲታገል አደረ፡፡ በያዕቆብ እምነት፣ጽናት እና ቁርጠኝነት ምክንያት እግዚያብሄር ጸሎቱን መልሶለት ነበር፡፡ በዚያ ምሽት የያዕቆብ ስም “ከእግዚያብሄር ጋር የሚታገል “ የሚል ትርጉም ወዳለው ወደ እስራኤል ተቀየረ፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 32፥28፣የግርጌ ማስታወሻ b፣ በተጨማሪም ኦሪት ዘፍጥረት 32፥24–32ይመልከቱ).1፡፡

ምስል
የያቦቅ ወንዝ

ያዕቆብ በያቦቅ ወንዝ አጠገብ እስራኤል የሚለውን ስም ተቀበለ፡፡

እስራኤል የሚለው ስም በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው፤እናም በመላው መጽሃፉ እና በመላው ታሪክ ጸንቶ የኖረ ስም ነው፡፡ ስሙ ብዙም ሳይቆይ ከአንድ በላይ ሰዎችን ማመልከት ጀመረ፡፡ እስራኤል 12 ወንዶች ልጆች ነበሩት፣እናም በጥቅሉ “የእስራኤል ቤት“፣“የእስራኤል ነገዶች“፣ “የእስራኤል ልጆች“ ወይም “እስራኤላውያን“ በመባል ይጠራሉ፡፡

በመላው ታሪክ ውስጥ የእስራኤል ልጆች ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ውስጥ ለመጡበት ለአንዱ የዘር ሃረጋቸው ትልቅ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ትውልዳቸው የቃልኪዳን ማንነታቸው አስፈላጊ ክፍል ነበር፡፡ ሃዋርያው ጳውሎስ “የቢንያም ወገን“ እንደነበረ ተናግሯል፡፡(ሮሜ 11፥1)፡፡ ሌሂ የነሃስ ሰሌዳዎቹን እንዲያመጡ ልጆቹን ወደ ኢየሩሳሌም በላከ ጊዜ አንደኛው ምክንያቱ ሰሌዳዎቹ “ የአባቶቹን የትውልድ ሃረግ“ ስለያዙ ነበር(1 ኔፊ 5፥14በተጨማሪም 1 ኔፊ 3፥3ይመልከቱ)፡፡ ሌሂ የዮሴፍ ዝርያ መሆኑን አወቀ እናም የእርሱ ትውልድ ከእስራኤል ቤት ጋር ስላላቸው ዝምድና ግንዛቤ በመጪዎቹ አመታት ለእነርሱ አስፈላጊ መሆኑ ተረጋገጠ( አልማ 26፥363ኔፊ 20፥25ይመልከቱ)፡፡

ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ “ የእስራኤል መሰባሰብ“ በመሳሰሉትን አገላለጾች ስለ እስራኤል ልትሰሙ ትችላላችሁ፡፡ ስለ“እስራኤል አዳኝ“ “የእስራኤል ተስፋ“ እና “እናንተ የእስራኤል ሽማግሌዎች“ እንዘምራለን፡፡2 በእነዚህ ጉዳዮች ረገድ ስለጥንቷ እስራኤል መንግስት ወይንም እስራኤል ስለምትባለው ስለዘመናዊቷ አገር እስራኤል ብቻ እያወራን እና እየዘመርን አይደለም፡፡ ይልቁን ከአለም ሃገራት ወደ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እየተሰበሰቡ ስለሉት ነው የምንናገረው። በእግዚያብሄር ጽኑ ስለሆኑት፣በረከቶቹን በትጋት ስለሚፈልጉት እናም በጥምቀት አማካኝነት የእርሱ የቃል ኪዳን ህዝቦች ስለሆኑት ነው እያወራን ያለነው።

የፓትርያርክ በረከታችሁ ከአንዱ የእስራኤል ቤት ነገድ ጋር ግንኙነት እንዳላችሁ ይናገራል። ያ ከአንድ አስደሳች የቤተሰብ ታሪክ መረጃ የበለጠ ነው። የእስራኤል ቤት አካል መሆን ማለት ከሰማያዊ አባት እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የቃልኪዳን ግንኙነት አላችሁ ማለት ነው። እንደ አብርሃም ለእግዚያብሄር ልጆች ”በረከቶች” መሆን አለባችሁ ማለት ነው(ኦሪት ዘፍጥረት 12፥ 2አብርሃም 2፥ 9–11)። በጴጥሮስ አንደበት “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፣የንጉስ ካህናት ቅዱስ ህዝብ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ“ ማለት ነው(1 ጴጥሮስ 2፥9)። እናንተ ከእርሱ ጋር የገባችሁትን ቃል ኪዳን በማክበር “በእግዚያብሄር የምትጸኑ“ ናችሁ ማለት ነው።

ማስታወሻዎች

  1. “እግዚያብሄር ይገዛል” ወይም “እግዚያብሄር ይዋጋል ወይም ይታገላል” የሚሉትን ጨምሮ እስራኤል ለሚለው ስም ሌሎች ተስማሚ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች አሉ።

  2. መዝሙሮች ቁጥሮች. 6259፣እና 319

ምስል
የያዕቆብ የቤተሰብ ሐረግ

የያዕቆብ የቤተሰብ ሐረግ ምስል በኬት ኤል.ቢቨርስ

አትም