ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መጋቢት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 42–50 ፦“እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”


መጋቢት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 42-50፤ ’”እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው፣’“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“መጋቢት 14–20 (እ.አ.አ)፡፡ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 42–50፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የግብጹ ዮሴፍ

የግብጹ ዮሴፍ ምስል በሮበርት ቲ. ባሬት

መጋቢት 14–20 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 42-50

“እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”

ቅዱሳን መጻህፍትን ማንበብ መንፈስን ይጋብዛል። በምታነቡበት ጊዜ ከምታነቡት ጋር በቀጥታ የማይዛመዱ ቢሆኑም የእርሱን ማነሳሳት አዳምጡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ዮሴፍ በወንድሞቹ ወደ ግብጽ ከተሸጠ 22 አመት ገደማ ሆኖት ነበር። በሃሰት መከሰስን እና መታሰርን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፏል። በመጨረሻም ወንድሞቹን እንደገና ባያቸው ጊዜ ዮሴፍ ከፈርዖን ቀጥሎ በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ነበረ። በቀላሉ ሊበቀላቸው ይችል ነበር፤ እናም በዮሴፍ ላይ አድርገውት የነበረው ግምት ውስጥ ሲገባ በቂ ምክንያት ያለው ሊመስል ይችላል። ሆኖም ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር አላቸው። ያ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን በስቃዩ መለኮታዊ አላማን እንዲያዩ ረዳቸው። “እግዚያብሄር ለመልካም አሰበው”(ኦሪት ዘፍጥረት 50፥20)ሲል ነገራቸው ምክንያቱም “የአባቱን ቤተሰዎች ሁሉ“(ኦሪት ዘፍጥረት 47፥12)ከርሃብ ለማዳን የሚያስችል ቦታ ላይ አስቀምጦታልና።

በብዙ መንገዶች የዮሴፍ ህይወት የኢየሱስ ክርስቶስን ይመስላል። ምንም እንኳን ሃጢያታችን ታላቅ ስቃይ አስከትሎበት የነበረ ቢሆንም ከርሃብ ከከፋ እጣ ፈንታ ሁላችንንም በማውጣት አዳኙ ይቅር ይላል። ይቅርታ መቀበልም ሆነ መስጠት ቢያስፈልገን—የሆነ ጊዜ ሁላችንም ሁለቱንም ማድረግ ያስፈልገናል—የዮሴፍ ምሳሌ እውነተኛ የፈውስ እና የእርቅ ምንጭ ወደሆነው ወደአዳኙ ይጠቁመናል።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 45፥1–850፥20

“እግዚያብሄርም አድናችሁ ዘንድ ከናንተ በፊት ላከኝ።“

ስለዮሴፍ እንደማንበባችሁ፣​ በእሱ ታሪክ እና በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ተልዕኮ መካከል አንዳች ተመሳሳይነትን አይታችኋል? ዮሴፍ በቤተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና አዳኙ በእግዚያብሄር ቤተሰብ ውስጥ ካለው ሚና ጋር እንዴት እንደሚመሳሰል ልታስቡ ትችላላችሁ። በዮሴፍ ተሞክሮዎች እና “በታላቅ መድሃኒትም ያድነን ዘንድ” በተላከው በአዳኙ ተልዕኮ መካከል ምን ተመሳሳይነትን ታያላችሁ ? (ኦሪት ዘፍጥረት 45፥7)።

ኦሪት ዘፍጥረት 4550፥15-21

ይቅርታ ፈውስን ያመጣል።

ዮሴፍ ወንድሞቹ ያደረጉበትን አስከፊ ነገሮች ይቅር ስለማለቱ ማንበባችሁ በአሁኑ ወቅት ይቅር ለማለት ስለተቸገራችሁበት ስለአንድ ሰው እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል። ወይንም ምናልባት አንድ ከባድ ይቅር የማለት ፈተና ከፊታችሁ አለ። በሁለቱም መንገድ ዮሴፍ ለምን ይቅር ማለት ቻለ ብሎ ማሰላሰል ሊረዳ ይችላል። በ ኦሪት ዘፍጥረት 4550፥15–21ውስጥ ስለዮሴፍ ባህርይ እና ዝንባሌ ምን ፍንጭ ታገኛላችሁ? ተሞክሮዎቹ ይበልጥ ይቅር ባይ እንዲሆን ተጽዕኖ አድርገውበት ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? የዮሴፍ ምሳሌ በአዳኙ እርዳታ ይበልጥ ይቅር ባይ ለመሆን እንዴት እንደምትችሉ ምን ይጠቁማል?

በተጨማሪም በእርሱ ይቅር ባይነት የተነሳ የዮሴፍ ቤተሰብ ያገኛቸውን በረከቶች አስተውሉ። ይቅር በማለት ምን በረከቶችን አይታችኋል? ያስቀየማችሁን ሰው ለመርዳት ተነሳሽነት ይሰማችኋል?

በተጨማሪም ኦሪት ዘፍጥረት 33፥1–4ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 64፥9–11፤ ላሪ ጄ. ኤኮ ሆክ፣ “Even as Christ Forgives You, So Also Do Ye፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018(እ.አ.አ)፣ 15–16 ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፍጥረት 49

በያዕቆብ በረከቶች ውስጥ ያለው ወካይ ምልክት ትርጉም ምንድን ነው?

ያዕቆብ ለትውልዱ የሚያስተላልፋቸው በረከቶች ግልጽ ምስሎችን ያካትታሉ ፤ነገር ግን አንዳንድ አንባቢያን ለመረዳት አስቸጋሪ ሆነውም ሊያገኟቸው ይችላሉ። ዳግም የተመለሰው ወንጌል ምስጋና ይግባውና ተጨማሪ ግንዛቤን ይሰጠናል። በ ኦሪት ዘፍጥረት 49፥22–26ለዮሴፍ ስለተሰጠው በረከት ስታነቡ፣የሚከተሉትን ጥቅሶችም አንብቡ፣ እናም ምን ግንዘዛቤ እንደሚሰጡ ተመልከቱ፦ 1 ኔፊ 15፥122 ኔፊ 3፥4–5ያዕቆብ 2፥25ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 50፥44

ኦሪት ዘፍጥረት 49፥8–12ውሰጥ ያለውን የይሁዳን በረከት ስታነቡ ንጉስ ዳዊት እና ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለቱም የይሁዳ ትውልዶች እንደሆኑ አስታውሱ። በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ የትኞቹ ቃላት እና ሃረጎች አዳኙን ያስታውሷችኋል? የዮሃንስ ራዕይ 5፥5–6፣9‑1 ኔፊ 15፥14-15ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 45፥59133፥46–50ይመልከቱ።

ስለያዕቆብ ልጆች እና ከእነሱ ስለተወለዱት የእስራኤል ነገዶች ይበልጥ ለመማር የምትወዱ ከሆነ ለያንዳንዱ በ የቅዱሳን መጻህፍት መምሪያ (scriptures.ChurchofJesusChrist.org)ውስጥ የሚገኝ መረጃ አለ።

ኦሪት ዘፍጥረት 50፥24-25ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ኦሪት ዘፍጥረት 50፥24–38 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ።

“ባለራዕይን ጌታ አምላኬ ያስነሳል።“

በዮሴፍ ህልሞች ( ኦሪት ዘፍጥረት 37፥5–11ይመልከቱ) አማካኝነት እና በፍቺዎቹ( ኦሪት ዘፍጥረት 40–41ይመልከቱ) ጌታ ከቀናት ወይም ከአመታት በኋላ ስለሚሆኑት ነገሮች ገልጿል። ነገር ግን በተጨማሪ ጌታ ከክፍለ ዘመናት በኋላ ምን እንደሚሆን ለዮሴፍ ገልጿል። በተለይ ስለሙሴ እና ስለጆሴፍ ስሚዝ ነቢያዊ ተልዕኮዎች አውቋል። በ ኦሪት ዘፍጥረት 50፥24–25 እና በ ጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም፣ ኦሪት ዘፍጥረት 50፥24–38 (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጽ) ውስጥ የዮሴፍን ቃላት ስታነቡ አነዚህን ነገሮች ማወቁ ዮሴፍን እና የእስራኤልን ልጆች እንዴት ባርኳቸው የነበረ ሊሆን እንደሚችል ራሳችሁን ጠይቁ። ይህ ትንቢት በጆሴፍ ስሚዝ አማካኝነት ዳግም መመለሱ ለጌታ አስፈላጊ የነበረው ለምንድን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?(በተጨማሪም 2ኔፊ 3ን ይመልከቱ።)

ጆሴፍ ስሚዝ በጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ኦሪት ዘፍጥረት 50፥ 27–28፣ 30–33 ውስጥ ያሉትን ትንቢቶች የፈጸመው እንዴት ነበር ?( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 1፥17–2320፥7–1239፥11135፥3ይመልከቱ)።

ምስል
የግብጹ ዮሴፍ ጆሴፍ ስሚዝ የወርቅ ሰሌዳዎችን ሲቀበል በራዕይ ሲያይ

የግብጹ ዮሴፍ ምስል በፖል ማን

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና ለቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 42–46ቤተሰባችሁ ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር ሲገናኝ የሚያሳይን ታሪክ ለመተወን ሊወዱ ይችላሉ። (“ዮሴፍ እና ርሃቡ፣” በ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች ሊረዳ ይችላል።) ተዝናኑበት—ከፈለጋችሁ አልባሳትን እና ዘንጎችን ተጠቀሙ። የቤተሰቡ አባላት የገጸ ባህርያቱን ስሜቶች እና እይታዎች ለመረዳት እንዲሞክሩ አበረታቷቸው፡፡ በተለይ ጆሴፍ ስለወንድሞቹ በተሰማው ስሜት እና ይቅርታ ባደረገላቸው ጊዜ በተሰማቸው ስሜት ላይ ልታተኩሩ ትችላላችሁ። ይህም ይቅር ባይነት ቤተሰባችሁን በምን መንገድ ሊባርክ እንደሚችል ወደሚዳስስ ውይይት ሊያመራ ይችላል።

ዮሴፍ ወንድሞቹን ከብዙ አመታት በኋላ እንደገና ሲያገኛቸው ለመጨረሻ ጊዜ ካያቸው በኋላ ተቀይረው እንደነበር ያሳዩት እንዴት ነው? ከነሱ ተሞክሮዎች ስለንስሃ ምን ልንማር እንችላለን?

ኦሪት ዘፍጥረት 45፧3-1150፧19-21በግብጽ የነበረው ተሞክሮ አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም “ እግዚያብሄር ለመልካም እንዳሰበው“(ኦሪት ዘፍጥረት 50፧20) ዮሴፍ አወቀ። ቤተሰባችሁ እግዚያብሄር ወደ በረከት የቀየራቸው መከራዎች አጋጥሞት ያውቃል?

በመከራ ጊዜ የእግዚያብሄርን ርህራሄ የሚያመለክቱ (እንደ “How Firm a Foundation” [መዝሙር፣ ቁጥር 85]) ያሉ መዝሙሮች ይህንን ውይይት ሊያበለጽጉት ይችላሉ። ከዮሴፍ ተሞክሮዎች የትኞቹ ዝርዝሮች መዝሙሩ የሚያስተምረውን በምሳሌነት ያሳያሉ?

ኦሪት ዘፍጥረት 49፧9-11፣ 24-25፡፡በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ሚናዎች እና ተልዕኮዎች የሚያስተምረን ምን እናገኛለን? (በነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉ ሃረጎችን ለመረዳት እርዳታ ለማግኘት፣ ስለ ኦሪት ዘፍጥረት 49 በ“ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች“) ውስጥ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለመጀመሪያ ክፍልይመልከቱ፡፡

የሚመከር መዝሙር፦ “How Firm a Foundation፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 85።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

ሙዚቃን ተጠቀሙ። የቤተሰብ አባላት በመዝሙሮች እና በህጻናት መዝሙሮች ግጥሞች ውስጥ የወንጌል እውነቶችን እንዲፈልጉ እርዷቸው። የተቀደሰ ሙዚቃን መደበኛ የወንጌል ጥናታችሁ አካል ለማድረግ መንገዶችን ፈልጉ።

ምስል
ያዕቆብ ወንድ ልጆቹን ሲባርክ

ያዕቆብ ወንድ ልጆቹን ሲባርክ፣ በ ሃሪ አንደርሰን

አትም