ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መጋቢት 7–13 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 37-41 ፦”ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ”


“መጋቢት 7–13 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 37-41፤ ‘ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ፣‘“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“መጋቢት 7–13 (እ.አ.አ) ኦሪት ዘፍጥረት 37-41፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
የግብጹ ዮሴፍ በእስር ቤት

የግብጹ ዮሴፍ በእስር ቤት ምስል በጄፍ ዎርድ

መጋቢት 7–13 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 37–41

”ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ”

ኦሪት ዘፍጥረት 37-41ን ስታነቡ የቅዱስ ጽሁፉ መልዕክት ከህይወታችሁ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እንድታዩ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳችሁ ጸልዩ፡፡ የምትቀበሏቸውን ማንኛውንም ሃሳቦች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

አንዳንድ ጊዜ መጥፎ ነገሮች በጥሩ ሰዎች ላይ ይከሰታሉ። ህይወት ያንን ትምህርት በግልጽ ያስተምረናል፤የያዕቆብ ልጅ የጆሴፍ ህይወትም እንዲሁ። እግዚያብሄር ከአባቶቹ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ወራሽ ነበር ፤ነገር ግን በወንድሞቹ ተጠልቶ እና ለባርነት ተሸጦ ነበረ። የጲጥፋራ ሚስት ስትቀርበው ሃቀኘነቱን ለማላላት አሻፈረኝ አለ፤ ስለዚህም ወደ ወህኒ ተጣለ። ታማኝነቱ በጨመረ ቁጥር የሚገጥመውም መከራ የሚበረታ ይመስል ነበር። ይህ ሁሉ መከራ ግን በእግዚያብሄር ተቀባይነት የማጣት ምልክት አልነበረም። በርግጥ በዚህ ሁሉ ውስጥ “እግዚያብሄር ከዮሴፍ ጋር ነበረ “(ኦሪት ዘፍጥረት 39-3)። የዮሴፍ ህይወት የዚህ ጠቃሚ እውነት መገለጫ ነበረ:እግዚያብሄር አይተወንም። ፕሬዚዳንት ዲየተር ኤፍ.ኡክዶርፍ እንዲህ ሲሉ አስተምረዋል“ አዳኙን መከተላችሁ መከራዎቻችሁን አያስወግዳቸውም፣“ ። “ነገር ግን በእናንተ እና ሰማያዊ አባት ሊሰጣችሁ በሚፈልገው እርዳታ መካከል ያለውን ግድግዳ ያስወግዳል። እግዚያብሄር ከእናንተ ጋር ይሆናል”(“A Yearning for Home፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2017(እ.አ.አ)፣ 22)።

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 37፧1-283941:9–45

በመከራው ”ጌታ ከዮሴፍ ጋር ነበረ”።

በተደጋጋሚ መልካም እድል ዮሴፍን የራቀው ይመስል ነበር፤ ነገር ግን ጌታ አልራቀውም ። የዮሴፍን ታሪክ ስታነቡ እንደነዚህ ያሉትን ጥያቄዎች አሰላስሉ፦ ዮሴፍ በመከራዎቹ ጊዜያት ወደ እግዚያብሄር እንዲቀርብ ምን አደረገ። ጌታ ”ከእርሱ ጋር” የነበረው እንዴት ነዉ?? (ኦሪት ዘፍጥረት 39፧2-3፣ 21፣23)፡፡

ስለህይወታችሁ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ልትጠይቁም ትችላላችሁ፡፡ በመከራችሁ ጊዜያት ጌታ እንዳልተዋችሁ ምን ማስረጃ አይታችኋል? ለቤተሰብ አባላት እና ለመጪው ትውልድ ልምዳችሁን እንዴት ማካፈል እንደምትችሉ አስቡ ( 1 ኔፊ 5፧14ን ይመልከቱ)፡፡ ወደፊት መከራዎች ሲያጋጥሟችሁ ታማኝ ሆናችሁ ለመቆየት ራሳችሁን ለማዘጋጀት አሁን ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

በተጨማሪም ዮሃንስ 14፧18ሮሜ 8፧28አልማ 36፧3ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 121፧7–8፤ ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “The Joy of the Saints፣” ሊያሆና፣ ህዳር ፣2019፣ 15–18 ይመልከቱ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 37፧5-114041፧1-38

ታማኝ ከሆኩኝ ጌታ ይመራኛል እንዲሁም ያነሳሳኛል።

ሽማግሌ ዴቪድ ኤ.ቤድናር “መገለጦች ለምሳሌ በህልም፣በራዕይ፣ከሰማያዊ መልዕክተኞች ጋር በመነጋገር እና በመነሳሳት የሚተላለፉትን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ይተላለፋሉ “ሲሉ አስተምረዋል(“የመገለጥ መንፈስ፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2011(እ.አ.አ)፣ 88)። ጌታ እውነቶችን ለዮሴፍ፣ ለፈርኦን ጠጅ አሳላፊዎች አለቃ እና ለእንጀራ አበዛዎች አለቃ ለመግለጥ ህልሞችን ተጠቅሟል። ጌታ እነዚህ ህልሞች እንዴት እንደሚፈቱም ለዮሴፍ ገልጧል። ከ ኦሪት ዘፍጥረት 37፧5-1140፧5–841፧14–25፣ 37–38 ከጌታ ራዕይን ስለመቀበል እና ስለመረዳት ምን ትማራላችሁ? ለምሳሌ፦መገለጥ ለመረዳት ከባድ መስሎ ሲታይ ከዮሴፍ ምሳሌ ምን ትማራላችሁ ( ኦሪት ዘፍጥረት 40፧841፧16ይመልከቱ)?

ምስል
ዮሴፍ በወህኒ ህልም ሲፈታ

ዮሴፍ የጠጅ አሳላፊውን እና የእንጀራ አበዛውን ህልም ሲፈታ፣ በፍራንኮ ጄራርድ

ጌታ ፍላጎቱን ለእናንተ እንዴት እየገለጸላችሁ እንደሆነ አሰላስሉ? ጌታ በሰጣችሁ መገለጥ ላይ ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ምን እያረጋችሁ ነው? ተጨማሪ ምሪት ከእርሱ የምትሹት እንዴት ነው?

በተጨማሪም የራስል ኤም. ኔልሰንን፣ “ራዕይ ለቤተክርስቲያኗ እና ራዕይ ለህይወታችን፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2018 (እ.አ.አ)፣ 93–96፤ሚሼል ክሬይግ፣መንፈሳዊ አቅም፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019(እ.አ.አ)፣19–21 ይመልከቱ.።

ኦሪት ዘፍጥረት 3839፥7-20

በጌታ እርዳታ ከፈተና እርቃለሁ፡፡

በምትፈተኑበት ጊዜ የዮሴፍ ምሳሌ ማበረታቻ እና ጥንካሬ ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 39ውስጥ ስለተሞክሮው ስታነቡ ጆሴፍ ፈተናን ለመቋቋም ምን ነገሮችን እንዳደረገ አስተውሉ፡፡ ለምሳሌ፦

  • የጲጥፋራን ሚስት እንቅስቃሴን ገፋ (ቁጥር 8)፡፡

  • ሃጢያት እግዚያብሄርን እና ሰዎችን እንደሚያሰቀይም ተገነዘበ(ቁጥር 8–9)፡፡

  • ምንም እንኳን “ቀን በቀን“ ቢቀጥልም በፈተናው “አልተጠመደም “(ቁጥር 10)፡፡

  • “ ልብሱን ተወ እና …ወደ ውጭ ሸሸ“ (ቁጥር 12)፡፡

የዮሴፍን ምሳሌ በእምሯችሁ ይዛችሁ ፈተናን ለማስወገድ እና ለመቋቋም እቅድ ማውጣትን አስቡ፡፡ ለምሳሌ ሊያጋጥማችሁ የሚችልን ፈተና ስታስቡ፣ማስወገድ ያለባችሁን ሁኔታዎች ልታስወግዱ እና ፈተና በሚመጣ ጊዜ በሰማይ አባት ላይ እንድትደገፉ እቅድ ማውጣት ትችላላችሁ( 2ኔፊ 4፧18፣27–33ይመልከቱ)፡፡

ፈተና:

ሊወገዱ የሚገባቸው ሁኔታዎች:

ምላሽ መስጫ እቅድ

ይህ ዮሴፍ ፈተና ባጋጠመው ጊዜ ስለነበረው ጥንካሬ የሚያወራው ዘገባ በ ኦሪት ዘፍጥረት38ከሚገኘው ከቀደመው ከወንድሙ ከይሁዳ ዘገባ በጣም የተለየ ነው፡፡ ምዕራፍ 3738እና 39፣በአንድነት ስለንጽህና ምን ያስተምራሉ?

(በተጨማሪም 1 ቆሮንቶስ10፧131 ኔፊ 15፧23-243 ኔፊ 18፧17-18ን ይመልከቱ፡፡)

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና ለቤት ምሽት ሃሳቦች

ዘፍጥረት 37ከዮሴፍ ወንድሞቸ አንዱ ብትሆኑ ኖሮ ቅናት ከርሱ ጋር ያላችሁን ግንኙነት እንዳያዳክመው ምን ታደርጉ ነበር? እርስ በርሳችን “በሰላም መነጋገር“ እንዴት ይረዳናል(ቁጥር4)፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 39፡፡“The Refiner’s Fire” እና “After the Storm” የሚሉት ቪዲዮዎች(ChurchofJesusChrist.org)በፈተናቸው ጊዜ ፊታቸውን ወደ ጌታ በማድረግ ጥንካሬ ስላገኙ ሰዎች ተሞክሮዎች ያወራሉ፡፡ ምናልባት ከእነሱ ውስጥ አንዳቸውን ልታዩ እና ዮሴፍ ሰለተሞክሮዎቹ ቪዲዮ ለመስራት ቢፈልግ ምን ሊል እንደሚችል ማውራት ትችላላችሁ፡፡ I’m Trying to Be Like Jesus” (የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ 78–79) አብራችሁ ልትዘምሩ እና ዮሴፍ መከራ ባጋጠመው ጊዜ ቤተሰባችሁ ሊያጋራው የሚችለውን ምክር ልትፈልጉ ትችላላችሁ፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 39፥7–12እነዚህን ጥቅሶች ማንበብ ከቤተሰባችሁ ጋር ስለንጽህና ህግ ለመወያየት መልካም አጋጣሚ ሊፈጥር ይችላል። ለዚህ ውይይት ሊረዱ የሚችሉ አንዳንድ መረጃዎች እነሆ፤ ያዕቆብ 2፥28አልማ 39፥3–9፤ “Sexual Purity” (በ For the Strength of Youth [2011(እ.አ.አ)]፣ 35–37 ውስጥ የሚገኝ)፤ “Sexual Intimacy Is Sacred and Beautiful” (በ Help for Parents [2019(እ.አ.አ)]፣ AddressingPornography.ChurchofJesusChrist.orgውስጥ የሚገኝ)።

ኦሪት ዘፍጥረት 41፥15–57 በዮሴፍ አማካኝነት ጌታ የግብጽን ህዝብ ስለመባረኩ ከእነዚህ ጥቅሶች ምን እንማራለን? ወደፊት ለሚከሰቱ ድንገተኛ ሁኔታዎች ስለመዘጋጀት ምን ልንማር እንችላለን? እንደቤተሰብ በተሻለ ሁኔታ የተዘጋጃችሁ ለመሆን ምን ልታደርጉ እንደምትችሉ ተወያዩ፡፡ ለሃሳቦች“Emergency Preparedness፣” topics.ChurchofJesusChrist.orgበወንጌል አርስቶች ውስጥ ይመልከቱ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “Jesus Is Our Loving Friend፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ58፡፡

የግል ጥናትን ማሻሻል

ቅዱሳን መጻህፍትን ከሕይወታችሁ ጋር አመሳስሉ። ስታነቡ በቅዱሳን ጽሁፎች ውስጥ ያሉ ታሪኮች እና ትምህርቶች በሕይወታችሁ ውስጥ እንዴት እንደሚተገበሩ አስቡ። ለምሳሌ፦ ዮሴፍ በግብጽ ውስጥ የነበረው ታማኝነት መከራ ቢኖርም ለጌታ ታማኝ ሆናችሁ እንድትቆዩ እንዴት ሊያነሳሳችሁ ይችላል?

ምስል
የዮሴፍ ወንድሞች ኮቱን ሲወስዱበት

የዮሴፍ ወንድሞች ኮቱን ሲወስዱበት፣ ምስል በሳም ሎውሎር

አትም