ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
የካቲት 28–መጋቢት 6 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 28-33 ፦”በእውነት እግዚያብሄር በዚህ ስፍራ ነው”


“የካቲት–መጋቢት 6 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 28-33 ፦‘በእውነት እግዚያብሄር በዚህ ስፍራ ነው፣’“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“የካቲት 28–መጋቢት 6 (እ.አ.አ) ኦሪት ዘፍጥረት 28–33፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ቲሁአና ሜክሲኮ ቤተመቅደስ

የካቲት 28–መጋቢት 6 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘፍጥረት 28–33

”በእውነት እግዚያብሄር በዚህ ስፍራ ነው”

ኦሪት ዘፍጥረት 28–33ን ስታነቡ ከያዕቆብ እና እና ከቤተሰቦቹ ምሳሌነት ምን እንደምትማሩ አሰላስሉ። የምትቀበሏቸውን ሃሳቦች መዝግቡ።

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

ኦሪት ዘፍጥረትምዕራፍ 28 እና 32 ነቢዩ ያዕቆብ ስለነበሩት ሁለት መንፈሳዊ ገጠመኞች ይናገራል። ሁለቱም የተከሰቱት በምድረ በዳ ነበር ነገር ግን በጣም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ነበር የተከሰቱት። በመጀመሪያው ገጠመኝ ያዕቆብ ሚስት ለማግኘት ወደ እናቱ ሃገር እየሄደ ነበር እናም በመንገዱ በድንጋይ ትራስ ላይ ምሽቱን አሳለፈ። በዚህ ሰው በሌለበት ቦታ ጌታን ለማግኘት ጠብቆ ላይሆን ይችላል፤ነገር ግን እግዚያብሄር ራሱን ህይወት ቀያሪ በሆነ ህልም ለያዕቆብ ገለጠ፤ያዕቆብም ”በእውነት እግዚያብሄር በዚህ ስፍራ ነው፤እኔ አላወኩም ነበር” አለ(ኦሪት ዘፍጥረት 28፥16)። ከአመታት በኋላ ያዕቆብ ራሱን በድጋሚ በምድረበዳ አገኘው። በዚህ ጊዜ ሞት ሊያስከትል ከሚችለው ከተነናደደ ወንድሙ ከኤሳው ጋር መገናኘትን በመጋፈጥ ወደ ከነአን እየተመለሰ ነበር። ነገር ግን ያዕቆብ በረከት በፈለገ ጊዜ በምድረበዳ ውስጥ ቢሆንም እንኳን ጌታን መጠየቅ እንደሚችል ያውቅ ነበር ( ኦሪት ዘፍጥረት 32ይመልከቱ)።

እግዚያበብሄርን በረከት እየጠየቃችሁ ራሳችሁን በራሳችሁ ምድረበዳ ልታገኙት ትችላላችሁ። ምናልባት የናንተ ምድረበዳ ያዕቆብ እንደነበረው አስቸጋሪ ቤተሰባዊ ግንኙነት ሊሆን ይችላል። ምናልባት ከእግዚያብሄር እንደራቃችሁ ወይም በረከት እንደሚያስፈልጋችሁ ሆኖ ይሰማችሁ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ በረከቶቹ ሳይታሰቡ ይመጣሉ በሌላ ጊዜ ከትግል በኋላ ይመጣሉ። ፍላጎታችሁ ምንም ቢሆን፣ በምድረ በዳም ብትሆኑ “ጌታ በዚህ ቦታ እንደሆነ“ ታውቃላችሁ።

ምስል
Learn More image
ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 2829፥1–18

በቤተመቅደስ ውስጥ የአብርሃም በረከቶች ቃል ተገብተውልኛል፡፡

ሚስት ለማግኘት ወደ ሃራን እየሄደ ሳለ ያዕቆብ እግዚያብሄር ከላይ የቆመበት ከምድር ወደ ሰማይ የተዘረጋ መሰላል በህልም አየ፡፡ በህልሙ ውስጥ እግዚያብሄር ከአብርሃም እና ከይስሃቅ ጋር ያደረገውን ያንኑ ቃልኪዳን ከያዕቆብ ጋር አደሰው( ኦሪት ዘፍጥረት 28፥10–17ይመልከቱ፤ በተጨማሪም ኦሪት ዘፍጥረት12፥2–326፥1–4ን ይመልከቱ)፡፡ ፕሬዚዳንት ማሪየን ጂ.ሮምኒ መሰላሉ ምን ሊወክል እንደሚችል ይህን ሃሳባቸውን አካፍለዋል: “ያዕቆብ ከጌታ ጋር በዚያ የገባው ቃል ኪዳን ቃል የተገቡትን በረከቶች ለማግኘት እርሱ እራሱ የሚወጣቸው የመሰላሉ መወጣጫዎች እንደነበሩ ተገነዘበ —ወደሰማይ ለመገግባት እና ከእግዚያብሄር ጋር ለመሆን የሚያበቁ በረከቶች ፡፡… ቤቴል ለያዕቆብ እንደነበረች ሁሉ ቤተመቅደሶችም ለኛ ለሁላችን እንደዚያው ናቸው ”(“ቤተመቅደሶች—ወደሰማይ መግቢያ በሮች፣” ኢንዛይን፣ መጋቢት. 1971(እ.አ.አ)፣ 16)፡፡

ኦሪት ዘፍጥረት 28፥10–22 ሌላ ምን ቃላት እና ሃረጎች በያዕቆብ ተሞክሮ እና በቤተመቅደስ በረከቶች መከካል ያለውን ግንኙነት ይጠቁማሉ? እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣​የገባችኋቸውን ቃል ኪዳኖች አስቡ፤ ምን ሃሳቦች ወደናንተ መጡ?

ኦሪት ዘፍጥረት 29፥1–18ስታነቡ ያዕቆብ ከራሄል ጋር ያደረገው ጋብቻ እግዚያብሄር ከያዕቆብ ጋር በቤቴል ላደሰው ቃል ኪዳን እንዴት አስፈላጊ እንደነበረ አስቡ (“የእግዚያብሄር ቤት“፤ ኦሪት ዘፍጥረት 28፥10–19ን ይመልከቱ)፡፡ በ ኦሪት ዘፍጥረት 29–33ስለያዕቆብ ህይወት ማንበባችሁን ስትቀጥሉ ይህንን ተሞክሮ አስታውሱ። የጌታ ቤት ወደ እግዚያብሄር ያቀረባችሁ እንዴት ነው?

በተጨማሪም የዩን ህዋን ቾይን“Don’t Look Around, Look Up!” ይመልከቱ ሊያሆና፣ ግንቦት 2017(እ.አ.አ)፣ 90–92።

ኦሪት ዘፍጥረት 29፧31-3530፧1-24

ጌታ በመከራዎቼ ያስታውሰኛል።

ምንም እንኳን ራሄል እና ሊያ ከእኛ በተለየ ጊዜ እና ባህል ውስጥ የኖሩ ቢሆንም እኛ ሁላችንም የተሰሟቸውን አንዳንድ ስሜቶች መገንዘብ እንችላለን። ኦሪት ዘፍጥረት 29፥31-35 እና 30፥1–24ን ስታነቡ፣ እግዚያብሄር ለራሄል እና ለሊያ የነበረውን ይቅርታ የሚገልጹ ቃላትን እና ሃረጎችን ፈልጉ። እግዚያብሄር እንዴት “መከራችሁን እንደሚያይ“ እና “እንደሚያስታውሳችሁ“ አሰላስሉ(ኦሪት ዘፍጥረት 29፥3230፥22)።

እንዲሁም እግዚያብሄር የሚሰማን ቢሆንም በጥበቡ ሁልጊዜ የጠየቅነውን እራሱን እንደማይሰጠን ማስታወስ ያስፈልጋል። ሰማያዊ አባታችን ስለሚመልስልን የተለያዩ መንገዶች ለመማር “የጸሎት መልሶች” (ሊያሆና፣ ግንቦት 2019(እ.አ.አ) ፣11–14) የሚለውን የሽማግሌ ብሩክ ፒ.ሄልስ መልዕክት ማጥናትን አስቡ።

ስለዚህ ታሪክ ባህላዊ ዳራ ተጨማሪ ለማግኘት የብሉይ ኪዳን የተማሪው መማሪያ: ኦሪት ዘፍጥረት–2 ሳሙኤል 2003(እ.አ.አ)፣ 86–88ይመልከቱ፡፡

ምስል
ያዕቆብ እና ኤሳው ሲተቃቀፉ

ያዕቆብ እና ኤሳው ሲተቃቀፉ ምስል በሮበርት ቲ. ባሬት

ኦሪት ዘፍጥረት 32–33

አዳኙ በቤተሰባችን ውስጥ የሚከሰት አለመግባባትን እንድንቋቋም ይረዳናል።

ያዕቆብ ወደ ከነዓን በተመለሰ ጊዜ ኤሳው እንዴት እንደሚቀበለው “ፈርቶ እና ተጨነቆ“ ነበር(ኦሪት ዘፍጥረት 32፥7)። በ ኦሪት ዘፍጥረት 32–33 ውስጥ ስለያዕቆብ ከኤሳው ጋር መገናኘት እና ወደዚያ ስለመሩት ስሜቶቹ ስታነቡ—ምናልባት መታከም ስለሚፈልገው ስለራሳችሁ ቤተሰብ ልታስቡ ትችላላችሁ። ምናልባት ይህ ታሪክ ለአንድ ሰው መልካም ነገር ለማድረግ ጥረት እንድታደርጉ የሚያነሳሳችሁ ሊሆን ይችላል። እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎች ንባባችሁን ለመምራት ሊረዱ ይችላሉ:

  • ያዕቆብ ኤሳውን ለመገናኘት እንዴት ተዘጋጀ?

  • ኦሪት ዘፍጥረት 9–12ውስጥ ካለው የያዕቆብ ጸሎት ለናንተ ምን ጎልቶ ይታያችኋል?

  • ከኤሳው ምሳሌነት ስለ ይቅርባይነት ምን ትማራላችሁ?

  • አዳኙ የቤተሰብ ግንኙነታችንን እንድንጠግን የሚረዳን እንዴት ነው?

በተጨማሪም ሉቃስ 15፥11–32፤ጄፍሪ አር ሆላንድ፣ “የማስታረቅ አገልግሎት፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2018 (እ.አ.አ)፣ 77–79 ይመልከቱ

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፍጥረት 28–33ልጆች በእነዚህ ምዕራፎች ያሉ ኩነቶችን እንዲገነዘቡ ለመርዳት “የዕቆብ እና ቤተሰቡ” የሚለውን (ከ የብሉይ ኪዳን ታሪኮች) ተጠቀሙ። ምናልባት የቤተሰብ አባላት በያንዳንዱ ስዕል ላይ ቆም ሊሉ እና እንደ የትዳር አስፈላጊነት፣ቃል ኪዳን ፣ስራ እና ይቅርባይነት ያሉ ምን ትምህርቶች እየተላለፉ እንደሆነ ሊለዩ ይችላሉ።

ኦሪት ዘፍጥረት 28፥10–22ቃል ኪዳኖቻችን እንዴት እንደመሰላል እንደሆኑ ለመነጋገር መሰላል(ወይንም የመሰላል ስዕል) ልትጠቀሙ ትችላላችሁ። ምን ቃል ኪዳኖች ገብተናል፤እንዴትስ ወደ እግዚያብሄር ያቀርቡናል? የቤተሰብ አባላት በ ኦሪት ዘፍጥረት 28፥10–22ውስጥ ስለተገለጸው የያዕቆብ ጸሎት ስዕል መሳል ሊወዱ ይችላሉ።

Nearer, My God, to Thee፣”የሚለው መዝሙር(መዝሙር፣ ቁጥር 100 )በያዕቆብ ህልም አነሳሽነት የተጻፈ ነበር። ቤተሰባችሁ መዝሙሩን ሊዘምር እና እያንዳንዱ ስንኝ ምን እንደሚያስተምር ሊወያይ ይችላል።

ኦሪት ዘፍጥረት 32፥24–32ለመታገል የሚፈልጉ የቤተሰብ አባላት ሊኖሯችሁ ይችላሉ። “ትግል“ ከጌታ በረከቶችን ስለመፈለግ ለመግለጽ ጥሩ መንገድ የሆነው ለምንድን ነው? ኢኖስ 1፥1–5አልማ 8፥9–10 “ከእግዚያብሄር ጋር … መታገል” ማለት ምን ማለት እደሆነ ምን ይጠቁማሉ?

ኦሪት ዘፍጥረት 33፥1–12ከብዙ አመታት መራራ ስሜቶች በኋላ ያዕቆብ እና ኤሳው መልሰው ተገናኙ። ያዕቆብ እና ኤሳው ዛሬ ቢያነጋግሩን በቤተሰባችን አለመግባባት በሚኖርበት ጊዜ የሚረዳን ምን ሊሉን ይችላሉ?

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦ “Dearest Children, God Is Near You፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር. 96።

የግል ጥናትን ማሻሻል

ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልከቱ። ብሉይ ኪዳን በታሪኮች እና በምልክቶች አማካኝነት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመሰክራል። ወደ አዳኙ የሚያመለክቱ እና በተለይ ለናንተ ትርጉም ያላቸው ጥቅሶችን መጻፍን እና ምልክት ማድረግን አስቡ።

ምስል
ያዕቆብ በደረጃ ላይ ሆኖ ስለመላዕክት ሲያልም።

የያዕቆብ ህልም በቤቴል፣ በኬን ስፔንሰር

አትም