ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
መጋቢት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘጸአት1–6 ፦ “ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ”


“መጋቢት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘጸአት 1–6 ፦ ‘ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ፣’“ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)

“መጋቢት 21–27 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘጸአት 1–6 ፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፥ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ሙሴ እና የሚቃጠል ቍጥቋጦ

ሙሴ እና የሚቃጠለው ቍጥቋጦ፣ በሃሪ አንደርሰን

መጋቢት 21–27 (እ.አ.አ)

ኦሪት ዘጸአት 1–6

“ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ”

ጥናታችሁን በጸሎት ጀምሩ እናም በ ኦሪት ዘጸአት:1–6 ውስጥ ለህይወታችሁ እና በእግዚያብሄር መንግስት ውስጥ ለምትሰጡት አገልግሎት አግባብነት ያለው መልዕክት ለማግኘት እርዳታን ጠይቁ፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

በግብጽ ለመኖር የቀረበላቸው ግብዣ የያዕቆብን ቤተሰብ ቃል በቃል አድኖታል፡፡ ነገር ግን ከመቶ አመታት በኋላ የአነሱ ዝርያዎች “ዮሴፍን ባላወቀ“ አዲስ ፈርኦን በባርነት ተወስደው እና ተሸብረው ነበር፡፡(ኦሪት ዘጸአት 1–6) እስራኤላውያን እግዚያብሄር ለምን በእነርሱ በቃልኪዳን ህዝቡ ላይ ይህ እንዲደርስባቸው እንደፈቀደ መጠየቃቸው ተፈጥሯዊ ነበር፡፡ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አስታውሶ ነበር? አሁንም የእርሱ ህዝቦች ነበሩ? ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደነበር ማየት ይችል ነበር?

ተመሳሳይ ጥያቄዎችን የመጠየቅ ፍላጎት ያደረባችሁ ጊዜያት ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እግዚያብሄር እያለፍኩበት ያለውን ሁኔታ ያውቃል? ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፡፡ የእርዳታ ልመናዬን ሊሰማ ይችላል? በኦሪት ዘጸአት ያለው የእስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት የመውጣት ታሪክ እንዲህ ያለውን ጥያቄ ይመልሳል፡፡በግልጽ፦ እግዚያብሄር ህዝቡን አይረሳም፡፡ ከእኛ ጋር የገባቸውን ቃል ኪዳኖች ያስታውሳል፤ እናም በራሱ ጊዜ እና መንገድ ይፈጽማቸዋል፡፡( ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 88፥68) “በተዘረጋ ክንድ አድናችኋለሁ“ ሲል ይናገራል፡፡ “ ከተገዥነ[ታችሁም] ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚያብሄር ነኝ“(ኦሪት ዘጸአት 6፥6–7)፡፡

ስለኦሪት ዘጸአት አጭር ማብራሪያ ለማግኘት በመጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ውስጥ “ኦሪት ዘጸአት“ የሚለውን ይመልከቱ፡፡

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፀአት 1–2

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኜ ነው።

በኦሪት ዘጸአት መጽሃፍ ውስጥ ካሉ ዋና ጭብጦች አንዱ እግዚያብሄር ህዝቡን ከጭቆና የማውጣት ሃይል መኖሩ ነው። በ ኦሪት ዘፀአት 1 የተገለጸው የእስራኤላውያን በባርነት መወሰድ በሃጢያት እና በሞት ምክንያት ለምንጋፈጠው እስር እንደምልክት ሆኖ ሊታይ ይችላል( 2 ኔፊ 2፥26–279፥10አልማ 36፥28ን ይመልከቱ)። እናም ሙሴ የእስራኤል አዳኝ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ወይም ወኪል ሆኖ ሊታይ ይችላል( ኦሪት ዘዳግም 18፥18–191 ኔፊ 22፥20–21ን ይመልከቱ)። እነዚህን ንጽጽሮች በማስታወስ ኦሪት ዘፀአት 1–2 ን አንብቡ። ለምሳሌ፦ ሙሴም ኢየሱስም በልጅነታቸው ከሞት ተጠብቀው እንደነበር ( ኦሪት ዘፀአት 1፥222፥10; ማቴዎስ 4፥1–2ይመልከቱ) እንዲሁም ሁለቱም አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊት በምድረበዳ ቆይተው እንደነበር ልታስተውሉ ትችላላችሁ( ኦሪት ዘፀአት 2፥15–22ማቴዎስ 4፥1–2ን ይመልከቱ)። ከኦሪት ዘፀአት ስለመንፈሳዊ እስር ሌላ ምን ማስተዋሎችን ትማራላችሁ? ስለአዳኙ ነጻ አውጪነትስ?

በተጨማሪም ዲ. ቶድ ክሪስቶፈርሰን፣ “መዋጀት፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2013 (እ.አ.አ)፣ 109–12 ይመልከቱ።

ምስል
ህጻኑ ሙሴ በቅርጫት ውስጥ

ሙሴ በቄጤማዎች ውስጥ © Providence Collection/ፈቃዱ የተገኘው ከ goodsalt.com

ኦሪት ዘፀአት 3–4

እግዚያብሄር የእርሱን ስራ እንዲሰሩ ለሚጠራቸው ሃይልን ይሰጣል።

ዛሬ ሙሴን በታላቅ ነቢይነቱ እና መሪነቱ እናውቀዋለን። ነገር ግን ጌታ መጀመሪያ ሲጠራው ሙሴ ራሱን እንደዚያ አላየም። “ወደ ፈርኦን የምሄድ እኔ ማን ነኝ“? ሲል አሰበ።” (ኦሪት ዘፀአት 3፥11) ነገር ግን ጌታ ሙሴ ማን እንደሆነ— እንዲሁም ምን አይነት ሰው ሊሆን እንደሚችል በርግጥ ያውቅ ነበር። ኦሪት ዘፀአት 3–4ን በምታነቡበት ጊዜ፣ ጌታ እንዴት ማረጋገጫ እና ለስጋቶቹ መልስ እንደሰጠው አስቡ። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ብቁነት እንደሌላችሁ ሲሰማችሁ ሊያነሳሳችሁ የሚችል ምን ነገር ታገኛላችሁ? ጌታ አገልጋዮቹ የእርሱን ፈቃድ እንዲያደርጉ በብዙ ሃይል የሚባርካቸው እንዴት ነው?( ሙሴ 1፥1–10, 24–396፥31–39, 47ን ይመልከቱ)። እግዚያብሄር በናንተ ወይንም በሌሎች አማካኝነት ስራውን ሲሰራ ያያችሁት መቼ ነው?

ስለሙሴ ህይወት እና አገልግሎት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ በ መጽሃፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ወይም የቅዱሳን መጻህፍት መመሪያውስጥ “ሙሴ“ የሚለውን ይመልከቱ።

ኦሪት ዘፀአት 5–6

የጌታ አላማዎች በራሱ ጊዜ ይፈጸማሉ፡፡

ልክ እግዚያብሄር አዞት እንደነበረው ምንም እንኳን ሙሴ በድፍረት ወደ ፈርኦን ቢሄድም እና እስራኤላውያንን እንዲለቅ ቢነግረውም ፈርኦን አልተቀበለም፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የእስራኤላውያንን ህይወት ይበልጥ አዳጋች አድርጎት ነበር፡፡ ሙሴ እግዚያብሄር እንዲያደርግየጠየቀውን ነገር እያደረገ የነበረ ቢሆንም ነገሮች ለምን እየሰሩ እንዳልነበረ ሙሴ እና እስራኤላውያን አስበው ሊሆን ይችላል( ኦሪት ዘፀአት 5፥22–23)፡፡

የእግዚያብሄርን ፈቃድ እያደረጋችሁ የነበረ ቢሆንም የጠበቃችሁት ስኬት እንዳልተገኘ ተሰምቷችሁ ያውቃል? ሙሴ እንዲጸና ለመርዳት ጌታ ምን እንደተናገረ በመፈለግ ኦሪት ዘፀአት 6፥1–8ን ከልሱ፡፡ ጌታ የእርሱን ፈቃድ እንድታደርጉ እንዴት ነው የረዳችሁ?

ኦሪት ዘፀአት 6፥3

ይሆዋ ማን ነው?

ይሆዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ስሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን የሚያመለክተውም ቅድመ-ምድራዊ አዳኙን ነው። የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም እንደ አብርሃም፣ይስሃቅ፣እና ያዕቆብ ያሉ ነቢያት አዳኙን በስም ያውቁት እንደነበር ግልጽ ያደርጋል ( ኦሪት ዘፀአት 6፥3፣ የግርጌ ማስታወሻ cይመልከቱ)፡፡ በተለምዶ “ጌታ“ የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ በሚከሰትበት ጊዜ ይሆዋን ያመለክታል፡፡ በ ኦሪት ዘፀአት 3፥13–15፣ውስጥ “ያለ እና የሚኖር” የሚለው የማዕረግ ስምም ይሆዋን የሚያመለክት ነው (በተጨማሪም ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 38፥139፥1ይመልከቱ)።

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘፀአት 1–2ብዙ ሴቶች ለእስራኤላውያን አዳኝ ለማስነሳት በእግዚያብሄር እቅድ ውስጥ ወሳኝ ሚናዎች ተጫውተዋል። እንደ ቤተሰብ ስለ አዋላጆቹ ስለ ሲፓራ እና ስለፉሃ (ኦሪት ዘጸአት1፥15–20)፤ስለሙሴ እናት ስለዮካብድ እና ስለእህቱ ስለማርያም (ኦሪት ዘጸአት 2፥2–9ኦሪት ዘኁልቁ 26:59)፤ስለፈርኦን ሴት ልጅ (ኦሪት ዘጸአት 2፥5–6, 10)፤ እና ስለሙሴ ሚስት ስለ ሲፓራ (ኦሪት ዘጸአት 2፥16–21)ን ልታነቡ ትችላላችሁ። እነዚህ ሴቶች የእግዚያብሄር እቅድ እንዲስፋፋ ያደረጉት እንዴት ነው? የእነሱ ተሞክሮዎች የኢየሱስ ክርስቶስን ተልዕኮ የሚያስታውሱን እንዴት ነው? የሴት ዘመዶቻችሁን እና የሴት ቅድመ አያቶቻችሁን ምስልም ልትሰበስቡና ታሪካቸውን ልታጋሩ ትችላላችሁ። በጻድቅ ሴቶች እንዴት ተባርከናል? የፕሬዚዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ለእህቶቼ ልመና፣”ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.አ.አ)፣ 95-98 መልዕክት ውይይታችሁን ሊያዳብረው ይችላል።

ኦሪት ዘጸአት 3፥1–6ሙሴ ወደሚቃጠለው ቁጥቋጦ በቀረበ ጊዜ አክብሮታዊ ፍርሃት ለማሳየት ጌታ ጫማውን እንዲያወልቅ ነገረው። ለተቀደሱ ቦታዎች አክብሮታዊ ፍርሃት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ለምሳሌ፥ ቤታችንን የጌታ መንፈስ የሚያድርበት የተቀደሰ ቦታ ለማድረግ ምን ማድረግ እንችላለን? በሌሎች የተቀደሱ ቦታዎች የተሻለ አክብሮታዊ ፍርሃት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ኦሪት ዘጸአት 4፥1–9ጌታ ሙሴን እንደላከው ለእስራኤላውያን ምልክት ይሆን ዘንድ ለሙሴ ሶስት ተአምራትን የማድረግ ሃይል ሰጠው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን ያስተምሩናል?

ኦሪት ዘፀአት 5፥2ጌታን “ማወቅ” ማለት ለኛ ምን ማለት ሊሆን ይችላል? እንዴት አወቅነው?(ለምሳሌ አልማ 22፥15–18ን ይመልከቱ)። ከእርሱ ጋር ያለን ግንኙነት እርሱን ለመታዘዝ ባለን ፍላጎት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?(በተጨማሪም ዮሃንስ 17፥3ሞዛያ 5፥13ን ይመልከቱ)።

ልጆችን ለማስተማር ጠቃሚ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትን ይመልከቱ፡፡

የሚመከር መዝሙር፦ “አምልኮት ፍቅር ነው፣” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ31፡፡

የማሰተማር ዘዴያችንን ማሻሻል

የጥናት ጆርናል መዝግቡ፡፡ በምታጠኑበት ጊዜ የሚመጡላችሁን ሃሳቦች፣ጥያቄዎች ወይም ግንዛቤዎች ለመመዝገብ ጆርናል ወይም ማስታወሻ ደብተር ጠቃሚ ሆኖ ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡

ምስል
የፈርዖን ሴት ልጅ ህጻኑን ሙሴ ስታገኝ

ሙሴ በፈርኦን ሴት ልጅ በቄጤማ መሃል እንደተገኘ በ ጆርጅ ሶፐር

አትም