“መጋቢት 28 (እ.አ.አ)---ሚያዝያ 3 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘጸአት 7-13 ፦‘ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፣’“ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)
“መጋቢት 28–ሚያዝያ 3 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘጸአት 7–13፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)
መጋቢት 28–ሚያዝያ 3 (እ.አ.አ)
ኦሪት ዘፀአት 7–13
“ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ“
ኦሪት ዘፀአት 7–13ን ስታነቡ እና ስታሰላስሉ የሚመጡላችሁን ግንዛቤዎች መዝግቡ፡፡ ይህንን ዘወትር ስታደርጉ የመንፈስ ቅዱስን የሹክሹክታ ድምጽ የመለየት ችሎታችሁ ያድጋል፡፡
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ተከታታይ ቸነፈር ግብጽን አጎሳቆላት ነገር ግን አሁንም ፈርኦን እስራኤላውያንን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሆኖም እግዚያብሄር ሃይሉን ማሳየቱን እና “እኔ እግዚያብሄር እንደሆንኩ“ እና “በምድር ሁሉ እንደኔ ያለ እንደሌለ“ የሚለውን ፈርኦን እንዲቀበል አጋጣሚ መስጠቱን ቀጠለ፡፡(ኦሪት ዘፀአት 7፥5፤ 9፥14) ይህ በእንዲህ እንደለ ሙሴ እና እስራኤላውያን ስለነሱ የሚደረጉትን እነዚህን የእግዚያብሄር ሃይል መገለጫዎች ያዩት ከአክብሮታዊ ፍርሃት ጋር መሆን አለበት፡፡ በርግጠኝነት፣ አነዚህ እየቀጠሉ የነበሩት ምልክቶች በእግዚያብሄር ላይ ያላቸውን እምነት አረጋገጡት እንዲሁም የእግዚያብሄርን ነቢይ የመከተል ፍላጎታቸውን አጠናከሩት፡፡ ከዚያም፣ዘጠኝ አስፈሪ መቅሰፍቶች እስራኤላውያንን ለማስለቀቅ ባለመቻላቸው፣አስረኛው ቸነፈር ነበር—የፈርኦንን የበኩር ልጅ ያካተተው የበኩር ልጅ ሞት—በመጨረሻ ምርኮው እንዲጠናቀቅ ያደረገው፡፡ ይህ ተገቢ ይመስላል ምክንያቱም በያንዳንዱ መንፈሳዊ ምርኮ በትክክል አንድ ብቻ ማምለጫ መንገድ አለ፡፡ ከዚህ በፊት ምንም ሌላ ነገር ሞክረን የነበረ ቢሆን ከእስራኤል ልጆች ጋር እንደነበረው ሁሉ ከእኛም ጋር ነው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕት ፣በበኩር ልጅ፣፣ባልረከሰ የበግ ደም—ብቻ ነው ሁላችን የምንድነው፡፡
ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
ልቤን ለማለስለስ መምረጥ እችላለሁ።
ፈቃዳችሁ ልክ እንደ ፈርኦን የእግዚያብሄርን ፈቃድ በከባዱ እንደማይቃወም ተስፋ ይረጋል። አሁንም ሁላችንም ልቦቻችን መለስለስ ያለባቸውን ያህል ለስላሳ የማይሆኑበት ጊዚያት አሉን። ስለዚህ በ ኦሪት ዘፀአት 7–10ውስጥ ከሰፈሩት የፈርኦን ተግባራት የምንማራቸው ነገሮች አሉ። በነዚህ ምእራፎች ውስጥ ስላሉት መቅሰፍቶች ስታነቡ፣ ከፈርኦን መልሶች ምን ጎልቶ ይታያችኋል? በራሳችሁ ውስጥ ወደግትርነት የሚያዘነብሉ ተመሳሳይ ዝንባሌዎችን ታያላችሁ? ለስላሳ ልብ መኖር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከነዚህ ምዕራፎች ምን እንደምትማሩ አሰላስሉ።
የ ኦሪት ዘፀአት 7፥3, 13፤ 9፥12፤ 10፥1, 20, 27፤ 11፥10 የጆሴፍ ስሚዝ ትርጉም ጌታ የፈረርኦንን ልብ እንዳላጠጠረው—ፈረርኦን የራሱን ልብ እንዳጠጠረ (ለያንዳንዱ ጥቅስ የተቀመጡትን የግርጌ ማስታወሻዎች ይመልከቱ) ግልጽ ያደርጋል።
ከሚከተሉት ቅዱሳን ጽሁፎች ለስላሳ ልብ ስለመፍጠር ምን ትማራላችሁ? 1 ኔፊ 2፥16፤ ሞዛያ 3፥19፤ አልማ 24፥7–8፤ 62፥41፤ ኤተር 12፥27።
በተጨማሪም ሚካኤል ቲ.ሪንግዉድ፣ “An Easiness and Willingness to Believe፣” ሊያሆና ህዳር 2009(እ.አ.አ)፣ 100–102 ይመልከቱ።
የአይሁድ ፋሲካ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ ምልክት ነው።
በ ኦሪት ዘፀአት 11፥4–5ውስጥ ከተገለጸው አስረኛ መቅሰፍት የመዳኛው ብቸኛ መንገድ ጌታ ለሙሴ የሰጠውን የፋሲካ ስርአት በመባል የሚታወቀውን በ ኦሪት ዘፀአት12ውስጥ ያለውን መመሪያ በትክክል መከተል ነበር። ፋሲካ በምልክቶች አማካኝነት ልክ ጌታ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት እንዳወጣቸው እኛንም ከሃጢያት ባርነት እንደሚያወጣን ያስተምረናል። በፋሲካ መመሪያዎች እና ምልክቶች ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እና የሃጢያት ክፍያውን የሚታስታውሳችሁ ምን ታገኛላችሁ? እነዚህ መመሪያዎች እና ምልክቶች የሃጢያት ክፍያውን በረከቶች እንዴት እንደምትቀበሉ ምን ይጠቁሟችኋል? ለምሳሌ፣ የበጉን ደም በበሩ መቃን እና ጉበን ላይ መቀባት ምንን ሊወክል ይችላል?“(ቁጥር 7) “ጫማችሁን በእግራችሁ በትራችሁንም በእጃችሁ” ማለት ለእናንተ ምን ማለት ነው ? (ቁጥር 11)፡፡
በተጨማሪም ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 89፥21ን ይመልከቱ፡፡
ኦሪት ዘጸአት 12፥14–27፣24–27፤ 13፥1–16
ቅዱስ ቁርባን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት መዳኔን እንዳስታውስ ይረዳኛል።
በምርኮ መወሰዳቸው የረዥም ጊዜ ትዝታ ከሆነ በኋላም እንኳን አዳኙ እንዳዳናቸው እስራኤላውያን ሁልጊዜ እንዲያስታውሱ ፈለገ። ለዚህ ነው የፋሲካን በአል በየአመቱ እንዲያከብሩ ያዘዛቸው። በ ኦሪት ዘጸአት 12፥14–17፣24–27፤ 13፥1–16ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ስታነቡ እግዚያብሄር የሰጣችሁን በረከቶች ለማስታወስ ምን እያረጋችሁ እንደሆነ አስቡ። ያንን መታሰቢያ “ለልጅ ልጃችሁ“ እንዴት ማቆየት ትችላላችሁ?( ኦሪት ዘጸአት 12፥14, 26–27ይመልከቱ)።
በፋሲካ በአል እና በቅዱስ ቁርባን አላማዎች መካከል ምን ተመሳሳይነት ትመለከታላችሁ? ስለፋሲካ ማንበባችሁ ቅዱስ ቁርባንን እና ለዚያ ስርአት ይበልጥ ትርጉም ስለመስጠት እንዴት ያስታውሳችኋል? ኢየሱስ ክርስቶስን ”ሁልጊዜ ለማስታወስ” ምን ማድረግ እንደምትችሉ አስቡ(ሞሮኒ 4፥3፤ 5፥2፤ በተጨማሪም ሉቃስ 22፥7–8, 19–20ን ይመልከቱ)።
ጌታ እንድታስታውሱ የሚፈልጋቸውን ሌሎች ነገሮችንም ልታሰላስሉ ትችሉ ይሆናል፤ለምሳሌ ሄለማን 5፥6–12፤ ሞሮኒ 10፥3፤ ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 3፥3–5, 10፤ 18፥10፤ 52፥40።
በተጨማሪም ዮሃንስ 6፥54፤ “Always Remember Him” (ቪዲዮ)፣ ChurchofJesusChrist.org፤ “The Sacrament of the Lord’s Supper፣” በ የቤተክርስቲያኗ ፕሬዚዳንቶች ትምህርቶች: ሆዋርድ ደብልዩ. ሀንተር (2015(እ.አ.አ)), 197–206ውስጥ ይመልከቱ።
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ኦሪት ዘፀአት 7–12።ምናልባት ጌታ እንደ ሃይሉ መገለጫ ወደ ግብጽ ስለላካቸው መቅሰፍቶች ካነበባችሁ በኋላ ቤተሰባችሁ ጌታ ዛሬ ሃይሉን እያሳየስለሚገኝባቸው መንገዶች ሊያካፍል ይችላል።
-
ኦሪት ዘጸአት 8፥28፣32፤ 9፥27–28፣34–35።እነዚህ ጥቅሶች ቃላችንን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት ውይይት ለመጀመር ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ምናልባት የቤተሰብ አባላት ሌሎች ለማድረግ የተስማሙበትን ነገር ሲያደርጉ ያዩት መቼ እንደሆነ ልምዶችን ሊያጋሩ ይችላሉ።
-
ዘጸአት 12፥1–42። ዘጸአት 12፥1–42 ን አብራችሁ ካነበባችሁ በኋላ የኢየሱስ ክርስቶን የሃጢያት ክፍያ ለማስታወስ እንደቤተሰብ ልታደርጉ የምትችሏቸውን ነገሮች በቁራጭ ወረቀት ላይ ልትጽፉ ትችላላችሁ። በበሩ መቃን እና ጉበን ( ቁጥር 23ይመልከቱ) ላይ ያለው የበጉ ደም አዳኙን ስለሚወክል አነዚህን ወረቀቶች በደጃፋችሁ አካባቢ ልታስቀምጡ ትችላላችሁ። ከፋሲካው እንደ ያልቦካ ቂጣ(ብስኩቶች ወይም ቶርቲላዎች) ያሉ አንዳንድ ምግቦችን ወይንም መራራ ቅጠሎችን (የሾርባ ቅጠል ወይም የሆርስራዲሽ ስር) ልትበሉ እና ፋሲካው እግዚያብሄር እንዴት ህዝቡን እንዳዳነ እንድናስታውስ እንደሚረዳን ልትወያዩ ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ያልቦካው ቂጣ ከእስር ለማምለጥ ዳቦው እሰስኪነፋ ድረስ ጊዜ እንዳልነበራቸው ያስታውሳቸው ነበረ። መራራው ቅጠል የባርነትን አስከፊነት ያስታውሳቸው ነበረ።
-
ኦሪት ዘጸአት 12፥14፣24–27።ምናልባት ከሚቀጥለው የቅዱስ ቁርባን ስብሰባችሁ በፊት እነዚህን ጥቅሶች በቤተሰብ ደረጃ ልትከልሷቸው ትችላላችሁ። እነዚህ ጥቅሶች ከቅዱስ ቁርባን ጋር የሚዛመዱት እንዴት ነው? ቅዱስ ቁርባንን እንዴት አዳኙ ለኛ ላደረገልን ነገር ይበልጥ ሙሉ “መታሰቢያ“ ማድረግ እንችላለን?
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት፣ የዚህን ሳምንት መዘርዝር በ ኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፦ “In Memory of the Crucified፣” መዝሙሮች፣ ቁጥር 190።