ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 11–17 (እ.አ.አ) ፋሲካ፦ “ሞትን ለዘላለም ይውጣል“


“ሚያዝያ 11–17 (እ.አ.አ)፡፡ ፋሲካ፦’ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣’” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) 2021 (እ.አ.አ)

“ሚያዝያ 11–17 (እ.አ.አ)፡፡ ፋሲካ፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)

ምስል
ድንጋዩ ከበሩ ላይ የተነሳ መቃብር

ባዶ መቃብር ምስል በማሪና ክሩቼንኮ

ሚያዝያ 11–17 (እ.አ.አ)

ፋሲካ

“ሞትን ለዘላለም ይውጣል“

በዚህ ሳምንት ስለአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ስታነቡ እና ስታሰላስሉ ስለከፈለው መስዋዕትነት ሃሳቦቻችሁን እና ስሜቶቻችሁን በጆርናላችሁ ወይንም በዚህ ዝርዝር ውስጥ በተሰጠው ክፍት ቦታ መመዝገብን አስቡ፡፡

ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ

የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት “የሁሉም የሰው ልጆች ታሪክ እምብርት ነው“ “The Living Christ: The Testimony of the Apostles፣” ChurchofJesusChrist.org)፡፡ ያ ማለት ምን ማለት ነው? በከፊል፣የአዳኙ ህይወት በእያንዳንዱ እስከዛሬ በኖረ ወይም ወደፊት በሚኖር የሰው ልጅ ዘላለማዊ ፍጻሜ ላይ በርግጠኝነት ተጽዕኖ ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በዚያ የመጀመሪያ የፋሲካ እሁድ በትንሳኤው የተደመደመው የኢየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ተልዕኮ በመላው ታሪክ ውስጥ ሁሉንም የእግዚያብሄር ህዝቦች ያገናኛል ልትሉም ትችላላሁ፦ከክርስቶስ በፊት የተወለዱት በአምነት በጉጉት ጠብቀውት ነበር ፤( ያዕቆብ 4፥4ይመልከቱ)እንዲሁም ከዚያ በኋላ የተወለዱት እርሱን በእምነት ያስቡታል፡፡ የብሉይ ኪዳን ዘገባዎችን እና ትንቢቶችን ስናነብ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም አናገኝም ነገር ግን የጥንት አማኞች ለመሲሃቸው እና ለአዳኛቸው የነበራቸውን እምነት እና ናፍቆት ማስረጃ እናያለን፡፡ ስለዚህ እኛ እርሱን ለማስታወስ የተጋበዝን እርሱን በጉጉት ከጠበቁት ጋር ያለን ግንኙነት ሊሰማን ይችላል፡፡ በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ“ የሁላችንንበደል በእርሱ ላይ አኖረ“ (ኢሳይያስ 53፥6፤ ሰያፍ ጽሁፍ ተጨምሯል) እናም ” ሁሉ በክርስቶስ ህያዋን ይሆናሉ”(1 ቆሮንቶስ 15፥22፤ ሰያፍ ጽሁፍ ተጨምሯል)

ምስል
የግል ጥናት ምልክት

ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች

ብሉይ ኪዳን ስለአዳኙ የሃጢያት ክፍያ ይመሰክራል።

በብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ምንባቦች ወደ አዳኙ አገልገግሎት እና የሃጢያት ክፍያ ይጠቁማሉ። የሚከተለው ሰንጠረዥ እነዚህን አንዳንድ ምንባቦች ይዘረዝራል። እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ፣ ስለአዳኙ ምን ሃሳብ ይመጣላችኋል?

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዘካሪያስ 9፥9

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 21፥1–11

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዘካሪያስ 11፥12-13

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 26፥14–16

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ኢሳይያስ 53:4

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 8፥16–1726፥36–39

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ኢሳይያስ 53፥7

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 14፥60–61

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 22፥16

አዲስ ኪዳን

ዮሃንስ 19፥17–1820፥25–27

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 22፥18

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥35

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 69፥21

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥34፣ 48.

ብሉይ ኪዳን

መዝሙረ ዳዊት 118፥22

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 21፥42

ብሉይ ኪዳን

ኢሳይያስ 53፥9፣12

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥57–60ማርቆስ 15፥27–28

ብሉይ ኪዳን

ኢሳይያስ 25፥8

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 16፥1–6ሉቃስ 24፥6

ብሉይ ኪዳን

ትንቢተ ዳንኤል12፥2

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 27፥52–53

በመጽሃፈ ሞርሞን ስለአዳኙ የተሰጡ ትንቢቶች እና ትምህርቶች እጅግ ብዙ እና ግልጽ ናቸው፡፡ እምነታችሁ እንደዚህ ባሉ ምንባቦች እንዴት እንደሚጠናከር አስቡ: 1 ኔፊ 11፥31–332 ኔፊ 25፥13ሞዛያ 3፥2–11፡፡

በአዳኙ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ሰላም እና ደስታ ማግኘት እችላለሁ፡፡

በዘመናት ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት ወደ እርሱ ለመጡት ሁሉ ሰላምን እና ደስታን ሰጥቷል( ሙሴ 5፥9–12ን ይመልከቱ)፡፡ ስለሚሰጠው ሰላም እና ደስታ የሚመሰክሩትን የሚከተሉትን ቅዱሳን ጽሁፎች ማጥናትን እና ይህንን ስታደርጉም ሰላም እና ደስታ እንዴት ልትቀበሉ እንደምትችሉ አስቡ መዝሙረ ዳዊት 16፥8–1130፥2–5ትንቢተ ኢሳይያስ 1225፥8–940፥28–31ዮሃንስ 14፥2716፥33አልማ 26፥11–22፡፡

በተጨማሪም ዳልን ኤች. ኦክስ፣ “Strengthened by the Atonement of Jesus Christ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015(እ.አ.አ)፣ 61–64; ሻረን ኢዩባንክ፣ “Christ: The Light That Shines in Darkness፣” ሊያሆና፣ ግንቦት 2019(እ.አ.አ)፣ 73–76፤ “I Stand All Amazed፣” መዝሙሮች፣ ቁ. 193 ይመልከቱ፡፡

ምስል
ክርስቶስ በመስቀል ላይ

የሀዘን ቀን ጎልጎታ፣ በጄ. ከርክ ሪቻርድስ

በሃጢያት ክፍያው አማካኝነት ኢየሱስ ክርስቶስ ሃጢያትን፣ሞትን፣መከራዎችን እና ድካሞችን እንድቋቋም ሊረዳኝ ሃይል አለው፡፡

በመላው ቅዱሳን ጽሁፎች፣ ነቢያት ኢየሱስ ክርስቶስ ከሃጢያት እና ከሞት ሊያወጣን የሚያስችል ሃይል እንዳለው እና መከራዎቻችንን እና ድካሞቻችንን ለመቋቋም እንደሚረዳን መስክረዋል፡፡ ክርስቶስ በህይወታችሁ ልዩነት ያመጣው እንዴት ነው? እርሱ ለናንተ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እነዚህን ጥቅሶች ስታነቡ እነዚህን ጥያቄዎች አሰላስሉ እና ስለአዳኙ ያላችሁን ሃሳቦች እና ስሜቶች መዝግቡ፡፡

በተጨማሪም ዋልተር ኤፍ.ጎንዛሌዝ፣ “The Savior’s Touch፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2019(እ.አ.አ)፣ 90-92 ይመልከቱ፡፡

ምስል
የቤተሰብ ጥናት ምልክት

ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች

ኦሪት ዘጸአት 12፥1–28፡፡ፋሲካን ስታከብሩ በዚህ ወር መጀመሪያ ስለአይሁድ ፋሲካ የተማራችሁትን ቤተሰባችሁ ሊከልስ ይችላል፡፡ የአዳኙ የሃጢያት ክፍያ የተከናወነው ከእግዚያብሄር ፋሲካ ጋር በአንድ አይነት ጊዜ መሆኑ ትርጉም ያለው የሆነው ለምንድን ነው?

በአዳኙ ህይወት የመጨረሻ ሳምንት ውስጥ ምን እንደተደረገ ማጠቃለያ ለማግኘት “Holy Week” በ ComeuntoChrist.org/2016/easter/easter-weekውስጥ ይመልከቱ፡፡ ስለአዳኙ የመጨረሻ ሳምንት ድርጊቶች የሚያወሱ ቅዱሳን ጽሁፎችን ለማግኘት “The Last Week: Atonement and Resurrection”ከወንጌሎች ጋር የሚስማማ (በመጽሃፍ ቅዱስ ተጨማሪ ገጾች)ይመልከቱ፡፡

ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡፡ትንቢተ ኢሳይያስ 53 ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢቶች ማንበብ የቤተሰባችሁ አባላት የአዳኙን የሃጢያት ክፍያ እንዲገነዘቡ ሊረዳ ይችላል፡፡ ቤተሰባችሁ የትኞቹን ጥቅሶች ወይም ሃረጎች በተለይ ጉልህ ሆኖ ያገኘዋል? ስለአዳኙ የሃጢያት ክፍያ የራሳችሁን ምስክርነት የምታካፍሉበት የቤተሰብ የምስክርነት ስብሰባ ማዘጋጀትን አስቡ፡፡

”የክርስቶስ ልዩ ምስክሮች” የወንጌል ላይብረሪ መተግበሪያ እና ChurchofJesusChrist.org ”የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ ምስክር”የተባለ እያንዳንዱ የቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለቱ ሃዋርያት ሸንጎ አባል ስለኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ምስክርነት የሚያካፍልበት የቪዲዮዎች ስብስብ አላቸው፡፡ ምናልባት ቤተሰባችሁ ከነዚህ ቪዲዮዎች አንዳንዶቹን ሊመለከት እና ከእርሱ ምርጥ አገልጋዮች ከተሰጡት ምስክርነቶች ስለኢየሱስ ክርስቶስ ምን እንደተማራችሁ ልትነጋገሩ ትችላላችሁ፡፡ እንደ ቤተሰብ ስለክርስቶስ ያላችሁን ምስክርነት ማካፈል የምትችሉባቸውን መንገዶች ተወያዩ፡፡ ለምሳሌ፦በዚህ የፋሲካ እሁድ አንድ ሰው በቤተክርስቲያን ከእናንተ ጋር እንዲያመልክ ልትጋብዙ ትችላላችሁ።

መዝሙሮች እና የልጆች መዝሙሮችሙዚቃ አዳኙን ለማስታወስ እና መንፈሱን ወደ ቤታችን ለመጋበዝ ወሳኝ መንገድ ነው። የቤተሰብ አባላት እንደ“Christ the Lord Is Risen Today” (መዝሙሮች፣ ቁ. 200) ወይም “Did Jesus Really Live Again?” (የልጆች መዝሙር መጽሃፍ፣ 64).ያሉ መዝሙሮችን ሊያካፍሉ እና ስለፋሲካ ወይም ስለኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙሮችን ወይም የልጆች መዝሙሮችን ሊዘምሩ ይችላሉ። ሌሎች መዝሙሮችን ወይም የህጻናት መዝሙሮችን ለማግኘት በ መዝሙሮች እና የልጆች መዝሙር መጽሃፍ.ርዕስ ማውጫ ፈልጉ።

ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት ፥ የዚህን ሳምንት መዘርዝርኑ፤ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።

የሚመከር መዝሙር፦“Did Jesus Really Live Again?የልጆች መዝሙር መፅሀፍ፣ 64።

የምናስተምርበትን ዘዴ ማሻሻል

የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ኑሩ። “[በቤታችሁ] እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ አስተማሪ ለመሆን ምናልባት ልታደርጉት የምትችሉት በጣም አስፈላጊው ነገር …በሙሉ ልባችሁ ወንጌልን መኖር ነው። የመንፈስ ቅዱስን ወዳጅነት ለማግኘት ብቁ ለመሆን ዋነኛው መንገድ ይህ ነው። በትጋት መሞከር—እንዲሁም ስትሰናከሉ በአዳኙ የሀጢያት ክፍያ አማካኝነት ይቅርታን መለመን እንጂ ፍጹም መሆን አይጠበቅባችሁም“(በአዳኙ መንገድ ማስተማር 13)።

ምስል
ክርስቶስ በመቃብር የተሰበረ ድንጋይ በር ላይ ቆሞ

ለዚህ አላማ ነው የመጣሁት በዮንግሱንግ ኪም

አትም