“ሚያዝያ 18–24 (እ.ኤ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 18–20 ‘ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፣’“ ኑ፤ ተከተሉኝ----ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ብሉይ ኪዳን 2022 (እ.አ.አ) (2021)
“ሚያዝያ 18–24 (እ.አ.አ)፡፡ ኦሪት ዘፍጥረት 18–20፣” ኑ፤ ተከተሉኝ—ለግለሰቦች እና ለቤተሰቦች፦ 2022 (እ.አ.አ)
ሚያዝያ 18–24 (እ.አ.አ)
ኦሪት ዘፀአት 18–20
“ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን“
እህት ሚሼል ክሬግ ሲያስተምሩ “እንደ [ኢየሱስ ክርስቶስ]ታማኝ ደቀመዝሙር ከትዕዛዛቶቹ ጋር አብሮ የሚሄድ ለናንተ የተሰራ የግል መነሳሳትን እና መገለጥን ታገኛላችሁ(“Spiritual Capacity፣” .ሊያሆና፣ ህዳር. 2019፣ 21)። ኦሪት ዘጸአት 18–20ን ስታነቡ የምትቀበሉትን መንፈሳዊ መነሳሳት መዝግቡ እና ተግባራዊ አድርጉ።
ያሳደረባችሁን ስሜት መዝግቡ
ከግብጽ እስከ ሲና ተራራ ግርጌ የነበረው የእስራኤላውያን ጉዞ በተዐምራት የተሞላ ነበረ—የጌታ አቻ የለሽ ሃይል፣ፍቅር፣እና ይቅርታ የማይካዱ መገለጫዎች። ነገር ግን እነሱን ከግብጽ ነጻ ከማውጣት እና አካላዊ ርሃባቸውን እና ጥማታቸውን ከማርካት ያለፈ ጌታ ለነሱ በመጋዘኑ በረከቶች ነበሩት። የቃል ኪዳን ህዝቡ እንዲሆኑት ፈለገ፣የእርሱ “ልዩ ሃብት“ እና “የተቀደሰ ህዝብ“(ኦሪት ዘጸአት 19፥5–6)። ዛሬ የዚህ ቃል ኪዳን በረከቶች ከአንድ ሀገር ወይም ህዝብ አልፈው ሄደዋል። “ለሚወዱ[ት] ትዕዛ[ዙ]ን ለሚጠብቁ እሰከ ሺህ ትውልድ ድረስ“ ይቅርታውን ስለሚያሳይ እግዚያብሄር ሁሉም ልጆቹ የቃል ኪዳን ህዝቦቹ እንዲሆኑ፣“ድምጹን እንዲታዘዙ እና [የእርሱን] ቃል ኪዳን እንዲጠብቁ” ይፈልጋል(ኦሪት ዘጸአት 19፥5)፣(ኦሪት ዘጸአት 20፥6)።
ለግል ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት ሃሳቦች
የጌታን ስራ የመስራትን ”ሸክም ለመሸከም” መርዳት እችላለሁ።
ሙሴ ከአማቱ ዮቶር የተቀበለውን ምክር ስታነቡ በ ቁጥር 21ውስጥ እንደተገለጹት እንደ “የታመኑ ሰዎች“ (አንደዳንድ ጊዜ “እምነት የሚጣልባቸው“ ሰዎች ተብሎ ይተረጎማል) የምትሆኑት እንዴት እንደሆነ አስቡ። የቤተክርስቲያን መሪዎቻችሁን ”ሸክም ለመሸከም” እንዴት መርዳት ትችላላችሁ?(ቁጥር 22) ለምሳሌ፦ይህ ምክር በአገልግሎት ጥረታችሁ እንዴት ተግባራዊ ሊሆን ይችላል?
እናንተም አንዳንድ ጊዜ እጅግ በጣም ብዙ ነገሮችን ለመስራት በመሞከር እንደ ሙሴ ሆናችሁ እንደሆነም ልታስቡ ትችላላችሁ። የዮቶር ምክሮች ለናንተ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው?
በተጨማሪም ሞዛያ 4፥27፤ሄንሪ ቢ አይሪንግ፣ “The Caregiver፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2012 (እ.አ.አ)፣ 121-24 ይመልከቱ።
የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች ለእርሱ ሃብቶች ናቸው፡፡
የጌታ “የተመረጠ ርስት” መሆን ማለት ለናንተ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ?(ኦሪት ዘጸአት19፥5)። ፕሬዚደንት ረሰል ኤም ኔልሰን ለዚህ ሃረግ አንድ ማብራሪያ ሰጥተዋል፦ “በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተመረጠ ርስት የሚለው ቃል የተተረጎመው ሴጉላህ፣ ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ‘ዋጋ ያለው ንብረት‘ ወይም ‘ሃብት‘ ማለት ነው … በጌታ አገልጋዮች ዘንድ የተመረጠ ርስት ተብለን መታወቅ ለእኛ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ምስጋና ነው።(“Children of the Covenant፣” ኢንዛይን፣ ግንቦት 1995(እ.አ.አ)፣ 34)። ቃል ኪዳናችሁን መጠበቃችሁ “የተመረጠ ሃብት“ እንደሚያደርጋችሁ ማወቃችሁ በምትኖሩበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?
በተጨማሪም ጌሪት ደብልዩ.ጎንግ፣ “Covenant Belonging፣” ሊያሆና ህዳር 2019(እ.አ.አ)፣ 80-83 ይመልከቱ።
የተቀደሱ ልምምዶች ዝግጅት ያስፈልጋቸዋል።
የእስራኤል ልጆች “ከእግዚያብሄር ጋር ከመገናታቸው“ (ኦሪት ዘፀአት 19፥10–17)በፊት መዘጋጀት ያስፈልጋቸው እንደነበር እና ከእርሱ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን መጠበቅ ( ኦሪት ዘፀአት19፥5ይመልከቱ) እንደነበረባቸው ጌታ ለሙሴ ነገረው። በቤተመቅደስ እንደመገኘት ወይም ቅዱስ ቁርባንን እንደመውሰድ ባሉ በህይወታችሁ ቅዱስ በሆኑ ልምምዶች ለመካፈል ዝግጀት ለማድረግ ምን ታደርጋላችሁ? በእነዚህ ልምምዶች ለመካፈል ይበልጥ በብቃት ለመዘጋጀት ምን ማድረግ ትችላላችሁ? ሌሎች መንፈሳዊ ልምምዶችን አስቡና ዝግጅታችሁ በምትካፈሉት የልምምድ አይነት እንዴት ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አሰላስሉ።
እግዚያብሄር ይቅር ባይ ነው።
ኦሪት ዘጸአት 20ን ስታነቡ ከአስርቱ ትዕዛዛት የትኞቹን እያከበራችሁ እንደሆነ እንደሚሰማችሁ እና የትኞቹን ይበልጥ በታማኝነት ማከክበር እንደምትችሉ እንደሚሰማችሁ አስተውሉ። ልትሰሩበት የምትፈልጉትን አንድ ትዕዛዝ ልትመርጡ እና ተዛማች ቅዱሳን ጽሁፎችን በማንበብ በጥልቀት ልታጠኑት ትችላላችሁ( የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ ን በ scriptures.ChurchofJesusChrist.orgይመልከቱ) ወይም ለአጠቃላይ ጉባኤ መልዕክቶች ( topics የሚለውን ክፍል በ conference.ChurchofJesusChrist.org) ውስጥ ይመልከቱ። በጥናታችሁ ውስጥ ትዕዛዙን ለሚያከብሩ ስለሚመጡ በረከቶች ማካተትን አስቡ። እነዚህ በረከቶች እግዚያብሄር ለናንተ ያለውን ይቅርታ እና ፍቅር የሚያሳዩት እንዴት ነው?
በተጨማሪም፣ ካሮል ኤም. ሰቴፈንስ “ከወደዳችሁኝ ትእዛዛቴን ጠብቁ፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2015 (እ.ኤ.አ), 118–20 ይመልከቱ፡፡
በህይወቴ ጌታን ማስቀደሜ አስፈላጊ ነው፡፡
ኦሪት ዘጸአት 20፥1–7 ን ማንበብ በህይወታችሁ ቅድሚያ ስለምትሰጧቸው ነገሮች እንድታስቡ ሊያነሳሳችሁ ይችላል—በዝርዝር ልትጽፏቸውም ትችላላችሁ፡፡ ከእግዚያብሄር በፊት ልታስቀድሟቸው የምትችሏቸው አንዳንድ “አማልክት” ወይም “የተቀረ[ጹ] ምስ[ሎች]”ምን ምን ናቸው?(ኦሪት ዘጸአት 20፥3–4) ጌታን ማስቀደም በህይወታችሁ አስፈላጊ ለሆኑ ሌሎች ነገሮች ሊረዷችሁ የሚችሉት እንዴት ነው? በሰማይ አባት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላችሁን ትኩረት ለመጨመር ምን ለማድረግ እየተነሳሳችሁ ነው?
በተጨማሪም“No Other Gods፣” ሊያሆና፣ ህዳር 2013(እ.አ.አ)፣ 72–75. ይመልከቱ፡፡
ለቤተሰብ ቅዱሳን መጻህፍት ጥናት እና የቤት ምሽት ሃሳቦች
-
ኦሪት ዘጸአት 18፥8–12፡፡ስለእግዚያብሄር ማዳን ሙሴ የሰጠው ምስክርነት በዮቶር ላይ ምን ተጽዕኖ ነበረው? ጌታ ለቤተሰባችን ምን ታላቅ ነገር አድርጓል? ተሞክሯችንን ለማን ማካፈል እንችላለን? እነዚህን ተሞክሮዎች ለወደፊት ትውልዶች ማቆየት የምንችለው እንዴት ነው?
-
ኦሪት ዘፀአት 34–26።አነዚህ ጥቅሶች ቤተሰባችሁ ስለአካባቢያችሁ ኤጲስ ቆጶስ፣የወጣት መሪዎች ወይም የህጻናት አስተማሪዎች እንዲያስብ ሊያነሳሱ ይችላሉ፡፡ ለአንድ ሰው ለመሸከም “የሚያደክሙ“ (ኦሪት ዘጸአት 18፥18) የሚመስሉ ምን ሃላፊነቶች አሉባቸው? ሸክሞቻቸውን በማውረድ ለማገዝ ምን ማድረግ እንችላለን?
-
ኦሪት ዘጸአት 20፥3–17፡፡አስርቱ ትዕዛዛትን እንደቤተሰብ መወያየት የምትችሉበትን ትርጉም ያለው መንገድ አስቡ፡፡ ለምሳሌ፣ በ ኦሪት ዘጸአት 20፥3–17 ውስጥ ያሉትን ትዕዛዛት በአስር ቁራጭ ወረቀቶች ልትጽፉ ትችሉ ይሆናል፡፡ ከዚያም የቤተሰብ አባላት በሁለት ምድቦች ሊያስተካክሏቸው ይችላሉ: (1)እግዚያብሄርን ማክበር እና (2) ሌሎችን መውደድ (በተጨማሪም ማቴዎስ 22:36–40ይመልከቱ)፡፡ በዚህ ሳምንት በያንዳንዱ ቀን አንድ ወይም ሁለት ትዕዛዛት መምረጥን እና በጋራ በዝርዝር መወያየትን አስቡ፡፡ ለምሳሌ፣ይህንን ትዕዛዝ ማክበር ቤተሰባችንን የሚያጠነክረው እንዴት ነው? ጌታ የታዘዘው እንዴት ነዉ?
-
ኦሪት ዘፀአት 20፥12፡፡ ኦሪት ዘፀአት 20፥12ን ይበልጥ ለመረዳት ቤተሰባችሁ ”ማክበር” የሚለውን ቃል ብያኔ ቢፈልግ ሊረዳው ይችል ይሆናል፡፡ ከዚያም የቤተሰብ አባላት ወላጆቻችንን የሚያከብሩ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ነገሮችን ዝርዝር ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ እንደ“Quickly I’ll Obey” (የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ 197) ያሉ ቤተሰብን ስለማክበር የሚያወሱ መዝሙሮችን ልትዘምሩ እና በዝርዝራችሁ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ሃሳቦች አዳዲስ ስንኞችን ለመጻፍ ልትጠቀሙ ትችላላችሁ፡፡
ልጆችን ለማስተማር ተጨማሪ ሃሳቦችን ለማግኘት የዚህን ሳምንት መዘርዝር በ ኑ፣ ተከተሉኝ—ለህጻናትይመልከቱ።
የሚመከር መዝሙር፦ “ትዕዛዛቱን ጠብቁ፣” የህጻናት መዝሙር መጽሃፍ፣ 146–47።