2010–2019 (እ.አ.አ)
በቃል ኪዳን አባል መሆን
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


በቃል ኪዳን አባል መሆን

የእግዚአብሔር መሆን እና አንዱ ከሌላው ጋር በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ መመላለስ በቃል ኪዳን አባል በመሆን መባረክ ነው።

ውድ ወንድም እና እህቶች ፤ ይህ ታሪክ ስለ አንድ የፃናት ክፍል ውስጥ ስላለ ልጅ ነው፡፡ውድ “ለፊደል ሀ ፣ ለፊደል ለ … ለፊደል ሰ አመሰግናለሁ።” የልጁ ጸሎት ይቀጥላል፣ “ለ ፀ፣ ፈ፣ ፐ ፊደሎች አመሰግናለሁ። ውድ የሰማይ አባት፣ ለቁጥር 1፣ ለቁጥር 2 አመሰግናለሁ።” የመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዋ ሀሳብ ያዛት ግን ጠበቀች። ልጅም እንዲህ አለ፣ “ለቁጥር 5፣ ለቁጥር 6 አመሰግናለሁ—እናም ለመጀመሪያ ክፍል አስተማሪዬም አመሰግናለሁ። ጸሎቴን እንድፈጽም የፈቀደችልኝ ብቸኛዋ ሰው እርሷ ብቻ ናትና።”

የሰማይ አባት የእያንዳንዱን ልጅ ጸሎት ይሰማል። ፍጻሜ በሌለው ፍቅር በኩል፣ በቃል ኪዳን እንድናምን እና አባል እንድንሆንም ይጠራናል።

ይህ ዓለም እውነት በሚመስል ነገር ግን እውነት ባልሆነ፣ ባልተጨበጠ ብዥታ ፣ ምትሃት የተሞላ ነው። ብዙዎች የሚያልፉ እና ጥልቀት የሌላቸው ናቸው። ጭንብሎቹን፣ ማስመሰልን፣ እና በመንጋ መውደድን እና መጥላትን ስናስወግድ፣ ከአስቸኳይ ጊዜ አከባቢ ፣ ከስጋ ግንኙነት ፣ ወይም ዓለማዊ የሆነ የግል ጥቅም ፍላጎት ከማሳደድ በላይ እንናፍቃለን። በምስጋናም፣ ትርጉም ላላቸው መልሶች የምንደርስበት መንገድ አለ።

በቃል ኪዳን እርሱን እና በክልላችን ያሉትን ለማፍቀር እዳለው ወደ እግዚአብሔር ታላቅ ትእዛዛት ስንመጣ፣ የምናደርገው እንደ እንግዳ ሳይሆን፣ ግን በቤት እንዳለ ልጅ ነው።1 የጥንቱ እንቆቅልሽ አሁንም እውነት ነው። በቃል ኪዳን አባል በመሆን የአለም ማንነታችንን በመተው፣ ነጻ፣ ህያው፣ እውነተኛ የኛን የተሻለ ዘለአለማዊ ማንነትን እናገኛለን2 እናም ከሁሉም በላይ አስፈላጊ የሆኑትን ግንኙነቶችን ለመግለፅ እንችላለን። በቃል ኪዳን አባል መሆን በህይወታችን ውስጥ የእግዚአብሄር ሀይል እንዲገለጥ በሚጋብዙ ቅዱስ ስርዓቶች በኩል ለእግዚአብሔር እና ለሌላው ቃል ኪዳንን መግባት እና መጠበቅ ነው።3 እኛ ሁላችንን ቃል ኪዳን ስንገባ፣ እኛ ከሆንነው የበለጠ ለመሆን እንችላለን። በቃል ኪዳን አባል መሆን ቦታ፣ አስተያየት፣ የመሆን ችሎታ ይሰጠናል። ወደ ህይወት እና ደህንነትም የሚያስደርስ እምነትን ይሰራል።4

መለኮታዊ ቃል ኪዳኖች ለእግዚአብሄር እና ከእርሱ፣ እና በዚህም ለእያንዳንዳችንም እና ለእያንዳንዳቸው ለሚመጣ ፍቅር ምንጭ ይሆናሉ። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር እራሳችንን ከምንወደው የበለጠ ይወደናል ወይም እራሳችንን ከምናውቀው በላይ ያውቀናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን እና የግል ለውጥ (ንስሐ) ምህረትን፣ ጸጋን፣ ይቅርታን ያመጣሉ። እነዚህ በሟችነት የምናገኛቸውን የተጎዳነውን ፣ የብቸኝነትን ፣ የፍትሕ መጓደልን ያፅናናሉ። እግዚአብሔር በመሆኑ ፣ የሰማይ አባታችን የእግዚአብሔርን ታላቅ ስጦታ ማለትም ደስታውን፣ ዘላለማዊ ህይወቱን እንድንቀበል ይፈልጋል።5

አምላካችን የቃል ኪዳን አምላክ ነው። በተፈጥሮው ፣ “ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል ምሕረትንም ያሳያል።”6 ቃል ኪዳኖቹም “ጊዜ እስከምትቆይ፣ ​​ወይም ምድር እስከምትቆም፣ ወይም ለመዳን ከፊቱ ላይ አንድ ሰው እስካለ ድረስ”7 ይጸናል። በውስጣችን በህልውና እርግጠኛአለመሆን እና ጥርጣሬ ውስጥ እንድንባዝን አይደለም ፣ ነገር ግን “ከሞት ገመድ ይልቅ ጠንካራ” ከሚሆነው ከሚወዱት የቃል ኪዳን ግንኙነቶች ለመደሰት ነው።8

የእግዚአብሔር ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች መስፈርቶቻቸው ሁለንተናዊ እና እድሎቹ እንደግለሰብ ናቸው። በእግዚአብሔር ፍትህ እያንዳንዱ ግለሰብ በሁሉም ቦታ እና ዕድሜ የግል ሥነ-ስርዓቶችን ሊቀበል ይችላል። ነጻ ምርጫ ተግባራዊ ይሆናል—ግለሰቦች የቀረቡትን ስነስርዓቶች ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ይመርጣሉ። የእግዚአብሔር ስርዓቶች የቃል ኪዳኑን መንገድ ላይ መመሪያ መስጠቶችን ይሰጣሉ። የልጆቹን ወደቤት የሚመልስበትን የእግዚአብሔር ዕቅድ፣ የመዳን እቅድ፣ የደህንነት እቅድ፣ የደስታ እቅድን ብለን እንጠራዋለን። ቤዛነት ፣ ደህንነት ፣ የሰለስቲያል ደስታ የሚቻለው ኢየሱስ ክርስቶስ “ይህን ፍጹም የኃጢያት ክፍያ ስላከናወነ” ነው።9

የእግዚአብሔር መሆን እና አንዱ ከሌላው ጋር በቃል ኪዳኑ መንገድ ላይ መመላለስ በቃል ኪዳን አባል በመሆን መባረክ ነው።

በመጀመሪያ ፣ የቃል ኪዳን አባል የመሆን ማዕከላዊነት “የአዲሱ ቃል ኪዳን አስታራቂ”10 በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ ነበር። “በአብ ቃል ኪዳን በኩል … በክርስቶስ ስንቀደስ”11 ሁሉም ነገር ለጥቅማችን አብረው መስራት ይችላሉ። እያንዳንዱ መልካም እና ቃል የተገቡ በረከቶች ሁሉ እስከ መጨረሻው በታማኝነት ለሚጸኑት ሁሉ ይመጣል። “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ደስተኛነት፣ በሁሉም ጊዜያዊ እና መንፈሳዊነገሮች መባረክ፣” እና “በማይቋረጥ ደስታ ከእግዚአብሔር” ጋር መኖር ነው።12

ቃል ኪዳኖቻችንን በመጠበቅ፣ አንዳንድ ጊዜ ከመላእክት ጋር እንደሆንን ሆኖ ሊሰማን ይችላል። እኛ የምንወዳቸው እና በዚህኛው የመጋረጃው ወገን ያሉት የሚባርኩልንን፣ እንዲሁም ከመጋረጃው በሌላኛው ወገን የሚወዱንን እና የሚባርኩንን እንሆናለን።

በቅርቡ እህት ጎንግ እና እኔ በቃል ኪዳን አባል መሆን በጣም በላቀ ሁኔት በአንድ የሆስፒታል ክፍል ውስጥ አየን። አንድ ወጣት አባት የኩላሊት ቅየራ በጣም ይፈልጋል ፡፡ ቤተሰቡ ኩላሊት እንዲቀበል ሲጾሙ ፣ ሲያለቅሱ እና ሲጸልዩ ነበር፡፡። ሕይወት አድን የሚሆን ኩላሊት እንደተገኘ ዜናው ገና ሲመጣ፣ ባለቤቱ በለሆሳስ “ሌላኛው ቤተሰብ ደህና ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” አለች። በቃል ኪዳኑ አባል መሆን በሐዋሪያው ጳውሎስ ቃላት፣ “በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና” ነው ።”13

በህይወት ጎዳና ላይ፣ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ልናጣ እንችላለን ፣ ግን እሱ በጭራሽ በእኛ ላይ እምነት ከመጣል ወደኋላ አይልም። ቀድሞ እንደነበረው፣ የእርሱ የበረንዳ መብራት ሁልጊዜ እንደበራ ነው። መንገዱን ወደሚያመለክቱ ወደ ቃል ኪዳኖቹ እንድንመጣ ወይም እንድንመለስ ይጋብዘናል። “ገና ሩቅ ስፍራ”14 እያለን እንኳ እኛን ለማቀፍ እና ለመቀበል ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃል። ለልምምድ ምሳሌ ፣ ቅስት ፣ ወይም የተገናኙ ነጥቦችን በእምነት ዐይን ስንመለከት፣ የእርሱን ርህራሄ እና ማበረታቻ፣ በተለይም በፈተናዎቻችን፣ በሀዘኖቻችን እና በተግዳሮቻችን እንዲሁም ደስታችን ውስጥ ማየት እንችላለን። ሆኖም ብዙውን ጊዜ እንሰናከላለን ወይም እንወድቃለን፣ ወደ እርሱ መጓዛችንን የምንቀጥል ከሆነ እሱ በየደረጃው ይረዳናል።

ሁለተኛ፣ መፅሐፈ ሞርሞን በኪዳናዊው አባልነት እጃችን ልንይዘው የምንችለው ማስረጃ ነው። መፅሐፈ ሞርሞንም እንደ አዲስ ቃል ኪዳን ትንቢት የተተነበየ የእግዚአብሔር ልጆች የሚሰበሰብበት መሳሪያ ነው።15 መፅሐፈ ሞርሞንን በራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ስናነበው፣ በጸጥታም ሆነ ድምጻችንን ከፍ አድርገን፣ እግዚአብሔርን “በንፁህ ልባችሁ፣ ከእውነተኛ ስሜት፣ እና በክርስቶስ በማመን፣” እግዚአብሔርን መጠየቅ እንችላለን፣ እናም በቅዱሱ መንፈስ ኃይል መፅሐፈ ሞርሞን እውነት እንደሆነ የእግዚአብሔርኝ፡ማረጋገጫ እንቀበላለን።16 ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችን እንደሆነ፣ ጆሴፍ ስሚዝ የዳግም መመለስ ነቢይ እንደሆነ፣ እናም የጌታ ቤተክርስቲያን በስሙ እንደምትጠራ፣ እንዲሁም የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን እንደምትባል ማረጋገጫን ይጨምራል።17

የመፅሐፈ ሞርሞን የሌሂ ልጆች ፣ለሆናችሁት “የነቢያት ልጆች” በጥንት እና ዘመናዊ ቃል ኪዳን ለእናንተ ይናገራል።18 አባቶቻችሁ እናንተ፣ ዘሮቻቸው በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ካለው ከአቧር የሚመጣውን ድምፅ እንድታውቁ የቃል ኪዳን ቃል ተቀበሉ።19 ስታነቡ የሚሰማዎት ያ ድምፅ “የቃል ኪዳኑ ልጆች” እንደሆናችሁ20 እና ኢየሱስም መልካሙ እረኛ እንደሆነ ነው።

መፅሐፈ ሞርሞን፣ በአልማ ቃላት፣ “እርሱን በማገልገል እናም ትዕዛዛቱን በመጠበቅ፤ በእናንተ ላይ መንፈሱን በብዛት ያፈስባችሁ ዘንድ”21 እያንዳንዳችንን ይጋብዘናል።ወደተሻለው ለመለወጥ በምንፈልግበት ጊዜ፣ አንድ ሰው እንዳለው፣ ​​“ሀዘንተኝነታችንን ለማቆም እና ደስተኛ ለመሆን ደስተኞች በመሆን”፣ለመመሪያ፣ ለእርዳታ እና ብርታት ክፍት እንሆናለን። የእግዚአብሔር እና የታማኝ አማኞች ማኅበረሰብ አባል ለመሆን በቃል ኪዳን ስንመጣ፣ በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ ቃል የተገባውን በረከት እንቀበላለን።22

ልጆቹን ሁሉ ለመባረክ የተመለሰው የክህነት ስልጣን ሦስተኛው የቃል ኪዳኑ አባል የመሆን አካል ነው። በዚህ ዘመን፣ መጥምቁ ዮሐንስ እና ሐዋሪያው ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የክህነት ስልጣንን በዳግም ለመመለስ ከእግዚአብሔር የተላኩ ባለግርማ መልእክተኞች ሆነው መጥተዋል።23 የእግዚአብሔር ክህነት እና ስነስርአቱ በምድር ላይ ግንኙነቶችን ያጣፍጣሉ እና የቃል ኪዳን ግንኙነቶች በሰማይ ውጤታማ እንዲሆኑ ስልጣን ይሰጣሉ።24

ክህነት ቃል በቃል ከህጻን አልጋ እስከ መቃብር — ከሕፃን ልጅ ስም እና እስከ መቃብር መቀደስ ድረስ ሊባርክ ይችላል። የክህነት በረከቶች ይፈውሳሉ፣ ያፅናናሉ. እናም ያማክራሉ። የይቅርባይነት ፍቅር እስኪመጣ ድረስ አንድ አባት ለልጁ የርህራሄ የክህነት በረከቱን በሰጠበት ወቅት በልጁ ተቆጥቶ ነበር። በቤተሰቧ ውስጥ ብቸኛ አባል የነበረችው ውድ ወጣት ሴት የተመስጦ የክህነት በረከትን እስክትቀበል ድረስ እግዚአብሔር እንደሚወዳት እርግጠኛ አልነበረችም። በዓለም ዙሪያ ክቡር ፓትርያርኮች የአባቶችን በረከቶች ለመስጠት በመንፈሳዊ ይዘጋጃሉ። ፓትርያርኩ እጆቻቸውን በራሳችሁ ላይ ሲጭኑ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለው ፍቅር ይሰማቸዋል እናም ይገልጹታል። በእስራኤል ቤት የዘር ሃረጋችሁን ያስታውቃል። ከጌታ የሚመጡ በረከቶችን ያሳያል። በተለየ ሁኔታ ርህራሄ የሞላባት የአንድ ፓትርያርክ ባለቤት አባታቸው የአባቶች በረከቶች በሚሰጥባቸው ቀናት እርሷ እና ቤተሰቧ መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንደሚጋብዙ ነግራኛለች።

በመጨረሻም፣ በቃል ኪዳን አባል መሆን የሚመጣው የጌታን ነብይ ስንከተል እና ጋብቻን ጨምሮ በቃል ኪዳናዊ ኑሮን ደስ የምንሰኝ ከሆነ ነው። የራሳችንን እና የቤተሰባችንን ደስታ በየቀኑ ከእራሳችን በፊት ስንመርጥ የቃል ኪዳን ጋብቻ ሰማያዊ እና ዘላለማዊ ይሆናል። “እኔ” ወደ “እኛ” ሲለወጥ፣ አብረን እናድጋለን። አብረን እናረጃለን፣ አብረን በወጣትነት እናድጋለን። እራሳችንን በመርሳት በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እርስ በርሳችን ስንባርክ፣ ደስ ደስታችን እና ተስፋችን በዘለአለም ሲቀደሱ እናገኛቸዋለን።

ሁኔታዎች የሚለያዩ ቢሆኑም፣ የምንችለውን ሁሉ ስናደርግ፣ የምንችለውን ያህል ስናደርግ፣ እና በቅን መንገድ የእርሱን እርዳታ ስንጠይቅ እና ስንሻ፣ ጌታ በወቅቱ እና በአሰራሩ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይመራናል።25 የጋብቻ ቃል ኪዳኖች ቃል በሚገቡት በጋራ ምርጫ አስገዳጅ ናቸው—እግዚአብሔር እናእኛ ለነጻ ምርጫ ያለንን ክብር የምናስታውስበት እና አብረን በምንፈልግበት የእሱ እርዳታ በረከት የምናስታውስበት ነው።

በቤተሰብ ትውልዶች ሁሉ ላይ በቃል ኪዳን አባል የመሆን ፍሬዎች በቤታችን እና በልባችን ውስጥ ይሰማቸዋል። እነዚህን በግል ምሳሌዎች እንድሳያችሁ ፍቀዱልኝ።

እህት ጎንግ እና እኔ ወደጋብቻ ለመድረስ በፍቅር እያለን፣ ስለነጻ ምርጫ እና ውሳኔዎች ተማርኩኝ። ለጊዜም፣ በሁለት የተለያዩ አገሮች ውስጥ በሁለት የተለያዩ አህጉሮች ላይ እንኖር ነበር። በዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ውስጥ ፒኤችዲ አግኝቻለሁ ብዬ በሐቀኝነት መናገር የምችለው ለዚህ ነው።

“የሰማይ አባት ሆይ ሱዛንን ላግባት?” ብዬ ስጠይቅም፤ የሰላም ስሜት ተሰማኝ። ግን በእውነተኛ ፍላጎት መጸለይ ተምሬ በነበረ ጊዜ ነበር፣ “የሰማይ አባት ፣ ሱዛንን እወዳለሁ እናም ማግባት እፈልጋለሁ። እኔ ጥሩ ባለቤት እና አባት ለመሆን በምችለው ለመጣር ቃል እገባለሁ”—እርምጃ በወሰድኩ እና ጥሩ ውሳኔዎቼን በምወስንበት ጊዜ በዚያን ጊዜ ጠንካራ መንፈሳዊ ማረጋገጫዎች መጡ።

አሁን የእኛ የጎንግ እና ሊንዚ FamilySearch የቤተሰብ ዛፎች፣ ታሪኮች፣ እና ፎቶግራፎች እኛ እንድንገኝ፣ እና በትውልድ የቃል ኪዳን አባል በመሆን እንድንገናኝ ይረዱናል።26 ለእኛ የተከበሩ ቅድመ አባቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፥

ምስል
አሊሻ ብሉኦር ባንገርተር

የአያት አያት አሊስ ብላወር ባንግተር፣ በአንድ ቀን ሶስት ሰዎች እንድታገባቸው የጠየቋት፣ በኋላም ቅቤ በምትሰራበት ጊዜ ሹራብ ለመስራት ትችል ዘንድ ባለቤቷን ቅቤት በወተት በምትሰራበት መሳሪያ ላይ በእግሯ የምትገፋበትን እንዲሰራላት የጠየቀችም።

ምስል
ሎየይ ክዩ ቸር

የሴት አያቱ ሎይ ኬ ቻር ልጆቹን በጀርባው እና የቤተሰቡ ጥቂት እቃዎችን በሃዋይ ቢግ አይላንድ ላይ ሲያቋርጡ በአህያ ላይ ያስቀመጠው ነበር። የቻር ቤተሰብ ትውልዶች ቃል ኪዳኖች እና መስዋዕትነቶች ዛሬ ቤተሰባችንን ይባርካሉ።

ምስል
ሜሪ አልስ ፖኦውል ሊንድሰይ

የሴት አያት ሜሪ አሊስ ፓውሌ ሊንድሲ ባለቤቷ እና የመጀመሪያ ልጇ ከጥቂት ቀናት ተለያይተው በድንገት ሲሞቱ ከአምስት ትናንሽ ልጆች ጋር ቀረች። ለ47 ዓመታት ያህል መበለት በመሆን፣ ግራም ቤተሰቧን ከአካባቢ መሪዎች እና አባሎች ባገኘችው ጽኑ ፍቅር ለማሳደግ ችላለች። በእነዚያ ብዙ ዓመታት፣ ግራም ጌታ የሚረዳት ከሆነ፣ እርሷ እንደማታጉረመርም ቃል ገባች። ጌታ ረዳት። እርሷም በምንም አላጉረመረመችም።

ወንድሞች እና እህቶች፣ በመንፈስ ቅዱስ ተመሰክሮላቸው፣ መልካም እና ዘላለማዊ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘላለማዊ አባታችን እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ እና በኃጢያት ክፍያው ላይ ያተኮረ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ስለኢየሱስ ክርስቶስ መመስከር የመፅሐፈ ሞርሞን የቃል ኪዳን አላማ ነው።27 በመሐላ እና ቃል ኪዳን በኩል፣ በዳግም የተመለሰው የእግዚአብሔር የክህነት ስልጣን በቃል ኪዳኑ ጋብቻ ፣ በትውልድ ትውልድ ቤተሰብ፣ እና በግል በረከቶችን ጨምሮ ሁሉንም የእግዚአብሔር ልጆች ለመባረክ የታሰበ ነው።

አዳኛችን እንዲህ አወጀ፤ “እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ጌታ ክርስቶስ ነኝ፤ አዎን፣ መጀመሪያውና መጨረሻው እናም የአለም ቤዛ የሆንኩት እኔ ነኝ።”28

ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምር ከእኛ ጋር ሆኖ፣ በቃል ኪዳን አባል በመሆን፣ እስከመጨረሻም እርሱ ከእኛ ጋር ነው። ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።

አትም