2010–2019 (እ.አ.አ)
መስቀላችንን ማንሳት
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

መስቀላችንን ማንሳት

የራስን መስቀል ማንሳት እና አዳኝን መከተል ማለት በአለማዊ ልምዶች ውስጥ አለመሳተፍ እና በጌታ ጎዳና በእምነት መቀጠል ማለት ነው።

በነዚህ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ከመሪዎቻችን ግሩም ትምህርቶችን አግኝተናል፡፡ እነዚህን በመንፈስ ምሪት የተጻፉ እና ወቅታዊ ትምህርቶችን በሕይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ የምንጥር ከሆነ ጌታ ፣ በጸጋው አማካኝነት እያንዳንዳችን መስቀላችንን እንድንሸከም እና ሸክማችንን ቀላል ለማድረግ እንደሚረዳን እመሰክራለሁ።1

በቄሳርያ ፊልጵስዩስ አቅራቢያ በነበረበት ጊዜ አዳኝ በኢየሩሳሌም ውስጥ በሽማግሌዎች ፣ በካህናት አለቆች እና በጸሐፍት እጅ ምን እንደሚሰቃይ ለደቀ መዛሙርቱ ገልጦላቸዋል፡፡ እርሱ ስለ ሞቱ እና ስለ አስደናቂው ትንሣኤው በቀጥታ አስተማራቸው፡፡2 በዚያን ጊዜ፣ ​​ደቀመዛሙቱ በምድር ላይ ያለውን የሱን መለኮታዊ ተልእኮ ሙሉ በሙሉ አልተረዱም፡፡ ጴጥሮስ ራሱ ፣ አዳኙ የተናገረውን ሲሰማ ወደ ጌታ ሄዶ “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም፡፡” ሲል ገሠጸው ፡፡3

ለስራው መሰጠቱ መገዛትን እና መከራን እንደሚጨምር ደቀመዛሙርቱ እንዲረዱ ለመርዳት አዳኝ በአፅንኦት ይህንን አወጀ፤

“በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።

ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል ፤ ገር ግን ለኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣ ሁሉ ያድናታል”

“ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?”4

በዚህ አዋጅ አማካኝነት እሱን ለመከተል ፈቃደኛ የሆኑ ሁሉ እራሳቸውን መካድ እና መሻታቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን መቆጣጠር፣ ሁሉንም መስዋትነት በማድረግ፣ አስፈላጊ ከሆነም እንኳን ሕይወትን እስከመስጠት፣ እሱ እንዳደረገው ሙሉ በሙሉ ለአባቱ ፈቃድ መገዛት አለባቸው።5 በእውነቱ ይህ ነፍስን ለማዳን የሚከፍለው ዋጋ ነው። ደቀመዛሙርቱ ለጌታ መስዋእትነት እና መሰጠት በእውነቱ ምን ማለት እንደሆነ በትክክል እንዲረዱ ለማድረግ ኢየሱስ የመስቀል ምሳሌን ሆን ብሎ እና ዘይቤያዊ በሆነ መንገድ ተጠቅሞበታል ፡፡ የመስቀል ምስል በደቀ መዛሙርቱ እና በሮማውያን ግዛት ነዋሪዎች ዘንድ የታወቀ ነበር ምክንያቱም ሮማውያን የሚሰቀሉ ሰዎችን በሕዝብ ፊት የራሳቸውን መስቀል እንዲሸከሙ እና ወደመሰቀያው ቦታ እንዲጓዙ ያስገድዷቸዋል፡፡6

ስለ እሱ የተጻፈውን ሁሉ ለመረዳት7 እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ምን እንደሚጠበቅባቸው አዕምሯቸው የተከፈተው ከትንሳኤ በኋላ ነበር።8

በተመሳሳይ ሁኔታ ፣ ወንድሞች እና እህቶች ፣ ሁላችንም መስቀሎቻችንን በእራሳችን ላይ ለመውሰድ እና እርሱን የመከተልን አስፈላጊነት በበለጠ ለመረዳት አእምሯችን እና ልባችንን መክፈት አለብን ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ሁላችንም መስቀሎቻችንን ማንሳት እና እሱን የመከተልን አስፈላጊነት ሙሉ በሙሉ መረዳት አለብን፡፡ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ እንደምንማረው፣ መስቀልን በራሳቸው ላይ ለመውሰድ የሚፈልጉ ሁሉ ከእየሱስ ፍቅር የተነሳ፣ ከሃጥያት ይርቃሉ እና የዓለምን ምኞት ሁሉ ይከዳሉ እና ትእዛዛቱን ይጠብቃሉ።9

ከእግዚአብሄር ፈቃድ ጋር የሚቃረንን ሁሉ ለማስወገድ እና የተጠየቅነውን መስዋትነት ለማቅረብ እና የእርሱን ትምህርቶች መከተል መወሰናችን፣ በችግርም ጊዜ ቢሆን ፣ በነፍሳችን ድክመት ወይም ማህበራዊ ግፊቶች እና ትምህርቶቹን በሚቃወሙ ዓለማዊ ፍልስፍናዎች ወቅት እንኳን ለመፅናት ይረዳናል ፡፡

ለምሳሌ፣ ዘላለማዊ ጓደኛን ያላገኙ እናም ብቸኝነትና ተስፋ መቁረጥ ለሚሰማቸው፣ ወይም በፍቺ ውስጥ አልፈው እንደተተዉ እና እንደተረሱ ለሚሰማቸው፣ መስቀላችንን እንድንሸከም የተሰጠን የአዳኝ ግብዣ እና እሱን መከተል ማለት በጌታ ጎዳና ላይ በእምነት መቀጠል፣ የክብርን ምሳሌ ጠብቆ መኖር፣ በመጨረሻም ከእግዚአብሔር ፍቅር እና ምህረት ላይ ያለንን ተስፋ የሚወስዱ ዓለማዊ ልምዶችን አለማድረግ እንደሆነ አረጋግጥላችኋለሁ።

ይህም መርህ በተመሳሳይ ጾታ ለሚሳቡ፣ እና ተስፋ የቆረጡ እና አቅመቢስነት ለሚሰማቸውም ሁሉ ይሆናል፡፡ ምናልባት በዚህም ምክንያት ከእናንተ መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ከእንግዲህ ለእናንተ እንዳልሆነ ይሰማችኋል፡፡ ጉዳዩ ይህ ከሆነ፣ በአባት እግዚአብሄር እና በደስታ እቅዱ ውስጥ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በቤዛዊ መስዋእትነቱ እና በትእዛዛታቸውም መኖር ሁል ጊዜ ትስፋ እንዳለ አረጋግጥላችኋለሁ። ትዕዛዛቱን ጠብቀን የምንጸና እና የማንንቀሳቀስ ከሆንን 10 እናም ሁልጊዜ መልካም ስራን የምንሰራ ከሆንን11ፍጹም በሆነው ጥበቡ፣ በኃይሉ፣ በፍትሑ እና በምሕረቱ ፣ ጌታ የእርሱ እንድንሆን ያትመናል እና ከእርሱም ዘንድ መተን የዘላለም መዳንን እንድንቀበል ያደርገናል።

ከባድ ኃጢአት ለሠሩ ሰዎች፣ ይህንኑ ተመሳሳይ ግብዣ መቀበል ማለት ሌሎች ነገሮችን በመጨመር ፣ በእግዚአብሔር ፊት እራስን ዝቅ ማድረግ፣ አግባብነት ያላቸውን የቤተክርስቲያን መሪዎች ማማከር እና ንስሀ መግባት እና ኃጢያትን መተው ማለት ነው፡፡ ይህ ሂደት፣ በአደንዛዥ ዕፅ፣ አልኮሆል እና የራቁት ምስል ጨምሮ አሰልቺ ከሆኑት ሱሶች ጋር የሚዋጉትን ​​ሁሉ ይባርካል። እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ በመጨረሻ ከጥፋተኝነት ስሜት፣ ከሐዘን፣ እና ከመንፈሳዊ እና አካላዊ ባርነት ነፃ ወደሚያወጣው አዳኝ ያመጣል። በተጨማሪም፣ የቤተሰብ፣ የጓደኞችን፣ እና ብቃት ያላቸውን የህክምና እና የምክር ባለሙያዎችን ድጋፍ ለማግኘት ትፈልጉ ይሆናል፡፡

እባካችሁ ከተከታታይ ሽንፈት በኋላ ተስፋ አትቁረጡ እና እራሳችሁን ኃጢያቶችን መተው የማትችሉ እና ሱሰኝነትን ለማሸነፍ እንደማትችሉ አድርጋችሁ አታስቡ፡፡ መትጋትን አቁማችሁ ከዛም በድክመትና በሃጥያት መቀጠል አይኖርባችሁም። በአዳኝ እንዳስተማረው ውስጣዊውን ዕቃ ለማንፃት ፍላጎት በማሳየት ሁል ጊዜ የሚቻላችሁን ለማድረግ ጣሩ12። አንዳንድ ጊዜ ለተወሰኑ ችግሮች መፍትሄዎች ከወራት እና ወራት ተከታታይ ጥረት በኋላ ይመጣሉ። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኘው” እኛ ሁሉንም ካደረግን በኋላ፣ በጸጋው እንድናለን”13 የሚለው ቃል ኪዳን ለዚህም ሁኔታ ተግባራዊ የሚሆን ነው። እባካችሁ አስታውሱ፣ የአዳኝ የፀጋ ስጦታ የግድ ማድረግ የምንችላቸውን ነገሮች በሙሉ ካደረግን በኋላ ብቻ አይደለም የሚመጣው። የራሳችንን ጥረት ከማድረጋችን በፊት፣ በሂደት ላይ እያለን እና ከጥራታችን በኋላ የእሱን ጸጋ ልንቀበል እንችላለን።14

ችግሮቭን ለማሸነፍ በምናደርገው ጥረት ፣ እግዚአብሔር ለመፈወስ እና በተአምራት መስራት በእምነት ስጦታዎች እንደሚባርከን እመሰክራለሁ ፡፡15 እኛ ለራሳችን ማድረግ የማንችላቸውን ለእኛ ያደርግልናል፡፡

በተጨማሪም፣ መራራነትን፣ ንዴትን፣ መቀየምን ወይም የማይገባ በሚመስል የሃዘን ሰንሰለት ታስረን ያለን ሰዎች የራሳችንን መስቀልን በማንሳት አዳኙን መከተል ማለት እነዚህን ስሜቶች ወደጎን አድርገን ወደ ጌታ እንዲረዳን መዞር ማለት ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ አሉታዊ ስሜቶችን የምንይዝ ከሆንን፣ የጌታ መንፈስ ተጽዕኖ በሕይወታችን ሳይሆን ልንኖር እንችላለን። ለሌሎች ሰዎች ንስሃ መግባት አንችልም፣ ነገር ግን ጉዳት ባደረሱብን ሰዎች ስር በእስራት ላለመያዝ ይቅርታ ማለት እንችላለን16

ጠጣር ልቦቻችንን በአዲስ ልብ ለመተካት እንዲረዳን አዳኛችንን በመጋበዝ ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማምለጫ መንገድ እንዳለ ቅዱሳት መጻህፍት ያስተምሩናል፡፡17 ይህ እንዲሆን እኛ በድክመታችን፣ በፊቱ ራሳችንን ዝቅ አድርገን፣ 18 እናም የእርሱን እርዳታ እና ይቅርታን ለምነን፣19 በተለይም እሁድ በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባን በምንካፈሉበት ጊዜ ወደ ጌታ መምጣት ያስፈልገናል። የእርሱን ይቅርታ እና የእሱን እርዳታ ለመፈለግ ልንመርጥ እንችላለን፣ እናም ቁስላችን መፈወስ እንዲጀምር የጎዱንን ይቅር በማለት አስፈላጊ እና አስቸጋሪ የሆነውን እርምጃ እንውሰድ፡፡ ይህንን በምታደርጉበት ጊዜ ከጌታ ጋር አብሮ ከመሆን የሚመጣ የአምሮ ሰላም ሌሊታችሁ በእፎይታ እንደሚሞላ ቃል እገባላችኋለሁ፡፡

በ 1839(እ.ኤ.አ) በሊበርቲ እስርቤት ውስጥ እያለ፣ ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ በጣም ተግባራዊ የሚሆኑትን ትንቢቶች ለቤተክርስቲያኗ አባላት ደብዳቤ ጻፈ ፡፡ እንዲህም ብሎ ጻፈ፣ “ዙፋናት ቢሆኑ እና ጌትነት እና አለቅነት እና ሥልጣናት ሁሉ ይገለጣሉ እና ለኢየሱስ ክርስቶስም ወንጌል በብርታት ለጸኑት ሁሉ ይሰጧቸዋል።”20 ስለዚህ ፣ በገባው ቃል የሚታመኑ እና እስከመጨረሻው በመፅናት የአዳኝን ስም የሚይዙ ይድናሉ።21እናም ማለቂያ በሌለው ደስታ በእግዚአብሔር ዘንድ መኖር ይችላሉ ፡፡22

ወንድሞች እና እህቶች ፣ ሁላችንም በሕይወታችን ውስጥ ሀዘንን ፣ እረዳት የሌለን ፣ ተስፋ የመቁረጥ እና አልፎ አልፎም ድክመትን እንዲሰሙን የሚያደርጉ በሕይወታችን ውስጥ አስከፊ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል ፡፡ ከነዚህ ስሜቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ጌታን እንድንጠይቅ ያደርጉናል፣ “ለምን እንደዚህ ያሉ ሁኔታዎች እያጋጠሙኝ ያለሁት?” ወይም “የጠበኩት ነገሮች ያልተሟሉት ለምንድነው? መስቀሌን ተሸክሜ አዳኝን ለመከተል በኃይሌ ሁሉ እያደረግሁ ነው!”

ውድ ጓደኞቼ ፣ መስቀልን በራሳችን ላይ ማድረጋችን ትህትና እና በእግዚአብሔር እና በእርሱ ማለቂያ በሌለው ጥበቡ መታመንን እንደሚጨምር ማስታወስ አለብን። እርሱ እያንዳንዳችንን እና ፍላጎታችንን እንደሚያውቅ መገንዘብ አለብን። ደግሞም የጌታ ሰዓት ከኛ የተለየ መሆኑን መቀበል ያስፈልጋል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በረከትን እንሻለን እናም ጌታ እንዲፈጽም የጊዜ ገደብ እንመድባለን ፡፡ ለፍላጎታችን መልስ ለመስጠት የጊዜ ገደብ በእሱ ላይ በማስቀመጥ ለእርሱ ታማኝነታችንን ማረጋገጥ አንችልም። ይህንን ስናደርግ፣ ​​ላማናዊው ሳሙኤል የተናገራቸው ቃላት ተፈፃሚ የሚሆኑበት ጊዜ አልሆነም በማለት፣ ባመኑት መካከል ግራ መጋባት በመፍጠር በወንድሞቻቸው ላይ ሲያፌዙ የነበሩትን ተጠራጣሪ ኔፋውያንን እንመስላለን ፡፡23 ረጋ ብለን እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን ፣ ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ እና እያንዳንዳችንን እንደሚያውቅ በማወቅ በጌታ መታመን አለብን።24

ሽማግሌ ሶአሬስ እህት ካላማሲን ሲያገለግሉ

በቅርብ ጊዜ፣ ባሏ የሞተባት እህት ፍራንካ ካላማሲ ለተባለች፣ በአሰቃቂ በሽታ እየታገለች ላለች የማገልገል እድል አጋጥሞኝ ነበር። እህት ካልማሳ በዳግም በተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስትቀላቀል ከቤተሰቧ አባላት የመጀመሪያዋ ነበረችው። ባለቤቷ ፈጽሞ የተጠመቀ ባይሆንም ፣ ከወንጌል ሚስዮናውያን ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ ነበር እናም ብዙውን ጊዜ በቤተክርስቲያን ስብሰባዎች ላይ ይገኝ ነበር። እነዚህ ሁኔታዎች ቢኖሯትም እህት ካላማሲ ታማኝ ሆና ቀጥላ አራት ልጆን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አሳድጋለች። የባለቤቷን ማለፍ ተከትሎ ከአንድ ዓመት በኋላ፣ እህት ካላማሲ ልጆቿን ወደ ቤተመቅደስ ወሰደች እና በቅዱስ ስነስርዓቶች ተሳተፉ እና እንደ ቤተሰብ አብረው ታተሙ። ከእነዚህ ስነስርዓቶች ጋር የተያያዙት ተስፋዎች በህይወቷ ለመቀጠል የረዷትን ብዙ ተስፋን ፣ ደስታን እና ሁሴትን አምጥተውላታል፡፡

የካላማሲ ቤተሰብ በቤተመቅደስ ውስጥእህት ጆሲቪኒ በቤተመቅደስ

የበሽታው የመጀመሪያ ምልክቶች መታየት ሲጀምሩ ኤጲስ ቆጶስዋ ቡራኬን ሰጣት። በዚያን ጊዜ ለኤጲስ ቆጶሱ፣ ለመፈወስ እና እምነቷን እስከ መጨረሻው ለመጽናት እምነቷን በመግለጽ የጌታን ፈቃድ ለመቀበል ዝግጁ መሆኗን ነገረቻቸው።

በጎበኘኋት ጊዜ የእህት ካላማሲን እጅ በመያዝ እና ዓይኗን እያየሁ ከእግዚአብሄር እቅድ ላይ ያላት እምነት እና በእሷ ፍቅር እና ዕቅዱ ላይ ፍጹም የሆነ መተማመን እንዳላት በሚያሳይ ሁኔታ መላካዊ አንፀባራቂነትን አየሁ፡፡25 እያጋጠሟት ያሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ቢኖሯትም እንኳን መስቀሉን በማንሳት እስከ መጨረሻው በእምነቱ ለመጽናት ቁርጥ አቋም እንዳላት ተሰማኝ። የዚች እህት ሕይወት፣ የክርስቶስ ምስክርነት ፣ ለእምነቷ እና ለእርሱ ያላት ታማኝነት መግለጫ ነው።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ መስቀላችንን መሸከም እና አዳኝን መከተል የእርሱን ምሳሌ ለመከተል እና እንደ እርሱ ለመሆን መጣር እንደሚያስፈልግ እመሰክራለሁ26 የተፈጥሮን ሰው ፍላጎት በመካድ እና በመናቅ እንዲሁም ጌታን በመጠባበቅ የህይወት ሁኔታዎችን በትዕግሥት በመጋፈጥ ነው። ዘማሪው እንደጻፈው፤

“እግዚአብሄርን ተስፋ አድርግ፣ በርታ፣ ልብህም ይጽና፣ ጌታንም ተጠባበቅ።”27

“እርሱ ረዳታችን እና ጋሻችን ነው ፡፡”28

የጌታችንን ፈለግ በመከተል እና የህይወታችን የመጨረሻ ፈዋሽ የሆነውን እርሱን በመጠበቅ ለነፍሳችን ዕረፍት እንደሚሰጠን እና ሸክማችን ቀላል እና እንደሚያደርግልን እመሰክራለሁ ፡፡29 ስለእነዚህ ነገሮች የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም ነው፣ አሜን።