2010–2019 (እ.አ.አ)
ጠላትን ለማሸነፍ የሚያስችል ኃይል
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ጠላትን ለማሸነፍ የሚያስችል ኃይል

ሰላምን እንዴት እናገኛለን, ማን እንደሆንን እንዴት እናስታውሳለን፣ እናም ሦስቱን የጠላት ዘዴዎች እንዴት እንቋቋማለን?

ወንድሞች እና እህቶች፣ የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይና የቅዱሱ ቤተመቅደስ በረከቶችን የምትደሰቱበት እንዲሆን፣ እና ለሌሎችም እንዲሁ እንዲሆን ለመርዳት፣ ለምታደርጉት ሁሉ አመሰግናችኋለሁ። ለመልካምነታችሁ አመሰግናለሁ። አስደናቂ ናችሁ፣ ውቦች ናችሁ።

የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ሙሉ በሙሉ ወደመረዳት ስንመጣ የምናገኘውን የመንፈስ ቅዱስ ማረጋገጫ ተጽእኖ እንናውቅ ዘንድ ጸሎቴ ነው። “ቤተሰብ፥ ለአለም የተላለፈ አዋጅ” እንደሚለው፥ “የሰው ልጆች በሙሉ --ወንድና ሴቶች --በእግዚአብሔር አምሳል ነው የተፈጠሩት። እያንዳንዱም በሰማይ ወላጆች የተወደዱ የመንፈስ ሴት እና ወንድ ልጆች ናቸው፣ እናም ይህ ስለሆነም፣ እያንዳንዱ መለኮታዊ ተፈጥሮ እና ፍጻሜም አላቸው።”1 እኛ “የታላቁን የኋለኛው ቀን ሥራ በመመሥረት ለመሳተፍ በመጨረሻው ዘመን እንድንመጣ ተመርጠን የነበርን መንፈሶች ነን።”2 ፕሬዘደንት ራስል ኤም. ኔልሰን እንዳወጁት፥ “በነዚህ የኋለኛ ቀናት የመጨረሻ ክፍል ለሚያጋጥሟችሁ እና ለማንኛውም ነገሮች እንድትዘጋጁ በመንፈስ ዓለም ውስጥ ተምራችሁ ነበር።( ት &ቃ 138:56 ይመልከቱ፡፡) ያም ትምህርት ከእናንተ ጋር ይጸናል።”3

እናንተ የተመረጣችሁ የእግዚአብሄር ወንዶች እና ሴት ልጆች ናችሁ። ጠላትን ለማሸነፍ የሚያስችል ኃይል አላችሁ። ጠላት ግን ማን እንደሆናችሁ ያውቃል። ስለ መለኮታዊ ውርሳችሁ ያውቃል እናም ሶስት ዘዴዎችን በመጠቀም ምድራዊ እና ሰማያዊ ችሎታዎቻችሁን ሊገድብ ይፈልጋል።

  • ማታለል

  • ሀሳብ መስረቅ

  • ተስፋ ማስቆረጥ

ማታለል

ጠላት በሙሴ ዘመን ማታለልን ተጠቅሟል። ጌታ ለሙሴ እንዲህ አለው። …

እናም እነሆ፣ አንተ ልጄ ነህ፤

ለአንተ አንድ ሥራ አለኝ ፣… እናም አንተ በአንድያው ልጄ ምሳሌ ነህ።”4

ከዚህ አስደናቂ ራዕይ ብዙም ሳይቆይ ሰይጣን ሙሴን ለማታለል ሞከረ። የተጠቀማቸው ቃላት የሚያስደንቁ ነበሩ፥ “የሰው ልጅ ሙሴ ሆይ ፣ ስገድልኝ።”5 ማታለያው ሰይጣንን እንዲያመልክ በተጋበዘው ጥሪ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ማታለያውም ሙሴን የሰው ልጅ ብሎ የገለጸበት መንገድ ነበር። አስታውሱ፣ ጌታ ሙሴን በአንድያ ልጅ ምሳሌ የተፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ነግሮት ነበር።

ጠላት ሙሴን ለማታለል ሙከራ ከማድረግ አልታከተም ነበር፣ ነገር ግን ሙሴ “ሰይጣን፣ ከእኔ ራቅ፤ የክብር አምላክ ለሆነው ለዚህ አንድ አምላክ ብቻ እሰግዳለሁ” ሲል ተቃወመ።6 ሙሴ ማን እንደሆነ አስታወሰ—የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ።

ጌታ ለሙሴ የተናገረው ቃል በአናንተም ሆነ በእኔ ላይ ይሠራል። የተፈጠርነው በእግዚአብሔር አምሳል ነው፣ እርሱም እኛ የምንሠራው ሥራ አለው። ጠላት ማንነታችንን እንድንረሳው በማድረግ ለማታለል ይሞክራል። እኛ ማን እንደሆንን ካልገባን፣ ማን ለመሆን እንደምንችል ለመለየት ያስቸግራል።

ሀሳብ መስረቅ

በተጨማሪም ጠላት ሃሳባችንን በመስረቅ ከክርስቶስና ከቃል ኪዳኑ መንገድ ሊያርቀን ይሞክራል። ሽማግሌ ሮናልድ ኤ. ራዝባንድ የሚቀጥለውን አካፍለዋል፥ “የጠላት እቅድ ከመንፈሳዊ ምስክርነት የኛን ሀሳብ ሊያርቅ ነው፣ የጌታ መሻት ግን እኛን ማሳወቅ እና በእሱ ስራ ውስጥ እኛን ማሳተፍ ነው።”7

በዘመናችን ትዊተርን ፣ ፌስቡክን ፣ ኢንስታግራምን፣ የምናባዊ እውነታ ጨዋታዎችን እና ሌሎችንም ጨምሮ ብዙ ሀሳብን የሚሰርቁ ነገሮች አሉ። እነዚህ የቴክኖሎጂ እድገቶች አስገራሚ ናቸው፣ ነገር ግን ካልተጠነቀቅን መለኮታዊ ችሎታችንን እንዳናሟላ ሀሳባችንን ለሰርቁ ይችላሉ። እነሱን በተገቢው መልክ መጠቀም ፤ በሁለቱም የመጋረጃ ወገን ላይ ያለውን የተበታተነውን እስራኤል ለመሰብሰብ ስንሻ የሰማይ ኃይልን ሊያመጣ እና ተዓምራቶችን እንድንመሰክር ያስችለናል።

በቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን ረገድ ጥንቃቄ እናድርግ።8 ለሁለተኛ ምጽአቱ ስንዘጋጅ ቴክኖሎጂው ወደ አዳኝ እንድንቀርብ እና የእርሱን ስራ እንድንፈጽም የሚያስችልበትን መንገዶች በቀጣይነት እንፈልግ።

ተስፋ ማስቆረጥ

በመጨረሻም፣ ጠላት ተስፋ እንድንቆርጥ ይፈልጋል። እራሳችንን ከሌሎች ጋር ስናነፃፅር ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን ወይም ራሳችን የምንጠብቀውን ጨምሮ እንደሚጠበቀው እየኖርን እንዳልሆነ ሲሰማን ተስፋ ልንቆርጥ እንችላለን።

የዶክትሬት ፕሮግራሜን ስጀምር፣ ተስፋ ቆርጬ ነበር። ፕሮግራሙ በዚያ ዓመት አራት ተማሪዎችን ብቻ ነበር የሚቀበለው፣ እና ሌሎቹ ተማሪዎች ደግሞ በጣም ጎበዝ ነበሩ። ከፍተኛ የፈተና ውጤቶች እና በከፍተኛ የሥራ አመራር መደቦች የበለጠ የስራ ልምዶች የነበራቸው ነበሩ፣ እናም በችሎታቸው በራስ መተማመንን ያሳዩ ነበር። በፕሮግራሙ ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንቶቼ በኋላ፣ የተስፋ መቁረጥ እና የጥርጣሬ ስሜት ይይዘኝ ጀመር፤ ሊቆጣጠረኝ እንኳን ደርሶ ነበር።

ይህንን የአራት-ዓመት መርሃ-ግብር የምፈጽም ከሆንኩኝ፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ዘመን አጋማሽ መፅሐፈ ሞርሞንን አንብቤ መጨረስ እንዳለብኝ ወሰንኩ። በየቀኑ ሳነበው፣ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር እንደሚያስተምረኝ እና ሁሉንም ወደ ትውስታዬ እንደሚያመጣ አዳኝ የሰጠውን መግለጫ ተረዳሁ።9 የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንኩ በድጋሚ አረጋግጦልኛል፣ እራሴን ከሌሎቹ ጋር እንዳላነፃፅር አስታውሶኛል፣ እንዲሁም ለስኬት በመለኮታዊ ሚናዬ ላይ እምነት እንድጥል አድርጎኛል።10

ውድ ጓደኞቼ፣ ማንም ደስታችሁን እንዲሰርቅባችሁ አትፍቀዱ። ራሳችሁን ከሌሎች ጋር አታነጻጽሩ። የአዳኙን የፍቅር ቃላት አስታውሱ፥ “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።””11

ታዲያ ያንን እንዴት ማድረግ እንችላለን? ይህንን ሰላም እንዴት እናገኘዋለን, ማን እንደሆንን እንዴት እናስታውሳለን፣ እናም ሦስቱን የጠላት ዘዴዎች እንዴት እንቋቋማለን?

በመጀመሪያ ፣ የመጀመሪያው እና ታላቅ ትእዛዝ እግዚአብሔርን በልባችን፣ በኃይላችን፣ በአእምሯችን እና ጥንካሬያችን መውደድ መሆኑን አስታውሱ።12 የምንሰራው ሁሉ ለእርሱ እና ለልጁ ባለን ፍቅር መነሳሳት አለበት። ለእነሱ ያለንን ፍቅር ስናዳብር፣ ትእዛዛቶቻችውን ስንጥብቅ እራሳችንን የመውደድ እና ሌሎችን የመውደድ ችሎታችን ይጨምራል። አዳኝ እንደሚመለከታቸው ፤ እንደ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ስለምንመለከታቸው፣ ቤተሰብን፣ ጓደኞችን እና ጎረቤቶችን ማገልገል እንጀምራለን።13

ሁለተኛ፣ በየእለቱ፣ በየእለቱ፣ በየእለቱ ወደ አብ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጸልዩ።14 የእግዚአብሔር ፍቅር የሚሰማን እና ለእርሱ ፍቅር እንዳለን ለማሳየት የምንችለው በጸሎት አማካይነት ነው። በጸሎታችን ምስጋናችንን እንገልፃለን እንዲሁም ፈቃዳችንን ለእግዚአብሔር ለማስገዛት ጥንካሬ እና ድፍረትን እንዲሁም በሁሉም ነገር መመሪያ እንዲሰጠን እና አቅጣጫ እንዲቀመጥልን እንጠይቃለን።

“በዚህ ፍቅር ትሞሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆኑ ዘንድ፣ … እርሱ በሚመጣበትም ጊዜ እንደ እርሱ እንሆን ዘንድ፣ … በሙሉ በልባችሁ ሀይል ወደ አብ ፀልዩ”15 ብዬ አበረታታችኋለሁ።

ሦስተኛ፣ መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ ፣ በየቀኑ ፣ በየቀኑ አንብቡ እና አጥኑ።16 በአዕምሮዬ ውስጥ ጥያቄ አሰቀምጬ ሳነብ የመፅሐፈ ሞርሞን ጥናቶቼ በተሻለ መልኩ ይሄዳሉ። ከጥያቄ ጋር ስናነብ፣ ራዕይን ለመቀበል እንችላለን እንዲሁም ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እንዲህ ሲያውጅ እውነቱን እንደተናገረ መገንዘብ እንችላለን፥ “መፅሐፈ ሞርሞን በምድር ካሉ መፅሐፍት በሙሉ የበለጠ ትክክል [ነው]፣ …እናም ከየትኛውም መፅሐፍ በበለጠ በውስጡ ባሉት ሃሳቦች በመኖር ወንዶች እና ሴቶች ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡ ይችላሉ።”17 መፅሐፈ ሞርሞን የክርስቶስን ቃላት ይዟል እናም እኛ ማን እንደሆንን እንድናስታውስ ይረዳናል።

በመጨረሻም፣ በየሳምንቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየሳምንቱ ቅዱስ ቁርባንን ተካፈሉ። ቅዱስ ቁርባንን ጨምሮ፣ በቃል ኪዳን እና በክህነት ስርዓቶች በኩል ነው አምላካዊ ሀይል በሕይወታችን ውስጥ የሚገለጸው።18 ሽማግሌ ዴቪድ ኤ. ቤድናር እንዳስተማሩት፥ “የቅዱስ ቁርባን ስነስርዓት ቅዱስ እና ከልብ ንሰሀ ለመግባት እና መንፈሳዊ እድሳት ለማድረግ ተደጋጋሚ ግብዣ ነው። ቅዱስ ቁርባንን የመካፈል ድርጊት ብቻ፣ በራሱ የሀጢያት ስርየትን አያመጣም። ነገር ግን በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ በቅዱስ ቁርባን ስርዓት ላይ በጥንቃቄ ስንዘጋጅና ስንካፈል፣ የተገባልን ቃልኪዳን የጌታ መንፈስ ሁሌም ከእኛ ጋር ሊኖር እንደሚችል ነው።”19

በቅዱስ ቁርባን ስንካፈል፣ ጌቴሴማኒ ተብሎ በተጠራው በተቀደሰው የአትክልት ስፍራ የነበረውን የኢየሱስ ስቃይ እና የመስቀል ላይ መስዋዕቱን እናስታውሳለን። ቤዛችንን፤ አንድያ ልጁን በመላኩ ለአብ ምስጋናችንን እንገልጸለን፣ እናም ትእዛዛቱን ለመጠበቅ እና ሁል ጊዜም እሱን ለማስታወስ ፈቃደኛ መሆናችንን እናሳያለን።20 ከቅዱስ ቁርባን ጋር የተገናኘ መንፈሳዊ የእውቀት ብርሃን አለግላዊ ነው፣ ኃያል ነው፣ እና አስፈላጊ ነው።

ጓደኞቼ፣ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን ለመውደድ በምንጥርበት ጊዜ፣ ​​በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስንፀልይ፣ መፅሐፈ ሞርሞንን ስናጠና፣ እና በጸሎት ቅዱስ ቁርባንን ስንካፈል፣ በጌታ ጥንካሬ የጠላትን የማታለል ልምምዶችን ለማሸነፍ ፣ መለኮታዊ አቅማችንን የሚገድቡ ሀሳብ ሰራቂዎችን ለመቀነስ፣ እና የሰማይ አባታችን እና የልጁ ፍቅርን የመሰማት አቅማችንን የሚቀንስ ተስፋ መቁረጥን ለመቋቋም ችሎታ ይኖረናል። እንደ እግዚአብሔር ወንድ እና ሴት ልጆች ማን እንደሆንን በሙሉ ለመረዳት እንችላለን።

ወንድሞቸ እና እሀቶቸ ፍቅሬን አጋራችኋለሁ እንዲሁም የሰማይ አባት ህያው እንደሆነ እና ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ምስክርነቴን አውጃለሁ። እወዳቸዋለው። የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በምድር የተመሰረተች የእግዚአብሔር መንግስት ነች፡፡ ለመሲህ ዳግም ምፅዓት አለምን ለማዘጋጀት መለኮታዊ የስራ ምድብ ተሰጥቶናል። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።