የተወደዳችሁ ሴት ልጆች
በወጣት ሴቶች ውስጥ ዋንኛ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እናንተ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የማይናጋ እምነት እንዲኖራችሁ ነው።
ውድ እህቶቼ፣ ከእናንተ ጋር መሆን አስደሳች ነው፡፡ እኛ ነፍስን የሚዘረጋ እና የሚያነቃቃ ስሜትን የሚገልጽ ራእይ ምስከር እየሆንን ነወ፡፡
ስንጀምር፣ ከአንዳንድ ጓደኞች ጋር ላስተዋውቃችሁ እወዳለሁ፤ እነሱም በተሰጥኦ፣ በባህሎች እና በግላዊ እና በቤተሰብ ሁኔታዎች ልዩ የሆኑ ወጣት ሴት ልጆች ናቸው። እያንዳንዳቸው ልክ እንደ ሁላችሁም፤ ልቤን ማርከውታል።
በመጀመርያ ቤላን ተዋወቁአት። በአይስላንድ ውስጥ በሚገኘው ቅርንጫፏ እንደ ብቸኛ ወጣት ሴት ጠንክራ ቆማለች።
መፅሐፈ ሞርሞንን በየቀኑ ለማጥናት የወሰነችውን፤ ታማኝ የሆነችው አፍሪካዊት ጆሴፊንን ተዋወቁአት። ከዚ ቀላል ታማኝ ድርጊት የሚመጣውን ሀይል እና በረከት እያገኘች ነው።
እናም በመጨረሻ፤ ከስድስት አመታት ከካንሰር ፍልሚያ በኋላ ህይወቷ ያለፈውን ልዪ የሆነችውን ወጣት ሴት አሽትይንን ተዋወቁአት። የሷ የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ምስክርነት እስካሁን በልቤ ውስጥ ያስተጋባል።
እናንተሁላችሁምግሩም ወጣት ሴቶች ናችሁ። እናንተ፣ እያንዳንዳችሁ በየራሳችሁ ስጦታ እና ልምድ ልዩ ናችሁ፣ ሆኖም በሁሉም አስፈላጊ እና ዘላለማዊ መንገድ እኩል ናችሁ።
እናንተ ቃል በቃል የሰማያዊ ወላጆች መንፈሳዊ ልጆች ናችሁ። እናም ከነሱ ፍቅር እና ከአዳኛችሁ ፍቅር ምንም ነገር ሊለያችሁ አይችልም።1 ወደ እሱ እየቀረባችሁ በመጣችሁ ቁጥር፤ ትንሿን የህጻን ልጅ እርምጃ ወደፊት በመውሰድ እንኳን እንደ የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ደቀመዝሙር ወደ ነፍሳችው ውስጥ የሚሰፍነውን የአዳኙን ዘላቂውን ሰላም ታገኛላችው።
ፕሬዘዳንት ራስል ኤም ንኤልሰን የናንተን አንዳንድ “ቅዱሳዊ ግላዊ ችሎታዎችን” 2ሊያዳብር የሚችል እና የጽድቅ ምሳሌነታችሁን ሊጨምር የሚችል የሚያነሳሳ ማብራርያ እንዳቀርብ ጠይቀውኛልው። ዛሬ ምሽት አራት የሚስተካከሉ ክፍሎችን አሳውቃለው።
የወጣት ሴቶች ጭብጠ ሃሳብ
በመጀመርያ በወጣት ሴቶች ልብ ውስጥ የምናደርጋቸው ነገር ሁሉ እናንተ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የማይናጋ እምነት እና 3እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች ስለመለኮታዊ ማንነታችሁ እርግጠኛ እውቀት እንዲኖራችሁ ነው።
ዛሬ ምሽት፣ ለወጣት ሴቶች ጭብጠ ሃሳብ ክለሳ መግለፅ እወዳለው፡፡ እነዚህን አዲስ ጭብጠ ሃሳብ ስናገር መንፈስ ቅዱስ የነዚህን ቃላት እውነተኝነት ሲመሰክር እንዲሰማችሁ እፀልያለሁ።
እኔ መለኮታዊ ፍጥረት እና ዘላለማዊ እጣፋንታ ያለኝ የተወደድኩ የሰማያዊ ወላጆች ሴት ልጅ ነኝ፡፡ 4 5
እንደ የእየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙርነት6እንደ እሱ ለመሆን እጥራለሁ።7 ግላዊ ራእይ እሻለሁ ።በሱም መሰረት እተገብራለሁ። 8 እናም በተቀደሰ ስሙ ለሌሎች አስተምራለሁ፡፡9
በሁሉም ጊዜ እና በሁሉም ነገር እና በሁሉም ቦታ የእግዚአብሄር ምስክር ሆኜ እቆማለሁ፡፡ 10
ከፍ ለመደረግ ብቁ ለመሆን ስጥር፤11 ለንስሀ ስጦታ ከፍተኛ ቦታ እሰጣለው። 12እናም በየቀኑ ለመሻሻል እፈልጋለሁ፡፡ 13 በእምነት 14ቤቴን እና ቤተሰቤን አጠነክራለሁ፡፡15የተቀደሱ ቃልኪዳኖችን እገባለሁ እናም እጠብቃለሁ ፤16እናም የቤተመቅደስ ትእዛዛትን እና በረከቶችን እቀበላለሁ፡፡1718
“እኛ” ከሚለው ወደ “እኔ” የተለወጠውን ልብ ብላችሁ አጢኑ። እነዚህ እውነታዎች በግል እናንተን ይመለከታል፡፡ እናንተ የተወደዳችሁ የሰማይ ወላጆች ሴት ልጆች ናችሁ። እናንተ ቃል ኪዳን ያላችሁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ናችሁ። እነዚህን ቃላቶች እንድታጠኑ እና እንድታሰላስሉ እጋብዛችኋለሁ። ይህን ስታደርጉ የእውነተኝነታቸውን ምስክርነት እንደምታገኙ አውቃለው፡፡ ይህን እውነታ መረዳት ፈተናዎቻችሁን የምትጋፈጡበትን መንገድ ይለውጠዋል፡፡ ማንነታችሁን እና አላማችሁን ማወቅ ፍላጎታችሁን ከአዳኙ ጋር ለማሰለፍ ይረዳችሀል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስን ስትከተሉ ሰላም እና ምሪት ከናንተ ጋር ይሆናል፡፡
የወጣት ሴቶች ክፍሎች
ሁተኛው ማስተካከያ የወጣት ሴቶች ክፍሎች ላይ ተጽእኖ ያመጣል፡፡ ሽማግሌ ኔል ኤ. ማክስዌል እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፣ “ብዙ ጊዜ ሰዎች በጣም የሚያስፈልገቸው ነገር የተፈላጊነት ስሜት ባለው በተቀደሰ ቦታ ውስጥ ከህይወት ማእበል መጠለል ነው፡፡” 19 ክፍላችን ከማእበሎቹ መሸሸግያ ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተፈላጊነት ስሜት ያለው ቦታ መሆን አለባቸው፡፡ የተሻለ አንድነት በመገንባት ጥረት ውስጥ ጓደኝነትን ማጠንከር፣ ፣በወጣት ሴቶች ክፍል የተፈላጊነት ስሜትን ማዳበር፣ ለክፍሉ መዋቅር አንዳንድ ማስተካከያዎችን እያደረግን ነው፡፡
ከ100 ዓመታት በላይ ወጣት ሴቶች በሶስት ክፍል ተከፍለዋል፡፡ ወዲያዉኑ በመጀመር፤ የወጣት ሴት ልጆች መሪዎችን እና የቅርጫፍ ፕሬዘዳንቶችን በጸሎት የእያንዳንዷን ወጣት ሴት ፍላጎትን በማሰብ እና በእድሜ የአውራጃውን የተወሰነ ሁኔታ ባገናዘበ መንገድ እንዲያዋቅሯቸው እንጋብዛለን፡፡ ይህ ምን ሊመስል እንደሚችል የሚያሳዩ አንዳንድ ምሳሌዎች እነዚህ ናቸው፡፡
-
ጥቂት ወጣት ሴቶች ካሏችሁ፤ ሁሉም ሰው አንድ ላይ የሚሰበሰብበት አንድ የወጣት ሴቶች ክፍል ይኖራችዋል፡፡
-
ምንአልባት እድሜያቸው 12 አመት የሆኑ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ወጣት ሴቶች ቡድን እና እድሜያቸው የሚበልጥ ትንሽ የወጣት ሴቶች ቡድን ሊኖራችሁ ይችላል፡፡ ሁለት ክፍል እንዲኖራችሁ ትወስኑ ይሆናል ፤ የ 12 አመት ወጣት ሴቶች እና ከ13-18 አመት ወጣት ሴቶች
-
ወይንም 60 ወጣት ሴቶችን የሚካፈሉበት ብዙ አውራጃ ካላችሁ፤ ስድስት ክፍሎች ሊኖራችሁ ይችላል፣ ለአንድ እድሜ አንድ ክፍል፤ በየእድሜያቸው አዋቅሯቸው፡፡
ነገር ግን ክፍላችሁ በየትኛውም መንገድ ቢዋቀር፣ እናንተ ወጣት ሴቶች አንድነትን ለመገንባት ወሳኝ ናችሁ፡፡ በዙርያችሁ ላሉት ብርሃን ሁኑ፡፡ ከሌሎች ለመቀበል ተስፋ የምታደርጉትን የፍቅር እና የእንክብካቤ ምንጭ ሁኑ፡፡ በልባችሁ ውስጥ ባለው ጸሎት፤ ወደ ሰዎች መድረሳችሁንና እና ለጥሩ ነገር ሀይል መሆናችሁን ቀጥሉ፡፡ ይህን ስታደርጉ፤ ህይወታችሁ በደግነት ይሞላል፡፡ ሌሎችን በተመለከተ የተሻለ ስሜት ይኖራችኋል እናም በምላሹ የነሱን መልካምነት ማየት ትጀምራላቹ፡፡
የወጣት ሴቶች ክፍል ስሞች፡፡
ሶስተኛው፤ በዚ አዲሱ የክፍል አወቃቀር፤ ሁሉንም ክፍሎች አንድ ወደሚደርጋቸው “ወጣት ሴቶች” የሚለውን ስያሜ ይወስዳሉ፡፡ 20 የቢሀይቭ፣ የምያ ሜድ እና የልኦረል ስሞችን እንለውጣለን፡፡
የክፍል መሪዎችን ማጠናከር
የመጨረሻው ላሳውቅ የምፈልገው ክፍል፤ የክፍል መሪዎችን አስፈላጊነትን ነው፡፡ የወጣት ሴቶች ክፍል በምንም ያህል በወጣት እድሜ ቢዋቀርም ሁሉም ክፍል የክፍል መሪዎች ሊኖረው ይገባል፡፡!121ወጣት ሴቶች በወጣቶች መሀል መሪ ለመሆን የሚጠሩት በመለኮታዊ አሰራር ነው፡፡
የክፍል አመራሮች ሚና እና አላማ ጠንክሯል እናም በግልጽ ተገልጧል፡፡ የመዳን ስራ ከነዚህ ታላቅ ሀላፊነቶች ውስጥ ነው ፤ በተለይ በአገልግሎት፣ በሚስዮን ስራ፣ በማነቃቃት እና በቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ ውስጥ፡፡ 22 አዎን እንደዚህ ነው እስራኤልን የምንሰበስበው23—ታላቅ ስራ እንደ ጌታ የሻለቃ ወጣቶች ለሁሉም ወጣት ሴቶች ።
እንደምታውቁት በማንኛውም የቤተክርስቲያን ደረጃ ውስጥ ጌታ ህዝቡን ለመምራት መሪዎችን ይጠራል፡፡ ወጣት ሴቶች፤ የክፍል ፕሬዝዳንቶች አባል መሆን በሚያነሳሳ የመሪነት ንድፍ ለመሣተፍ የመጀመሪያ እድላችው ሊሆን ይችላል፡፡ አዋቂ መሪዎች፤ ለክፍል መሪዎች ጥሪ ቅድሚያ ስጡ፡፡ ከዛም የክፍል ፕሬዝዳንት በመምከርና በመምራት እንዲሳካላቸው ጎን ለጎን በመሆን አብራችሁ ምሩ፡፡24 የአንድ ክፍል አመራሮች የመሪነት ልምድ ደረጃ ምንም ቢሆን፤ ካሉበት እንዲጀምሩ እናም እንደ መሪነት ሊባርካቸው የሚችለውን ችሎታቸውን እና በራስ መተማመናቸውን እንዲያዳብሩ አድዷቸው፡፡ ቅርባቸው ሁኑ። ነገር ግን፤ በእነርሱ ምትክ አትስሩ፡፡ እነሱን ስትመሩ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ይመራችኋል፡፡
የወላጆችን እና የመሪዎችን እንደ መካሪነት ጠቃሚ ድርሻቸውን ለማብራራት አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ ክሎኢ የክፍል ፕሬዘደንት ለመሆን ተጠርታ ነበር፡፡ ብልህ የክህነት ስልጣን መሪዋ ብቁ የሆኑ የአመራር ስሞችን ለማግኘት የጌታን እርዳታ እንድትሻ አበረታታት፡፡ ክሎኢ ይልቁንም ቶሎ ከመወሰን ይልቅ በመጸለይ ብቁ የሆኑ አማካሪዎችን ለምረጥ የሚያስችላትን ተነሳሽነት አገኘች፡፡ ስለጸሀፊ ጸሎቷን እና ማሰላሰሏን ስትቀጥል፣ መንፈስ ቅዱስ በተደጋጋሚ ትኩረቷን ወዳልጠበቀቻት አንድ ወደቤተክርስቲያን እና ወደ ዝግጅቶች የማትመጣ ወጣት ሴት አመለከታት፡፡
በመልክቱ ባለመተማመን ክሎኢ ከናቷ ጋር ተነጋገረች፣ እሷም ራእይን የምንቀበልበት አንዱ መንገድ በተደጋጋሚ ሃሳቦችን ስናገኝ ነው ብላ አብራራች፡፡ በታደሰ የራስ መተማመን፤ ክሎኢ ይህችን ወጣት ሴት መምረጥ እንዳለባት ተሰማት፡፡ የቅርንጫፍ ፐሬዝዳንቱ ጥሪውን አስተላለፈ፣ ወጣት ሴቶቹም ጥሪውን ተቀበሉ፡፡ ለጥሪው ከተለዩ በኋላ ይህች መልካሟ ጸሀፊ፣ “ታውቂያለሽ እኔ ቦታ እንዳለኝ ወይም በቦታዎች አስፈላጊ እንደሆንኩ ተሰምቶኝ አያውቅም ነበር፡፡ ከነሱ ጋር እመጥናለሁ ብዪ አላሰብኩም ነበር፡፡ ነገር ግን በዚ ጥሪ፤ የሰማይ አባት ለኔ አላማ እና ቦታ እንዳለው ተሰማኝ፡፡” ክሎኢ ከእናቷ ጋር ስብሰባውን ጨርሰው ከሄዱ በሀላ፤ ክሎኢ በአይኖቿ እንባ እያቀረረ ወደ እናቷ ዞራ “ራእይ በእውነት ይሰራል! አለች፡፡ ራእይ በእውነት ይሰራል!”
የክፍል አመራሮች፤ የሱን ሴት ልጆች እንድትመሩ በጌታ ተጠርታችዋል፡፡ “ጌታ ያውቃቹሀል፡፡ … እናንተን መርጧችኋል።”25 ክህነት ስልጣን ባለውለጥሪው ተለይታችኋል።ይህ ማለት የጥሪያችሁን ግዴታ ስትተገብሩ፣ ክህነት ስልጣንን መለማመድ ትጀምራላችሁ፡፡ የምትሰሩት ታላቅ ስራ አላችሁ። የመንፈስ ቅዱስ ማነሻሻዎችን ተግብሩአቸው እናም ለነሱ ስሜት ይኑራችሁ። ይህን ስታደርጉ ብቻችሁን ስለማታገለግሉ በራስ በመተማመን ልታገለግሉ ትችላላችሁ፡፡
የክፍል ፕሬዘዳንቶች፤ ሽማግሌ ክዊንተን ኤል ኩክ ስላስተዋወቁት አዲሱ የአጥቢያ የወጣቶች ኮሚቴ፣ የናንተን ጠቢብነት፣ ድምጽ እና ሀይል እንፈልጋለን፡፡ እናንተ የወንድም እና የእቶቻችሁን ፍላጎት ለማሟላት የምትጠቅሙ ዋና መፍትሄዎች ናችሁ፡፡26
እነዚ የክፍል አወቃቀሮች እና የመሪነት ማስተካከያዎች ፤ ቅርንጫፎች እና ክልሎች ዝግጁ በሆኑበት ጊዜ ሊጀምር ይችላል፡፡ ነገር ግን በጥር 1፡2020(እ.አ.አ) ላይ በቦታው መሆን አለበት፡፡
ውድ እህቶቼ፣ እነዚህ ዛሬ የተናገርኳቸው ማስተካከያዎች ከጌታ የተሰጡ መመሪያዎች መሆናቸውን እመሰክራለው፡፡ እነዚህን ማስተካከያዎች በትጋት ስንተገብር፤ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል ያለንን ውሳኔያችንን ለማጠንከር እና ሌሎች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲመጡ ለመርዳት፤ ያለንን አላማችንን እንዳናጣ፡፡ ይህም እውነት እንደሆነ እመሰክራለሁ። በሱ በተቀደሰ ስራ ውስጥ በጣም አስፈላጊ እንድንሆን ስለፈቀደልን በጣም አመስጋኝ ነኝ፡፡
በቃልኪዳኑ መንገድ ስትጠጉ ይህን ማስተካከያ የመራውን መንፈስ እራሱ ቅዱስ እናንተን እንዲመራ እጸልያለሁ፡፡ ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።