2010–2019 (እ.አ.አ)
ቅድስና እና የደስታ እቅድ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ቅድስና እና የደስታ እቅድ

ታላቅ ደስታ የሚመጣው ከላቀ የግል ቅድስና ነው፡፡

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ደስታ ለማግኘት በምታደርጉት የግል ፍለጋችሁ የሚረዳችሁ ሃይል እንድታገኙ እጸልያለሁ። አንዳንዶች ቀድሞውኑ ደስተኛ ሊሆኑ ይችላሉ ፣ ነገርግን ተጨማሪ ደስታ እንዲቀርብለት ቢጠየቅ እምቢ የሚል የለም። እርግጠኛ የሆነ የዘላቂ ደስታ ግብዣን ለመቀበል ማንኛውም ሰው ይጓጓል ፡፡

ያንን ነው ሰማያዊ አባት፣ተወዳጅ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ አሁን በምድር ለሚኖር፣ ወደፊት ለሚኖር እና እሰከዛሬ ለኖረ ለያንዳንዱ የሰማያዊ አባት መንፈሳዊ ልጅ ያቀረቡት፡፡ ያ ግብዣ አንዳንድ ጊዜ የደስታ እቅድ ተብሎ ይጠራል። ነቢዩ አልማ ነበር በኃጢያት ሀዘን ቅርቃር ውስጥ የወደቀውን ልጁን ሲያስተምር እንደዚያ ብሎ የጠራው። ክፋት ለልጁ—ወይም ለሌላ ለማንኛውም የሰማይ አባት ልጅ ደስታ ሊሆን እንደማይችል አልማ ያውቅ ነበር።1

በቅድስና ማደግ ብቸኛው ወደ ደስታ የሚያደርስ መንገድ እንደሆነ ለልጁ አስተምሯል፡፡ የላቀ ቅድስና የሚመጣውም በኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ስንነጻ እና ፍጹም ስንሆን እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡2 በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነት በማሳደር፣ ሁልጊዜ ንስሃ በመግባት እና ቃልኪዳንን በመጠበቅ ብቻ ነው የምንናፍቀውን ዘላቂ ደስታ ለመለማመድ እና ከእኛ ጋር ለማቆየት የምንችለው።

የዛሬ ጸሎቴ የተሻለ ደስታ የሚመጣው የተሻለ የግለሰብ ቅድስና ሲኖር እንደሆነ እንድትረዱ እናም በዚያ እምነት ላይ እርምጃ እንድትወስዱ እንዳግዛችሁ ነው፡፡ ከዚያ በኋላም ይበልጥ ቅዱስ ለመሆን ለሚያበቃ ለዚያ ስጦታ ብቁ ለመሆን ምን ማድረግ እንደምንችል እኔ የማውቀውን አካፍላለሁ።

ቅዱሳት መጻሕፍት ሌሎች ነገሮችን ጨምሮ በክርስቶስ ላይ እምነት ማሳደርን ስንለማመድ3ታዛዥነታችንን በተግባር ስናሳይ4ንስሓ ስንገባ5ለእርሱ መስዋእት ስንሆን 6የተቀደሱ ስርአቶችን ስናከናውን እና ከእርሱ ጋር የገባነውን ቃልኪዳን ስንጠብቅ7እንደምንቀደስ ወይም የበለጠ ቅዱስ መሆን እንደምንችል ያስተምሩናል ፡፡ ለቅድስና ስጦታ ብቁ ለመሆን ትህትና ፣8የዋህነት9እና ትዕግሥት 10ይጠይቃል።

የበለጠ ቅድስናን የመፈለግ አንድ ገጠመኝ በሶልት ሌክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ለእኔ መጣ። መጠበቅ ስለሚገባኝ ነገር ጥቂት ተነግሮኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤተመቅደስ ገባሁ፡፡ “ቅድስና ለጌታ“ እና “የጌታ ማደሪያ“ የሚሉትን ጽሁፎች በህንጻው ላይ አይቼ ነበር፡፡ ታላቅ የመጓጓት ስሜት ተሰማኝ ፡፡ ይሁን እንጂ ለመግባት ዝግጁ ስለመሆኔ አሰብኩ፡፡

ወደ ቤተመቅደሱ ስንገባ እናትና አባቴ ከፊት ፊቴ ነበሩ፡፡ የብቁነት ማረጋገጫ የመግቢያ ፈቃዳችንን እንድናሳይ ተጠየቅን፡፡

ወላጆቼ መግቢያ ፈቃድ ማሳያ ወንበር ላይ የተቀመጠውን ሰው ያውቁታል፡፡ እናም ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ትንሽ ወደኋላ ቆዩ፡፡ ሁሉም ነገር አንጸባራቂ ነጭ ወደሆነበት ወደ አንድ ሰፊ ቦታ ብቻዬን ሄድኩ ፡፡ ከእኔ በላይ ከፍ ወዳለው ጣሪያ ተመለከትኩኝ ክፍት ሰማይ ይመስል ነበር። በዚያን ሰአት ከዚህ በፊት እዛ እንደነበርሁ ግልፅ ስሜት መጣብኝ ፡፡

ከዚያም አንድ ለስላሳ ድምጽ ሰማሁኝ—የራሴ ድምጽ አልነበረም፡፡አንድ በጣም ለስላሳ ድምጽ ሰማሁኝ—የእኔ አይደለም፡፡ በለስላሳ ድምጽ የተነገሩት ቃላት እነዚህ ነበሩ:“ከዚህ በፊት እዚህ አልነበርክም፡፡“ ከመወለድህ በፊት የነበረህን ጊዜ እያስታወስክ ነው፡፡ እንዲህ ባለ ቅዱስ ስፍራ ውስጥ ነበርክ፡፡ አዳኙ ወደቆምክበት ቦታ እንደሚመጣ ተሰምቶክ ነበር፡፡ እናም ልታየው ጓጉተህ ስለነበር ታላቅ ደስታ ተሰማህ፡፡”

በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ የነበረው ያ ገጠመኝ የዘለቀው ለአፍታ ብቻ ነበር፡፡ ነገርግን ትዝታው አሁንም ሰላምን ፣ ሃሴትን እና ጥልቅ ደስታን ያመጣል።

የዛን እለት ብዙ ትምህርቶችን ቀሰምኩኝ፡፡ አንደኛው መንፈስ ቅዱስ በትንሽ የዝምታ ድምጽ እንደሚናገር ነው፡፡ መንፈሳዊ ሰላም በልቤ ውስጥ በሚኖር ጊዜ እሰማዋለሁ፡፡ የደስታ እና የበለጠ ቅዱስ እየሆንኩ እየመጣሁ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ስሜትን ያመጣል። እናም ያ ሁልጊዜ በነዚያ የመጀመሪያዎቹ ወቅቶች በእግዚያብሄር ቤተመቅደስ የተሰማኝን ደስታ ያመጣል፡፡

በራሳችሁ እና በሌሎች ህይወት ውስጥ የደስታ ተአምር ከሚያድግ ቅድስና ይበልጥ አዳኙን በመምሰል እንደሚመጣ ተመልክታችኋል፡፡ በቅርብ ሳምንታት በአዳኙ ሙሉ እምነት እና በደስተኛ አንደበት ሞትን እየተጋፈጡ ከነበሩ ሰዎች አልጋ አጠገብ ነበርኩኝ፡፡

አንደኛው በቤተሰቦቹ ተከቦ ነበር፡፡ ወንድ ልጄ እና እኔ ስንገባ እርሱ እና ሚስቱ ድምጻቸውን ዝቅ አድርገው እየተነጋገገሩ ነበር፡፡ ለብዙ አመታት አውቃቸው ነበር፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ በህይወታቸው እና በቤተሰባቸው ህይወታቸው ውስጥ ሲሰራ አይቻለሁኝ፡፡

የህይወቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚደረጉትን የህክምና ጥረቶች ለማቆም አብረው መርጠዋል ፡፡ በሚያነጋግረን ጊዜ ጸጥ ያለ ስሜት ነበረ፡፡ ስለወንጌል እና በራሱ እና በቤተሰቡ ላይ ስላሳደረው ንጹህ የማድረግ ውጤት ምስጋናውን ሲገልጽ ፈገግ አለ፡፡ ስላሳለፈው አስደሳች የቤተመቅደስ አገልግሎት አመታት ተናገረ፡፡ በዚህ ሰው ጥያቄ ወንድ ልጄ ራሱን በተቀደሰ ዘይት ቀባው፡፡ እኔ የተቀባውን አሰርኩኝ፡፡ ይህን ሳደርግ በቅርቡ አዳኙን ፊት ለፊት እንደሚያየው ለመንገር ግልጽ ያለ ስሜት ነበረኝ፡፡

ደስታ ፣ፍቅር እና የአዳኙ ማረጋገጫ እንደሚሰማው ቃል ገባሁለት፡፡ ስንወጣ ሞቅ ያለ ፈገግታ አሳየ፡፡ የመጨረሻ ቃላቶቹም “ካቲን እንደምወዳት ንገራት“ የሚል ነበር፡፡ ባለቤቴ ካትሊን ለረዥም አመታት የእርሱ ቤተሰብ ትውልዶች የጌታን ግብዣ እንዲቀበሉ እንዲመጡ፣ የተቀደሱ ቃልኪዳኖችን እንዲያደርጉ እና እንዲጠብቁ እናም በውጤቱ ለሚመጣው ደስታ ብቁ እንዲሆኑ አበረታታቸዋለች፡፡

ከሰአታት በኋላ ሞተ፡፡ በሞተ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የሟቹ ባለቤት ለእኔና ለባለቤቴ ስጦታ አመጣችልን፡፡ ስናወራ እየሳቀች ነበር፡፡ ደስ በሚል ሁኔታ እንዲህ አለች “ሀዘን እና ብቸኝነት ይሰማኛል ብዬ ጠብቄ ነበር“ ደስታ በጣም ይሰማኛል፡፡ ያ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህ?

ባሏን ምንያህል ትወደው እንደነበር እና እንዴት ሁለቱም ጌታን እንዳወቁት፣ እንደወደዱት፣ እና እንዳገለገሉት ስለማውቅ የደስታ ስሜቷ ቃል የተገባ ስጦታ መሆኑን ነገርኳት ምክንያቱም በታማኝ አገልግሎቷ የበለጠ ቅዱስ ተደርጋለች። ቅድስናዋ ለዚህ ደስታ ብቁ እንድትሆን አድርጓት ነበር።

ዛሬ ይህንን የሚያዳምጡ አንዳንዶች “ታማኝ ለሆኑ ሰዎች ቃል የተገባላቸውን ሰላምና ደስታ አኔን ለምን አይሰማኝም?“ ሲሉ ያስቡ ይሆናል፡፡ በከባድ መከራ ውስጥ በማለፍ ታማኝ ሆኛለሁ ነገር ግን ደስታ አይሰማኝም ፡፡ ”

ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝም ይሄው ፈተና ገጥሞታል፡፡ በሊበርቲ ሚዙሪ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት ታሰሮ በነበረ ጊዜ እፎይታ ለማግኘት ጸለየ ፡፡ ለጌታ ታማኝ ነበር ፡፡ በቅድስና አድጎ ነበር፡፡ ሆኖም ደስተኛ እንዳይሆን እንደታገደ ሆኖ ተሰማው፡፡

ጌታ በሟችነት ፈተናችን ለተወሰነ ወቅት እና ምናልባትም ለረዥም ጊዜ ሁላችንም የሚያስፈልገንን የታጋሽነት ትምህርት አስተማረው፡፡ ለታማኝ እና በስቃይ ላይ ለነበረው ነብይ የጌታ መልእክት ይህ ነበር፡፡

“እና ወደ ጉድጓድ ወይም ወደ ገዳዮች እጆች ከተጣልክ፣ እና የሞት ፍርድ ከተላለፈብህ፤ ወደ ጥልቁ ከተጣልክ፤ ወደፊት እና ወደኋላ የሚገፋው ውሀ በአንተ ላይ ከአደመ፤ አደገኛው ነፋሶችም የአንተ ጠላት ከሆኑ፤ ሰማዮችም ጭለማን የሚሰበስቡ ከሆኑ፣ እና ንጥረ-ነገሮች ሁሉ መንገድህን ለማሰናከል ከተጣመሩ፤ እና ከሁሉም በላይ፣ የሲኦል መንጋጋም አፍዋን በሰፊ ከከፈተችብህ፣ ልጄ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ለአንተ ልምድ እንደሚሰጡህ እና ለአንተ ጥቅም እንደሆኑም እወቅ።

“የሰው ልጅ ከሁሉም በታች ወርዷል። አንተ ከእርሱ ታላቅ ነህ?

ስለዚህ፣ ባለህበት መንገድ ቆይ፣ እና ክህነትም ከአንተ ጋር ይቆያል፤ ገደቦቻቸው ተወስነዋል፣ ሊያልፉትም አይችሉም። ቀናትህ የታወቁ ናቸው እና አመታትህም ከዚህ በታች አይቀነሱም፤ ስለዚህ፣ ሰው ማድረግ የሚችለውን አትፍራ፣ እግዚአብሔር ከዘለአለም እስከ ዘለአለም ከአንተ ጋር ነውና።11

የሃጢያት ክፍያው ይበልጥ ቅዱስ እንዲያደርገው ከባድ ዋጋ ለከፈለው ለኢዮብ ጌታ የሰጠው ይኸው ተመሳሳይ ትምህርት ነበር። ስለእርሱ ከተነገረው ከመግቢያው፣ እዮብ ጻድቅ እንደነበረ እናውቃለን፡“ዑፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ።12

ከዚያም ኢዮብ ሀብቱን ፣ ቤተሰቡን ብሎም ጤናውን አጣ። ኢዮብ በከባድ ችግር ያገኘው ትልቅ ቅድስናው ለታላቅ ደስታ ብቁ ስለማድረጉ ጥርጣሬ አድሮበት እንደነበረ ታስታውሱ ይሆናል፡፡ ለኢዮብ መከራን ያመጣበት ቅድስና መሰለው ፡፡

ሆኖም ጌታ ለዮሴፍ ስሚዝ የሰጠውን ተመሳሳይ የማስተካከያ ትምህርት ለኢዮብ ሰጠው ፡፡ ኢዮብ አሳዛኝ ሁኔታውን በመንፈሳዊ ዓይኖች እንዲመለከት አደረገው። እርሱ አለ፥

እስቲ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ ልጠይቅህ፣ አንተም መልስልኝ።

“ምድርን በመሠረትሁ ጊዜ አንተ የት ነበርህ? በእርግጥ የምታስተውል ከሆንህ፣ ንገረኝ።

ካወቅህ፣ መጠኗን ለይቶ ማን ወሰነ? በላይዋስ መለኪያ ገመድ የዘረጋ ማን ነው?

መሠረቶቿ ምን ላይ ተተከሉ? የማእዘን ድንጋይዋንስ ማን አቆመ?

ይህም የሆነው የንጋት ከዋክብት በዘመሩበት ጊዜ፣ መላእክትም እልል ባሉበት ጊዜ ነበር፡፡13

ከዚያ በኋላ ኢዮብ እግዚአብሔር ፍትሐዊ አይደለም በማለቱ ተፀፀተ ፤ ኢዮብ ፈተናዎቹን ከፍ ባለና በተቀደሰ መንገድ እንዲያይ ተፈቀደለት ፡፡ ተናዞ ነበር።

“ኢዮብም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤

“አንተ ሁሉን ማድረግ እንደምትችል፣ ዕቅድህም ከቶ እንደማይሰናከል ዐወቅሁ።

አንተ፣ ‘ያለ ዕውቀት ዕቅዴን የሚያደበዝዝ ይህ ማን ነው’ አልኸኝ፤ በእርግጥ ያልገባኝን ነገር፣ የማላውቀውንና ላስተውለው የማልችለውን ጒዳይ ተናገርሁ።

ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤ አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።

“ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤ አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።

ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”14

ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።” ነገርግን ምናልባት የኢዮብ ትልቁ በረከት በችግር እና በንስሃ በቅድስና ማደጉ ነበር፡፡ ገና ወደፊት ሊኖር ለነበሩት ቀናት ታላቅ ደስታ ለማግኘት ብቁ ሆኖ ነበር፡፡

ታላቅ ቅድስና በቀላሉ በመጠየቅ አይመጣም። እግዚያብሄር እንዲቀይረን የሚያስፈልገውን ነገር በማድረግ ነው የሚመጣው፡፡

ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን ለኔ እጅግ ታላቅ የሚመስለኝን በቃል ኪዳኑ መንገድ ወደ ታላቅ ቅድስና እንዴት መሄድ እንደሚቻል ምክር ሰጥተዋል፡፡ እንዲህ ብለው ሲመክሩ መንገዱን ጠቁመዋል፡

“በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ ያለውን የማበርታት ሃይል ተለማመዱ—በየቀኑ ትንሽ ሻል ያለ ነገር የማድረግን እና የመሆንን፡፡

ንስሃ ለመግባት ስንመርጥ መለወጥን እንመርጣለን! አዳኛችን ልንሆን ወደምንችለው ምርጥ እኛነታችን እንዲለውጠን እንፈቅድለታለን፡፡ በመንፈስ ለማደግ እና ደስታን ለመቀበል እንመርጣለን—በእርሱ ነጻ የመውጣት ደስታ፡፡ ንስሃ ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆንን እንመርጣለን“

ቅዱስ ለመሆን ስለምናደርገው ጥረታችን ፕሬዚደንት ረሰል ኤም.ኔልሰን ማበረታቻቸውን ሲቀጥሉ፡ “ጌታ በዚህ ጊዜ ፍጹምነት አይጠብቅብንም።… ነገር ግን ንፅህናችን እያደገ የሚመጣ እንዲሆን ይጠብቅብናል፡፡ በየቀኑ የሚደረግ ንስሃ የንጽህና መንገድ ነው፡፡”15

ፕሬዚደንት ዳለን ኤች ኦክስ በቀደመ የጉባኤ ንግግራቸው በቅድስና እንዴት እንደምናድግ እና ወደ እርሱ እየሄድን እንደሆነ እንዴት ልናውቅ እንደምንችል ይበልጥ በግልጽ ማየት እንድችል ረድተውኛል፡፡ እንዲህ ብለው ነበር “መንፈሳዊነት ላይ እንዴት መድረስ እንችላለን? ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከኛ ጋር እንዲሆን የሚያስችል ደረጃ ያለ ቅድስና ላይ እንዴት እንደርሳለን?። የዚህን አአለም ነገሮች በዘላለማዊ እይታ ወደማየት እና ወደመገምገም እንዴት እንመጣለን?16

የፕሬዚደንት ኦክስ ምላሽ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አፍቃሪ አዳኛችን በታላቅ እምነት በመያዝ ነው የሚጀምረው፡፡ ያም በየቀኑ ምህረትን ወደመፈለግ እና ትእዛዛቱን በመጠበቅ እርሱን ለማስታወስ ወደመፈለግ ይመራናል፡፡ ያ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለ ታላቅ እምነት በየቀኑ ቃሉን ከመመገብ ይመጣል፡፡

“More Holiness Give Me” የሚለው መዝሙር ይበልጥ የተቀደስን ለመሆን እርዳታ ለማግኘት ስለምንጸልይበት መንገድ ይጠቁማል፡፡ ደራሲው የምንፈልገው ቅድስና ሁሉን ነገር ካደረግን በኋላ በጊዜ ሂደት ከአፍቃሪ አምላክ የሚሰጥ ስጦታ እንደሆነ በጥበብ ይጠቁማል፡፡ የመጨረሻዎቹን ስንኞች አስታውሱ:

የበለጠ ንጽህናን ስጠኝ፣

ለማሸነፍ የበለጠ ጥንካሬን፣

ከመሬት እርከኖች የበለጠ ነፃነትን፣

ለቤት የበለጠ ጉጉትን፡፡

ለመንግሥቱ ይበልጥ ተስማሚ፣

ለበለጠ ጥቅም ላይ እውላለሁ ፣

የበለጠ የተባረከ እና የተቀደሰ

የበለጠ ፣ አዳኝ ፣ እንደ አንተ።17

የግል ሁኔታዎቻችን ምንም አይነት ቢሆኑ፣ ወደቤታችን በምናደርገው የቃልኪዳን መንገድ ላይ የትኛውም ቦታ ላይ ብንሆን ታላቅ ቅድስና ለማግኘት የምንጸልየው ጸሎት ምላሽ ያግኝ፡፡ ጸሎቶቻችን ሲመለሱ ደስታችን እንደሚያድግ አውቃለሁኝ፡፡ ዘግይቶ ሊሆን ይችላል የሚመጣው ነገር ግን መምጣቱ አይቀርም፡፡ ከአፍቃሪ ሰማያዊ አባት እና ከተወዳጅ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ያ ማረጋገጫ አለኝ፡፡

ጆሴፍ ስሚዝ የእግዚያብሄር ነብይ እንደነበር፣ ፕሬዚደንት ረሰል ኤም.ኔልሰን በዚህ አሁን ህያው ነቢይ እንደሆኑ እመሰክራለሁ፡፡ እግዚያብሄር አባት አለ እንዲሁም ይወደናል፡፡ በቤተሰብ ደረጃ ወደቤታችን ወደ እርሱ እንድንመለስ ይፈልጋል፡፡ አፍቃሪ አዳኛችን በዚያ መንገዳችን ላይ እንድንከተለው ይጋብዘናል፡፡ መንገዱን አዘጋጅተውልናል፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስም፣ አሜን።