2010–2019 (እ.አ.አ)
ወንጌልን በማካፈል ደስታን ማግኘት
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ወንጌልን በማካፈል ደስታን ማግኘት

የኛን እና በአቅራቢያችን ያሉትን ህይወት ይባርክ ዘንድ ወደ እርሱ እንድንመለስ የሚጠብቀን፤ የሚወደን የሰማይ አባት አለን።

ከምወዳቸው የህፃናት መዝሙር መካከል አንዱ እንዲህ በሚሉ ቃላት ይጀምራል።

እኔ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ።

ማን እንደሆንኩ አውቃለሁ።

የእግዚአብሔርን እቅድ አውቃለሁ።

በእምነት እከተለዋለሁ።

በአዳኙ በኢየሱስ ክረስቶስ አምናለሁ።1

እንዴት ያለ ቀላልና የሚያምር የምናምነውን እውነት የሚገልጽ ነው!

እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን ማን እንደሆንን እናውቃለን። “እግዚአብሔር የመንፈሶቻችን አባት እንደሆነ እናውቃለን። እኛ… ልጆቹ ነን፣ እናም ያፈቅረናል። ወደ ምድር ከመምጣታችን በፊት ከእርሱ ጋር በገነት ውስጥ ኖረናል።”

የእግዚአብሔርን እቅድ እናውቃለን። እርሱ ሲያቀርበው አብረነው ነበርን። የእግዚአብሔር ሙሉ አላማ—ስራው እና ክብሩ—እያንዳንዳችን በረከቶቹን በሙሉ መካፈል እንድንችል ነው። እሱ… ይህን አላማውን ለመፈጸም ፍጹም የሆነ እቅድ አዘጋጅቷል። ወደ ምድር ከመምጣታችን በፊት ይህን … የደስታ… የቤዛ እና … የመዳን እቅድ ተረድተን ተቀብለናል።

“ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር እቅድ ዋና ክፍል ነው። በኃጢያት ክፍያው በኩል ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱን አላማ አሟልቷል ፤ እናም እያንዳንዳችን አለመሞትን እና ከፍታን ማግኘት እንድንችል አደረገ። ሰይጣን፣ ወይም ዲያብሎስ፣ የእግዚአብሔር እቅድ ጠላት ነው።” ከመጀመርያም ጀምሮ።

“ነጻ ምርጫ ወይም የመምረጥ ችሎታ፣ እግዚአብሔር ለልጆቹ ከሰጣቸው ታላቅ ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው። … ኢየሱስን ወይም ሰይጣንን ለመከተል መምረጥ አለብን።”2

እነዚህ ለሌሎች ማካፈል የምንችላቸው ቀላል የሆኑ እውነቶች ናቸው።

እናቴ ለመነጋገር ዝግጁ በመሆን እና አጋጣሚን በማወቅ እንደዚህ አይነት ቀላል እውነቶችን ስላካፈለችበት ጊዜ ልንገራችሁ።

ከብዙ አመታት በፊት ከወንድሜ ጋር ለጉብኝት ወደ አርጀንቲና እየተመለሰች ነበር። እናቴ መብረር ስለማትወድ ከወንድ ልጆቼ መሃል አንዱን የምቾትና የጥበቃ በረከት እንዲሰጣት ጠየቀች። ወንጌልን መማር የሚፈልጉ የብዙ ሰዎችን ልብ ለመንካት እና ለማጠንከር በልዩ ምሪት እና አቅጣጫ በመንፈስ ቅዱስ አያቱን ለመባረክ ተነሳሳ።

 የፖል ቤተሰብ

በሶልት ሌክ አውሮፕላን ማረፍያ እናቴና ወንድሜ ከበረዶ ላይ መንሸራተት ጉብኝት ከቤተሰቧ ጋር የምትመለስ የ7 አመት ልጅ ጋር ተገናኙ። ቤተሰቦቿ ለምን ያህል ጊዜ ከአያቴና ከወንድሜ ጋር ስታወራ እንደነበር ልብ ካሉ በኋላ ልጃቸውን ለመቀላቀል ወሰኑ። ራሳቸውንና ልጃቸውን ኤድዋርዶ እና ማሪያ ሱዛና እና ጊያዳ ፖል ብለው አስተዋወቁ። ከዚህ ጣፋጭ ቤተሰብ ጋር ተፈጥሮአዊ እና ደስ የሚል ግንኙነት ነበር።

ሁለቱም ቤተሰቦች በአንድነት ወደ ቦነስ አይረስ አርጀንቲና በተመሳሳይ በረራ ላይ በመሆናቸው ደስ አላቸው። ንግግራችው በቀጠለ ጊዜ እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ስለተመለሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን ሰምተው እንደማያውቁ እናቴ አስተዋለች።

ሱዛና መጀመሪያ ከጠየቀቻቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ “ወርቃማ ሃውልት በላዩ ላይ ስላለው የሚያምር ቤተ መዘክር ትነግሪኛለሽ?” የሚል ነበር።

እናቴም ያ የሚያምር ህንጻ ቤተ መዘክር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ቀን ተመልሰን አብረን መኖር እንድንችል ቃልኪዳን የምንገባበት የጌታ ቤተመቅደስ ነው ብላ አስረዳቻቸው። ሱዛና ከሶልት ሌክ ጉዟቸው በፊት የሆነ ነገር መንፈሷን እንዲያጠነክር ጸልያ እንደነበር ለእናቴ ተናገርች።

በበረራው ወቅት እናቴ ቀላል ነገር ግን ጠንካራ የወንጌል ምስክርነት ሰጠች እናም ሱዛናን በምትኖርበት ሃገር ምስዮናዊያንን እንድታገኝ ጋበዘቻት፡፡ ሱዛና “እንዴት ነው ማገኛቸው?” ብላ እናቴን ጠየቀቻት።

እናቴም “ልታጪያቸው አትችይም፣ ነጭ ሸሚዝና ከረባት የለበሱ ሁለት ወጣት ወንዶች ወይም በጥሩ ሁኔታ የለበሱ ወጣት ሴቶች ናቸው።ሁልጊዜ ስማቸውና ‘የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን’ የሚል ባጅ ይለብሣሉ።”

ቤተሰቦቹ በቦነስ አይረስ አየር ማረፍያ የስልክ ቁጥር ተቀያይረው ተሰነባበቱ። ከዚያን ጊዜ በኋላ የእናቴ ጓደኛ የሆነችው ሱዛና እናቴን አየር መንገድ ውስጥ ጥላት በመሄዷ እጅግ አዝና እንደነበረ ብዙ ጊዜ ነግራኛለች። እንዲህ አለች “እናትሽ ታበራ ነበር። ልገልጸው አልችልም ነገር ግን ወደኋላ ልተወው የማልችለው ድምቀት ነበራት።

ሱዛና ወዲያው ወደ ትውልድ ቦታዋ እንደተመለሰች እሷና ልጇ ጊያዳ ከቤታቸው ጥቂት ቤቶች አለፍ ብላ ወደምትኖረው የሱዛና እናት ልምምዳቸውን ለማካፈል ሄዱ። እየነዱ ሳለ ሱዛና እናቴ እንደነገረቻት አይነት የለበሱ ሁለት ወጣት ወንዶች ጎዳና ላይ ሲራመዱ አየች። በመንገዱ መሃል መኪናዋን አቆመችና ወረደች እናም “ከኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ናችሁ?” ብላ ሁለቱን ወጣት ወንዶች ጠየቀች።

እነርሱም። “አዎን“ አሏት።

“ምስዮናውያን?” ብላ ጠየቀች።

“አዎን ነን!” ብለው መለሱላት።

ከዚያም “መኪናዬ ውስጥ ግቡ፤ ወደቤቴ ልታስተምሩኝ ትመጣላችሁ” አለች ።

 የፖል ቤተሰብ

ከሁለት ወራት በኋላ ማሪያ ሱዛና ተጠመቀች። ልጇ ጊያዳም ዘጠኝ አመት ሲሞላት ተጠመቀች። ምንም ቢሆን የምንወደው ኤዱዋርዶ ላይ አሁንም እየሰራንበት ነው።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሱዛና ካገኘኋቸው ታላቅ ምስዮናውያን መካከል አንዷ ሆነች። እሷ ልክ እንደ ሞዛያ ወንድ ልጅ ነበረች ብዙ ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ በማምጣት።

በንግግራችን መሃል “ምስጢርሽ ምንድነው? እንዴት ነው ወንጌልን ከሌሎች ጋር የምታካፈይው?” ብዬ ጠየኳት።

እንዲህ አለችኝ “በጣም ቀላል ነው። ሁል ጊዜ ከቤቴ ከመውጣቴ በፊት ወንጌልን በህይወቱ ወደሚያስፈልገው ሰው እንዲመራኝ የሰማይ አባትን በጸሎት እጠይቀዋለሁ። አንዳንድ ጊዜ መጽሃፈ ሞርሞንን ለነሱ ለማካፈል ይዤ እሄዳለሁ ወይም ከምስዮናውያን ካርድ እሰጣቸዋለሁ እናም አንድ ሰውን ማናገር ስጀምር በቀላሉ ሰለቤተክርስትያኑ ሰምተው ያውቁ እንደሆን እጠይቃቸዋለሁ።”

በተጨማሪም እንዲህ አለች “ሌላ ጊዜ ደግሞ ባቡር እየጠበኩ እንዲሁ ፈገግ እላለሁ። አንድ ቀን አንድ ሰውዬ ተመለከተኝና ‘ስለምንድነው ፈገግ ምትዪው?’ አለኝ። ባልጠበኩት መልኩ አስገረመኝ።

“ ‘ፈገግ የምለው ደስተኛ ስለሆንኩ ነው’ ብዬ መለስኩ።

እሱም ቀጥሎ ‘ስለምንድነው እንዲህ በጣም የምትደሰቺው?’ አለኝ።

“እኔም ‘የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባል ነኝ እናም ያ ነው ደስተኛ የሚያደርገኝ’ ብዬ መለስኩ። ስለዚያ ሰምተህ ታውቃለህ?’”

አላውቅም ሲላት ካርድ ሰጠችው እናም የሚመጣውን እሁድ አገልግሎት እንዲካፈክ ጋበዘችው። በቀጣዩ እሁድ በር ላይ ሰላም አለችው።

ፕሬዘደንት ዳለን ኤች. ኦክስ እንዳስተማሩት፥

“ሁሉም አባላት ወንጌልን ለማካፈል እንዲችሉ የሚረዷቸው ሶስት ነገሮች አሉ። …

አንደኛሁላችንም በዚህ አስፈላጊ የማዳን ስራ ላይ ለመርዳት ለፍላጎት መጸለይ እንችላለን። …

ሁለተኛ ራሳችን ትዕዛዛትን መጠበቅ አለብን። … ታማኝ አባላት የተመለሰውን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን የማካፈል ታላቅ ስራ ላይ ለመሳተፍ ሲሹ እንዲመራቸው የአዳኙ መንፈስ … ሁል ጊዜ ከእነርሱ ጋር ይሆናል።

ሶስተኛ ወንጌልን ለሌሎች ለማካፈል … በየግል ሁኔታችን እኛ ምን ማድረግ እንዳለብን ለማወቅ ለተነሳሽንት … እንዲሁም የተቀበልነውን መነሳሳት ተግባራዊ ለማድረግ መጸለይ አለብን።.”3

ወንድሞች፣ እህቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች እንደ ጓደኛዬ ሱዛና ሆነን ወንጌልን ለሌሎች ማካፈል እንችላለን? የእምነታችን ተከታይ ያልሆነን ጓደኛ እሁድ እለት ቤተክርስትያን እንዲመጣ መጋበዝ እንችላለን? ወይም የመጽሃፈ ሞርሞንን ቅጂ ለዘመድ ወይም ለጓደኛ መስጠት እንችላለን? በቤተሰብ ፍለጋ ላይ ሌሎች ቅድመ አያቶቻቸውን እንዲያገኙ መርዳት ወይም ኑ ተከተሉኝን ስናጠና በሳምንቱ ዉስጥ የተማርነውን ማካፈል እንችላለን? በህይወታችን ደስታ የሚያመጡ ነገሮችን ለሌሎች ማካፈል እና የበለጠ እንደ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን እንችላለን? ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልሱ አዎን ነው! ማድረግ እንችላለን!

በቅዱሳን መጻህፍት የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስትያን አባላት “በጌታ የወይን ስፍራ ለሰዎች የነፍስ ደህንነት እንዲያገለግሉ” ተልከዋል የሚለውን እናነባለን።138 ይህ የማዳን ስራ የምስዮናዊ ስራ፣ የተቀየሩትን ማቆየት፣ ንቁ ያልሆኑ አባላትን ማነቃቃት፣የቤተመቅደስ እና የቤተሰብ ታሪክ ስራ እና ወንጌልን ማስተማርን ያካትታል።4

እህቶችና ወንድሞች፣ ጌታ ይፈልገናል። በትቃ “እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፣ ነገር ግን ዘወትር የህይወትን ቃል በአዕምሮዎቻችሁ ውስጥ አከማቹ፣ እና ይህም በዚያች ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰው ተመዝኖ የሚሰጠው ይሰጣችኋል።”5ብሏል።

ከዚህም በተጨማሪ ቃል ገብቶልናል

“እናም መሆን ካለበት ቀኖቻችሁን ሁሉ ንስሃን በመጮህ ብታገለግሉ፣ እናም አንድም ነብስም ቢሆን እንኳን ወደ እኔ አምጡ፣ በአባቴ መንግስት ከሱ ጋረ ደስታችሁ ታላቅ ይሆናል!

“እናም አሁን፣ ወደ አባቴ ቤት ባመጣችሁት አንድ ነብስ ደስታችሁ ታላቅ ከሆነ፣ ወደ እኔ ብዙ ነብሶችን ብታመጡ ደስታችሁ ምን ያህል ይሆናል!”6

የጀመርኩት የህጻናት መዝሙር ሚያጠቃልለው በዚህ ታላቅ ቃል ነው

በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ።

ስሙን አከብራለሁ።

ትክክለኛውን ነገር አደርጋለሁ።

የሱን ብርሃን እከተላለሁ።

የእርሱን እውነት አውጃለሁ።7

እነዚህ ቃላት እውነት እንደሆኑ እናም የኛን እና በአቅራቢያችን ያሉትን ሊባርክና ወደ እርሱ እንድንመለስ የሚጠብቀን የሚወደን የሰማይ አባት እንዳለን እመሰክራለሁ ወንድሞችንና እህቶችን ወደሱ ለማምጣት ፍላጎት እንዲኖረን ጸሎቴ ነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. “የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን,” የልጆች መዝሙር መጽሃፍ 77፡፡

  2. Preach My Gospel: A Guide to Missionary Service (2018), 48.

  3. ዳለን ኤች. ኦክስ፣ “የተመለሰውን ወንጌል ማካፈል, ሊያሆና,ህዳር. 2016፣እ.ኤ.አ 58.

  4. መፅሀፈፍ 2 ቤተክርስቲያናን ማስተደር5.0ChurchofJesusChrist.org; ኤል.ዊትኒ ክሌይተን ተመልከቱ፡፡ድሮ እና አሁን የደህንነት ስራሊያሆና መስከረም 2014.23 (እ.አ.አ)

  5. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 84፥85

  6. ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች 18፡15–16

  7. “የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን” 77