2010–2019 (እ.አ.አ)
ከእግዚአብሔር ጋር የተባበሩ የቃልኪዳን ሴቶች
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ከእግዚአብሔር ጋር የተባበሩ የቃልኪዳን ሴቶች

ታልቅ እና መልካም የእግዚአብሔር ሴት ልጆች፣ ባዘጃጀላቸው በየትኛውም መንገድ እና ቦታ በማገልገል ሁሌም እናት የሚሆኑት፣ የሚመሩት እና የሚያገለግሉት ከእግዚአብሔር ጋር አጋር የሆኑ የቃልኪዳን ሴት በመሆን ነው።

ለእናንት ለመናገር በመባረኬ አመስጋኝ ነኝ። የእግዚአብሔር የቃልኪዳን ሴት ልጆች ። ዛሬ ማታ፤ የኔ አላማ እናንተ ለትጠራቸሁበት ስለታላቁ አገልግሎታችሁ ለማበርታታት ነው። አዎ፤ ድምፄን የምትስማ እያንዳንዷ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ከጌታ ጥሪን ተቀብላለች።

ጥሪያችሁ የጀመረው፤ እንደ ሴት ልጆቹ በፍጹም በሚያቃችሁ እና በሚወዳችሁ እግዚአብሔር በተመረጠላችሁ ቦታና ጊዜ፣ የምድራዊ ሕይወታቸሁን ስትጀምሩ ነው። በመንፈስ ዓለም፣ ያውቃችሁ እና ያስተምራችሁ ነበር። እናም በዓለም ታሪክ በጥቂት አጋጣሚ ወደ ሚገኝ፣ ወደ መጠመቂያው ገንዳው እንድትጋበዙ የሚያስችል እድል የምታገኙበት ስፍራ ላይ አስቀመጣችሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ በተጠራ አገልጋይ እነዚህን ቃላቶች ሲነግሩ ሰማቸሁ፥ “በኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጠኝ ስልጣን መሰረት በአብ፤ በወልድ፤ እናም በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠምቅሻለሁ። አሜን።”1

ልክ ከውሃው እንደወጣችሁ፤ ሌላ የአገልግሎት ጥሪ ተቀብላችኋል። ልክ እንደ አዲስ የቃልኪዳን የእግዚአብሔር ሴት ልጅ፤ በኃለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ጥሪን ተቀበላችሁ እናም ቃል ኪዳን ገባችሁ፤ በዚያም አባልነታችሁ ተረጋገጠ። የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችሁ ላይ ለመውሰድ፣ ትእዛዙን ለመጠበቅ እና እርሱን ለማገልገል ከእግዚአብሄር ጋር ቃልኪዳን ገባችሁ።

እያንዳንዱ ይህን ቃልኪዳን ያደረገ፣ ጌታ ለሚጠራው ወይም ለሚጠራት አገልግሎት ያ ሰው በትክክል የሚመጥን ነው። ነገር ግን የእግዚአብሄር የቃልኪዳን ሴት እና ወንድ ልጆቹ፣ ሁሉም አንድ ጠቃሚ እና አስደሳች ጥሪን ይካፈላሉ። ይህም ሌሎችን ለእርሱ ማገልገል ነው።

ለሴቶች ሲናገሩ፣ ፕሬዝዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ጌታ የእርሱን ስራ ስለመቀላቀል ያደረገውን ጥሪ አስደናቂ ማጠቃለያ ሰጥተዋል። ፕረዝደንት ኔልሰን ጥሪያችሁን በዚህ መልኩ አስረድተዋል “ጌታ ‘እንሆ፣ ስራዬ እና ክብሬ ይህ ነው፣ የሰውን ህያውነትን እና ዘለአለማዊ ህይወትን ማምጣት ነው’ ብሎአል።ሙሴ 1፥39። የእርሱ አምላኪ ሴት ደቀመዛሙርት ልጆቹም በእውነት፣ ‘የኔ ስራ እና ክብር ፣ የምወዳቸውን ይህ ሰማያዊ ግብ ላይ እንዲደርሱ መርዳት ነው’ ማለት ይችላሉ።

“ከሴቶች መለኮታዊ ተልእኮ አንዱ ፣ ሌሎች ሰዎች ሰማያዊ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ መርዳት ነው። እንደ እናት፣ አስተማሪ ወይም እንደተንከባካቢ ቅዱስ፣ ነብስ ያለው ጭቃን የተስፋዋን ቅርጽ ትሰጠዋለች። ከእግዚአብሄር ጋር በአጋርነት፣ የእርሷ መለኮታዊ ተልእኮ መንፈሶች እንዲኖሩ እና ነብሳት እንዲታነጹ መርዳት ነው። ይህ የተፈጠረችበት መለኪያ ነው። ይህም ብቃት የሚሰጥ፣ የሚያጠግብ እና ከፍ የሚያደርግ ነው።”2

የግል የአገልግሎት ተልእኮአችሁ የሚያተኩረው እንደ እናትነት፣ መሪ ወይም እንደ አገልጋይ እህት ባሉ ጥሪዎች መቼ ወይም ለምን ያሃል ጊዜ እንደሆነ አታውቁትም። ጌታ፤ ከፍቅር የተነሳ፤ የጥሪአችን ሰአትን፣ እርዝምትን፣ ወይም ቅደም ተከተልን የመምረጥ እድል አልተወልንም። ቢሆንም ግን ከቅዱሳን መጸሃፍት እና በህይወት ካሉ ነብያት ሁሉም ጥሪዎቻችሁ በዚህ ህይውት ሆነ በሚመጣው ለሁሉም የእግዚአብሄር ሴት ልጆች እንደሚመጡ ታውቃላችሁ። እናም እነዚህ ሁሉ በውድ ቤተሰብ ውስጥ ለዘላለማዊ ህይወት መዘጋጃዎች ናቸው —ከእግዚአብሔር ስጦታዎች ታላቁ ስጦታ። 3

ሁሉንም ጥረታችንን ፍጻሜውን በአእምሮአችን አድርገን አሁን በመዘጋጀት በጥበብ እናቅና። ይህ ስራ በጣም ቀላል ሆናል ምክንያቱም እነዚህ ሁሉም ጥሪዎች በአብዛኛው ተመሳሳይ ዝግጅት ስለሚጠይቁ።

አገልጋይ እህት በሚለው ጥሪ እንጀምር። አባት በሞተበት ቤተሰብ ውስጥ እንደ 10አመት ሴት ልጅ ጥሪ ተሰጥቶሽ ወይም በቅርቡ ከተማዋ በእሳት እንደተጎዳ የሴቶች መረዳጃ ፕሬዝዳንት ወይም ሆስፒታል ውስጥ ከቀዶ ህክምና እያገገምሽ ያለች—ከጌታ የእርሱ አገልጋይ ሴት እንድትሆኝ የተሰጠሽን ጥሪ ማሟላት ትችያለሽ።

እነዚያ የተለያዩ የአገልግሎት ጥሪዎች ይመስላሉ። ነገር ግን ሁሉም ጠንካራ፣ የሚወድ ልብ፣ ጌታ መንገድ ሳያዘጋጅ ምንም ትእዛዝ እንደማይሰጥ ፍራቻ የሌለው እምነት፣ እናም ለእርሱ ሄዶ ለማድረግ ፍላጎትና ዝግጅት ይፈልጋል።4

ዝግጁ ስለሆነች፤ የ10አመቷ ሴት ልጅ በቅርቡ መበለት የሆነችው እናቷ ዙሪያ እጇን በማድረግ እና እንዴት ቤተሰቧን እንደምትረዳ በጸሎት ትጠይቃለች። እንደዛ ማድረግ ትቀጥላለች።

የሴቶች መረዳጃ ፕሬዝዳንቷ ያልተጠበቀው እሳት ባካባቢዋ ከመከሰቱ በፊት ለማገልገል ተዘጋጅታለች። ሰዎቹን ለማወቅ እና ለመውደድ በቅታለች ። በኢየሱስ ክርስቶስ ያላት እምነት በአመታቶች ውስጥ አድጓል ፤ ለእርሱ ለምታደርጋችው ጥቃቅን አገልግሎቶች ለጌታ ላደረገችው ጸሎቶች መልስ ተቀብላለች። ባላት የረጅም ጊዜ ዝግጅት፤ በጭንቀት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን እና ሰዎችን ለማገልገል እህቶቿን ለማዋቀር ዝግጁ እና ጉጉ ነበረች።

በሆስፒታል ውስጥ ከቀዶ ህክምና እያገገመች ያለችው እህት፤ እንደ እርሷ ላሉት ታካሚዎች ለማገልገል ዝግጁ ነበረች። ዘመናኗን ሁሉ ለሁሉም እንግዶች እሱን ወይም እሷን ልክ እንደ ራስዋ ጎረቤት እና ጓደኛ በጌታ አገልግሎት አድርጋለች። በልቧ በሆስፒታል የማገልገል ጥሪ ስሜት ሲሰማት፤ ሌሎችን በድፍረት እና በልዩ ፍቅር ስላገለገለች፤ ሌሎቹ ታካሚዎች ቶሎ ባልተሻላት ብለው መመኘት ጀመሩ።

አገልጋይ ለመሆን እንደሚዘጋጁት ሁሉ፤ በጌታ መሪ ሆኖ ለመጠራት ያ ቀን ሲመጣ ዝግጁ መሆን እና መቻል አለባችሁ። በጥልቅ የቅዱሳን መጸሃፍት ፍቅር ስር የተተከለ ሰዎችን ያለፍርህት ለመምራት እና ለማስተማር የሚያስችል የኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ይጠበቅብናል። ከዚያም መንፈስ ቅዱስን እንደ ቋሚ አጋር ለመቀበል ዝግጁ እንሆናለን። “የወጣት ሴቶች ፕሬዝዳንት አማካሪ ድንጋጤ በበዛበት ድምጽ “እህት አልቫሬዝ ዛሬ አሟታል ማን የሷን ክፍል ይሸፍንላታል?” ስትል “አደርገዋለሁ” ለማለት ትጓጓላችሁ።

ጌታ ለዚያ ለአስደናቂው እናትነት በሚጠራችው ጊዜ ተመሳሳይ ዝግጅትን ይጠይቃል። ግን ከሌሎቹ በተለየ ተጨማሪ ወዳጅ የሆነ ልብን ይጠይቃል። በልባችሁ ከነበረው የኢየሱስ ክርስቶስ እምነት በላይ ይጠይቃል። እናም ለመንፈስ ቅዱስን ተጸዕኖ፣ ምሪት እና መጽናናትን ለመጸለይ ይበቃል ተብሎ ከተሰማቸሁ ይበልጥም ችሎታ ያስፈልገዋል።

የእናትን ፍላጎት በየተኛውም እድሜ ያለ ሰው ለማወቅ እንደሚችል በምክኒያታዊነት ለመጠይቅ ትችላላችሁ። ይሄ ዋጋ ያለው ጥያቄ ነው። ወንዶች ሁሉን ነገር ማውቅ አይችሉም፤ ነገር ግን አንድ አንድ ትምህርቶችን በራዕይ ከእግዚአብሔር መማር እንችላልን። እናም በይበልጥ በመመልከት ጭምር መማር እንችላለን፤ የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ ለመሻት አጋጣሚውን ስንጠቀም የምናየውን እናገናዝባልን።

ካትሊን ጆንስን አይሪንን ለ57 ዓመታት በትዳር ውስጥ ስገነዘባት ቆይቼለሁ ። የአራት ወንድ ልጆች እና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነች። ዛሬ ፤ ከመቶ በላይ የቅርብ ቤተስብ አባላት እና ከመቶ በላይ ወደ እናትነት ልቧ ላቀርበቻችው የእናትነትን ተጸዕኖ ጥሪ ተቀብላለች።

የፕሬዝዳንት ኔልስን ስለ ሴት መለኮታዊ አላማ የሰጡትን ፍጽም የሆነ ገለፃ አስታውሱ፡፟ የእናትነት አላማዋንም ጨምሮ “እንደ እናት፣ አስተማሪ ወይም እንደተንከባካቢ ቅዱስ፣ ነብስ ያለው ጭቃን የተስፋዋን ቅርጽ ትሰጠዋለች። ከእግዚአብሄር ጋር በአጋርነት፣ የእርሷ መለኮታዊ ተልእኮ መንፈሶች እንዲኖሩ እና ነብሳት እንዲታነጹ መርዳት ነው። ይህ የተፈጠረችበት መለኪያ ነው።”5

የቻልኩትን ያህል መንፈስ እንዳረጋገጠልኝ፤ ባለቤቴ ካትሊን ያንን ለአባታችን ሴት ልጆች የስጠውን ትዕዛዝ ተከትላለች። ለኔ ቁልፍ ቃል ሆኖ የመጣልኝ “ነብስ ያለው ጭቃን የተስፋዋን ቅርጽ ትሰጠዋለች … ከእግዚአብሄር ጋር በአጋርነት።” በጉልበት አላደረገችም። ቀረፃች ። ለተስፋዋ ናሙናዎች ነበሯት እናም ለእነዛ ለምትወዳቸው እና እናት ለሆነቻቸው ይህንኑ ለመቅረጽ ሞክራለች። በጸሎት ለዓመታት እንደተገነዘብኩት ናሙናዋ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ነበር፣።

ታልቅ እና መልካም የእግዚአብሔር ሴት ልጆች፣ ባዘጋጀላቸው በየትኛውም መንገድ እና ቦታ በማገልገል ሁሌም እናት የሚሆኑት፣ የሚመሩት እና የሚያገለግሉት ከእግዚአብሔር ጋር አጋር የሆኑ የቃልኪዳን ሴት በመሆን ነው። ፣ ልክ እንደ ቃልኪዳን ጠባቂ የእግዚአብሔር ሴት ልጅ ወደ እሱ ስትመለሱ ወደ ስማይ ቤታችሁ በምታደርጉት ጉዞ ላይ ደስታ እንድምታገኙ ቃል እገባላችኃለሁ።

እኔ እግዚአብሔር አብ ህያው እንደሆነ እናም እንደሚያፈቅራችሁ እመስክራልሁ። ጸሎቶቻችሁን ይመልስላችኋል፡፡ ተወዳጅ ልጁም በእያንዳንዱ ዝርዝር የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ይመራል። ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልስን የእርሱ በህይወት ያሉ ነቢይ ናቸው። እናም ጆሴፍ ስሚዝ እግዚአብሄር አብ እና ኢየሱስ ክርስቶስን በፓልማይራ ኒው ዮርክ በቅዱስ ጥሻ ውስጥ አይቶል እና አናግሮአል። ያ እውነት እንደሆነ አውቃልሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኛችሁ እንደሆነና እንደሚወዳችሁ እመሰክራለሁ። በሃጥያት ክፍያው አማካኝነት መንጻት ትችላላችሁ እናም ወደናንተ በሚመጡ ከፍ ባለው እና ቅዱስ ጥሪዎች ከፍ ትደረጋላችሁ። ይህንን የምመሰክረው ቅዱስ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።”

አትም