2010–2019 (እ.አ.አ)
መንፈሳችን አካላቶቻችንን እንዲቆጣጠር ስልጣን መስጠት፡፡
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


መንፈሳችን አካላቶቻችንን እንዲቆጣጠር ስልጣን መስጠት፡፡

በዚህ ህይወት ልንማራቸው ከምንችላቸው ይበልጥ አስፈላጊ ነገሮች አንዱ በዘላለማዊ መንፈሳዊ ተፈጥሯችን ላይ እንዴት እንደምናተኩር እና ክፉ ፍላጎቶቻችንን እንዴት እንደምንቆጣጠር መሆኑ ለእኔ ግልጽ ይመስለኛል፡፡

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ባለፈው ዓመት የጥቅምት ወር አጠቃላይ ጉባኤ ሲቃረብ ጥቅምት 3 ቀን 1918 ዓ.ም.ለፕሬዝዳንት ጆሴፍ ኤፍ. ስሚዝ ስለመንፈሳዊው አለም የተሰጠውን ራእይ 100 ኛ ዓመት ለማጉላት የጉባኤ ንግግሬን አዘጋጅቼ ነበር።

ንግግሬን ለትርጉም ከሰጠሁኝ ከጥቂት ቀናት በኋላ የተወደደችው ዘላለማዊ አጋሬ ባርባራ ምድራዊ የሙከራ ጊዜዋን አጠናቀቀች እናም ወደ መንፈሳዊው አለም ተሻገረች፡፡

ቀኖቹ ወደ ሳምንት ሲቀየሩ ከዚያም ወደ ወራቶች አሁን ደግሞ ባርባራ ካረፈች አመት ቢሞላትም፤ ይህንን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለአብዝቼ እያደነኩኝ እራሴን አገኘዋለሁ: “በሞት ላጣችኋቸው በተለይም የክብር ትንሳኤ ተስፋ ለሌላቸው ባለቀሳችሁ መጠን በአንድ ላይ በክብር ትኖራላችሁ፡፡“1 ባርባራ እና እኔ ለ67 አመታት “በፍቅር ለመኖር“ ተባርከን ነበር፡፡ ነገር ግን “ላጡት ነገር ማንባት“ ምን ማለት እንደሆነ በጣም ግላዊ በሆነ መንገድ ተምሪያለሁ፡፡ “አቤት እንዴት እንደምወዳት እና እንደምትናፍቀኝ“

ብዙዎቻችን ሌሎች እስኪለዩን ድረስ ለእኛ የሚያደርጉትን ነገር ለመለየት እንደምንቸገር እገምታለሁ፡፡ ባርባራ ሁልጊዜ ስራ የበዛባት እንደሆነች አውቃለሁ ነገርግን ቤተሰብ፣ ቤተክርስቲያን እና ማህበረሰብ በእርሷ ላይ ያለውን የማያቋርጥ ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ አልተረዳሁም ነበር፡፡ ቤተሰባችን እንዲሠራ በዓመታት ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት የተደጋገሙ በየዕለቱ የተቀደሱ ጥረቶች ነበሩ። እናም በዚህ ሁሉ በቤተሰባችን ውስጥ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ ወይም ደግነት የጎደለው ቃል ስትናገር ሰምቶ የሚያውቅ ማንም የለም፡፡

በዚህ ባለፈው አመት የትዝታ ጎርፎች አጥበውኛል፡፡ የሰባት ልጆች እናት ለመሆን ያደረገችውን አካላዊ ጥረት የሚፈልግ ምርጫ አስቤበታለሁ፡፡ የቤት እመቤትነት መሆን የምትፈልገው ብቸኛው የሙያ መስክ ነበር፣ እናም በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ባለሙያ ነበረች፡፡

ብዙውን ጊዜ እኔና ልጆቼን በምትከታተልበት ሁኔታ እደነቃለሁ፡፡ ምግብ ማዘጋጀት በራሱ አስቸጋሪ ስራ ነበር፣ በየሳምንቱ ቤተሰባችን የሚያወጣውን የሚታጠብ የልብስ ክምር እንደማጠብ ያሉ ተግባሮችን መጥቀስ ትተን ጫማዎችን ማስተካከል እና ልጆቹ የሚበቃቸውን ልብስ እንዲለብሱ የማድረግ ስራዎች ነበሩ፡፡ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ለኛ አስፈላጊ ለሆኑ ጉዮች ፊታችንን የምናዞረው ወደእርሷ ነው፡፡ እናም ለእኛ አስፈላጊ የነበሩ በመሆናቸው ምክንያት ለእርሷም አስፈላጊ ነበሩ፡፡ በአንድ ቃል እጹብ ድንቅ ነበረች—እንደሚስት፣ እንደእናት እንደጓደኛ እንደጎረቤት እና እንደእግዚያብሄር ሴት ልጅ፡፡

አሁን ወደሚቀጥለው ተሸጋግራለች፣ በህይወቷ የመጨረሻ ወራት ወደ ቤት ስመለስ ከእሷ አጠገብ ለመቀመጥ በመምረጤ የአንዳንድ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን መጨረሻ በመደጋገም ስንመለከት እጇን በመያዜ ደስተኛ ነኝ — ምክንያቱም የአልዛይመር በሽታ ከግማሽ ቀን በፊት እንዳየቻቸው ለማስታወስ ስለማያስችላት ነበር፡፡ እነዚያ ልዩ እጅ የመያዝ ጊዜ ትዝታዎች አሁን ለእኔ በጣም ውድ ናቸው ፡፡

ወንድሞች እና እህቶች እባካችሁን ወደቤተሰባችሁ አባላት አይኖች ውስጥ በፍቅር የመመልከትን እድል አትጡ ፡፡ ልጆች እና ወላጆች እርስ በእርሳችሁ ተፈላለጉ፣ እንዲሁም ፍቅራችሁን እና አድናቆታችሁን ግለጹ፡፡ አንዳንዶቻችሁ እንደ እኔ እንዲህ ያለው አስፈላጊ ግንኙነት ካለፈ በኋላ አንድ ቀን ልትነቁ ትችላላችሁ፡፡ እያንዳንዱ ቀን ልባችሁ በምስጋና ፣ በጥሩ ትዝታ፣ አገልግሎት እና ብዙ ፍቅር ተሞልቶ በህብረት ኑሩ፡፡

በዚህ ባለፈው አመት ውስጥ ስለሰማይ አባታችን እቅድ እሰከዛሬ ካደረኳቸው የበለጠ በጥልቀት አስቤያለሁ። አልማ ልጁን ኮሪአንተንን ሲያስተምር “ታላቁ የደስታ እቅድ“ሲል ጠቅሶታል፡፡2

ዕቅዱን ሳስብ ወደ አዕምሮዬ ደጋግሞ የሚመጣው ቃል “መልሶ መገናኘት” የሚለው ነው፡፡ በአፍቃሪ ሰማያዊ አባታችን የተነደፈ በውስጡም ታላቅ እና ክብራማ ቤተሰብን መልሶ የማገናኘት ችሎታ ያለው—በእግዚያብሄር ቤት ባሎችን እና ሚስቶችን ፣ ወላጆችን እና ልጆችን፣ ትውልድን ከትውልድ ለዘላለም የሚያጣምር እቅድ ነው።

ያ ሃሳብ መጽናናትን እና እንደገና ከባርባራ ጋር እንደምሆን ማረጋገጫ አምጥቶልኛል፡፡ ምንም እንኳን አካሏ በእድሜዋ መገባደጃ ላይ የተጎሳቆለ ቢሆንም መንፈሷ ጠንካራ፣ ጨዋ እና ንጹህ ነበር፡፡ ቀኑ ሲመጣ በልበሙሉነት እና በሰላማዊ ማረጋገጫ “በአስደሳቹ በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት” መቆም እንድትችል በሁሉም ነገር እራሷን አዘጋጅታ ነበር ፡፡3 ግን እነሆኝ ፣ እኔ በሁለት ቀናት ውስጥ 91 ዓመት አመቴ ፣ አሁንም እንዲህ እያልኩ አስባለሁ ፣ “ዝግጁ ነኝን? እጆችዋን በድጋሚ ለመያዝ የሚያስችለኝን ማድረግ የምችለውን ነገር ሁሉ እያደረኩኝ ነው?

እጅግ ቀላሉ መሰረታዊ በህይወት እርግጥ የሆነው ነገር ይህ ነው፤ ሁላችንም እንሞታለን፡፡ የምንሞተው አርጅተንም ሆነ በወጣትነታችን፣ በቀላሉም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ፣ ሀብታምም ሆንን ድሃ ፣ የተወደድንም ሆንን ብቸኝነት የሚሰማን ማናችንም ከሞት አናመልጥም፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት ፕሬዘደንት ጎርደን ቢ. ሒንክሊ ስለዚህ ጉዳይ በተለይ ትርጉም ያለው ነገር ተናግረዋል፤ “ዋስትናው ምንኛ ጣፋጭ ነው ፣ በትክክል ካገባን እና በትክክል ከኖርን ፣ ግንኙነታችን ይቀጥላል ፣ ምንም እንኳን ሞት አይቀሬ ቢሆን እና ጊዜው ቢነጉድም ይህንን ከማዋቃችን የሚመጣው ሰላም ምንኛ ያጽናናል“4

አኔ በርግጠኝነት በትክክል አግብቻለሁኝ! ያንን በተመለከተ ጥርጥር ሊኖር አይችልም፡፡ ነገርግን ያ በቂ አይደለም እንደ ፕሬዚደንት ሂንክሊ፡፡ በትክክል መኖርም ይኖርብኛል፡፡5

ዛሬ፣ ብዙውን ጊዜያችሁን በማህበራዊ ሜዲያ ላይ የምታሳልፉ ከሆነ “በትክክል መኖር” ማለት የሚያደናግር ሃሳብ ሊሆን ይችላል፣ በተለይ ማንኛውም ድምጽ ስለእግዚያብሄር እና ለልጆቹ ስላለው እቅድ እውነትን ወይም ሃሰትን መናገር በሚችልበት ሁኔታ፡፡ ከምስጋና ጋር የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ስንሞት የተሻልን የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ ዘላለማዊ እውነተኛ የወንጌል መርሆዎች አሉን፡፡

ከመወለዴ ከጥቂት ወራት አስቀድሞ፣ ሃዋርያው አያቴ ሽማግሌ ሜልቪል ጄ.ባላርድ ለብዙዎች በትክክል የመኖር አስፈላጊነትን ምንነት የያዘ ንግግር አደረገ፡፡ “ለነፍስ የሚደረግ ትግል“ የሚል ርእስ የነበረው ንግግሩ በአካላችን እና በዘላለማዊው መንፈሳችን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ያተኩር ነበር፡፡

ሰይጣን “የነፍሳችን ጠላት“ “በምኞት፣በምግብ ወይም ሌሎች አካላዊ ፍላጎቶች፣ በስጋ ምኞት”አማካኝነት እንደሚያጠቃን በማብራራት “ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ሊያገጥመው የሚችለው ታላቁ ግጭት…ከራስ ጋር የሚደረገው ጦርነት ይሆናል“ ብሎ ነበር፡፡6 “ስለዚህ ዋነኛው ጦርነት በመለኮታዊ እና መንፈሳዊ ተፈጥሯችን እና በሰው ስጋዊ ተፈጥሮ መካከል ነው፡፡“ ወንድሞች እና እህቶች “ሁሉን በሚያስተምረው“ በመንፈስ ቅዱስ በጎ ተጽእኖ እና በክህነት ሃይል እና በረከቶች መንፈሳዊ እርዳታ እንደምንቀበል አስታውሱ፡፡ 7 እርዳታ በክህነት ሃይል እና በረከትም ሊመጣ ይችላል፡፡

አሁን ልጠይቃችሁ “እናንተ ጋር ይህ ጦርነት እንዴት ነው? “

ፕሬዘደንት ዴቪድ ኦ.ማኬይ እንዲህ ብለዋል “የሰው ልጅ በምድር የሚኖርበት ምክንያት ጥረቱን ፣ አዕምሮውን ፣ ነፍሱን የሚያደርገው ለአካላዊ ተፈጥሮው ምቾት እና እርካታ አስተዋጽኦ በሚያደርጉ ነገሮች ላይ እንደሆነ ወይም መንፈሳዊ ባሕርያትን እንደ ሕይወቱ ዓላማ እንደሚያደርግ ለመፈተን ነው፡፡”8

ይህ በስጋዊ እና በመንፈሳዊ ተፈጥሮዎቻችን መካከል የሚደረገው ውጊያ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በመጨረሻው ንግግሩ ንጉስ ቢንያም እንዲህ ሲል አስተማረ፣ “ተፈጥሯዊው ሰው ከአዳም ውድቀት ጀምሮ ለእግዚያብሄር ጠላት ነው፣ እናም እርሱም ለመንፈስ ቅዱስ ግብዣ ፈቃደኛ ካልሆነና፣ ተፈጥሯዊ ሰውነቱን ካልቀየረ እናም በጌታ በክርስቶስ የሃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ እስካልሆነ በስተቀር”9

ሃዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ሲል አስተምሯል “እንደስጋ ፈቃድ የሚኖሩ የስጋን ነገር ያስባሉና እንደመንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ፡፡“

“ስለስጋ ማሰብ ሞት ነውና ስለመንፈስ ማሰብ ግን ህይወትና ሰላም ነው፡፡“10

በዚህ ህይወት ልንማራቸው ከምንችላቸው ይበልጥ አስፈላጊ ነገሮች አንዱ በዘላለማዊ መንፈሳዊ ተፈጥሯችን ላይ እንዴት እንደምናተኩር እና ክፉ ፍላጎቶቻችንን እንዴት እንደምንቆጣጠር መሆኑ ለእኔ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ይህ ያን ያህል አስቸጋሪ መሆን የለበትም፡፡ ከሥጋዊ አካላችን በላይ ረዘም ላለ ጊዜ የነበረው መንፈሳችን በቅድመምድር ዓለም ውስጥ ክክፋት ጽድቅን በመምረጥ ረገድ ቀድሞውኑ ስኬት አግኝቷል ፡፡ ምድር ከመሰራቷ በፊት ይወዱን ከነበሩ እና አሁንም ከሚወዱን ሰማያዊ ወላጆች ጋር እንደ ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻቸው ሆነን በመንፈሳዊው አለም ኖረናል፡፡

እናም አዎ፣ በዚያ ቅድመ ምድር አለም ህይወትን የሚቀይር ውሳኔ እና ምርጫ ማድረግ ነበረብን፡፡ በዚህ ምድር ላይ ኖሮ የነበረ ወይም ወደፊት የሚኖር እያንዳንዱ ሰው የሰማያዊ አባትን የደህንነት እቅድ ለመቀበል ለመምረጥ አስፈላጊ ውሳኔ አድርጓል፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችንም ወደ ምድር የመጣነው ከተረጋገጠ መንፈሳዊ ተፈጥሮ እና ዘላለማዊ እጣ መዝገብ ጋር ነው።

ለአፍታ ስለዚያ አስቡ፡፡ እውነተኛ ማንነታችሁ ይህ ነው ፣ እና ሁልጊዜ እንደዚሁ ነበራችሁ:ከዘላለማዊ መንፈሳዊ ምንጭ እና ከሚትረፈረፉ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የወደፊት አጋጣሚዎች ጋር የእግዚያብሄር ወንድ እና ሴት ልጆች። እናንተ በመጀመሪያም ፣ ከሁሉም በላይ እና ሁል ጊዜ—መንፈሳዊ ፍጡር ናችሁ ፡፡ እናም አንድ ሰው ሥጋዊ ተፈጥሮን ከመንፈሳዊ ተፈጥሮ ለማስቀደም ሲመርጥ፣ከእውነተኛው እና ከትክክለኛው መንፈሳዊ ማንነቱ ጋር የሚቃረን ነገር እየመረጠ ነው፡፡

አሁንም ሥጋ እና ምድራዊ ግፊቶች ውሳኔ አሰጣጥን እንደሚያወሳስቡ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ በቅድመ ሟች መንፈሳዊ ዓለም እና በዚህ ሟች ዓለም መካከል ባለው የመርሳት መጋረጃ ምክንያት አንድ ሰው ከእግዚአብሔር እና ከመንፈሳዊ ተፈጥሮው ጋር ያለውን የግንኙነት እይታ ሊያጣ ይችላል ፣ እናም ሥጋዊ ተፈጥሮው አሁን ለሚፈልገው ነገር ቅድሚያ ሊሰጥ ይችላል። ከስጋ ነገሮች የመንፈስ ነገሮችን ለመምረጥ መማር ይህ የምድራዊ ልምምድ የሰማይ አባት እቅድ ክፍል ከሆነበት ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው። በተጨማሪም ለዚህ ነው እቅዱ በጠንካራ እና እርግጠኛ መሠረት በሆነው በጌታችን እና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ላይ የተገነባው ፣ እናም ሀጢያቶቻችን፣ ለሥጋችን ስንል የምናደርጋቸውን ስህተቶችንም ጨምሮ በቋሚ ንስሃ እንዲወገዱ እናም እኛ መንፈሳዊነት ላይ በማተኮር መኖር እንድንችል ፡፡ ከክርስቶስ መንፈሳዊ ትምህርት ጋር ለመስማማት ሥጋዊ ፍላጎቶቻችንን የምንቆጣጠርበት ጊዜ አሁን ነው ፡፡ ለዚህ ነው የንስሃ ጊዜያችንን ማዘግየት የማይገባን፡፡11

ስለሆነም ንስሐ ከራስ ጋር በምናደርገው ውጊያ አስፈላጊ መሣሪያ ይሆናል ፡ ባለፈው አጠቃላይ ጉባኤ ፕሬዚደንት ረሰል ኤም.ኔልሰን ይህንኑ ውጊያ ጠቅሰው ሲያስታውሱን “ንስሃ ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ ለመለወጥ እንመርጣለን! አዳኛችን ልንሆን ወደምንችለው ምርጥ እኛነታችን እንዲለውጠን እንፈቅድለታለን፡፡ በመንፈስ ለማደግ እና ደስታን ለመቀበል እንመርጣለን—በእርሱ ነጻ የመውጣት ደስታ፡፡ ንስሃ ለመግባት በምንመርጥበት ጊዜ ይበልጥ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆንን እንመርጣለን!“12

ማታ ማታ ውሎዬን ከሰማይ አባት ጋር በጸሎት ስገመግም ፣ ምንም አይነት ስህተት ሰርቼ ከሆነ ይቅር እንድባል እጠይቃለሁ እንዲሁም ነገ የተሸልኩኝ ለመሆን ለመጣር ቃል እገባለሁ፡፡ ይህ መደበኛ የቀን ተቀን ንስሐ መንፈሴ ስጋዬን ማን ሃላፊ እንደሆነ እንዲያስታውሰው እንደሚረዳው አምናለሁ፡፡

ሁላችን ያለን ሌላኛው ሀብታችን የጌታችንን እና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የኃጢያት ክፍያ እና ፍቅር ለማስታወስ የቅዱስ ቁርባንን በመካፈል እራሳችንን በመንፈስ የምናድስበት ሳምንታዊ አጋጣሚ ነው።

ወንድሞች እና እህቶች ወደ ውድ ወዳጆቻቸሁን በደስታ ወደ ምታግኙበት ወደ መንፈስ አለም የምትገቡበት ቀን ሳይመጣ ሁላችሁም ራሳችሁን ትንሽ ገታ እንድታደርጉ እና አሁን ሥጋዊ ተፈጥሯችሁን በማስገዛት እና መለኮታዊነታችሁን ፣መንፈሳዊ ተፈጥሯችሁን ሃይል በመስጠት ምን ደረጃ ላይ እንዳላችሁ እንድታስቡ አበረታታቸኋለሁ ፤ ለዚህም እመስክራለሁ እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በትህትና እፀልያለሁ አሜን፡፡ ፡፡ 12

አትም