2010–2019 (እ.አ.አ)
ስሙን ማክበር
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


ስሙን ማክበር

በቃልኪዳን ማንነት እና በአባልነት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠራለን፡፡

ወላጆች የልጃቸውን መወለድ በጉጉት ሲጠብቁ ፣ ለአዲሱ ህጻን ስም የማውጣት ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ምናልባት ስትወለዱ በቤተሰባችሁ ውስጥ ለትውልዶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ስም ተቀብላችኋል፡፡ ወይም ምናልባት የተሰጣችሁ ስም በተወለዳችሁበት አመት ወይም አካባቢ ታዋቂ ነበር፡፡

ነቢዩ ሄለማን እና ባለቤቱ ለህጻን ወንድ ልጆቻቸው ኔፊ እና ሌሂ ትርጉም ያለው የቤተሰብ ስም ሰጥተዋቸዋል፡፡ ሄለማን ለወንድ ልጆቹ ይህን ነገራቸው፡፟

“የመጀመሪያ ወላጆቻችንን ስም ሰጥቻችኋለው …ስማችሁን ስታስቡ እነርሱን ታስታውሱ ዘንድ ነው ፤ እናም እነርሱን ስታስታውሱ ስራቸውን ታስታውሱ ዘንድ ነው፤…መልካም እንደነበሩ እንዴት እንደተባለና ፣ ደግሞ እንደተጻፈ እንድታውቁ ዘንድ ነው፡፡”

“ስለዚህ ልጆቼ መልካም የሆኑትን እንድታደርጉ እፈልጋለው፡፡”1

የኔፊ እና የሌሂ ስም የወላጆቻቸውን መልካም ስራ እንዲያስታውሱ ረድቷቸዋል እናም መልካምንም እንዲያረጉ አበረቷቷቸዋል፡፡

እህቶች ፤ የትም ቦታ ብንኖር፣ ምንም አይነት ቋንቋ ብንናገር ወይም 8 አመት ወይ 108 አመት ብንሆን ይህን ተመሳሳይ አላማ ያለው ልዩ ስም እንጋራለን፡፡

“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና…ሁላችሁ በክርስቶስ እየሱስ አንድ ናችሁና፡፡”2

እንደ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን “በጥምቀት ስነስርአት በመጀመሪያ የክርስቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ ፍቃደኛ እንደሆንን ቃል ገብተናል፡፡”3 በዚህ ቃልኪዳን ውስጥ እሱን ሁልጊዜ ለማስታወስ ፣ ትእዛዛቱን ለመጠበቅ፣ እና ሌሎችን ለማገልገል ቃል ገብተናል፡፡ ይህን ቃልኪዳን ለመፈጸም ያለን ፍቃደኝነት በያንዳንዱ የሰንበት ቀን ቅዱስ ቁርባንን ስንካፈል ይታደሳል እናም “በአዲሱ ህይወት በመመላለስ” በሚመጣው በረከት እንደሰታለን፡፡ 4

ስንወለድ የተሰጠን ስም የግል ማንነታችንን ያንጸባርቃል እናም በምድራዊ ቤተሰባችን ውስጥ አባልነት ይሰጠናል፡፡ ነገር ግን በጥምቀት ድጋሚ ስንወለድ”፣ስለማንነታችን ያለን መረዳት አድጓል፡፡ እናም አሁን በገባችሁት ቃል ኪዳን የተነሳ የክርስቶስ ልጆች ተብላችሁ ትጠራላችሁ፣…እነሆም ፣…በመንፈስ ወልዷችኋል፤ ልባችሁ በስሙ በማመን ተለውጧል ብላችኋልና፤ ስለዚህ እናንተ ከእርሱ ተወልዳችኋል፡፡5

ስለዚህ በቃልኪዳን ማንነት እና በአባልነት ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንጠራለን፡፡ “እናም ሁሉን በሚችለው ጌታ በክርስቶስ ስም ካልሆነ በስተቀር ለሰው ልጆች ደህንነት እንዲመጣ የሚሰጥ ምንም ስም ወይም መንገድ፣ ወይም ዘዴ የለም፡፡”6

የእየሱስ ስም ከመወለዱ ከብዙ ጊዜ በፊት ይታወቅ ነበር ። ለንጉስ ቢንያም፤ አንድ መልአክ ተነበየለት ፣ “እናም እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ… ተብሎ ይጠራል፤ እናም እናቱ ማርያም ተብላ ትጠራለች፡፡”7 የሱ “የቤዛነት ፍቅር” 8ወንጌሉ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ፣ ከአዳምና ከሄዋን ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ ፣ “ለሀጢያታቸው ስርየት የትኛውን ምንጭ መመልከት እንዳለባቸው” እንዲያውቁ፤ ለእግዚአብሄር ልጆች እንዲታወቅ ሆኗል፡፡ 9

ባለፈው አመት፣ ፕሬዘደንት ራስል ኤም ኔልሰን ለእህቶች “የተበተኑትን እስራኤላዊያን እንዲሰበሰቡ በመርዳት የወደፊቱ እንድታቀኑ” በማለት ነብያዊ ልመና አድርሰዋል፡፡ መጽሀፈ ሞርሞንን እንድናነብ እና “ስታነቡም፣ ስለ አዳኝ የሚናገረውን ወይም የሚያመለክተውን እያንዳንዱ ጥቅስ በቀለም እንድታስመለክቱ አበረታታችኋለሁ” ብሎ ጋብዞናል፡፡ ከዚያም፣ “ስለክርስቶስ በመናገር፣ በክርስቶስ በመደሰት፣ እና ስለክርስቶስ ለቤተሰቦቻችሁና ለወዳጆቻችሁ ለመስበክ በሀሳብ ተዘጋጁ” ብሎ ጠይቆናል።2 ምናልባት “እናንተ እና እነሱ ወደ አዳኙ ይቀርባሉ… እናም ለውጦች፣ እንዲሁም ታምራቶች፣ መከሰት ይጀምራሉ ብሎ የገባውን የቃልኪዳን ፍሬ ማየት ጀምራችሁ ይሆናል፡፡10

አዳኙን ሁልጊዜ ለማስታወስ የገባነው ቃልኪዳን —ብዙ ህዝብ በተስበስበበት ስፍራ ውስጥ ሆነን ወይም ድርጊታችንን ከእግዚአብሄር በስተቀር ማንም በማያቅበት ጸጥ ባለ ስፍራችን ውስጥ ለእውነት እና ጽድቅ እንድንቆም ጥንካሬ ይሰጠናል፡፡ እሱን ስናስታውሰው እና ስሙን ስንሸከም፣ ራስን ዝቅ ለሚያደርጉ ንጽጽሮች ወይም ከልክ ላለፉ ፍርዶች ቦታ የለንም፡፡ አይናችን አዳኙ ላይ ሆኖ፣ ራሳችንን በትክክለኛው ማንነታችን እንመለከታለን—እንደ ተወዳጅ የእግዚአብሄር ልጅ፡፡

የኛን ቃልኪዳን ማሰታወሳችን አለማዊ ጭንቀቶችን ጸጥ ያሰኛል፣ የግል ጥርጣሬን ወደ ድፍረት ይቀይራል፣ እናም በፈተና ጊዜያት ውስጥ ተስፋ ይሰጣል፡፡

እናም በቃልኪዳኑ መንገድ ላይ ከእርምጃችን ተደናቅፈን ስንወድቅ፤ የሱን ስም እና ለኛ ያለውን የፍቅር ደግነት ብቻ ነው ማስታወስ ያለብን፡፡ “እርሱ ሁሉም ስልጣን፣ ሁሉም ጥበብ፣ እናም ሁሉም ግንዛቤ አለውና፤ ሁሉንም ነገር ያውቃልና፣…ንስሀ ለሚገቡት በስሙ ለሚያምኑት መሀሪ ነውና፡፡”11 በእርግጥም ለነዛ ፤ በተሰበረ ልብ እና በተዋረደ መንፈስ፣ “የተሻለ ለማድረግ እናም የተሻለ ለመሆን” ለሚሹ ሁሉ ከእየሱስ ስም በላይ ጣፋጭ ስም የለም፡፡12

ፕረዘዳንት ኔልሰን “ጸጥተኛ እና የተመቻቸ ክርስቲያን መሆን የምችሉበት ጊዜ አልፏል ብለው አስተምረዋል፡፡ ሀይማኖታችሁ እሁድ ላይ ቤተክርስትያን መገኘት ብቻ አይደለም፡፡ ከእሁድ ጠዋት እስከ ቅዳሜ ማታ ድረስ እውነተኛ ተከታይ ሆነን መገኘት ነው፡፡ … ‘የግማሽ ጊዜ’ የጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን ብሎ ነገር የለም፡፡”13

የእየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ ፍቃደኝነታችን ከቃላቶች ልውውጥ የበለጠ ነው፡፡ ትግበራ የሌለው ቃልኪዳን ወይም በባህል እንዲሁ የተፈጠረ አይደለም፡፡ አንድ ግለሰብ ሁኔታውን ሲቀይር የሚደረግ ስርአተ ባህል አይደለም ወይም የምናደርገው የስም ምልክት አይደለም፡፡ እንዲሁ መደርደሪያ ላይ ምናስቀምጠው ወይም ግድግዳ ላይ የምንሰቅለው ነገር ነው እያለ አይደለም፡፡ የሱ ስም በልባችን ላይ ተጽፎ ፣ እና “[በእኛ] ምስል ተቀርጾ” ፤ “የሚቀመጥ”14 ነው፡፡15

የአዳኙ ቤዛዊ መስዋእትነት ሁልጊዜ በሃሳባችን፣ በድርጊታችን፣ እና ከሌሎች ጋር ባለን መስተጋብር ሁሉ መታወስ አለበት፡፡ እሱ ስማችንን ብቻ ሳይሆን የሚያስታውሰው ፤ እኛንም ሁልጊዜ ያስታውሰናል፡፡ አዳኙ እንዳስተማረው፥

“በእውኑ ሴት ከማህፀንዋ ለተወለደው ወንድ ልጅ እስከማትራራ ድረስ የምታጠባውን ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነርሱ ይረሱ ይሆናል እኔ ግን አልረሳሽም።

“እነሆ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለው፡፡”16

ፕሬዘደንት ጆርጅ አልበርት ስሚዝ “የተሸከማችሁትን ስሞች አክብሩ፣ ምክንያቱም አንድ ቀን… ለሰማይ አባታችሁ… በነዛ ስሞች ምን እንዳደረጋችሁ የምትናገሩበት እድል እና ግዴታ ይኖራችኋል፡፡”ብለው አስተምረዋል፡፡17

በጥንቃቄ እንደተመረጡት የኔፊ እና የሌሂ ስሞች፣የጌታ እየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ተከታይ እንደሆንን ሊባል እና ሊጻፍ ይችላል? በፍቃደኝነት በላያችን ላይ የወሰድነውን የእየሱስ ክርስቶስን ስም እናከብራለን? ለፍቅራዊ ደግነቱ እና ለአዳኝ ሀይሉ “አገልጋይ እና ምስክሮች”ም ነን?18

ብዙም ሳይቆይ፤ መጽሀፍ ሞርሞን እያዳመጥኩ ነበር፡፡ በ 2ተኛ ኔፊ የመጨረሻው ምእራፍ ውስጥ ኔፊ ከዚህ በፊት ሳነብ በተመሳሳይ መልኩ ያላነበብኩትን ነገር ሲናገር ሰማሁት፡፡ በመዝገቡ ሁሉ ውስጥ ስለ “አዳኙ”፣ “የእስራኤል ቅዱስ”፣ “የእግዚአብሄር በግ”፣ እና “መሲህ” ያስተምራል እናም ይመሰክራል፡፡ ግን መዝገቡን ሲዘጋ እኚህን ቃላት ሲናገር ሰማሁት፡ “በግልጽነት እደሰታለው፤ በእውነት እደሰታለው፣ በእኔ እየሱስ እደሰታለው፣ ነፍሴን ከሲኦል አድኗታልና፡፡”19 እኚህን ቃላት ስሰማ ልቤ ስለተደሰተች ደጋግሜ ማዳመጥ ነበረብኝ፡፡ የራሴን ስም እንደማውቀው እና ምላሽ እንደምሰጥበት ሁሉ ያንን ጥቅስንም አወኩት እናም ምላሽም ሰጠሁ፡፡

ጌታ “አዎን ስሜን ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ ይህ የተባረከ ህዝብ ነው፤ በስሜም ይጠራሉና፣ እናም እነርሱ የኔ ናቸው፡፡”ብሏል፡፡20

እንደ ኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችን 21የሱን ስም በፍቅር፣በትጋት፣ እና በመልካም ስራዎች እናከብራለን ፤ “የክርስቶስን ስም በደስታ [በላያችን ላይ እንወስዳለን]”፡፡ “የእግዚአብሄር በግ፣ አዎን እንዲያውም የዘላለማዊ አባት ልጅ” እንደሆነ መሰክራለው፡፡22 በተቀደሰ ልጁ በእየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን፡፡

አትም