2010–2019 (እ.አ.አ)
ፍሬ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ፍሬ

አይኖቻችሁን እና ልቦቻችሁን በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእርሱ ብቻ በሚገኘው ዘላለማዊ ደስታ ላይ ያተኮሩ ያድርጓቸው።

ምን እንደምታስቡ አውቃለሁ! አንድ ተጨማሪ ንግግር ብቻ፣ከዚያ ፕሬዘዳንት ራስል ኤም. ኔልሰን ሲናገሩ እንሰማለን። ተወዳጁን ነቢያችንን እየጠበቅን ሳለን ለጥቂት ደቂቃዎች ንቁ ላደርጋችሁ ተስፋ በማድረግ አንድ መሳጭ ርእስ መርጫለሁ፡የእኔ ርእሰ ጉዳይ ፍሬ ነው፡፡

ፍሬ

እንጆሪዎች ፣ሙዞች፣ሃብሃቦች እና ማንጎዎች ወይም ይበልጥ እንግዳ የሆኑት እንደ ኪዋኖ ወይም ሮማን ያሉ ፍራፍሬዎች ከቀለም፣ሸካራነት፣እና ከጣፋጭነት ጋር ፍራፍሬዎች ለረዥም ጊዜ ውድ ምግብ ናቸው፡፡

በምድር አገልግሎቱ ጊዜ፣ አዳኙ መልካም ፍሬን ዘላለማዊ ዋጋ ካላቸው ነገሮች ጋር አነጻጽሯል፡፡። “ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ“ ብሏል፡፡1 መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ 2 “ለዘላለም ህይወት ፍሬን“ እንድንሰበስብ አበረታቶናል፡፡3

በመጽሃፈ ሞርሞን ውስጥ በደንብ በምናውቀው ግልጽ ህልም ነብዩ ሌሂ ራሱን ”በጨለማ እና የማያስደስት ምድረበዳ” አግኝቶታል፡፡ የቆሸሸ ውሃ፣የጨለማ ጭጋግ፣ የማይታወቅ መንገድ እና የተከለከለ መንገድ እንዲሁም “አንድን ሰው ደስተኛ ለማድረግ መልካም ወደሆነ“ ወደ ቆንጆ ዛፍ የሚያመራ ከብረት በትሩ4 ጋር የሚወስድ የጠበበና የቀጠነ መንገድ አለ፡፡ ሌሂ ስለሕልሙ ሲተርክ እንዲህ ይላል: “ከፍሬዋ …ተካፈልኩኝ….ከዚህ በፊት ከቀመስኩት ሁሉ ጣፋጭ እንደሆነች አየሁ…፡፡ ከዚህች ፍሬ ስካፈልም ይህም ነፍሴን በደስታ ሞላው፡፡” ከሌላው ፍሬ ሁሉ በላይ አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁና፡፡” 5

የህይወት ዛፍ ከጣፋጭ ፍሬው ጋር

የዛፉ እና የፍሬው ትርጉም

ይህ ዛፍ ከውድ ፍሬው ጋር ምንድን ነበር የሚያመለክተው? “የእግዚያብሄርን ፍቅር“ ይወክላል 6እንዲሁም የሰማያዊ አባታችንን ድንቅ የደህንነት እቅድ ይናገራል፡፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል።7

ይህ ውድ ፍሬ አቻ የሌለውን የአዳኙን የሃጢያት ክፍያ አስደናቂ በረከቶች ያመለክታል፡፡ ከሞትን በኋላ እንደገና መኖር ብቻ አይደለም ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለን እምነት ፣ንስሃ እና ትእዛዛቶችን በመጠበቅ ሃጢያቶቻችን ይቅር ሊባሉልን ይችላሉ ከዚያም አንድ ቀን በአባታችን እና በልጁ ፊት ጽዱ እና ንጹህ ሆነን እንቆማለን፡፡

ከዛፉ ፍሬ መካፈላችን በተጨማሪም የተመለሰውን ወንጌል ስርአቶች እና ቃልኪዳኖች እንደምንቀበል ያመለክታል—መጠመቅ፣የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል እና ከላይ የሃይል ቡራኬን ለመቀበል ወደእግዚያብሄር ቤት መግባት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ቃልኪዳኖቻችንን በማክበር ጻድቅ ከሆኑ ቤተሰቦቻችን ጋር ለዘላለም የመኖር መጠነሰፊ ቃልኪዳን እንቀበላለን፡፡8

መልአኩ “ለነፍስም በጣም ደስ የሚያሰኝ ነው“ ብሎ መግለጹ አያስደንቅም፡፡9 በእውነትም እንደዚያ ነው!

እውነተኛ ሆኖ የመኖር ፈታኝ ሁኔታ

ሁላችንም እንደተማርነው የተመለሰውን ወንጌል ውድ ፍሬ ካጣጣምን በኋላም እንኳን እውነተኛ እና ታማኝ ሆኖ መቆየት በቀላሉ የሚሆን አይደለም፡፡ ልባችንን ከተለማመድነው ደስታ እና ውበት ዘወር ለማድረግ የሚሞክሩ መሰናክሎችን፣ማታለያዎችን፣ግራ መጋባቶችን፣ሁካታዎችን፣ወጥመዶችን እና ፈተናዎችን መጋፈጣችንን እንቀጥላለን፡፡

በዚህ መከራ ምክንያት የሌሂ ህልም ማስጠንቀቂያም ያካትታል! ከውሃው ወንዝ ባሻገር ያለው ትልቅና ሰፊ ህንጻ ከሁሉም የእድሜ ክልል የተውጣጡ ሰዎች ነበሩበት በጻዲቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ላይ እጃቸውን እየጠቆሙ እና እየተሳለቁባቸው ነበር፡፡

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት ለማዋረድ እና ለመሳለቅ ተስፋ በማድረግ በህንጻው ውስጥ የነበሩት ሰዎች የሚያሳፍሩ፣የሚሳለቁ እና ትእዛዛቱን በሚጠብቁ ላይ የሚስቁ ነበሩ፡፡ እናም አማኞቹ ላይ በተሰነዘረው የጥርጣሬ እና የክብር መነፈግ የቃላት ጦርነት ምክንያት ፍሬውን በልተው ከነበሩት አንዳንዶች አፍረው ነበር፡፡ የአለም ሃሰተኛ ማማለያ አታለላቸው፤ከፍሬው ፊታቸውን አዞሩ፤እናም ጌታ እንዳለውም “ወደ ተከለከለው መንገድ ገቡና ጠፉ፡፡“10

ዛሬ በአለማችን ውስጥ ጠላት ሙሉ ጊዜያቸውን ትልቁን እና ሰፊውን ህንጻ በህብረት ለማስፋፋት የሚሰሩ ብቁ የግንባታ ባለሙያዎችን መልምሏል፡፡ ቤታችንን ለመውረር ተስፋ በማድረግ በአደንቋሪ የኢንተርኔት ድምጽ ማጉያ ሲጮሁ የጠቋሚዎቹ እና የተሳላቂዎቹ ማስፋፊያ ወንዙን ተሻግሯል፡፡11

“ጠላት ምስክርነቶችን ለማጥፋት እና የጌታን ስራ ለማስተጓጎል ጥረቶቹን በአራት እጥፍ እያሳደገ ነው“ ሲሉ ፕረሬዚደንት ኔልሰን ተናግረዋል፡፡12 የሌሂን ቃላት አስታውሱ “ነገር ግን እኛ አላዳመጥናቸውም“13

መፍራት ባያስፈልገንም በንቃት መጠበቅ አለብን፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትናንሽ ነገሮች መንፈሳዊ ሚዛናችንን ሊያሻሽሉ ይችላሉ ፡፡ እባካችሁ ጥያቄዎቻችሁ ፣ የሌሎች ስድብ ፣ እምነት የለሽ ጓደኞች ወይም በመጥፎ አጋጣሚዎች የሚሰሩ ስህተቶች እና ተስፋ አስቆራጭ ነገሮች ውድ ከሆነው የዛፍ ፍሬ ከሚመጡት ጣፋጭ ፣ ንጹህ እና ነፍስን የሚያረኩ በረከቶች እንዲያርቋችሁ አትፍቀዱ። አይኖቻችሁን እና ልቦቻችሁን በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእርሱ ብቻ በሚገኘው ዘላለማዊ ደስታ ላይ ያተኮሩ ያድርጓቸው።

የጄሰን ሃል እምነት

በሰኔ ካቲ እና እኔ በጄሰን ሃል ቀብር ላይ ተገኝተን ነበር፡፡ ሲሞት እድሜው 48 የነበረ ሲሆን የካህናት ቡድን ፕሬዚደንት ሆኖ እያገለገለ ነበረ፡፡

ህይወቱን ስለቀየረው ኩነት የተናገራቸው የጄሰን ቃላት እነዚህ ነበሩ:፡

“[በ 15 ዓመቴ] የውሃ ውስጥ አደጋ ደርሶብኝ ነበር … አንገቴ ተሰበረ እንዲሁም ከደረቴ እሰከታች ድረስ ሽባ ሆኜ ነበር፡፡ እግሮቼን ሙሉ ለሙሉ እንዲሁም እጆቼን በከፊል መቆጣጠር ተሳነኝ፡፡ መራመድ፣መቆም፣…እንዲሁም እራሴን መመገብ አልችልም ነበር፡፡ በወጉ መተንፈስም ሆነ መናገር አልችልም ነበር፡፡14

“‘ [በሰማይ ያለህ] አባት ሆይ፣‘እጆቼ ብቻ ቢንቀሳቀሱልኝ እንደምድን አውቃለሁ‘ ስል ለመንኩኝ፡፡ እባክህ፣ አባት ፣እባክህ፡፡…

“‘እግሮቼን ጠብቃቸው እጆቼን መጠቀም እችልም ዘንድ እለምንሃለሁ’”15

ጄሰን እጆቹ በፍጹም አልተፈወሱም፡፡ ከሰፊው ህንጻ የሚመጡ ድምጾች ይሰማችኋል? ጄሰን ሃል እግዚያብሄር ጸሎቶችህን አይሰማም! እግዚያብሄር አፍቃሪ አምላክ ከሆነ እንዴት እንደዚህ ይተውሃል? በክርስቶስ ለምን ታምናለህ?” ጄሰን ሃል ድምጻቸውን ሰማ ግን አላዳመጣቸውም፡፡ ከዚያ ይልቅ ከዛፉ ፍሬ መመገቡን ቀጠለ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለው እምነት የማይናወጥ ሆነ፡፡ ከዩኒቨርሲቲ ተመረቀ እንዲሁም “የህይወቴ ፍቅር“ ሲል የሚገልጻትን ኮሎት ኮልማንን በሶልት ሌክ ቤተመቅደስ አገባ፡፡16 ከ16 አመት የትዳር ዘመን በኋላ ሌላ ተአምር የሆነው ውድ ልጃቸው ኮልማን ተወለደ፡፡

ጄሰን እና ኮለት ሃል
የሃል ቤተሰብ

እምነታቸውን እንዴት አሳደጉ? ኮሎት ስታብራራ “በእግዚያብሄር እቅድ እናምን ነበር እናም እሱ ተስፋ ሰጠን፡፡ ጄሰን ሙሉ ጤነኛ እንደሚሆን እናውቅ ነበር… የሃጢያት ክፍያው ተስፋ በምንቆርጥበት ጊዜ ወደፊት እንድንቀጥል የሚያስችለንን አዳኝ [ኢየሱስ ክርስቶስን] እግዚያብሄር እንደሰጠን እናውቅ ነበር፡፡17

ኮልማን ሃል

በጄሰን ቀብር ላይ የ10 አመቱ ኮልማን አባቱ እንዲህ ብሎ እንዳስተማረው ተናግሯል “ሰማያዊ አባት ለኛ እቅድ አለው፣የምድር ህይወት ምርጥ ነው እናም ከቤተሰቦቻችን ጋር እንኖራለን … ነገርግን መከራን ማለፍ ይኖርብናል እንዲሁም ስህተቶችን እንሰራለን፡፡”

ቀጥሎም ኮልማን: “ሰማያዊ አባት እግዚያብሄር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደምድር ላከ፡፡ ስራውም ፍጹም መሆን ነበረ፡፡ ሰዎችን መፈወስ፡፡ እነርሱን ማፍቀር፡፡ ከዚያም ለህመማችን፣ለሃዘናችን እና ለሃጢያታችን ሊሰቃይ፡፡ ከዚያም ለእኛ ሲል ሞተ፡፡ ከዛም ኮልማን እንዲህ ሲል አከለ “ይህንን በማድረጉ ሳቢያ ኢየሱስ አሁን ምን እንደሚሰማኝ ያውቃል፡፡”

“ኢየሱስ ከሞተ ከሶስት ቀን በኋላ በፍጹም አካሉ ህያው ሆኖ መጣ፡፡ ይህ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የአባቴ አካል ፍጹም እንደሚሆን እና እንደቤተሰብ አንድ ላይ እንደምንሆን አውቃለሁ፡፡

የሃል ቤተሰብ

ከህጻንነቴ ጀምሮ በያንዳንዱ ምሽት፣”፣”አባቴ እንዲህ ይለኝ ነበር፣‘አባትህ ይወድሃል፣ሰማያዊ አባት ይወድሃል እንዲሁም አንተ ጥሩ ልጅ ነህ፡፡’ ሲል ያጠቃልላል ኮልማን።18

ደስታ የሚመጣው በአየሱስ ከክርስቶስ ምክንያት ነው፡፡

ፕሬዚደንት ኔልሰን የሃል ቤተሰብ ለምን ደስታ እና ተስፋ እንዳለቸው ገልጸዋል፡፡ እንዲህ ብለዋል

“የሚሰማን ደስታ ካሉን የህይወታችን ሁኔታዎች ጋር ግንኘነት አነስተኛ ነው እናም በህይወታችን ትኩረት ከምንሰጠው ነገር ጋር ያላቸው ተዛምዶ ታላቅ ነው።

የህይወታችን ትኩረት በእግዚያብሄር የደህንነት እቅድ …እና በኢየሱስ ክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ሲሆን፣ በህይወታችን ከተከሰተውም ወይም ካልተከሰተውም ሁኔታ ባሻገር ደስታ ሊሰማን ይችላል። ደስታ ከሱና በሱ ምክንያት ይመጣል። እሱ የደስታ ሁሉ ምንጭ ነው።

“ ወደ አለም ከተመለከትን ደስታን አናገኝም… ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረው ደስታ በፈቃደኝነት የጻድቅ ህይወትን ለመምራት በመጣር የሚመጣ ስጦታ ነው።19

ስትመለሱ የተገባላችሁ ቃልኪዳን

ለተወሰነ ጊዜ ያለ ዛፉ ፍሬ ከነበራችሁ፣የአዳኙ እጆች ሁልጊዜ በሰፊው የተዘረጉ እንደሆኑ ቃል እገባላችኋለሁ፡፡ “ንስሃ ግቡ እናም ወደ እኔ ኑ“ሲል ይጣራል፡፡20 ፍሬው የተትረፈረፈ ነው እንዲሁም በወቅቱ ይመጣል፡፡ በገንዘብ አይገዛም እንዲሁም በቅንነት የሚፈልግ ማንም አይከለከልም፡፡21

ወደ ዛፉ ለመመለስ እና አሁንም ፍሬውን ለመቅመስ የምትፈልጉ ማንኛችሁም በጸሎት መንፈስ ፍላጎታችሁን ለሰማይ አባታችሁ ግለጹለት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በሃጢያት ክፍያ መስዋእቱ ሃይልም እመኑ፡፡ “በነገር ሁሉ“ ወደአዳኙ ስትመለከቱ 22የዛፉ ፍሬ የናንተ፤ስትቀምሱት የጣፈጠ፣ለነፍሳችሁ አስደሳች ፣“ከእግዚያብሄር ስጦታዎች ሁሉ የበለጠ“ እንደሚሆን ቃል እገባላችኋለሁ፡፡23

ሽማግሌ አንደርሰን ከፖረቱጋል ቅዱሳን ጋር በሊዝበን ቤተመቅደስ ምርቃት ላይ

የዛሬ ሶስት ሳምንት ባለቤቴ ካቲ እና እኔ የፖርቹጋል ሊዝበን ቤተመቅደስ ምርቃት ላይ በታደምንበት ወቅት የአዳኙን ፍሬ ደስታ በሙሉ እይታ አየሁኝ፡፡ የተመለሰው ወንጌል እውነት ፖርቹጋል የሃይማኖት ነጻነት እንዳገኘች በ1975 ተከፈተ፡፡ የአማኞች ስብስብ፣ ቻፕል እንዲሁም ከ1000 ማይሎች የቀረበ ቤተመቅደስ ባልነበረበት ጊዜ መጀመሪያ ፍሬውን የቀመሱ ብዙ የተከበሩ ቅዱሳን የተወደደው ዛፍ ፍሬ በፖርቱጋል ሊዝበን በእግዚያብሄር ቤት አሁን በብዛት ስለሚገኝ ከኛ ጋር ይደሰታሉ፡፡ ልባቸውን በአዳኙ ላይ ያደረጉትን እነዚህን የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እንዴት እንዴት እንደማከብራቸው፡፡

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለእኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።24

ፕሬዚዳንት ኔልሰን ዛሬ በአለም ዙሪያ ለሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ንግግር ሲያደርጉ እንዲህ ብለው ነበር “ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እናንተ የእየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች በመከተል የሚመጣ ፍሬ ህያው ምሳሌዎች ናችሁ፡፡ ከዚያም እንዲህ ሲል አከለ “አመሰግናችኋለሁ! እወዳችኋለሁ፡፡“25

እንወዶታለን ፣ፕሬዚደንት ኔልሰን።

የመገለጥ ሃይል በተወደደው ፕሬዚደንታችን ላይ እንደሆነ የአይን ምስክር ነኝ፡፡ እርሱ የእግዚአብሔር ነቢይ ነው። እንደ ጥንቱ ሌሂ ፕሬዚደንት ራስል ኤም. ኔልሰንም የእግዚያብሄርን ቤተሰቦች እንድንመጣ እና ከዛፉ ፍሬ እንድንካፈል ይማፀኑናል ፡፡ ምክሩን ለመከተል ትህትና እና ጥንካሬ እንዲኖረን ይሁን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚያብሄር ልጅ እንደሆነ በትህትና እመሰክራለሁ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል እና ጸጋ ዘላቂ ዋጋ ያላቸውን ሁሉንም ነገሮች ያመጣል፡፡ ስለዚህ የምመሰክረው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. ማቴዎስ 16፣25።

  2. ማቴዎስ 16፣25።

  3. ዮሐንስ 14፥18።

  4. በጥር 2007(እ.ኤ.አ.)መጀመሪያ አካባቢ፣እንደ ሰባዎቹ አመራር አባል በየካቲት 4 2007 (እ.ኤ.አ. )በበሪግሃም ያንግ ዩኒቨርሲቲ ለሚቀርብ ዲቮሽናል ንግግር ዝግጅት በማደርግበት ወቅት ሽማግሌ ዴቪድ ኤ.ቤድናርን በየካቲት 4 2007 (እ.ኤ.አ.) ለሚቀርበው ለዛው ተመሳሳይ ታዳሚ ምን እየተዘጋጀ እንደነበር ጠየኩት፡፡ የሚያቀርበው ንግግር የብረቱን በትር መያዝን የተመለከተ እንደሆነ ሲነግረኝ ተገርሜ ነበር ፡፡ልጆቹ ታሪኩን ወደዱት እና የብረት በትሩን በፅኑነት መያዝ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነም ተማሩ። ለንግግሬ መርጬ የነበረው ርዕስ ይህ እራሱ ነበር ፡፡ ጽሑፋችንን አንዳችን ለሌላችን ካሳየን በኋላ አቀራረባችን የተለያየ እንደሆነ ተገነዘብን ፡፡ “የሕይወት ውሃ“ መጠራቀሚያ በሚል ርእስ ያዘጋጀው ንግግር ቅዱሳን ጽሁፎችን አጠቃሎ ትኩረቱን በብረት በትር ወይም በእግዚያብሄር ቃል ላይ ያደረገ ነበር፡፡ በንግግሩ “እኔና እናንተ የብረቱን በትር አጥብቀን እንድንይዝ በሚያስችለን ሁኔታ በየቀኑ ቅዱሳን ጽሁፎችን እያነበብን፣ እያጠናን እና እየመረመርን ነው? “ ሲል ጠይቋል፡፡

    ከዚያም ከሽማግሌ ቤድናር ጋር ከተወያየሁ ከሳምንት በኋላ ፕሬዚደንት ቦይድ ኬ.ፓከር “ የሌሂ ህልም እና እናንተ “ የሚል ርእስ ያለው የቢ.ዋይ. ዩ. ዲቮሽናል ንግግር አደረገ፡፡ ፕሬዚደንት ፓከር የብረት ዘንግን በግል መገለጥ እና መነሳሳት መልክ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ወደ እኛ ስለመምጣታቸው አፅን ኦት ሰጥተዋል። እንዲህ ብለዋል: - “በትሩን ብትይዙ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ወደፊት የለው መንገዳችሁ ሊሰማችሁ ይችላል። … የብረት ዘንግን ያዙ ፣ እናም አትልቀቁ። በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት፣ በሕይወታችሁ ውስጥ መንገዳችሁ

    የህዳር 2007 (እ.ኤ.አ.)” የነቢያትን ቃላት አጥብቃችሁ ያዙ”የሚለው ርእሴ የህያው ነቢያትን ቃላት የሚወክለው የብረት በትር ነበር፡፡

    የእነዚህ ሦስት ንግግሮች መገናኘት እንዲሁ የአጋጣሚ ጉዳይ አልነበረም ፡፡ እነዚህ ሶስት ንግግሮች ለተመሳሳይ ታዳሚዎች ሲዘጋጁየብረት በትሩን ወይም የእግዚያብሄርን ቃል ሶስት ገጽታዎች የለዩት የጌታ እጆች በስራ ላይ ነበሩ፡(1)ቅዱስ ጽሁፍ ወይም የጥንት ነቢያት ትምህርቶች (2) የህያው ነቢያት ትምህርቶች እና (3) የመንፈስ ቅዱስ ሃይል ይህ ለኔ ጠቃሚ የመማር አጋጣሚ ነበር፡፡

  5. 1 ኔፊ 8፥4–l12 ይመልከቱ።

  6. 1 ኔፊ 21፥16

  7. ዮሀንስ 3፥16

  8. ዴቪድ ኤ.ቤደናር, “Lehi’s Dream: Holding Fast to the Rod,” Liahona, Oct. 2011, 32–37 ይመልከቱ፡፡

  9. 1 ኔፊ 21፥16

  10. 1 ኔፊ 21፥16

  11. ቦይድ ኬ.ፓከር, “Lehi’s Dream and You” (Brigham Young University devotional, Jan. 16, 2007), speeches.byu.edu ይመልከቱ፡፡

  12. ራስል ኤም ኔልሰን “We Can Do Better and Be Better,” ኢንሳይን ወይም ሊያሆና፣ ግንቦት 2019 (እ.አ.አ)፣ 47።

  13. 1 ኔፊ 21፥16

  14. ስቴፈን ጄሰን ሃል, “The Gift of Home,” New Era, Dec. 1994, 12.

  15. ስቴፈን ጄሰን ሃል፣ “Helping Hands,New Era,ጥቅምት፣1995፡፡

  16. ከኮሌት ሃል ለሽማግሌ አንደርሰን የተጻፈ የግል ደብዳቤ ፡፡

  17. ከኮሌት ሃል ለሽማግሌ አንደርሰን የተጻፈ የግል ደብዳቤ ፡፡

  18. በኮልማን ሃል ለሽማግሌ አንደርሰን እንዳካፈለው በኮሌት ሃል ፡፡

  19. ራስል ኤም. ኔልሰን፣ “ደስታ እና መንፈሳዊ ደህንነት፣ሊያሆና፣ ህዳር 2016 (እ.አ.አ)፣ 82።

  20. 3 ኔፊ 21፥6

  21. 2 ኔፊ 26፥2533 ይመልከቱ።

  22. ትምህርት እና ቃልኪዳኖች 6፥36

  23. 1 ኔፊ 21፥16

  24. ዮሀንስ 15፥5

  25. Russell M. Nelson, “The Second Great Commandment,” Liahona, Nov. 2019, xx.