2010–2019 (እ.አ.አ)
የናንተ ታላቅ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

የናንተ ታላቅ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ

አዳኙ በየቀኑ ምቾታችሁን እና ደህንነታችሁን ወደ ጎን እንድትተዉ እና በደቀ-መዝሙርነት ጉዞ ላይ እንድትቀላቀሉት ይጋብዛችኋል፡፡

“በመሬት በጉድጓድ ውስጥ ትንሽዪ ሰውነትና ጸጉራም እግር ያለው ሰው

የተወደደ ከብዙ አመታት በፊት የተጻፈ ተወዳጅ የህጻናት ምናባዊ ልብ-ወለድ “በመሬት በጉድጓድ ውስጥ ትንሽዪ ሰውነትና ጸጉራም እግር ያለው ሰው ይኖር ነበር”በሚል አረፍተ ነገር ይጀምራል፡፡1

የቢልቦ ባጊንስ ታሪክ በጣም አስገራሚ የሆነ እድል ፤ ለአጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ፣ ለነቂቅ ነገር፣ እና የትልቅ ሽልማት ተስፋ እድል ስለቀረበለት ይበልጥ የተለመደ እና የማያስገርም ስለሆነ ትንሽዪ ሰውነትና ጸጉራም እግር ስላለው ሰው ነው፡፡

ችግሩ ከሁሉ ይበልጥ ራሳቸውን የሚያከብሩ ትንሽዪ ሰውነትና ጸጉራም እግር ያላቸው ሰዎች ከአጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ጋር ምንም ንክኪ አይፈልጉም፡፡ ህይወታቸው ሙሉ አተኩሮው ምቾት ላይ ነው፡፡ ሲያገኙ በቀን ሲዲስቴ መብላት እናም ቀናቸውን ጓሯቸው ውስጥ ማሳለፍ፣ ታሪኮችን ከእንግዶች ጋር መለዋወጥ፣መዘመር፣የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት፣ እና በቀላል የህይወት ሀሴቶች መደሰት ያስደስታቸዋል፡፡

ነገር ግን ቢልቦ የትልቅ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ እድል ሲገጥመው የሆነ ነገር በልቡ ውስጥ ጠልቆ በድንገት ጨመረ፡፡ ነገሩ ከሚጀምርነት ጊዜ አንጻር ጉዞው አስቸጋሪ እንደሚሆን ተረድቷል፡፡ እንዲሁም አደገኛ፡፡ ሊመለስ የማይችልበትም እድል እንኳን አለ፡፡

ቢሆንም ግን የጀብዱ ጥሪው የልቡ ጥግ ደርሷል፡፡ እናም ስለዚህ ይህ አስገራሚ ያልሆነ ትንሽ ሰውነትና ጸጉራም እግር ያለው ሰው ምቾትን ወደኋላ ትቶ እዛ አድርሶ ክዛም መልሶ በሚያመጣው ”ወደ ትልቁ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ መንገዱን ጀመረ፡፡ 2

የናንተ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ

ምናልባት ይህ ታሪክ ከብዙዎቻችን ጋር የሚስማማበት አንዱ ምክንያት የኛም ታሪክ ስለሆነ ነው፡፡

ከድሮ ድሮ ጊዜ በፊት ፤እኛ ከመወለዳችን በፊት እነኳን፤ሰአቱ ግልጽ ባልሆነ እድሜ አና ከትውስታ ተጋርዶ ፣ እኛም ወደ አጓጊ እና ያልተለመደ ልምድ ጉዞ እንድንጀምር ተጋብዘን ነበር፡፡ በእግዚአብሄር ፤በሰማይ አባታችን ነበር ሃሳቡ የቀረበው፡፡ ይህን አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ መቀበል የሱን የቅርብ መገኘት ምቾት እና ጥበቃ መተው ይሆናል ማለት ነው፡፡ በማይታወቅ አደጋ እና ፈተና ለተሞላ ጉዞ ወደ ምድር መምጣት ይሆናል፡፡

ቀላል እንደማይሆን አውቀናል፡፡

ነገር ግን ፣አካልን እና የሟችነትን ጥልቅ ደሰታዎችና ሀዘኖችንም ማጋጠም አጠቃሎ የከበሩ ሀብቶች እንደምናገኝም አውቀን ነበር፡፡ መታገልን፣ መሻትን፣ እና መፍጨርጨርን እንማራለን፡፡ ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ራሳችን እውነታዎች ላይ እንደርሳለን፡፡

በእርግጥ በመንገዳችን ላይ ብዙ ስህተቶችን እንደምንሰራ አውቀን ነበር፡፡ ነገር ግን በእየሱስ ክርስቶስ ታላቅ መስዋትነት ምክንያት ከመተላለፎቻችን መንጻት፣ በመንፈሳችን የጠራን እና የነጻን ፣እናም አንድ ቀን ትንሳኤ እንደሚናረግ እና ከምንወዳቸው ጋር በድጋሚ እንደምንገናኝ ፤ ቃልኪዳንም ነበረን፡፡

እግዚአብሄር ምን ያህል እንደሚወደን ተማርን፡፡ እሱ ህይወት ሰቶናል እናም ስኬት እንድናገኝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህም ፣እሱ ለኛ አዳኝ አዘጋጀልን፡፡ ቢሆንም ግን የሰማይ አባታችን “ለናንተ ስለተሰጣችሁ ለራሳችሁ ምረጡ” ብሏል፡፡3

በብዙ የሚቆጠሩ የመንፈስ ወንድሞች እና እህቶቻችን ሃሰቡን ስለተቋወሙት፤ የእግዚአብሄርን ልጆች ያስጨነቃቸው እናም እንኳን ያስፈራቸው የሟችነት ግዜ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ክፍሎች ነበሩ ማለት ነው፡፡4

በግብረገብ ነጻ ምርጫ ስጦታና ሀይል ፤ልንማር የምንችለውን እና ለዘላለም ልንሆን የምንችለው አቅም አደጋውን ብንወስድ እንኳን ምንም ማለት እዳልሆነ ወሰንን፡፡ 5

እናም ስለዚህ የእግዚአብሄርን እና የሱን የተወደደ ልጅ ቃልኪዳኖች እና ሀይል ተማምነን ጥሪውን ተቀበልን፡፡

እኔ ተቀብያለው፡፡

እናንተም እንደዛው::

የመጀመሪያ ኑሯችን ያለውን ደህንነት ትተን እናም ወደ እዛ እናም ተመልሰን ለመምጣት በራሳችን ትልቅ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ላይ ጉዞ ለመጀመር ተስማማን፡፡

ለአጓጊ እና ላልተለመደ ጉዞ ጥሪ

እናም ሆኖም ግን ፣ የሟችነት ህይወት እኛን የሚያዘናጋበት መንገድ አለው ፤ አይደለም? ከእድገት እና ከመሻሻል ይልቅ ምቾትን እና ቅለትን በመምረጥ የትልቁን ፍለጋችንን እይታ እናጣለን፡፡

አሁንም የሆነ ፤ በልባችን ውስጥ የዘለቀ፤ ይበልጥ ለከፍተኛ እና ለከበረ አላማ የሚራብ የማይካድ ነገር ይቀራል ፡፡ ይህ ረሃብ ሰዎች ወደ ወንጌሉ እና የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚሳቡበት አንድ ምክንያት ነው፡፡ የተመለሰው ወንጌል በጣም በድሮ ጊዜ ለተቀበልነው አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ጥሪ አዳሽ ነው፡፡ አዳኙ በየቀኑ ምቾታችሁን እና ደህንነታችሁን ወደ ጎን እንድትተዉ እና በደቀ-መዝሙርነት ጉዞ ላይ እንድትቀላቀሉት ይጋብዛችኋል፡፡

በዚህ መንገድ ላይ ብዙ እጥፋቶች አሉ፡፡ ኮረብታዎች፣ ሸለቆዎች፣ ጠመዝማዛ መንገዶች አሉ፡፡ ምናባዊ ሸረሪቶች፣ድንክ ወይም ግዙፍ የሆኑ ፍጡራን እንኳን፣ እናም አንድ ድራገን ወይም ሁለት እንኳን ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ግን መንገዱ ላይ ከቆያችሁ እና በእግዚአብሄር ከተማመናችሁ ፤በመጨረሻ ወደ ታላቁ መድረሻችሁና ወደ ሰማያዊ ቤታችሁ ለመመለስ መንገዱን ታገኙታላችሁ፡፡

ስለዚህ እንዴት ነው ምጀምሩት?

በጣም ቀላል ነው፡፡

ልባችሁን ወደ እግዚአብሄር አዘንብሉ፡፡

በመጀመሪያ ልባችሁን ወደ እግዚአብሄር ለማዘንበል መምረጥ አለባችሁ፡፡ በየቀኑ እሱን ለማግኘት ጣሩ፡፡ እሱን መውደድን ተማሩ፡፡ እናም ከዛ ፍቅር፤ እናንተ ተምሮ ፣ ለመረዳት፣ እና አስተምሮዎቹን ለመከተል እንዲያነሳሳችሁ ፍቀዱለት፡፡ ህጻን እስከረዳው ድረስ እንኳን የተመለሰው የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ለኛ በግልጽ እና በቀላል መንገድ ነው የተሰጠን፡፡ ቢሆንም ግን የእየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የህይወት ውስብስብ ጥያቄዎች ለሚባሉት መልስ አለው እናም በጣም ጥልቅ እና ውስብስብ ከመሆኑ የተነሳ በህይወት ሙሉ ጥናትና ማሰላሰል እንኳን ፤ አንድ ሺኛውን ክፍል ለመረዳት እንችላለን፡፡

በዚህ ጀብድ ውስጥ ችሎታችሁን በመጠራጠር፣ የምታመነቱ ከሆነ፤ደቀመዝሙርነት ነገሮችን ፍጹማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ ሳይሆን፤ነገሮችን አውቀን ማድረግ እንደሆነ አስታውሱ፡፡ ከችሎታዎቻችሁ በላይ እውነት ማን እንደሆናችሁ የሚያሳየው ምርጫዎቻችሁ ነው፡፡6

ስትወድቁ እንኳን ለግፊት ራሳችሁን ላለመስጠት ወይም ተስፋ ላለመቁረጥ መምረጥ ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ድፍረታችሁን አግኙ፣ ወደፊት ቀጥሉ፣ እናም ተነሱ፡፡ ያ የጉዞው ትልቁ ፈተና ነው፡፡

እግዚአብሄር ፍጹም እንዳልሆናችሁ ፤ባንዳንድ ሰአት እንደምትወድቁ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ከማሸነፍ ይልቅ ስትቸገሩ አሳንሶ አይወዳችሁም፡፡

ልክ እንደ አፍቃሪ ወላጅ ፣እሱ ፈልጋችሁ መጣራችሁን እንድትቀጥሉ ነው የሚፈልገው፡፡ ደቀመዝሙርነት ፒያኖ ለመጫወት እንደመማር ነው፡፡ ምናልባት በጀመሪያ ልትጫወቱት የምትችሉት ትንሽ የሚታወቅ “የቾፕስቲክ”የትያትር ሙዚቃ ብቻ ይሆናል፡፡ ነገርግን ልምምዳችሁን ከቀጠላችሁ አሁን ልታወጡት ያልቻላችሁት ቀላል ዜማ አንድ ቀን ለአስገራሚ የተቀናበረ የሙዚቃ ድርሰት ሶናታስ፣ ራፍሶዲስ ፣ እናም ኮነሰርቶስ ይበቃል፡፡

አሁን ያ ቀን በዚህ ህይወት ላይመጣ ይችላል፤ ነገር ግን ይመጣል፡፡ እግዚአብሄር የሚጠይቀው በንቃተ ህሊና መጣራችሁን እንድትቀጥሉ ብቻ ነው፡፡

ለሌሎች በፍቅር ድረሱ

ስለዚህ የመረጣችሁት መንገድ አንድ መሳጭ ተጻራሪ የሚመስል ነገር አለ፤በወንጌሉ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ውስጥ ለማደግ ብቸኛው መንገድ ሌሎች እንዲያድጉ መርዳት ነው፡፡

ሌሎችን መርዳት የደቀመዝሙርነት መንገድ ነው፡፡ እምነት፣ ተስፋ፣ ርህራሄ፣ እና አገልግሎት እኛን እንደ ደቀመዝሙር ያጠራናል፡፡

ደሃውን እና የተቸገረውን ለመርዳት፣ ስቃይ ውስጥ ላሉ ለመድረስ፣ በምታደርጉት ጥረት ውስጥ የራሳችሁ ተፈጥሮ ይጠራል እናም ይታደሳል፣ መንፈሳችሁ ይተልቃል፣ ትንሽ ኮራ ብላችሁ መራመድ ትችላላችሁ፡፡

ነገር ግን ይህ ፍቅር በምላሹ ክፍያን ከጠበቅን ሊመጣ አይችልም፡፡ እውቅናን፣ ሙገሳን፣ ወይም ውለታን የሚጠብቅ አይነት አገልግሎት ሊሆን አይችልም፡፡

እውነተኛ የእየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እግዚአብሄርን እና ልጆቹን በምላሹ ምንም ነገር ሳይጠብቁ ይወዳሉ፡፡ ቅር የሚያሰኙንን ፣የማይወዱንን እንወዳለን፡፡ የሚሳለቁብንን፣ መጥፎ የሚያረጉንን፣ እና ሊጎዱን የሚፈልጉትን እንኳን፡፡

ልባችሁን በክርስቶስ ንጹህ ፍቅር ስትሞሉ ለጥላቻ፣ ለፍርድ፣ እና ለማዋረድ ቦታ አትተዉም፡፡ የእግዚአብሄርን ትእዛዛት እሱን ስለምትወዱት ትጠብቃላችሁ፡፡ በዚህ ሂደት በቀስታ በሃሳቦቻችሁ አና ድርጊቶቻችሁ ይበልጥ ክርስቶስን ትመስላላችሁ፡፡7 ከዚህ የበለጠ ምን አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ሊኖር ይችላላል?

ታሪካችሁን አካፍሉ

ሶስተኛው በዚህ ጉዞ ውስጥ በደንብ ለመቻል የምጥረው ነገር የእየሱስ ክርስቶስን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ እና በማንነታችን አለማፈር ነው፡፡

እምነታችንን አንደብቅም፡፡

አንቀብረውም፡፡

በተቃራኒዉ ከሌሎች ጋር ስለ ጉዞአችን በተለመደና ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ እናወራለን፡፡ ያንን ነው ጓደኞች የሚያረጉት---ለነሱ አስፈላጊ ስለሆኑ ነገሮች ያወራሉ፡፡ ለልባቸው ቅርብ ስለሆኑ ነገሮች እና ለነሱ ለውጥ ስለሚፈጥሩ ነገሮች፡፡

ያንን ነው የምታረጉት፡፡ በኋለኛው ቀን ቅዱሳን የእየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አባልነታችሁ ያላችሁን ታሪኮች እና ልምዶች ትነግራላችሁ፡፡

አንዳንድ ጊዜ ታሪካችሁ ሰዎችን ያስቃል፡፡ አንዳንዴ ያስለቅሳቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በትዕግስት፣ በቀላሉ በማገገም እና ፣ ወደ እግዚአብሄር ትንሽ በይበልጥ የቀረበ ሌላ ሰአትን ፣ ሌላ ቀንን በድፍረት መጋፈጥ እንዲቀጥሉ ይረዳል፡፡

ልምዶቻችሁን በአካል፣ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ፣ በቡድን፣በሁሉም ቦታ አካፍሉ፡፡

እየሱስ ለተከታዮቹ ከነገራቸው የመጨረሻዎቹ ነገሮች አንዱ የተነሳውን የክርስቶስን ታሪክ በአለም ዙሪያ ሄደው እንዲያካፍሉ ነበር፡፡8 ዛሬ ያንን ታላቅ ትእዛዝ በደስታ እንቀበላለን፡፡

ምን አይነት ታላቅ መልዕክት ነው ማካፈል ያለብን፤ በእየሱስ ክርስቶስ ምክንያት ሁሉም ወንድ፣ ሴት፣ እና ልጅ በደህና ወደ ሰማያዊ ቤታቸው መመለስ ይችላሉ ፤ እዛም በክብር እና በጽድቅ ይኖራሉ!

ሌላም ልናካፍለው የሚገባ ተጨማሪ ጥሩ ዜና አለ፡፡

እግዚአብሄር በኛ ዘመን ለሰው ተገለጠ! በሂወት ያሉ ነብይ አሉን፡፡

እግዚአብሄር የተመለሰውን ወንጌል እና የእየሱስ ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያንን “እንድትሸጡ” እንደማይፈልግ ላስታውሳችሁ፡፡

በቀላሉ የሚጠብቀው በመስፈሪያ ስር እንዳትደብቁት ነው፡፡

እና ሰዎች ቤተ-ክርስቲያኑ ለኛ አይሆንም ብለው ከወሰኑ፤ ያ የነሱ ምርጫ ነው፡፡

እናንተ ወድቃችኋል ማለት አይደለም፡፡ እነሱን በመልካም መንከባከባችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡ ድጋሚ እነሱን መጋበዛችሁንም አያስቀርም፡፡

በማህበራዊ ግኙኝነት እና በሩህሩህ ደፋር ደቀመዝሙርነት መሃል ያለው ልዩነት—ግብዣ ነው፡፡

ሁሉንም የእግዚአብሄር ልጆች ፤ በህይወት ውስጥ ያላቸው ቦታ ምንም ቢሆን፣ ዘራቸው ወይም ሃይማኖታቸው ምንም ቢሆን፣ የህይወት ውሳኔዎቻቸው ምንም ቢሆን እንወዳቸዋለን እናም እናከብራቸዋለን፡፡

በኛ ድርሻ በኩል “ኑ እና እዩ! እንላለን፡፡ ለራሳችሁ እንዴት የደቀመዝሙርነትን መንገድ መጓዝ ሽልማት ያለው እና የሚያስከብር እንደሆነ እወቁ፡፡

“አለም የተሻለ ቦታ እንዲሆን ለማድረግ ስንጥር ሰዎች እንዲመጡ እና እንዲያግዙን እንጋብዛለን፡፡”

እናም “ኑ እና ቆዩ እንላለን፡፡ እኛ ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ ነን፡፡ ፍጹማን አይደለንም፡፡ እግዚአብሄርን እንተማመናለን እናም የሱን ትዕዛዛት ለመጠበቅ እንጥራለን፡፡

“ተቀላቀሉን እናም የተሻልን ታደርጉናላችሁ፡፡ እናም በዛ ሂደት ውስጥ እናንተም የተሻላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ ይህን አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ አንድ ላይ እንውሰድ፡፡

መቼ ልጀምር?

ጓደኛችን ቢልቦ ባጊንስ የጀብዱው ጥሪ ውስጡ ሲቆሰቁሰው፣ ጥሩ የመኝታ እንቅልፍ ለመታኛት፣ በአጥጋቢ ቁርስ ለመደሰት፣ እና በጠዋት ለመጀመር ወሰነ፡፡

ልክ ቢልቦ ሲነቃ ቤቱ እንደተመሰቃቀለ ተመለከተ፣እና ከተከበረ እቅዱ ሃሳቡ ለመወሰድ ደርሶ ነበር፡፡

ነገር ግን ከዛ ጓደኛው ጋንዳልፍ መጣና “መቼ ነው ምትመጣ?” ብሎ ጠየቀው፡፡9 ጓደኛው ላይ ለመድረስ ለራሱ ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን ነበረበት፡፡

እናም ስለዚህ በጣም የተለመደው እና የማያስገርመው ትንሽዪው እግረ ጸጉራሙ ሰው በፊለፊት በሩ ወደ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ መንገድ ኮፍያውን፣ ከዘራውን፣ እና የኪስ መሃረቡን እንኳን እስኪረሳ በፍጥነት ወጣ፡፡ ሁለተኛውን ቁርሱን እንኳን ሳይጨርስ ነበር የሄደው፡፡

ምናልባት ለሁላችንም የሚሆን ትምህርት አለ እዚ ውስጥ፡፡

ታላቁን የመኖር እና ከድሮ ጊዜ በፊት የሰማይ አባታችን ለኛ ያዘጋጀውን ነገር ለማካፈል እኔ እና እናንተ መነሳሳት ከተሰማን፤ አረጋግጥላችኋለው የእግዚአብሄርን ልጅ እና የኛን አዳኝ በሱ የአገልግሎት እና የደቀ-መዝሙርነት መንገድ ላይ ለመከተል ቀኑ ዛሬ ነው፡፡

ሁሉም ነገር ፍጹማዊ በሆነ መልኩ የሚሰተካከልበትን ጊዜ ስንጠብቅ ሙሉ ህይወታችንን ልንፈጅ እንችላለን፡፡ እግዚአብሄርን ለመሻት፣ ለሌሎች ለማገልገል፣ እና ልምዳችንን ለሌሎች ለማካፈል በደንብ ቁርጠኛ ለመሆን አሁን ነው ሰአቱ፡፡

ኮፍያችሁን፣ ከዘራችሁን፣ መሃረባችሁን፣ እና የተመሰቃቀለ ቤታተዉት፡፡10

ያንን መንገድ እየተጓዝን ላለን ሰዎች ደሞ ድፍረትን፣ ርህራሄን፣ በራስ መተማመንን ውሰዱ እናም ቀጥሉ፡፡

መንገዱን ለተዋችሁ ደሞ ፤ እባካችሁ ተመለሱ፣ ድጋሚ ከኛ ጋር ተቀላቀሉ፣ አጠንክሩን፡፡

ላልጀመራችሁ ደሞ ፣ለምን ታዘገዩታላችሁ? የዚን ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ድንቅነት መቅመስ ከፈለጋችሁ፣የራሳችሁ በሆነው ትልቅ አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ ላይ እግራችሁን እርገጡ፡፡ ከሚስዮናዊያኖች ጋር ተነጋገሩ፡፡ ከኋለኛው ቀን ቅዱሳን ጓደኞቻችሁ ጋር ተነጋገሩ፡፡ ስለዚህ ታላቅ ስራ እና ድንቅነት ከነሱ ጋር አውሩ፡፡11

ለመጀመር ሰአቱ አሁን ነው!

ኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ!

ህይወታችሁ የበለጠ ትርጉም፣ከፍ ያለ አላማ፣ የጠነከረ የቤተሰብ ቁርኝት፣ እና ከእግዚአብሄር ጋር የበለጠ ግኑኝነት ሊኖረው እንደሚችል ከተሰማችሁ፤ እባካችሁ፣ ኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡

የራሳቸውን የተሻለ ማንነት ለመያዝ ፣ የተቸገሩትን ለመርዳት፣ እናም ይህን ምድር የተሻለ ለማድረግ የሚሻ ማህበረሰብ የምትፈልጉ ከሆነ ፣ኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡

ይህ ግሩም፣ አስደናቂ፣ እና አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ የሆነው ጉዞ ምን እንደሆነ ኑ እና እዩት፡፡

እግረ መንገዳችሁን እራሳችሁን ታገኛላችሁ፡፡

ትርጉምን ታገኛላችሁ፡፡

እግዚአብሄርን ታገኛላችሁ፡፡

የህይወታችሁን በጣም አጓጊ እና ያልተለመደ ጉዞ የተሞላ እና አስደናቂ የሆነ ጉዞ ታገኛላችሁ፡፡

ይህንንም የምመሰክረው በእየሱስ ስም ነው አሜን።

ማስታወሻዎች

  1. J. R. R. Tolkien,The Hobbit or There and Back Again (2001)እ.አ.አ, 3.

  2. Subtitle of ዎና ርእስበመሬት በጉድጓድ ውስጥ ትንሽዪ ሰውነትና ጸጉራም እግር ያለው ሰው

  3. ሙሴ 7፥35

  4. የእግዚአብሄር ልጆች ሁሉ እልል አሉ፣ መጽሀፈ እዮብ -13፡4–7፤ ዙፋኔንም ከእግዚአብሄር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለው፣ ትንቢተ ኢሳያስ 14፡12–13 ፤ በሰማይም ሰልፍ ሆነ፣ የዮሀንስ ራእይ 12፡7–11፡፡

  5. “ነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ነጻ ምርጫን ‘ያ ከሰማይ በጸጋ እንደ ምርጡ ስጦታ የተሰጠው የአእምሮ ነጻነት’ ብሎ ገልጾታል፡፡[ የነብዩ ጆሴፍ ስሚዝ ትምህርቶች, ኮምፕ.ጆሴፍ ፍኢልዲንግ ስስሚዝ (1977)እ.አ.አ, 49]፡፡ ይህ ‘የአእምሮ ነጻነት’፣ ወይም ነጻ ምርጫ፣ ግለሰቦች ‘ራሳቸውን እንዲወክሉ’ የሚያስችል ሀይል ነው፡፡(ት.&ቃ 58፡28)፡፡ ሁለቱንም ከጥሩ እና ከመጥፎ የመምረጥን ፍቃድ ልምምድ ወይም የጥሩን ወይም የመጥፎን ደረጃ መለየት እና የዛን ምርጫ ውጤቶችን የመለማመድ እድልን ያጠቃልላል፡፡ የሰማይ አባት ልጆቹን በጣም ከመውዱ እኛ ሙሉ አቅማችን ላይ እድንደርስ—እንደሱ እድንሆን ይፈልጋል፡፡ ለመሻሻል አንድ ሰው የራሱን ወይም የራሷን የፈለጉትን ምርጫ ለመምረጥ ውስጣዊ ችሎታ ሊይዝ ይገባል፡፡ ነጻ ምርጫ ለልጆቹ ላለው የሱ እቅድ በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ ‘እግዚአብሔር እንኳን ሰዎችን ነጻ ሳያረግ እንደ እሱ እንዲሆኑ ማድረግ አልቻለም’ [ዴቪድ ኦ ሚክኤይ “እየነጣንም እንሄዳለንን“? የሂወታችን ትልቁ ውሳኔ ,” Or Life’s Supreme Decision,” የዴዝእርት ዝኤና ሰኔ8, 1935 እ.አ.አ, 1]” (ባይርኦን አረር, “በመለኮታዊ እቅድ ውስጥ ነጻምርጫ እና ነጻነተ Window of Faith: Latter-day Saint Perspectives on World History, ed. Roy A. Prete [2005]እ.አ.አ, 162).

  6. በሳ ልብወለድ ውስጥሄሪ ፖተር እና የሚስጢሮቹ አዳራሽጸሀፊ ጄ.ኬ.ሮውሊንግ ሀዝ የሆግዎርት ዋናው ሀላፊ ዳንብልዶር ለወጣቱ ሄሪ ፖተር ተመሳሳይ ነገር ብላል፡፡ እንዲሁም ለሁላችንም ግሩም ምክር ነው ፡፡ ከዚ በፊት በሜሴጅ ተጠቅሜዋለው እናም ለመደገም ብቁ ነው በየ አስባለው፡፡

  7. “ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡” (1 ዮሀንስ ወንጌል 3፡2)

    የዚህ አይነት ለውጥ ለማሰብ ከአእምሯችን በላይ ቢሆንም ፤ “የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል፤

    “ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፤ አብረንም ደግሞ እድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን፡፡

    ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለው፡፡”(ሮሜ 8፡16-18)

  8. የማቴዎስ ወንጌል 28፥16-20 ይመልከቱ።

  9. Tolkien, The Hobbit, 33

  10. የሉቃስ ወንጌል 9፡59-62ተመልከቱ።

  11. See LeGrand Richards,ተመልከቱ። A Marvelous Work and a Wonder, rev. ed. (1966)እ.ኤ.አ፡፡