2010–2019 (እ.አ.አ)
ማወቅ፣ ማፍቀር፣ እና ማደግ
የጥቅምት 2019 (እ.አ.አ) አጠቃላይ ጉባኤ


2:3

ማወቅ፣ ማፍቀር፣ እና ማደግ

እኛም የበለጠ እንደ እርሱ እንድንሆን ዘንድ በዚህ ታላቅ የአገለግሎት ሥራ ሁላችንም ድርሻችንን እንድንገነዘብ ይሁን።ሁላችንም በዚህ ታላቅ የአገልጋይነት ሥራ ውስጥ የበኩላችንን እንገንዘብ።

እ.አ.አ. በ2016 የቤተመቅደስ አደባባይ ታበርናክል ዘማሪዎች ኔዘርላንድን እና ቤልጂየምን ለመጎብኘት መጡ። በዚያ አስደሳች ክስተት ውስጥ ተሳትፌ ስለነበረ ሁለት ጊዜ በእነሱ አፈፃፀም የመደሰት እድል ነበረኝ።

የጎንግ ተጫዋች

በአፈፃፀማቸው ወቅት የዚያን መጠን ያላቸው ዘማሪዎችን ማንቀሳቀስ ምን ያህል ከባድ ሥራ እንደሆነ አስብ ነበር። በእጅ በቀላሉ ሊሸከሟቸው ከሚችሉት ቫዮሊን፣ መለከት ወይም ሌሎች መሣሪያዎች ጋር በማወዳደር በአእምሮዬ በጣም አስቸጋሪ እና ምናልባትም በጣም ውድ ወደሆነ ትልቅ ጎንግ ተሳብኩ። ግን የዚህን የጎንግ እውነተኛ ተሳትፎ ስመለከት ጥቂት ጊዜያት ብቻ ነበር የተመታው፣ ሌሎቹን ትናንሽ መሳሪያዎች ግን ለኮንሰርቱ በብዛት ተጠቅመውባቸው ነበር። የጎንግ ድምፅ ባይኖር ኖሮ አፈፃፀሙ እንዳሁኑ እንደማይሆን አሰብኩ እናም ይህንን ትልቅ ጎንግ ውቅያኖሱን አቋርጦ ለማዘዋወር ጥረት መደረግ ነበረበት በማለት አሰብኹኝ።

የጎንግ ተጫዋች ከኦርኬስትራ ጋር

አንዳንድ ጊዜ እኛ፣ እንደዛ ጎንግ፣ በአፈፃፀሙ ውስጥ አነስተኛውን ክፍል ብቻ ለመጫወት ብቁ መሆናችን ሊሰማን ይችላል። ግን ድምጻችሁ ሁሉንም ልዩነቶች እየፈጠረ መሆኑን ልንገራችሁ።

ሁሉም መሳሪያዎች ያስፈልጉናል። አንዳንዶቻችን በት / ቤት በቀላሉ እንማራለን እንዲሁም ጥሩ ውጤት እናስመዘግባለን ፣ ሌሎች ደግሞ ጥበባዊ ችሎታ አላቸው። አንዳንዶች ነገሮችን ይነድፋሉ እና ይገነባሉ ወይም ሌሎችን ይንከባከባሉ፣ ይከላከላሉ ወይም ያስተምራሉ። ቀለምን እና ትርጉምን ወደዚህ ዓለም ለማምጣት ሁሉም ያስፈልጋል።

ለማበርከት ምንም ነገር እንደሌላቸው ለሚሰማቸው ወይም ለማንም አስፈላጊ ነገር ወይም ውጤት እንደሌላቸው ለሚሰማቸው፣ ለሌሎች በዓለም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንገኛለን ብለው ለሚሰማቸው እና በእነዚህ መካከል ለሚገኘኝ ለማንኛውም ሰው ይህንን መልእክት ማስተላለፍ እፈልጋለሁ።

በህይወት ጎዳና ላይ የትም ብትሆኑ፣ አንዳንዶቻችሁ ከመጠን በላይ ሸክም እንዳለባችሁ ስለሚሰማችሁ እራሳችሁን በዚያ መንገድ ላይ እንዳላችሁ እንኳን አታስቡም። ከጨለማው ወደ ብርሃን እንድትወጡ እጋብዛችኋለሁ። የወንጌል ብርሃን ሙቀትና ፈውስ ይሰጣችኋል እናም በእውነቱ ማን እንደነበራችሁ እና የህይወታችሁ ዓላማ ምን እንደ ሆነ እንድትረዱ ይረዳችኋል።

አንዳንዶቻችን ደስታን ለማግኘት በመሞከር የተከለከሉ መንገዶች ላይ እየተንከራተትን ነበር።

የደቀመዝሙርነትን መንገድ እንድንጓዝ እና ወደ እርሱ እንድንመለስ አፍቃሪ በሆነ የሰማይ አባት ተጋብዘናል። በፍጹም ፍቅር ያፈቅረናል።1

መንገዱ ምንድን ነው? መንገዱ እርስ በርሳችን በማገልገል ማን እንደሆንን እንድንገነዘብ እንድንረዳዳ ነው።

ለእኔ፣ ማገልገል መለኮታዊ ፍቅርን መለማመድ ነው።2 በዚህ መንገድ ሰጪው እና ተቀባዩ የንስሓ ፍላጎት የሚያገኙበትን ሁኔታን ለመፍጠር እንችላለን። በሌላ አገላለጽ፣ አቅጣጫ እንቀይራለን እንዲሁም ወደእርሱ እንቀርባለን እናም ይበልጥ እንደ አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንሆናለን፡፡

ለምሳሌ ለትዳር ጓደኛችን ወይም ለልጆቻችን ማሻሻል እንደሚያስፈልጋቸው ሁል ጊዜ መንገር አያስፈልግም፣ እነሱ ያንን ያውቃሉ። በሕይወታቸው ውስጥ አስፈላጊ ለውጦችን እንዲያደርጉ እና የተሻሉ ሰዎች እንዲሆኑ የሚያስችላቸው በፍቅር የተሞላ አካባቢ በመፍጠር ነው።

በዚህ መንገድ ንስሐ የየቀኑ የማጣራት ሂደት ይሆናል ፣ ይህም ለመጥፎ ባህሪ ይቅርታ መጠየቅንም ሊያካትት ይችላል። ለመፍረድ በጣም ፈጣን ወይም ለማዳመጥ በጣም ዝግተኛ የሆንኩባቸውን ሁኔታዎች አስታውሳለሁ እና አሁንም ይገጥሙኛል ። እናም በቀን መጨረሻ በግል ጸሎቴ ላይ ንስሀ ለመግባት እና የተሻልኩኝ እንድሆን ከሰማይ የመጣ ፍቅራዊ ምክር ተሰማኝ። በመጀመሪያ በወላጆቼ ፣ በወንድሜ እና በእህቶቼ እና በኋላ ደግሞ በባለቤቴ፣ በልጆቼ እንዲሁም በጓደኞቼ የተፈጠረው ፍቅር የተሞላበት አካባቢ የተሻለ ሰው እንደሆን ረድቶኛል።

ሁላችንም የት በተሻለ ሁኔታ ማድረግ እንደምንችል እናውቃለን። እርስ በእርስ በተደጋጋሚ እንዲያስታውሱ ማድረግ አያስፈልግም ፣ ግን እርስ በእርስ መዋደድ እና ማገልገል ያስፈልጋል እናም ይህንንም በማድረግ ለመለወጥ ፈቃደኛ የሆነ ሁኔታ እንዲኖር ያደርጋል።

በዚሁ ሁኔታ ውስጥ እኛ በትክክል ማን እንደሆንን እና ከአዳኝ ዳግም ምፅዓት በፊት የዓለም ታሪክ ውስጥ የእኛ ድርሻ ምን እንደ ሆነ እየተማርን ነው።

ስለ ድርሻዎ እያሰቡ ከሆነ፣ ለብቻዎ የሚሆኑበት ቦታ እንዲፈልጉ መጋበዝ እፈልጋለሁ እና የትኛውን ክፍል እንደሚጫወቱ እንዲያሳውቅዎ የሰማይ አባትን ይጠይቁ። በቃል ኪዳኑ እና በአገልጋይነት መንገዱ ላይ እግሮቻችንን ይበልጥ ስናቆማቸው መልሱ ቀስ በቀስ እና በኋላም ምናልባትም በግልፅ ይመጣል።

ጆሴፍ ስሚዝ በቃላት ጦርነት እና በአስተያየቶች ሁካታ መካከል በነበረበት ወቅት ያጋጠሙትን አንዳንድ ተመሳሳይ ችግሮች እያጋጠሙን ነን። በእራሱ ዘገባ ላይ እንደምናነበው ብዙውን ጊዜ ለራሱ እንዲህ ይጠይቃል፣ “ምን ይደረግ? ከእነዚህ ቡድኖች ሁሉ የትኛዎቹ ትክክል ናቸው፤ ወይስ ሁሉም የተሳሳቱ ናቸውን? ከእነርሱ አንዱ ትክክል ከሆነ፣ የትኛው ነው፣ እና እንዴትስ አውቀዋለሁ?” 3

“ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል”4 በሚለው በያዕቆብ መልእክት ውስጥ ባገኘው እውቀት፣ ጆሴፍ ከረጅም ጊዜ በኋላ “እግዚአብሔርን ለመጠየቅ”5 ቆራጥ አቋም ወሰደ።

በከፍተኛ ጭንቀቱ መካከል ሁሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ በማሰማት መጸለይን ገና ሞክሮ ስላልነበረ፣ ይህን አይነቱን ነገር በህይወቱ የሞከረው ለመጀመሪያ ጊዜ እንደነበር በተጨማሪም እናነባለን።6

እናም ከዚህ በፊት ፈጽሞ ባላደረግነው መንገድ ፈጣሪያችንን ስናነጋግረው ለእኛ የመጀመሪያ ሊሆን ይችላል።

በጆሴፍ ሙከራ ምክንያት፣ የሰማይ አባት እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በስም በመጥራት ለእርሱ ተገለጡ፣ እናም በዚህ ምክንያት ማን እንደሆንን እና በእውነቱ ትልቅ ዋጋ እንዳለን እናውቃለን።

በተጨማሪም በአስራዎቹ የለጋት ዕድሜ ውስጥ እያለ፣ ጆሴፍ ጓደኞቹ ሊሆኑ በሚገባቸው እና በደግነት ይይዙታል ተብለው በሚታመኑ ሰዎች ስደት እንደደረሰበት እናነባለን።7 ስለዚህም የደቀመዝሙርነት ሕይወት እንደመኖራችን መጠን የተወሰነ ተቃውሞ እንደሚጠብቀን እንጠብቃለን።

በአሁኑ ጊዜ የኦርኬስትራው አባል መሆን እንደማትችሉ ከተሰማችሁ እና የንስሐ ጎዳና ከባድ መስሎ ከታያችሁ፣ እባካችሁ ከቀጠልን ሸክማችን ከትከሻችን እንደሚወሰድ እና እንደገናም ብርሃን እንደሚኖር እወቁ። እርሱን ስንፈልገው የሰማይ አባት በጭራሽ አይተወንም። ልንወድቅ እና ልንነሳ እንችላለን እናም እርሱ ከጉልበታችን ላይ አቧራውን እንድናጸዳ ይረዳናል

አንዳንዶቻችን ቆስለናል ፣ ነገር ግን የጌታ የመጀመሪያ እርዳታ ቁሳቁስ ሁሉንም ቁስላችንን ለመሸፈን የሚያስችል በቂ መጠን ያላቸው ባንዶች አሉት።

እናም ያ ፍቅር ነው ያ ቅድመሁኔታ የሌለው ፍቅር የክርስቶስ ንጹህ ፍቅርም ብለን የምንጠራው፤ ያ ፍቅር ነው8 ወላጆች ለልጆቻቸው እና ልጆች ለወላጆቻቸው በሚያገለግሉባቸው በቤታችን ውስጥ አስፈላጊ የሆነው ፍቅር ነው። በዚያ ፍቅር በኩል፣ ልቦች ይለወጣሉ እናም የተወለዱ ምኞቶች ፈቃዱን ያደርጋሉ።

እንደሰማይ አባታችን ልጆች እና እንደ ቤተክርስቲያኑ አባላት ሁሉ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በኦርኬስትራዎቻችን ውስጥ ለማካተት የሚያስችለን ያ ፍቅር ነው እርስ በርሳችን ባለን መስተጋብር የሚያስፈልገው ፣ ስለሆነም አዳኝ በሚመጣበት ጊዜ ከመንግሥተ ሰማያት መላእክታዊ መዘምራን ቡድን አባላት ጋር በክብር ለመዘመር እንችላለን።

በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ስንሄድ አካባቢያችንን ማብራት ያለበት ያ ፍቅር ነው፡፡ ሰዎች ብርሃኑን ያስተውላሉ እናም ወደ እሱ ይሳባሉ። ያ የሚስዮናዊነት ሥራ ነው ሌሎችን “እንዲመጡ እና ፣ እንዲያዩ ፣ እንዲመጡ እና እንዲረዱ ፣ እንዲሁም እንዲመጡ እና እንዲቆዩ9 የሚስባቸው ።እባካችሁ ፣ ስለዚህ ታላቅ ስራ እና በዚህ ውስጥ ስላለን ድርሻ ምስክርነታችሁን ስትቀበሉ “ራእይን ተመልክቻለሁ፣አውቀዋለሁ፣ እግዚያብሄር እንደሚያውቀውም አውቃለሁ እናም ልክደው አልችልም“ ብሎ ካወጀው ከምንወደው ነብይ ከጆሴፍ ስሚዝ ጋር አብረን ደስ ይበለን፡፡10

እኔ ማን እንደሆንኩ እና እናንተ ማን እንደሆናችሁ እንደማውቅ እመሰክራለሁ። ሁላችንም የሚያፈቅረን የሰማይ አባት ልጆች ነን። የላከን እንድንወድቅ አይደለም ግን ወደ እርሱ በክብር እንድንመለስ ነው። እሱ በሚመጣበት ጊዜ የበለጠ እንደ እርሱ እንሆን ዘንድ በዚህ ታላቅ የአገልግሎት ሥራ ውስጥ ድርሻችንን እንድንረዳ ዘንድ ጸሎቴ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።