2010–2019 (እ.አ.አ)
ከዛፉ አጠገብ ቆዩ
ኤፕረል 2015


10:20

ከዛፉ አጠገብ ቆዩ

የሌሂ የህይወት ዛፍ ራእይ የእስከ መጨረሻው የመፅናት ሀይለኛ ምሳሌ ነው።

ፕሬዘዳንት ሄበር ጄ. ግራንት ከመሞታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ፣ ከወንድሞች አንዱ ቤታቸውን ጎብኝቶ ነበር። ከመሄዱ በፊት፣ ፕሬዘዳንት ግራንት እንዲህ ፀለዩ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ምስክርነቴን እንዳላጣ እና እስከ መጨረሻው በእምነት እንድቆይ ባርከኝ!”1 ወደ 27 አመት የቤተክርስቲያን ፕሬዘዳንትነት በኋላ፣ የልብ ፀሎቱ ይሄ ነበር። ማንም ሰው፣ በየትኛውም እድሜ፣ ከሰይጣን ተፅእኖ ነፃ እንዳልሆነ ምሳሌው ጉልህ ማስታወሻ ነው። ሁለቱ የሰይጣን በጣም ሀይለኛ መሳሪያዎች ማሳት እና ማታለል ናቸው።

እስከ መጨረሻው መጽናት የእውነተኛ ደቀመዝሙርነት መለያ ነው እና ለዘለአለማዊ ህይወት ወሳኝ ነው። ነገር ግን ፈተናዎች እና ችግሮች በመንገዳችን ሲመጡ፣ በብዛት እዚያው እንድንቆይ ይነገረናል። ግልፅ ልሁን፣ “እዚያው መቆየ” የወንጌል መርህ አይደለም። እስከመጨረሻው መፅናት ማለት በቀጣይነት ወደ ክርስቶስ መምጣት እና በእርሱ ፍጹም መሆን ነው።

እስከመጨረሻው መጽናት ለዘለአለማዊ ህይወት ወሳኝ ከሆነ፣ ለማመን ለምን እንታገላለን? ቅድሚያ የምሰጣቸው ነገሮችን በማፎካከር መካከል ስንያዝ እንታገላለን። በቸልተኝነት መታዘዝ እና ቀዝቃዛ መሰጠት እምነትን ያዳክማሉ። እስከ መጨረሸው መጽናት ለአዳኝ እና ለቃል ኪዳናችን ሙሉ መሰጠትን ይጠይቃል።

የሌሂ የህይወት ዛፍ ራእይ የእስከ መጨረሻው የመፅናት ሀይለኛ ምሳሌ ነው። እባካችሁ በፀሎት መንፈስ የሌሂን ህልም አጥኑ እና አሰላስሉ፤ ከዛ ከራሳችሁ ጋር አመሳስሉት። ያን ስታደርጉ፣ እስከመጨረሻው ለመፅናት የሚረዱንን ስድስት መርሆች በጥንቃቄ አስቡበት።

1. መፀለይ አትርሱ

“ጨለማ እና ድንግዝግዝ ውስጥ” በሌሂ ብቻ እንጀምር።2 እያንዳንዳችን የጨለማ እና ብቸኝነት ጊዜያት ያጋጥሙናል። “ህይወት ጨለማ እና ድንግዝግዝ ሲሆን፣ መፀለይ አትርሱ።”3 የፕሬዘዳንት ሄበር ጄ ግራንትን ምሳሌ ተከተሉ። እስከመጨረሻው ለመፅናት ጥንካሬ ፀልዩ። “ከዚህ የበለጠ ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ?” ብላችሁ የሰማይ አባትን ጠይቁ።

2. ወደ ክርስቶስ ኑ እና በእርሱ ፍፁም ሁኑ

በሌሂ ህልም ውስጥ የህይወት ዛፉ ማእከላዊ ትኩረት ነው። ሁሉም ነገር ወደ ህይወት ዛፍ ይጠቁማል። ዛፉ ክርስቶስን ይወክላል፣ እርሱም የእግዚአብሔር ፍቅር ንፁህ መገለጫ ነው። ፍሬው የእርሱ ዘለአለማዊ የሀጢአት ክፍያ ነው እና የእግዚአብሔር ፍቅር ትልቅ ማስረጃ ነው። ከምንወዳቸው ጋር ለዘለአለም መኖር ጣፋጭ እና ከምንም ነገር በላይ ተፈላጊ ነው። ይሄንን ስጦታ ለማስተዋል፣ ወደ “ክርስቶስ መምጣት፣ እና በእርሱ ፍፁማን መሆን” አለብን።4 እርሱ “መንገድ፣ እውነት፣ እና ህይወት” ነው።5 በስኬት እና በመልካም አድርጎት ህይወታችንን መሙላት እንችላለን፣ ነገር ግን በስተመጨረሻ፣ ክርስቶስን ለመከተል ቅዱስ ቃልኪዳንን ካልፈፀምን እና በእምነት ካልጠበቅናቸው፣ ነጥቡን ፈፅሞ እና ሙሉ በሙሉ እንስታለን።

3. በእምነተ ወደፊት ተጓዙ

ወደህይወት ዛፍ የሚመራ መንገድ አለ። ቀጥተኛ እና ጠባብ፣ ጥብቅ እና ልክ ነው። የእግዚአብሔር ትእዛዛት ጠብቅ ናቸው ነገር ግን የሚያግዱ አይደሉም። ከመንፈሳዊ እና አካላዊ አደጋዎች ይጠብቁናል እና ከመጥፋት ያድኑናል።

ታዛዥነት በክርስቶስ እምነትን ይገነባል። እምነት የድርጊት እና የሀይል መርህ ነው። የአዳኝ ምሳሌን በቀጣይነት መከተል መንፈሳዊ ሀይል እና ብቃትን ይፈጥራል። ያለ የሀጢያት ክፍያ አጠንካሪ እና አስቻይ ሀይል፣ በመንገዱ መቆየት እና መፅናት የማይቻል ነው።

“በክርስቶስ በመጽናት ቀጥሉ።”6

4. መፅሀፈ ሞርሞን ለመንፈሳዊ ኑሮ ቁልፍ ነው

የህይወት ጉዞ አስቸጋሪ ነው። ለመሳሳት፣ ከመንገዱ ለመውጣት እና ለመጠፋት ቀላል ነው። መከራ የዘለአለማዊ እድገታችን የማይቀር እና የሚያስፈልግ ክፍል ነው። መከራ ሲመጣ፣ ብዙም ያልተረዳችሁትን ነገር የምታውቁትን ነገር ሁሉ እንዳያሳጣችሁ። ታጋሽ ሁኑ፣ እውነትን ጠብቁ፤ መረዳት ይመጣል። ፈተናዎች አይናችንን ሊያውሩ እና ልባችንን ሊያደነድኑ የሚችሉ እንደ ጥልቅ ጨለማ ናቸው። “በቀጣይነት” 7የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቀን ካልያዝን እና ካልኖርነው፣መንፈሳዊ አዋቂ ከመሆን ይልቅ መንፈሳዊ እውር እንሆናለን። በየቀኑ በየቀኑ በየቀኑ መጽሐፈ ሞርሞንን እና በህይወት ያሉ ነብያትን ቃላት ፈልጉ!

5. አትሳቱ እና አትታለሉ

ማድመጥ ማለት በጥንቃቄ ትኩረት መስጠት ነው። በክርስቶስ የማያምኑትን መስማት እርሱን እንድታገኙ አይረዳችሁም። ለእውቀት ትልቁን ህንፃ መፈለግ ወደ እውቀት አይመራችሁም። እዚያ አልተለጠፈም። አዳኙ ብቻ “የዘለአለማዊ ህይወት ቃላት” አለው።8 ሌሎች ሁሉ ዝምብሎ ቃላት ናቸው። ትልቁ ህንፃ “የአለምን ከንቱ ሀሳብ እና ኩራትን”9 ያመለክታል፣ በሌላ አነጋገር፣ አሳች እና አታላይ። ሁሉም ነገር ያላቸው በሚመስሉ ጥሩ በለበሱ ሰዎች ተሞልቷል። ነገር ግን አዳኝን እና የሚከተሉት ላይ ያሾፋሉ። እነርሱ “ሁሌም ይማራሉ፣ ግን ወደ እውቀት በፍፁም አልመጡም።”10 በፖለቲካዊ ትክክል ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን በመንፈሳዊ ጠፍተዋል።

6. ከዛፉ አጠገብ ቆዩ

የሌሂ መልእክት ከዛፉ አጠገብ መቆየትን ነው። የምንቆይበት ምክንያት ወደ ጌታ ስለተቀየርን ነው። አልማ እንዲህ አስተማረ፣“እነሆ፣ልባቸውን ለወጠው፣ አዎን፣ ከጥልቅ ጨለማ አነቃቸው፣ እና ወደ እግዚአብሔር ነቁ።”11 ልባችንን ለእግዚአብሔር ስንሰጥ፣ መንፈስ ቅዱስ ዋና ተፈጥሮአችንን ይቀይረዋል፣ ወደ ጌታ በጥልቀት እንለወጣለን፣ እና ከዚያ በኋላ ትልቁን ህንፃ አንሻም። ጥልቅ ለውጥ የሚያመጡትን ነገሮች ማድረግ ካቆምን፣በመንፈስ ወደ ኋላ እንሄዳለን። ክህደት የመለወጥ ተቃራኒ ነው።

ለበፊት እና ለአሁን ሚስኦናውያን በሙሉ፤ ኤልደሮች እና እህቶች፣ ከሚስኦናችሁ እንዲሁ መመለስ አትችሉም፣ እንደ ዳክዬ በመዝለል ወደ ባቢሎን መግባት አይቻልም፣ በመንፈሳዊ ጥልቅ እንቅልፍ ሳይተኛ በቪድዮ ጨዋታዎች ትርጉም አልባ ነጥቦችን በማስቆጠር የማያልቁ ሰአታትን ማጥፋት አይቻላችሁም።እንዲሁም ለኦን ላይን የራቁት ምስል መገዛት አትችሉም እናም ያለ አደገኛ መንፈሳዊ ውጤቶች ጥሩነትን እና ልግስናን ችላ ማለት አትችሉም። መንፈስን ካጣችሁ፣ ጠፍታችኋል። አትሸወዱ እና አትታለሉ።

እውነተኛ ደቀመዛሙርት በግል ፀሎት፣ በፅኑ የቅዱስ መጽሀፍ ጥናት፣ የግል ታዛዥነት፣ እና እራስ ወዳድ ባልሆነ አገልግሎት እያንዳንዱን ቀን ለእግዚአብሔር ይነቃሉ። በዛፉ አከባቡ ቆዩ እና ነቅታችሁ ቆዩ።

ከብዙ አመታት በፊት፣ እህት ፒየርሰን እና እኔ የዋሺንግተን ታኮማ ሚስኦንን እንድንመራ ተጠርተን ነበር። ጥሪው በጣም አስገራሚ ነበር። በስራው ፍራቻ ሆኜ ከተቀጠርኩበት ካምፓኒ ሊቀመንበሩን እና ሲኢኦ አናገርኳቸው እና ስለ የሚስኦን ጥሪዬ አሳወኳቸው። ድርጅቱን ለመልቀቅ በነበረኝ ውሳኔ መናደዳቸው ይታይ ነበር። “መቼ ነው ይህንን የወሰንከው፣ እና ቀደም ብለህ ለምን አላወያየኸንም?” ብለው ጠየቁ።

በግልጽነት፣ ጽኑ መልስ ወደ አእምሮዬ መጣ። እንዲህ አልኩኝ፣ “ይሄንን ውሳኔ የ19 አመት ወጣት ሳለሁ ወስኜ ነበር፣ ኢየሱስን ለመከተል በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ቅዱስ ቃልኪዳን በገባሁ ጊዜ። ሙሉ ህይወቴን በእነዚያ ቃልኪዳኖች ላይ ነው የገነባሁት። እና አሁን እነሱን ለመጠበቅ ሙሉ ውጥኔ ነው።”

ከእግዚአብሔር ጋር ቃልኪዳን አንዴ ከገባን፣ ወደ ኋላ መመለስ የለም። ማስረከብ፣ ተስፋ መቁረጥ፣ እና መተው አማራጮች አይደሉም። በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ፣ ለደህንነት ምርጥ ደንብ አለ። ጀግና ደቀመዝሙርነትን ይጠይቃል! ለአማካይ እና ለግል ደስታ ደቀመዝሙራት ቦታ የለም። አማካይ የምርጥነት ተቃራኒ ነው፣ እና በአማካይ መሰጠት እስከመጨረሻው ከመፅናት ያግዳችኋል።

እየታገላችሁ፣ ግራ ገብቷችሁ፣ ወይም በመንፈሳዊ ጠፍታችሁ ከሆነ፣ ወደ ቀድሞ መንገድ እንደሚመልሳችሁ የማውቀውን አንድ ነገር አድታደርጉ እገፋፋችኋለሁ። መጽሐፈ ሞርሞንን በፀሎት መንፈስ በማንበብ እንደገና ጀምሩ እና ትምህርቶቹን በየቀኑ በየቀኑ በየቀኑ ኑሯቸው። ህይወታችሁን ስለሚቀይረው እና ክርስቶስን ለመከተል ያላችሁን ለውጥ ስለሚያጠነክረው ጥልቅ የመጽሐፈ ሞርሞን ሀይል እመሰክራለሁ። መንፈስ ቅዱስ ልባችሁን ይቀይራል፣ እና “ነገሮች በእውነት እንደሆኑት” እንድታይዋቸው ይረደችኋል።12 በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ያሳያችኋል። ይሄ ኔፊ ለእናንተ የገባው ቃል ነው፤

“ እናም አልኳቸው… የእግዚያብሄርን ቃል ለሚሰሙ ሁሉ፣ እናም እርሱን አጥብቆ የያዘ በፍፁም አይጠፋም፤ ፈተናዎችም የጠላት ክፉ ፍላፃ እነርሱን በማሳውር አሸንፈው ወይም ወደ ጥፋት ለመውሰድ አይችሉም።

“ስለዚህ፣ እኔ የእግዚያብሄርን ቃል እንዲቀበሉ አበረታታኋቸው፤ ሁሌም በሁሉ ነገሮች ትዛዛቶቹን ለመጠበቅ አስታውሱ።”13

ወንድሞች እና እህቶች፣ እስከመጨረሻው መፅናት የደቀመዝሙርነት ትልቁ ፈተና ነው። የየቀን ደቀመዝሙርነታችን ዘለአለማዊ እጣፈንታችንን ይወስናል። ለእግዚአብሔር መንቃት፣ ከእውነት ጋር መጣበቅ፣ የቤተመቅደስ ቅዱስ ቃልኪዳንን ጠብቁ፣ እና በዛፉ አጠገብ ቆዩ!

ትንሳኤ ስላደረገው ህያው ክርስቶስ ምስክርነቴን አካፍላለሁ። እርሱ እንዳለ አውቃለሁ። ታላቁ ፍላጎቴ ድንቅ የሆነው ምሳሌውን እስከ መጨረሻው በመከተል እውነተኛ እና ታማኝ መሆን ነው። በቅዱሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።