ቤተሰብ የእግዚአብሔር ነው
ሁላችንም በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ እንካተታለን እና እንፈለጋለን።
ስለወንጌል ንጹህ እና እውነት ከሚያስተምረው ከመጀመሪያ ክፍል መዝሙር በላይ በተጨማሪ የሚያምር እና የሚያስገርም ምን አለ? እናም በዚህ ምሽት የምትገኙት የመጀመሪያ ክፍል ሴቶች የምናቀርባቸው መዝሙሮች ምን እንደሆኑ ታውቃላችሁ። በመጀመሪያ ክፍል ፕሮግራማችሁ ባለፈው አመት እነዚህን ተምራችኋል።
በዚህ ስብሰባ መጀመሪያ በተዘመረው “ቤተሰብ የእግዚአብሔር ነው”1 ከሚለው መዝሙር ቃላት ውስጥ ንጹህ የሆነን ትምህርት እንድናስታውስ ተደርገናል። ቤተሰብ የእግዚአብሔር እንደሆነ ከመማር በተጨማሪ እኛ እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንደሆንን ተምረናል።
የመዝሙሩ የመጀመሪያ ክፍል እንዲህ ያስተምራል፥ “አባታችን ቤተሰብ አለው። ያም እኔ ነኝ! ያም እናንተ፣ ሌሎችም ናችሁ። ሁላችንም የእርሱ ልጆች ነን።” በቤተሰብ አዋጅ ውስጥ እንዲህ እንማራለን፣ “ከምድር ህይወት በፊት፣ የመንፈስ ወንድ እና ሴት ልጆች እግዚአብሔርን እንደ ዘለአለም አባታቸው ያውቁ እና ያመልኩ ነበር።” በዚያም ቦታ፣ ስለ ዘለአለማዊ ሴትነታችን ተማርን። እያንዳንዳችን፣ የሰማይ ወላጆች ተወዳጅ ሴት ልጅ” እንደሆንን ተማርን።2
ወደምድር የተጓዝንበት ስጋዊ ጉዞ እነዚያን እውነቶች አልቀየረም። እያንዳዳችንም በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ክፍል አለን እናም ተፈላጊ ነን።ምድራዊ ቤተሰቦች ሁሉ የተለያዩ ናቸው። እና ምንም እንኳን ጠንካራ ባህል የሚያከብር ቤተሰብ ለመገንባት ብንጥርም፣ በእግዚአብሔር ቤተሰብ አባል መሆን በምንም አይነት አቋም፣ እንዲሁም በጋብቻ አቋም፣ በወላጅነት አቋም፣ በገንዘብ አቋም፣ በህብረተሰብ አቋም፣ ወይም በኢንተርኔት ስለሁኔታችን በምንገልጽበት ሁኔታ ላይ የሚመካ አይደለም።
ክፍል አለን። “የሚወደን የሰማይ አባታችን የሴት ልጆች ነን፣ እናም እርሱንም እንወዳለን።”3
የመዝሙሩ ሁለተኛ ክፍል በመጀመሪያው ላይ ይገነባል። “እያንዳንዳችንን፣ በቤተሰቦች ውስጥ እንድንኖር እና እንድንማር፣ በመወለድ አማካኝነት ወደምድር ልኮናል።”
በምድር ህይወት ውስጥ፣ የሟችነት ጊዜ እንደሚያስፈልገን ተማርን። እኛም “ወደ ፍጹምነት እና በመጨረሻም እንደ ዘለአለም ህይወት ወራሾች መለኮታዊ እጣ ፈንታቸውን በመገንዘብ ልጆቹ ስጋዊ ሰውነት እና ምድራዊ አጋጣሚዎችን የሚያገኙበትን የሰማይ አባት እቅድ ተቀበልን።”4
ሽማግሌ ሪቻርድ ጂ. ስኮት እንደገለጹት፣ “ከቅድመ ህይወት አለም ውስጥ ወደዚህ የመጣንበት አላማችን ለመፈተን እና ለመሞከር ነበር።”5 ያም መሞከር የሚመጣው ይህን በሚያጋጥማቸው ግለሰቦች አይነት የተለያየ ነው። በመፋታት፣ ትቶ በመሄድ ምክንያት በሚመጣው ጉዳት እና አለመተማመን፣ ወይም ያላገባች እናት ከመሆን የተያያዙ ሀላፊነቶችን አጋጥመውኝ አያውቁም። የልጅን መሞት፣ ልጅ ለመውለድ አለመቻልን፣ ወይም ከአንድ አይነት ጾታ ጋር መዋደድን አጋጥሞኝ አያውቅም። መጎሳቀልን ወይም መጥፎ በሽታን ወይም ሱስንም በህይወቴ አጋጥሞኝ አያውቅም። እነዚህ እኔ የምሞከርበት እድሎች አልነበሩም።
ስለዚህ አንዳንዶቻችሁ፣ “እህት ስቲቨንስ፣ ይህ አይገባዎትም!” ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ይህንንም ትክክል ትሆኑ ይሆናል ብዬ እመልሳለሁ። የእናንተን ፈተና በሙሉ አልረዳም። ነገር ግን እንድንበረከክ ባደረጉኝ በግል ፈተናዬ በኩል፣ ይህ ከሚገባው፣ “ከሀዘን ጋር ከሚተዋወቀው”6፣ ሁሉም ካጋጠመው፣ እና ሁሉንም ከሚረዳው ጋር በደንብ ለመተዋወቅ ችያለሁ። በተጨማሪም፣ በሴት ልጅ፣ በእናት፣ በሴት አያት፣ በእህት፣ በአክስት፣ እና በጓደኛ በኩል የጠቀስኳቸው ስጋዊ ፈተናዎች አጋጥመውኛል።
እንደ እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ጠባቂ ሴት ልጆች እድላችን ከፈተናዎቻችን ለመማር ብቻ አይደለም። ይህም ቃል እንደገባነው ሌሎች የእግዚአብሔር ቤተሰብ አባላትን በሚታገሉበት በሀዘን እና በርህራሄ አንድ መሆን ነው።
ይህን ስናደርግ፣ አዳኝ የመንገዱ ችግሮችን እንደሚያውቅ እና በምንም ሀዘን ወይም ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እንደሚመራን መረዳት እና ማመንም ይመጣል።እርሱም የእውነት ልግስና ነው፣ እና ስንከተለውም ፍቅሩ በእኛ በኩል “ለዘለአለም ይጸናል”7
እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች እና እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቶች፣ “እግዚአብሔር በልባችን በተከላቸው በነዛ የሀዘን ስሜቶች መሰረት ተግብሩ።8 ተፅዕኖ ለማድረግ የምንችልባቸው ቦታዎች በቤተሰቦቻችን ብቻ የተገደቡ አይደሉም።
በቅርብ በቺንሌ አሪዞና ካስማ ከምትኖረው እህት ያዚ ጋር ለመገናኘት እድል ነበረኝ። ወደ ቤቷ ስትጋብዘኝ፣ በግድግዳዋ እና በጠረጴዛዋ ላይ ያሉትን የተለያዩ የቤተሰብ እና የሚስዮኖች ፎቶዎች ነበር መጀመሪያ ያየሁት። ስለዚህ “ስንት የልጅ ልጆች አሉሽ?” ብዬ ጠየኳት።
በጥያቄዬ ተገርማ፣ ተንከሻዋን ነቅንቃ ዝም አለች። በመልሷ ግራ በመጋባት፣ “ስንት የልጅ ልጆች እንዳሏት አታውቅም። ሁሉም ልጆች አያቴ ብለው ይጠሯታል። እርሷ ለሁሉም አያት ነች” ብላ ወደምትመልስልኝ የእሷ ሴት ልጇ፣ እህት ዬሎሄርን ተመለከትኩኝ።
እህት ያዜ ፍቅሯን እና ተፅዕኖዋን በደም ቤተሰብ ለሆኑት ብቻ እንዲሆን አታደርግም። መልካም በማድረግ፣ በመባረክ፣ በመንከባከብ፣ እና የእግዚአብሔር ቤተሰብን በመጠበቅ የተፅዕኖ ክቧን ማስፋፋት ምን እንደሆነ ተረድታ ነበር። “ሴት የልጅን እምነት ስታጠናክር፣ አሁን እና ለወደፊት ለቤተሰብ ጥንካሬ ታዋጣለች” የሚለውን ተረድታለች።9
ሶስተኛው የመዝሙሩ ክፍል የሟችነት ህይወት አላማን ይገልጻል፥ “እግዚአብሔር እንድንሆን የሚፈልገውን ለመሆን እንድንችል ቤተሰብ ሰጥቶናል።” አዳኝ እንዳስተማረው፣ “አንድ ሁኑ፤ እናም አንድ ካልሆናችሁ የእኔ አይደላችሁም።”10 የቤተሰብ አዋጅ እንደሚያስተምረው፣ እንደ ሰማይ ወላጆች ተወዳጅ ሴት ልጆች፣ መለኮታዊ የሆነ ፍጥረት፣ ዘለአለማዊ የሆነ ማንነት፣ እና አላማ አለን። እግዚአብሔር በግል ህይወታችን ልዩነት ቢኖረንም አንድ በመሆን፣ ወደ እርሱ ፊት ለመመለስ ፣ እንደ ዘለአለም ቤተሰቡ ከእርሱ ጋር ለመተሳሰር የሚያስፈልገንን በሙሉ ለመማር ፍላጎት ያለን ቃል ኪዳን ጠባቂ በመሆን አንድ እንድንሆን ይፈልገናል።11
“ወደ እግዚአብሔር ፊት እንድንመለስ እና ቤተሰቦች ለዘለአለም አንድ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ቅዱስ ስርዓቶች እና ቃል ኪዳኖች በቤተመቅደስ ውስጥ ይገኛሉ።”12 በጥምቀት እና በቅዱስ ቤተመቅደስ ውስጥ የምንቀበላቸው ስርዓቶች እና የምንገባቸው ቃል ኪዳኖች የእግዚአብሔርን ቤተሰብ በመጋረጃው ሁለት በኩል ያገናኛሉ፣ በዚህም “አንተ አባት ሆይ፣ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፣ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ” ብሎ በጸለየው በልጁ በኩል ከአባታችን ጋር ያገናኙናል።13
የምድራዊ ህይወት ጊዜአችንን የአዳኝን ትምህርቶች በማጥናት እና በመከተል ስናሳልፍ፣ በበለጠ ሁኔታ እንደ እርሱ እንሆናለን። ሌላ መንገድ የሌለበትን የእርሱን መንገድ እንረዳለን፣ ስጋዊ ፈተናዎችን እንቋቋማለን፣ እንፈወሳለን፣ እናም ወደ ሰማይ ቤታችን እንመለሳለን።
የመጨረሻው የመዝሙር ክፍልም ወደጀመረበት ይመለሳል፥ “በዚህን ነው ፍቅሩን የሚያካፍለው፣ ቤተሰብ የእግዚአብሔር ነውና።” አባት ለልጆቹ ያለው እቅድ የፍቅር እቅድ ነው፣ እናም ልጆቹን፣ ቤተሰቡን፣ ከእርሱ ጋር አንድ የሚያደርግ እቅድ ነው። ሽማግሌ ራስል ኤም ባለርድ እንዳስተማሩት፥ “የሰማይ አባት ለልጆቹ ሁለት ፍላጎቶች አሉት…። አለሟችነት እና ዘለአለማዊ ህይወት፣ ‘ይህም ማለት ከእርሱ ጋር በቤት ውስጥ መኖር ነው።’” 14 ይህን ፍላጎት ለማግኘት የሚቻለው የሰማይ አባት ለቤተሰቡ ያለውን የፍቅር እቅዱን ከሌሎች ጋር በመካፈል ነው።
ከ20 አመት በፊት፣ ቀዳሚ አመራር እና የአስራ ሁለት ሐዋሪያት ሸንጎ ለአለም በሙሉ ይህን አዋጅ አካፈሉ። ከዛ ጊዜ ወዲህ፣ በቤተሰብ ላይ ጥቃቱ ጨምሯል።
እንደ እግዚአብሔር ሴት ልጆች ያለብንን በቅዱስ ሀላፊነቶቻችንን ማሳካት ካለብን፣ የሰማይ አባት ለቤተሰብ ያለውን እቅድ እውነት ለማስተማር ያለን የግል ሀላፊነቶቻችንን መረዳት አለብን። ፕሬዘደንት ሀወርድ ደብሊው. ሀንተር እንደገለጹት፥
“የሚከብበንን ክፋት ለማቆም እና የዳኛችንን ስራ ወደፊት ለመግፋት የቤተክርስቲያኗን ሴቶች ከወንድሞች ጋር ማስተባበር በጣም አስፈላጊ ነው።…
“…ስለዚህ ቤተሰቦቻችንን፣ ቤተክርስቲያናችንን፣ እና ህብረተሰቦቻችንን በሀይለኛው የመልካም ተፅዕኖአችሁ እንድታገለግሉ እንጠይቃችኋለን።”15
እህቶች፣ እኛ እንካተታለን። ተፈቅረናል። እንፈለጋለን። መለኮታዊ አላማ፣ ስራ፣ ቦታ፣ እና ሀላፊነት በቤተክርስቲያኗ እና በእግዚአብሔር መንግስትና በዘለአለማዊ ቤተሰቡ ውስጥ አለን። በልባችሁ ውስጥ የሰማይ አባታችሁ እንደሚያፈቅራችሁ እና እናንትን እና የምታፈቅሯቸውን ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ እንደሚፈልግ ታውቃላችሁን? ልክ “የሰማይ አባት እና ልጁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እንደሆኑ…፣ ለእኛ ያላቸው ተስፋም ፍጹም ነው።”16 ለእኛ ያላቸው እቅድ ፍጹም ነው፣ እናም ቃል ኪዳናቸውም የተረጋገጠ ነው። ስለእነዚህ እውነቶች በምስጋና የምመሰክረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው፣ አሜን።