2010–2019 (እ.አ.አ)
ክህነት–ቅዱስ ስጦታ
ኤፕረል 2015


13:15

ክህነት–ቅዱስ ስጦታ

እያንዳንዳችን ለሰው ዘር ከተሰጡት በጣም ዕንቁ ከሆኑ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ስጦታ ተሰጥቶናል።

ከትውሳታዎቼ መካከል በጣም ግልፅ የሆነው አንዱ ትውስታዬ አዲስ እንደተሾመ ዲያቆን የክህነት ሰብሰባዎችን ስካፈልና ክህነትን የተቀበላችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ኑ”1 ሚለውን መዝሙር ስዘምር ነው። ዛሬ ማታ በዚህ የጉባኤ አዳሽ ውስጥና በእርግጥ በአለም ዙሪያ ለተሰበሰባችሁት የዛን ለየት ያለ “ክህነትን የተቀበላችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ኑ” የሚለውን መዝሙር መንፈስ አስተጋባለሁ። ጥሪዎቻችንን እናስብ፤ ስለ ግዴታቻችን እናስብ፤ ኃላፊነታችንን እንወቅ፤ እናም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንከተል። በእድሜ፣ በባህል ወይም በዜግነት ብንለያይም፣ በክህነት ጥሪዎቻችን እንደ አንድ ሆነናል።

የአሮናዊ ክህነት በመጥምቁ ዮሐንስ ለኦሊቨር ካውድሪና ለጆሴፍ ስሚዝ መመለስ ለእያንዳንዳችን በጣም ጠቃሚ ነው። በተመሳሳይ መልኩ፣ የመልከፀዴቅ ክህነት ለጆሴፍና ለኦሊቨር በጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ መመለስ ዋጋ የምንሰጠው ክስተት ነው።

ከተሸከምነው ክህነት ጋር የሚመጡትን ጥሪዎች፣ ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች በተገቢው መንገድ እንውሰዳቸው።

የዲያቆን ምልዓተ ጉባኤ ፀሐፊ ሆኜ ስጠራ ትልቅ ግዴታ ተሰማኝ። በዛ ጥሪ ውስጥ የተቻለኝን ለማድረግ ስለፈለኩኝ የጠበኳቸውን መዝገቦች በጣም በጥንቃቄ አዘጋጀሁ። በስራዬ በጣም ኮራሁ። በማንኛውም ቦታ ላይ ብሆንም በተቻለኝ አቅም ማድረግ የምችለውን በሙሉ ማድረግ ግቤ ሆኗል።

እያንዳንዱ ለአሮናዊ ክህነት የተሾመ ወጣት ወንድ የተሾመበት ጥሪ ቅድስና መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን እንዲሁም ያንን ጥሪ የሚያጎላበት እድሎች እንደተሰጠውተስፋ አደርጋለሁ። ዲያቆን ሆኜ የኤጲስ ቆጶሶቹ አመራር ከቤተክርስቲያናችን አንድ ማይል እርቀት ላይ ላሉት እስረኞች ቅዱስ ቁርባንን እንድወስድ ሲጠይቁኝ እንደዚህ አይነት እድልን ተቀብያለሁ። በዛ በተለየ የእሁድ ጠዋት ላይ የወንድም ራይትን በር ሳንኳኳ “ግባ” የሚል የደከመ ድምፁን ሰማሁ፣ በትንሽዬ ቤቱ ብቻ ሳይሆን በጌታ መንፍስ በተሞላ ቤቱ ውስጥ ገባሁ። የወንድም ራይትን አልጋ ተጠጋሁና የዳቦ ቁራሽ ከንፈሮቹ ላይ አስቀመጥኩኝ። ከዛ መጠጣት ይችል ዘንድ የውኃን ኩባያ ያዝኩት። ልወጣ ስል “ልጄ እግዚአብሔር ይባርክህ” ሲለኝ እንባዎች አይኑ ላይ አየሁ። እናም ለቅዱስ ቁርባንና ለተሸከምኩት ክህነት ባለኝ አድናቆት በእርግጥ እግዚአብሔር ባረከኝ።

ከዋርዳችን ማንም ዲያቆን፣ አስተማሪ ወይም ካህን ወደ ክላርክስተን ዩታ ከመጽሐፈ ሞርሞን ሶስቱ ምስክሮች አንዱ የሆነውን የማርቲን ሀሪስን የመቃብር ቦታ የማይረሳ ጉብኝት ሊረሳ የሚችል የለም። የመቃብሩን ሀውልት ከብበን ቆመን እና በጥልቅ የሚሰሙትን “የሶስት ምስክሮች ምስክርነት” ቃላትን ከቡድን መሪዎች አንዱ ሲያነብልን፣ ለዚያ ቅዱስ መፅሐፍ እና በዚያ ለሚገኙት እውነቶች ታላቅ ፍቅር አገኘን።

በእነዛ አመታት ወቅት አላማችን እንደ ሞዛያ ልጆች ለመሆን ነበር። ስለእነሱም ይህ ተብሏል፥

“እውነትን በማወቅ የጠነከሩ ነበሩ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ያውቁ ዘንድ ቅዱሳን መጽሐፍትን በትጋት የሚያጠኑ እና በቀላሉ የሚረዱ ነበሩ።

“ነገር ግን ይህ ብቻም አልነበረም፤ እራሳቸውን በጸሎትና በፆም አተጉ፤ ስለዚህ የትንቢት መንፈስ፤ እናም የራዕይ መንፈስ ነበራቸው፣ እናም በሚያስተምሩበት ጊዜም በእግዚአብሔር ኃይልና ሰልጣን አስተማሩ።”2

እንደ ሞዛያ ደፋርና ፃድቅ ወንድ ልጆች ከመጠራት የላቀ ለወጣት ወንድ አለ የምለው ብቁ ግብ አለ ብዬ አላስብም።

18ኛውን ልደቴን ስቃረብና በሁለተኛው የአለመ ጦርነት ለወጣት ወንዶች አስገዳጅ የነበረውን የውትድርና አገልግሎት ለመግባት ስዘጋጅ፣ የመልከፀዴቅ ክህነትን ለመቀበል ተመርጬ ነበር፣ ነገር ግን መጀመሪያ ለካስማ ፕሬዘደንቴ ፖል ሲ ቻይልድ ለቃለ መጠይቅ ስልክ መደወል ነበረብኝ። ቅዱሳት መጽሐፍትን የወደደና የተረዳ ነበረና ሌሎችም በተመሳሳይ መንገድ እንዲወዷቸውና እንዲረዷቸው አላማው ነበር። የእሱን የጠለቀና የሚመረምር ቃለ መጠይቆች ከአንዳንድ ጓደኞቼ በመስማት፣ የቅዱሳት መጽሐፍቴን እውቀት መጋለጥ ውስንነት ተመኘሁ፤ ስለሆነም ስደውልለት የሚቀጥለው እሁድ ቅዱስ ቁርባን ከመጀመሩ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ እንድንገናኝ ሃሳብ አቀረብኩኝ።

የእርሱም መልስ፥ “ኦ ወንድም ሞንሰን ያ ቅዱሳት መጽሐፍትን ለማንበብ በቂ ሰዓት አይሰጠንም” ነበር። ከዛ ከቅዱስ ቁርባኑ ሶስት ሰዓታት አስቀድሞ ለመገናኘት ሀሳብ አቀረበና በግል ምልክት የተደረገበትን ቅዱሳት መጽሐፍቶቼን ይዤ እንድመጣ ነገረኝ።

እሁድ እቤቱ ስደርስ በሞቀ ሁኔታ ተቀበለኝና ቃለ መጠይቁ ጀመረ። ፕሬዘደንት ቻየልድ እንዲህ አለኝ፣ “ወንድም ሞንሰን፣ አሮናዊ ክህነትን ተሸክመሃል። መልአክቶች አገልግዉህ ያውቃሉን?” እንደማያውቁ መልስ ሰጠሁ። እንደዚህ አይነት ነገር አጋጥሞኝ እንደነበር ሲጠይቀኝ በድጋሚ አጋጥሞኝ እንደማያውቅ መለስኩኝ።

እንዲህም አስተማረ፣ “ወንድም ሞንሰን፣ ከአዕምሮህ የትምህርትና ቃልኪዳኖችን 13ኛ ክፍል ተናገር።”

እኔም ጀመርኩኝ፣ “አገልጋይ ባልንጀሮቼ፣ የመላእክትን፣ እና የንስሀን ወንጌል፣ እና ለኃጢአት ስርየት በማጥለቅ የማጥመቅ አገልግሎት ቁልፎች የያዘውን የአሮንን ክህነት በመሲሁ ስም ለእናንተ እሰጣችኋለሁ”

ፕሬዘደንት ቻየልድ “አቁም” አለ። ከዛ ዝግ ባለ፣ ደግ በሆነ ድምፅ እንዲህ መከረኝ፣ “ወንድም ሞንሰን፣ እንደ አሮናዊ ክህነት ተሸካሚ ለመልአክቶች አገልግሎት እንደተሾምክ መቼም እንዳትረሳ።”

በዛን ቀን መልአክ በክፍሉ ውስጥ ያለ ነበር የሚመስለው። ቃለ መጠይቁን መቼም አልረሳሁትም። በአንድ ላይ በመሆን የአሮናዊ ክህነትንና የመልከፀዴቅ ክህነትን ግዴታዎች፣ ኃላፊነቶችና በረከቶች ስናነብ በዛ ወቅት የተሰማኝ መንፈስ አሁንም ይሰማኛል።

ሽማግሌ ሆኜ ተሾምኩኝ፣ እና በባህር ኃይል ውስጥ አገልግሎቴን ለማሟላት በምሄድበት ቀን፣ የዋርዴ የኤጲስ ቆጶስ አመራር አባል ከቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር በባቡሩ ጣቢያ ሊሰናበተኝ ተቀላቀለ። ባቡሩ ላይ ከመውጣቴ በፊት የሚስዮን መመሪያ መጽሐፍ የሚል ትንሽ ይዘት ያለው መጽሐፍ በእጄ ላይ አኖረ።

“ለማንኛውም ውሰደው የሆነ ቀን ሊጠቅምህ ይችላል” ብሎ መለሰልኝ።

ጠቃሚም ሆነ። ልብሶቼ ደህና እንዲሆኑና እንዳይጨማደዱ የሚረዳኝን ጠንካራ፣ አራት መዐዘን የሆነ ዕቃ ከቦርሳዬ ታች ለማሰቀመጥ ፈልጌ ነበር። ይሄ የሚስዮን መመሪያ መጽሐፍ የምፈልገው ነገር ነበር እና ለ12 ሳምንታት በሚገባ በቦርሳዬ ውስጥ አገለገለ።

ለገና በዓል እረፍት ከመሄዳችን በፊት ባለው ምሽት፣ ሃሳባችን ስለቤት ነበር። መአከሉ ፀጥ ብሎ ነበር፣ ነገር ግን ፀጥታው ከኔ ቀጥሎ ባለው አልጋ ላይ በነበረው የሞርሞን ጓደኛዬ በሊላንድ ሜረል የህመም ጩኸት ተሰበረ። ምን እንሆነ ጠየኩኝ እናም በጣም እንዳመመው ነገረኝ። ወደ ህክምና መአከሉ መሄድ አልፈለገም ነበር ምክንያቱም ይህን ማድረግ በሚቀጥለው ቀን ወደ ቤት ከመሄድ እንደሚያግደው አውቆ ነበርና።

ሰዓታት ባለፉ ቁጥር እየባሰበት መጣ። በመጨረሻ ሽማግሌ መሆኔን በማወቅ የክህነት በረከት እንድሰጠው ጠየቀኝ።

ከዚህ በፊት በረከት ሰጥቼ አላውቅም ነበር፣ በረከት ተቀብዬ አላውቅም ነበር እናም በረከት ሲሰጥም አይቼ አላውቅም ነበር። ለእርዳታ በውስጤ ከፀለይኩኝ በኋላ፣ ከቦርሳዬ ታች ያለውን የሚስዮን መመሪያ መጽሐፉን አስታወስኩኝ። በፍጥነት ቦርሳዬ ውስጥ ያሉትን ነገሮች አመጣሁኝና መጽሐፉን ወደ የምሽቱ ብርሃን ወስድኩት። አዛ አንድ ሰው የታመመን እንዴት እንደሚባርክ አነበብኩኝ። ብዙ ግራ የተጋቡ መርከበኞች እያዩ መባረኬን ቀጠልኩኝ። ሁሉንም ነገሮች ወደ ቦርሳዬ መልሼ ከማስገባቴ በፊት ሊላንድ ሜረል ልክ እንደ ህፃን እየተኛ ነበር። በሚቀጥለው ቀን ደህና ሆኖ ተነሳ። እያንዳንዳችን ለክህነት ኃይል የተሰማን ምስጋና የላቀ ነበር።

አመታቱ በረከት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በረከት ለመስጠት መቁጠር ከምችለው በላይ እድሎችን አምጥተውልኛል። በእያንዳንዱ እድሎች እግዚአብሔር ይህን ቅዱስ ስጦታ ስለሰጠኝ በጥልቅ አመስጋኝ ሆኛለሁ። ክህነትን አከብራለሁ። ብዙ ጊዜ ኃይሉን አይቻለሁ። ጥንካሬውን አይቻለሁ። ባመጣው ታምራቶች ተገርሜያለሁ።

ወንድሞች፣ እያንዳንዳችን ለሰው ዘር ከተሰጡት በጣም ዕንቁ ከሆኑ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ስጦታ ተሰጥቶናል። ክህነታችንን ስናከብርና ሕይወታችንን በሁሉም ጊዜ ብቁ እንደሆንን ሆነን ስንኖር፣ የክህነቱ በረከቶች በውስጣችን ያልፋሉ። በትምህርትና ቃልኪዳኖች ክፍል 121 ቁጥር 45 ውስጥ ያሉትን ብቁ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን የሚነግሩንን ቃሎች እወዳቸዋለሁ። እንዲህ ይላሉ፥ “አንጀትህም ለሁሉም ሰው እና ለእምነት ቤተ ሰዎች በልግስና ይሞላ፣ እና ምግባረ በጎነትም ሳያቋርጥ አስተሳሰብህን ያሳምር፤ ከዚያም ልበ ሙሉነትህ በእግዚአብሔር ፊት እየጠነከረ ይሄዳል፤ እና የክህነት ትምህርትም በነፍስህ ላይ እንደ ሰማይ ጠል ትንጠባጠብልሀለች።”

እንደ የእግዚአብሔር ክህነት ተሸካሚ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስራ ውስጥ ነን ያለነው። ጥሪዎቹን መልሰናል፤ በእርሱ ስራ ውስጥ ነው ያለነው። ስለ እርሱ እንማር። የእግራ አሻራዎቹን እንከተል። ይህን በማድረግ፣ እንድናከናውን ለሚጠራን ለማንኛውም አገለግሎት ዝግጁ እንሆናለን። ይህ የእርሱ ስራ ነው። ይህ የእርሱ ቤተክርስቲያን ነው። ሻምበላችን ነው፣ የክብር ንጉስ እንዲሁም የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ህያው እንደሆነ እመሰክራለሁ እናም ይህን ምስክር በቅዱስ ስሙ እመሰክራለሁ፣ አሜን።