2010–2019 (እ.አ.አ)
የክህነት እና የግል ፀሎት
ኤፕረል 2015


16:58

የክህነት እና የግል ፀሎት

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እግዚአብሔር በክህነት ውስጥ ሀይል ሊሰጠን ይችላል። የሚጠበቅብን በትህትና መጠየቅ ብቻ ነው።

በአለም ላይ ላሉ የክህነት ተሸካሚዎች ለመናገር ስለ ታመንኩ አመስጋኝ ነኝ። የዛ እድል ክብደት ይሰማኛል ምክንያቱ ጌታ በእናንተ ላይ ስለጣለው እምነት አንድነገር አውቃለሁ። ክህነት ከመቀበላችሁ ጋር፣ ለእግዚያብሄር ስም ለመናገር እና ለመተግበር መብት ተቀብላችኋል።

ከእግዚያብሄር መነሳሳትን ስትቀበሉ ብቻ ያ መብት እውነታ ይሆናል። ከዚያ በኋላ ብቻ ነው በእርሱ ስም መናገር የምትችሉት። እናም ከዚያ በኋላ ብቻ በእርሱ ስም መስራት ትችላላችሁ። እንደዚህ በማሰብ ስህተትን ሰርተን ይሆናል “ኦህ ያ ምንም አያስቸግረኝም። ንግግር ለመስጠት መቼም ብጠየቅ ወይም የክህነት በረከት መስጠት መቼም ቢያስፈልገኝ መነሳሳትን ማግኘት እችላለሁ።” ወይም ወጣት ዳቆን ወይም አስተማሪ እድሜዬ ሲያድግ ወይም እንደ ሚሲዮናዊ ስጠራ፣ ከዚያ በኋላ እግዚያብሄር የሚለውን እና የሚናገረውን አውቃለሁ።” በሚለው መፅናናትን ሊያገኙ ይችላሉ።

እግዚያብሄር ምን እንደሚል እና ምን እንደሚያደርግ ማወቅ የሚኖርባችሁን ቀን አስቡ። በክህነት ጥሪያችሁ ውስጥ የትም ብትሆኑ— ለሁላችንም አስቀድሞ መጥቷል። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ ጥቂት በሚስኦን መስክ ውስጥ አደኩ። አባሎች ተራርቀው ነበር የሚኖሩት፣ እናም ክፉኛ የጋዝ እጥረት ነበር። በቅርንጫፍ ውስጥ ዳቆን እኔ ብቻ ነበርኩ። ለፆም እና ምስክርነት ስብሰባ ወደ እኛ ቤት ውስጥ ሲመጡ አባሎች የፆም በኩራት ኤንቨሎፖቸውን ለቅርንጫፍ ፕሬዘዳንቱ ይሰጣሉ።

በ13 አመቴ፣ በትልቅ አጥቢያ ውስጥ ለመኖር ወደ ዩታህ ቤት ቀየርን። የመጀመሪያ የቤት ስራዬ ወደ ቤቶች በመሄድ በኩራቶችን መሰብሰብ እንደሆነ አስታውሳለሁ። ከኤንቨሎፖቹ መካከል አንዱ ላይ ያለውን ስም ተመለከትኩ እና የመጨረሻ ስሙ ከመፀሀፈ ሞርሞን ሶስት ምስክሮች መካከል ከአንዱ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ተገነዘብኩ። በራስ በመተማመን በሩን አንኳኳሁ። ሰውዬው በሩን ከፈተ፣ ተመለከተኝ፣ ፊቱን አጨማደደ፣ ዞር እንድል ጮኸብኝ። አንገቴን አቀርቅሬ ተመለስኩ።

ያ የዛሬ 70 አመታት አካባቢ ነበር፣ የሆነ ነገር መናገር እና ማድረግ እንደነበረብኝ ያንን ቀን በበሩ ደረጃ ላይ የነበረኝን ስሜት እስካሁን አስታውሳለሁ። የዛን ቀን ስወጣ በእምነት ፀልዬ ብቻ ቢሆን ኖሮ በር ላይ ከመርገጥ የበለጠ ጊዜን ለመቆየት እነሳሳ ሊሆን እችል ነበር፣ ፈገግ ብዬ፣ እንደዚህ እል ነበር፤ “ ስላገኘሁህ ደስ ብሎኛል። ባለፉት ጊዜያት አንተ እና ቤተሰብክ ለሰጣችሁት አመሰግናለሁ።”

ያንን ብል እና ባደርግ ኖሮ፣ የበለጠ ሊናደድ እና እንዲሁም ሊከፋ ይችል ነበር። ነገር ግን እኔ እንዴት ሊሰማኝ እንደሚችል አውቃለሁ። ዞር ብዬ ስሄድ ከተሰማኝ የሀዘን ስሜት ይልቅ፣ በአእምሮዬ እና በልቤ ውስጥ፤ “መልካምን አደረክ” የሚል የምስጋና ስሜት ተሰምቶኝ ሊሆን ይችል ነበር።

ሁላችንም ውሳኔያችን ያለ መነሳሳት በቂ በማይሆንበት ቦታ ላይ በእግዚያብሄር ስም መናገር እና መተግበር አለብን። እነኝ ሁኔታዎች ዝግጅት ለማድረግ ጊዜ በማይኖረበት ቦታ ላይ ወደ እኛ ሊመጡ ይችላሉ። ያ በእኔ ላይ በብዛት ተከስቷል። ከብዙ አመታት በፊት አባት በሆስፒታል ውስጥ በአስጊ ሁኔታ የተጎዳችው የ3 አመት ሴት ልጁ በደቂቃዎች ውስጥ ዶክተሩ እንደምትሞት እንደነገረው ሲያወራ ሆኗል። በባንዴጅ ባልታሰረው ግንባሯ በኩል እጆቼን ሳደርግ፣ የጌታ አገልጋይ እንደመሆኔ፣ ምን እንደማደርግ እና ምን እንደምል፣ ማወቅ ነበረበኝ።

በህይወት እንደምትኖር ቃላቶቹ ወደ አእምሮዬ እና ከንፈሮቼ መጡ። ዶክተሩ በአስጠሊታ ሁኔታ ከጎኔ ቆሞ ደነፋ እናም ከምንገድ ላይ ዞር እንድል እኔን ጠየቀኝ። በሰላም እና በፍቅር ስሜት ከሆስፒታሉ ክፍል ወጣሁ። ትንሽዋ ልጅ በህይወት ኖረች እናም በዛች ከተማ በመጨረሻዬ ቀን በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ ውስጥ መተላለፊ ላይ ወደ ታች ተራመደች። በጌታ አገልግሎት ለዛች ለትንሽ ልጅ እና ለቤተሰቦችዋ የተናገርኩት እና ካደረኩት የተሰማኝን ደስታ እና እርካታ እስካሁን አስታውሳለሁ።

የስሜቶቼ ልዩነት፣ በሆስፒታል እና እንደ ዳቆን ከበሩ ላይ ዞር ብዬ ስሄድ የተሰማኝ የሀዘን ስሜት፣ የመጣው የፀሎት ከክህነት ሀይል ጋር ያለውን ግንኙነት ስለተማርኩ ነበር። እንደ ዳቆን፣ በእግዚያብሄር ስም የመናገር እና የመስራት ሀይል ራእይን እንደሚጠይቅ ገና አልተማርኩም ነበር፣ እናም ሲያስፈልገን ለመንፈስ ቅዱስ አጋርነት ፀሎት እና በእምነት መስራትን ይጠይቃል።

ለበኩራት ወደእዛ በር ከመሄዴ በፊት በነበረው ምሽት ላይ፣ ልተኛ ስል ፀሎት አድርጌያለሁ። ነገር ግን ከሆደስፒታል የስልክ ጥሪ ከመምጣቱ ለሳምንታት እና ለወራት በፊት፣ የፀሎት እና በክህነት ውስጥ ሀይል እንዲኖረን የሚያስፈልገውን መነሳሳት እግዚያብሄር እንዲሰጠን የሚያስችለውን ፕሬሰዳንት ጆሴፍ  ኤፍ. ስሚዝ ያስተማሩትን ሂደት ለመከተል ጠረት አድርጌያለሁ። በቀላሉ እንዲህ አለ፤

“በብዙ ቃላቶች ወደ እሱ መጮህ የለበንም። በረጅም ፀሎቶች ልናደክመው አያስፈልገንም። ማድረግ የሚያስለልገን፣ እናም እንደ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን ማድረግ ያለብን፣ ለራሳችን ጥቅም፣ በብዛት ከፊቱ ሄደን፣ እሱን እንደምናስታውሰው ለመመስከር እና የሱን ስም በላያችን ላይ ለመውሰድ፣ ትዕዛዛቶቹን ለመጠበቅ በቅድስና መስራት።”1

እናም ከዚያ ለምን መፀለይ እንዳለብን ነግሮናል፣ የሱ አገልጋዮች እንደሞሆናችን ለእግዚያብሄር ለመናገር እና ለመስራት ቃል ገብተናል። እነዲህ አለ፤ “ ምትፀልት ምን ለማግኘት ነው? እግዚያብሄር ይቀበላችሁ ዘንድ፣ ፀሎታችሁን ይሰማ ዘንድ ፀልዩ።2

በይበልጥ የትኛውን ቃላት የመጠቀም ጉዳይ አይደለም፣ ነገር ግን የተወሰነ ትዕግስትን ይጠይቃል። በእርሱ የግል እውቅናን ለማግኘት ፍላጎት የሰማይ አባታችሁን ለመግባባት የሚደረግ ዘዴ ነው። ከሁሉም በላይ እሱ እግዚያብሄር ነው፣ የሁሉም አባት ነው፣ እናም ሆኖም ከልጆቹ ለአንዱ ሙሉ ትኩረትን ለመስጠት ፍቃደኛ ነው። ለዛም ይሆናል አዳኝ እነኚህን ቃላት የተጠቀመው፣ “ በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።”3

ስትንበረከኩ እና ጭንቅላታችሁን ዝቅ ስታደርጉ ተገቢውን የአምልኮ ስሜት ማግኘት በጣም የቀለለ ነው፣ ነገር ግን በብዛት ማድረግ እንዳለባችሁ፣ ባነሰ መደበኛ እና ዝግ ባለ ፀሎት የሰማይ አባታችሁን እየቀረባችሁ መሆኑን ሊሰማችሁ ይችላል። አብዛኛው ቀን ጫጫታ እና ሰዎች በዙሪያችሁ ይኖራሉ። እግዚያብሄር ፀጥ ያለ ፀሎታችሁን ይሰማል። ነገር ግን የሚረብሹ ነገሮችን ችላ ማለት ሊኖርባችሁ ይችላል መክንያቱም ከእግዚያብሄር ጋር ግንኙነት ያስፈለጋችሁ ሰዓት ፀጥ ባለ ጊዜያት ላይሆን ይችላል።

እናንተ እሱን ለማገልገል ያላችሁን ጥሪ እግዚያብሄር እንዲያውቅላችሁ መፀለይ ይኖርባችኋል ብለው ፕሬዘደንት ስሚዝ ሀሳብ ሰጡ። ስለጥሪያችሁ በተሟላ ዝርዝር አስቀድሞ ያውቃል። እናንተን ጠርቷችኋል፣ እናም ስለጥሪያችሁ በመፀለይ፣ እናንተ እንድታውቁ የበለጠ ይገልፅላችኋል።4

አንድ የቤት ለቤት አስተማሪ እየፀለየ ሳለ ማድረግ ሊኖርበት የሚችለውን ምሳሌ ሰጣችኋለሁ። እናንተ እነኚህን ለማድረግ አስቀድማችሁ ልታውቁ ትችላላችሁ፤

“የእያንዳንዱን አባል ቤት ጎብኙ፣ በድምፅ እና በሚስጢር እንዲፀልዩ እናም ለቤተሰብ ሀላፊነትታቸው እንክብካቤ እንዲሰጡ በመምከር……

“… ሁሌም ቤተክርስቲያኑን እንዲጠብቁ፣ አብሮ በመሆን እና እነሱን በማጠንከር፤

“በቤተክርስቲያን ውስጥ ሀጢያት እንዳይኖር በማድረግ፣ እርስ በእርስ ክፋትንም ቢሆን፣ ውሸትም ቢሆን፣ ሀሜት፣ ክፋት ያለው ንግግርንም ቢሆን፤

“በቤተክርስቲያኑ በአብዛኛው ጊዜ እንዲሰበሰቡ በማድረግ፣ እናም እንዲሁ ሁሉም አባላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በማድረግ።”5

አሁን፣ ልምድ ላለው የቤት ለቤት አስተማሪ እና ለታናሽ አጋሩም ቢሆን፣ ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያ በግልፅ የማይቻል ነው። ለማገልገል የተጠራችሁትን ቤተሰብ ወይም እነዲሁም ግለሰብ አስቡ። የሰው ልጅ ውሳኔዎች ወይም መልካም ሀሳቦች በቂ አይሆንም።

ስለዚህ ልቦችን ለማወቅ ፣ በደንብ የማታውቋቸውን ሰዎች በህይወታቸው እና በልቦቻቸው ውስጥ ምን የተሳሳተ ነገሮች እንዳሉ መንገዱን ለማወቅ ትፀልያላችሁ። እነርሱን ለመርዳት እና እግዚያብሄር ለነርሱ ባለው ፍቅር ስሜት በቻላችሁት መጠን ሁሉንም በማድረግ እግዚያብሄር እንድታደርጉ የሚያደርገውን ማወቅ አለባችሁ።

በጣም ጠቃሚ እና አስቸጋሪ የክህነት ጥሪዎች ስላላችሁ ነው ፕሬዘዳንት ስሚዝ ስትፀልዩ፣ በመንፈስ ይባርካችሁ ዘንድ ሁሌም እግዚያብሄርን ለምኑ ብለው ሀሳባቸውን የሰጡት። ለእናንተ ቋሚ ጓደኛ እንዲሆን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እግዚያብሄር የሚሰጠንን ያህል፣ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል። ለልጆቹ ባለን አገልግሎት ላይ ምሬትን እንዲሰጠን ለዛ ነው ሁሌም ለእግዚያብሄር መጸለይ ያለብን።

ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን ካልሄደ በስተቀር የክህነት አቅማችን ላይ መድረስ አንችልም። ለደስታ ሁሉ ጠላት እናንተ ኢላማዎች ናችሁ። ሀጢያት ለመስራት እርሱ የሚፈትናችሁ ከሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስ የመመራት ሀይላችሁን መቀነስ ይችላል እናም በውጤቱም በክህነት ውስጥ ያላችሁን ሀይል ይቀንሰዋል። ለዛ ነው ፕሬሰዳንት ስሚዝ ከሀጠያት እንዲያስጠነቅቀን እና እንዲጠብቀን ለእግዚያብሄር ሁሌም መፀለይ አለባችሁ ያሉት።6

በብዙ መንገድ አስጠንቅቆናል። ማስጠንቀቂያዎች የመዳን እቅድ አካል ናቸው። ነብያት፣ ሀዋሪያት፣ የካስማ ፕሬዘዳንቶች፣ ኢጲስ ቆጶሶች፣ እና ሚሲዮናዊያን ሁሉም መቅሰፍትን ለማምለጥ በእየሱስ ክርስቶስ እምነት፣ ንስሀ፣ የተቀደሱ ቃልኪዳኖች እንድንገባ እና እንድንጠብቅ የማስጠንቀቂ ድምፃቸውን የሚያነሱት።

እንደ ክህነት ተሸካሚነታችሁ፣ የጌታ ማስጠንቀቂያ ድምፅ ክፍል ልትሆኑ ይገባል። ነገር ግን እራሳችሁም ማስጠንቀቂያውን መስማት ያስፈልጋችኋል። በቀን ተቀን ህይወታችሁ ውስጥ ያለ መንፈስ ቅዱስ አጋርነት ጥበቃ በመንፈሳዊ መኖር እንደማትችሉ ያለውን ማስጠንቀቂያ መቀበል አለባችሁ።

እሱን ለማግኘት መፀለይ እና መስራታ አለባችሁ። በጨለማው ክፋት ውስጥ ቀጭኑ እና ጠባቡን ጎዳና የምታገኙት በዛ ምሬት ብቻ ነው። የነብያቶችን ቃላት ስታጠኑ እውነትን በመግለፅ መንፈስ ቅዱስ ምሬት ይሆናችኋል።

ምሬትን ማግኘት ከግድ የለሽ ማዳመጥ እና ማንበብ በላይ ይጠይቃል። የእውነትን ቃላት ከልባችሁ ውስጥ በታች ለማስቀመጥ በእምነት መፀለይ እና መስራት ይኖርባችኋል። እግዚያብሄር በእሱ መንፈስ እንዲባርካችሁ፣ ወደ እውነቶች ሁሉ እንዲመራችሁ እና ትክክለኛውን መንገድ እንዲያሳያችሁ መፀለይ ይገባችኋል። በህይወታችሁ ውስጥ እና በክህነት አገልግሎታችሁ ውስጥ እንደዛ ነው የሚያሲጠነቅቃችሁ እና የሚመራችሁ።

በእግዚያብሄር ክህነት ውስጥ ለማገልገል ጌታ ሀይላችሁን ለማጠንከር እንዲችል አጠቃላይ ጉባኤ ታላቅ እድልን ያቀርብላችኋል። በፀሎት እራሳችሁን ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ከሚፀልዩት ጋር እምነታችሁን ማገናኘት ትችላላችሁ። በዚህ ጉባኤ ውስጥ ብዙ ሰዎች ላይ ለብዙ በረከቶች ይፀልያሉ።

ነብያቶች የጌታ ቃል አቀባይ እንደመሆናቸው መንፈስ በነቢያቶች ላይ እንዲመጣ ይፀልያሉ። ለሀዋሪያቶች እና በእግዚያብሄር ለተጠሩ አገልዳዮች ሁሉ ይፀልያሉ። ያ እናንተን ከአዲስ ዳቆን እስከ ልምድ ያለው ከፍተኛ ካህን ድረስ ያላችሁትን ያጠቃልላል እና አንዳንዶች ወደ መንፈስ አለም በቅርቡ ሊሄዱ ሚችሉት ወጣትም እና አዛውንት ሁለቱም፣ “መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝ ባርያ።” የሚለውን የሚሰሙበት ቦታ ለሚሄዱትም።7

ያ ሰላምታ ሲሰጥ አንዳንዶች በእርሱ ይገረማሉ። በእግዚያብሄር የምድር መንግስት ውስጥ ትልቅ ስልጣን ይዘው ላያውቅ ይችላላ። አንዳንዶች ከስራቸው ትንሽ ውጤትን ያዩ ያህል ወይም አንዳንዶች ለማገልገል አንዳንድ እድሎች ተስጥቷቸው እንደማያውቅ ሊሰማቸው ይችላል። ሌሎች በዚህ ህይወት ውስጥ ተስፋ ያረጉት የማገልገል ጊዜ በቂ እንዳነሰባቸው ሊሰማቸው ይችላል።

ጌታ ጋር ሚዛን የሚደፋው የያዝነው ስልጣኖች ወይም ያገለገልንበት ጊዜ አይደለም። ይህንን ምንም ያህል ያገልግሉ ወይም የትም ይስሩ ክፍያው ተመሳሳይ የተከፈላቸው ስለ የወይን ተክል ሰራተኞቹ ከጌታ ምሳሌ እናውቃለን። ባገለገሉበት መንገድ ይሸለማሉ።8

በወይን ተክል ውስጥ ያለው ጊዜ ሊያልቅ የደረሰበትን ሰው አውቃለሁ። የካንሰር ህመም ለብዙ አመት ህክምና ተከታትሏል። በነኚህ የህክምና አመታት፣ በዋርድ ውስጥ ያሉ ልጆቻቸው ከቤት ለቀው የወጡ አባላትን ጋር ሳምንታዊ ስብሰባዎችን እንዲያደርግ እና በነሱ ላይ ሀላፊነት እንዲኖረው ጥሪን ተቀበለ፣ አንዳንዶች ባላቸው የሞተባቸው ነበሩ። የእርሱ ጥሪ በማህበረሰብ ውስጥ እና በወንጌል መማር ውስጥ መፅናናትን እንዲያገኙ መርዳት ነበር።

ለመኖር አጭር ጊዜ ብቻ እንዳልው የመጨረሻ የረጋ ትንበያን ሲያገኝ፣ የእርሱ ኤጲስ ቆጶስ ለስራ ጉዞ ሄዶ ነበር። ከሁለት ቀን በኋላ፣ በእሱ ከፍተኛ ካህን የቡድን መሪ አማካኝነት ለኤጲስ ቆጶሱ መልእክትን ላከ። እርሱ ስለስራው እንዲህ ይላል፤ “ኤጲስ ቆጶሱ ከከተማ ውጭ እንዳለ ይገባኛል፣ ስለዚህ እኔ ነኝ ወሳኙ። በሚቀጥለው ሰኞ በእኛ ቡድን ስብሰባ እንዲኖር እያሰብኩኝ ነው። ሁለት አባሎች ወደ ጉባኤው ማዕከል ለጉብኝት ሊወስዱን ይችላሉ። አንዳንድ አባላትን በመኪና እንዲወስዷቸው እና አንዳንድ ስካውቶችን ዊልቸሮችን እንዲገፉ መጠቀም እንችላለን። የሚመዘገበው ሰው ላይ በመመርኮዝ፣ አንዳንድ ተለቅ ያለንው እራሳችን ለማድረግ በቂ ልንሆን እንችላለን፣ ነገር ግን ካስፈለገን ለመርዳት ተጨማሪ እርዳታ እንዳለን ማወቅ ጥሩ ይሆናል። እርዳታ የሚሰጡት ቤተሰባቸውን ቢያመጡ ራሱ ጥሩ የቤተሰብ ምሽትም መሆን ይችላል። ለማንኛውም እቅዱን ከመለጠፌ በፊት አሳውቀኝ።… አመሰግናለሁ።”

እና ከዛም እርሱ በስልክ ጥሪ ኤጲስ ቆጶሱን አስደነቀው። እሱ ስለ እራሱ ሁኔታ ሳይጠቅስ ወይም በጀግንነት ጥረት፣ እንዲህ ጠየቀ፣ “ኤጲስ ቆጶስ፣ ለአንተ ማድረግ የምችለው ማንኛውም ነገር አለ?” የእርሱ የራሱ ሸክም በዝቶ እያለ የኢጶስ ቆጶሱ ሸክም እንዲሰማው ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። ወንድሞቹን እና እህቶቹን ለመርዳት ወጣት በነበረበት ጊዜ ስካውቲንግ ዝግጅት ለማዘጋጀት የተጠቀመበትን ተመሳሳይ እቅድ ለመፍጠር ያስቻለው መንፈስ ብቻ ነበር።

በእምነት ፀሎት፣ በማንኛውም ሁኔታ ብንሆንም እግዚያብሄር በክህነት ውስጥ ሀይልን ሊሰጠን ይችላል። ለእግዚአብሔር እንድንናገርለት እና እንድንሰራለት መንፈስ እንዲያሳየን በትህትና ቀላል ጥያቄዎችን መጠየቅ ነው የሚያስፈልገው፣ አድርጉት፣ እናም የዛን ስጦታ በብቁነት መኖርን ቀጥሉ።

እግዚያብሄር አባት ህያው እንደሆነ፣ እንደሚወደን፣ እና ፀሎቶቻችንን እንደሚሰማ ምስክርነቴን ሰጣችኋለሁ። ኢየሱስ በህይወት ያለ ክርስቶስ እንደሆነ፣ የኃጢያት ክፍያው ለመንፃት እና ለመንፈስ ቅዱስ አጋርነት ብቁ እንድንሆን እንዳስቻለን ምስክርነቴን እሰጣለሁ። በእምነታችን እና በትጋታችን አንድ ቀን “መልካም፣ አንተ በጎ ታማኝ ባርያ።”9 የሚለውን ደስታ የሚያመጣውን ቃላት እንደምንሰማ እመሰክራለሁ። በምናገለግለው ጌታ ያንን አስደናቂ ቡራኬ እንድንቀበል እፀልያለሁ። በኢየሱስ በክርስቶስ ስም፣ አሜን።