2010–2019 (እ.አ.አ)
ጌታን መሻት
ኤፕረል 2015


9:42

ጌታን መሻት

ስለ አዳኝ የእኛን መረዳት ጥልቅ ስናደርግ፣ በደስታ ለመኖር እና ያ ደስታ እንደሚቻል የፀና እምነትን ለመጨመር ፍላጎት ይኖረናል።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች፣ በዚህ አጠቃላይ ጉባኤ በአንድነት ስንካፈል ከፊታችሁ ምቆመው በታላቅ ደስታ ነው። ባለፉት ብዙ አመታት ውስጥ በአጠቃላይ ጉባኤ ላይ የሚሰጡት የጥበብ ቃላት፣ ምክር፣ መፅናኛ፣ እና ማስጠንቀቂያ ማዳመጥ ለእህት ቴክሴራ፣ ለቤተሰባችን፣ እና ለእኔ የማይቆጠር በረከት ሆኗል።

በዚህ ልዩ በሆነው የአመቱ ወቅት፣ በተለይ በዚህ የፋሲካ ሰንበት እለት፣ በአዳኝ ትምህርቶች እና የሱ ደግነት እና በህወይቴ ውስጥ ስለ ተወዳጅ ምሳሌው ጠቀሜታ ላይ ማንፀባረቅ የግድ ይኖርብኛል።

በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጠለቅ ያለ መረዳት ለወደፊቱ ታላቅ ተስፋ ይሰጠናል፣ ጉድለቶች ቢኖርብንም፣ ፃድቅ የሆኑ ግቦቻችንን ለማሳካት ተጨማሪ በራስ መተማመን ይሆነናል።

ጌታ እንዲህ አለ፣ “በሙሉ ሀሳባችሁ እኔን ፈልጉ፤ አትጠራጠሩ፣ አትፍሩ።”1 ጌታን መሻት እና የእርሱን መኖር ስሜት ማግኘት የየቀን መጠይቅ ሆኖ ዋጋ ያለው ጥረት ነው።

ወንድሞች እና እህቶች፣ ዛሬ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርቶችን እና የእርሱን የሀጢያት ክፍያ መረዳታችንን ለማሳደግ ወደር የሌላቸው የተለዩ እድሎች እና መመሪያዎች አሉን። እነዚህን መመሪያዎች በአግባቡ መጠቀም በደስታ የተሞላ ውጤታማ ህይወት እንድንኖር ይረዳናል።

በኢየሱስ ክርስቶስ የወይን ግንድ እና ቅርንጫፎች ዘይቤአዊ አነጋገር ውስጥ፣ እንዲህ አለ፤ “በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳልቻለው፤ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።”2

በህይወታችን ውስጥ በጣም ልዩ የሆነውን የክርስቶስ ሚናን በበለጠ ስንረዳ፣ እዚህ በሟችነት ኑሮ ውስጥ ደስታ ለማግኘት የሆነውን፣ አላማችንን የበለጠ እንረዳለን። ያ ደስታ ግን ፈተናዎችን እና መከራዎችን ከመለማመድ አያግደንም፣ ምንም እንኳን አንዳንድ ታላቅ እና ረቂቅ ችግሮች በእነዚያ ሁኔታዎች ውስጥ ደስታ ሊኖር እንደማይችል እንድናስብ ሊመሩን ይችላሉ።

በዚህ የሟችነት ጊዜ በብዛት የሚከሰቱ መከራዎች ቢኖሩም በቅድስና የመኖር እና በክርስቶስ የመሆን ደስታ እንደሚቀጥል በግል ተሞክሮዬ ምክንያት አውቃለሁ። በመጨረሻም፣ እነኚ መከራዎች በአብዛኛው ጊዜ ያዳብሩናለ፣ ያሻሽሉናል፣ እናም የመኖራችንን አላማ እና የእየሱስ ክርስቶስን የሀጢያት ክፍያ ጠለቅ ወዳለ መረዳት ይመሩናል። በእርግጥ፣ የደስታ ሙሉነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ብቻ መፈፀም ይችላሉ።3

“እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔም ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፤ እርሱ ብዙ ፍሬን ያፈራል።”4

ስለ አዳኝ የእኛን መረዳት ጥልቅ ስናደርግ፣ በደስታ ለመኖር እና ያ ደስታ እንደሚቻል የፀና እምነትን ለመጨመር ፍላጎት ይኖረናል። ስለዚህ፣ በእያንዳንዱ ቀን ለህይወት እና የእግዚያብሄሔርን ትዕዛዛት በተሻለ ጉጉት ለመጠበቅ ታላቅ አቅም ይኖረናል፣ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆንም እንኳን።

ዛሬ ማድረግ የምንችለውን ለነገ አንተወው። ወደ ክርስቶስ መምጣት ያለብን አሁን ነው ምክንያቱም “[እኛ] ካመነው [እሱን] ዛሬ ተጠርቶ እያለ [እኛ] እንሰራለን።”5

በየቀኑ፣ ከክርስቶስ ትምህርቶች ጋር ዘወትር ግኑኝነት ማድረግን ከግንዛቤ ልናስገባ ይገባናል። ትንሽ እና ቀላል ምልክቶች እና ተግባሮች የየቀኑን ፍላጎት ይሰራሉ።

  1. በህይወታችን ውስጥ የጌታን ጠቀሜታ መረዳታችንን ጥልቅ ማድረግ፣ እናም

  2. ወንጌልን በቅንነት የመኖር መሳሌያችንን ሲመለከቱ፣ የሰማይ አባት እና የልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅርን በእርግጥ ለሚሰማቸው እያደጉ ካሉ ትውልዶች ጋር ይህ መረዳትን ለማካፈል ፍቃደኝነት ይረዳል።

ስለዚህ የክርስቶስን እና የተልኮውን ምስክራችንን በማጠንከር ለነፍሶቻችን መድኃኒት የሚሆኑ በዚህ ዘመናዊ ጊዜ ያሉ አንዳንድ ቀላል ባህሪዎች ምንድን ናቸው።

Woman on a train with a cell phone illuminating her face.

በ2014(እ.አ.አ)፣ National Geographic ፎቶ ማወዳደሪያ ከ150 አገራት በላይ ባሉ ባለ ሙያ ፎቶ አንሺዎች እና በጣም ፍላጎት ባላቸው ሰዎች 9200 ፎቶዎችን ተቀበለ። አሸናፊው ፎቶ አነድ ሴት በተሳፋሪዎች በተሞላ ባቡር መሃል ሆና ያሳያል። ከተንቀሳቃሽ ስልኳ የሚመጣው ብርሃን ፊቷ ላይ አብርቷል። ከሌላኛው ተሳፋሪ ጋር ግልፅ መልዕክት ተቀባበለች፤ በአካል ብትገኝም፣ በእውነት ግን እዛ እንዳልነበረች ነው።6

የሞባይል መረጃ፣ ሰማርት ስለኮች፣ እና የማህበረሰብ አውታሮች በምድር ውስጥ ያለንን አኗኗር እና ከሌሎች ጋር እንዴት እንደምንቀራረብ በጥቅሉ ቀይረውታል።

በዚህ የዲጂታል ዘመን ውስጥ፣ ወሳኝ ከሆነው ዘላለማዊ ደስታ ከተሞላው ህይወት እራሳችንን በፍጥነት ሊያስወግደን ከሚችለው ወደ ቦታዎች እና እንቅስቃሴዎች እራሳችንን በቶሎ ማዘዋወር እንችላለን።

ይሄ ተያያዥ ህይወት፣ ካልተቆጣጠርናቸው፣ አብረን ከምንኖራቸው፣ የራሳችን ቤተሰብ ይልቅ ለማናውቃቸው ሰዎች ወይም አግኝተን ለማናውቃቸው ሰዎች ግኑኝነት ቅድሚያውን ሊሰጥ ይችላል።

ከዛ በተረፈ በግሩም የኢንተርኔት ምንጮች፣ በቤተክርስቲያን በተሰሩ እንደ በፅሁፍ እና በድምፅ ያሉ የቅዱስ መፅሀፍቶች እና አጠቃላይ ጉባኤ እትሞች፣ የእየሱስ ክርስቶስ ህይወት እና ትምህርቶች ቪዲዮ ምርቶች፣ የቤተሰብ ታሪካችንን የምንመዘግብበት ቦታ፣ እናም የሚያነሳሱ መዝሙሮችን በመስማት እድሎች እንደተባረክን ሁላችንም እናውቃለን።

በኢንተርኔት ባለን ሰዓት ላይ የምናደርገው ምርጫዎች እና ቅድሚያዎች ወሳኝ ናቸው። መንፈሳዊ እድገታችንን እና በወንጌል ውስጥ መብሰላችንን እና ለተሸለ አለም መዋጮ የማድረግ ፍላጎት እና የበለጠ ውጤታማ ህይወት እንድንኖር ሊወስኑ ይችላሉ።

ለነኚህ ምክንያቶች፣ ጤናማ የኦን ላይን ስራን ለማቋቋም ሶስት ቀላል ልማዶችን መጥቀስ እወዳለሁ። እነኚህ ልማዶች ለሰማይ አባትና ለልጁ፣ እየሱስ ክርስቶስ ለመቅረብ ለማደግ የሚጠቅሙ የቀን ተቀን የግል ግምገማን ያስገኛሉ።

ልማድ ቁጥር 1፤ ለምንጮች የቤተክርስቲያንን ህጋዊ ድህረ ገፅ ጎብኙ

በአብዛኛው በሳምንቱ ቀናቶች እነኚህን ምንጮች መጎብኘት ሁልም ለወንጌል ትምህርቶች እና ቤተሰባችን እና ጓደኞቻችን የበለጠ የቱ እንደሚጠቅም ለማሰብ እና ስለ እሱ ለማሰላሰል ብርታት ስሜት እንዲኖረን ይረዳናል።

ልምድ ቁጥር 2፤ የቤተክርስቲያኑ ህጋዊ ማህበራዊ ኔትወርኮች ላይ ተመዝገቡ

ይህ ምርጫ የጌታን እና የሱን ትምህርቶች ፍለጋችሁን ጥልቅ እንድታደርጉ እና ወንጌልን ለመረዳት ፍላጎታችሁን ለማጠንከር ወደ ዕይታችሁ ፍሬ ነገርን ያመጣላችኋል። በይበልጥም፣ ይህ ክርስቶስ ከእያንዳንዳችን ምን እነደሚጠብቅ ለማስታወስ ይረዳናል።

ልክ “ ያለ መልካም አራሽ መልካም መሬት እንደሌለ፣”7 ልክ እነደዛው ለጣቶቻችን እና ለአእምሮዎቻችን ከመጀመሪያ ጀምሮ ጠቃሚ የሆኑትን ቅድሚያ ካልሰጠን በቀር መልካም የኢንተርኔት ምርትም አይኖርም።

ልምድ ቁጥር 3፤ ተንቀሳቃሽ የስልክ እቃዎቻችሁን ወደ ጎን ለመተው ጊዜን ፍጠሩ

የኤሌክትሪክ መሳሪያዎቻችንን ለጊዜው ወደ ጎን አድርገን እና በእዚያ ፋንታ የቅዱሳንን ቃላት ገልፆች በመክፈት ወይም ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ግዜን መውሰድ ዘና ያደርጋል። በተለይ በጌታ ቀን፣ አዲስ መልእክት ወይም አዲስ የተለጠፈ ነገር እንዳላቹ ለማየት ያለ ማቋረጥ ግፊት ውጪ በቅዱስ ቁርባን ስብሰባ መካፈልን ሰላም ትቀምሳላችሁ።

ተንቀሳቃሽ መሳሪያ ወደ ጎን ለጊዜው የመተው ልምድ የህይወት ምልከታችንን ያዳብራል እና ያሰፋል፣ ምክንያቱም ህይወት በአራት ኢንች(10-ሴ.ሜ) አይወሰንም።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ፣ “ አብ እንደወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።”8 እግዚአብሔር ደስታ እንዲኖረን እና የእርሱ ፍቅር እንዲሰማን ይፈልጋል። ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን ይህ ደስታ እንዲቻል አደረገ። እርሱን በተሻለ ለማወቅ እና ወንጌሉን ለመኖር መንገዶች አሉን።

ትዛዛትን ስንጠብቅ ያለውን ደስታ እና በሰማይ አባት እና በልጁ፣ የኛ አዳኝ ፍቅር በመኖር የሚሰማንን ሰላም እና ደህንነት ምስክርነቴን አካፍላችኋለሁ። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን።