2010–2019 (እ.አ.አ)
አሁንም ድረስ ለእናንተ አስደናቂ ነው?
ኤፕረል 2015


10:13

አሁንም ድረስ ለእናንተ አስደናቂ ነው?

በወንጌል ተአምራት ላይ መደነቅ የእምነት ምልክት ነው። ያም በህይወታችን እና በአከባቢያችን ባለ ነገር ሁሉ የጌታን እጅ ማስተዋል ነው።

እፁብ ድንቅ ከሆነው የፓሪስ ከተማ አቅራቢያ ሚስቴ እና እኔ አምስት ልጆቻችንን በማሳደግ ታላቅ ደስታ ነበረን በነዚያ አመታት ጊዜ የዚህን አለም ድንቅ ነገሮች እንዲያውቁ ብዙ ፍቱን እድሎችን ለእነሱ ለማቅረብ ፈለግን በእያንዳንዱ በጋ፣ በጣም ትርጉም ያላቸውን ሀውልቶች፣ ታሪካዊ ቦታዎችን፣ እናም የአውሮፓ የተፈጥሮ አስገራሚ ነገሮችን ለመጎብኘት ቤተሰባችን ረጅም ጉዞን እናደርግ ነበር በስተመጨረሻም፣ በፓሪስ አካባቢ 22 አመታትን ካሳለፍን በኋላ፣ ቤት ለመቀየር ዝግጁ ነበርን ልጆቼ ወደ እኔ መጥተው “አባ በጭራሽ የሚያሳፍር ነው! ህይወታችንን በሙሉ እዚህ ኖረናል፣ እናም የአይፈል ማማን አይተን አናውቅም!”

በዚህ አለም ውስጥ ብዙ አስገራሚ ነገሮች አሉ ቢሆንም፣ አንዳንዴ በተከታታይ ሁኔታ ከአይኖቻችን ፊት ሲኖሩን፣ እንደ ዋዛ እናያቸዋለን እንመለከታለን፣ ነገር ግን በእርግጥ አናይም፤ እንሰማለን፣ ነገር ግን በእርግጥ አናዳምጥም።

በምድራዊ አገልግሎቱ ጊዜ፣ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤

“የምታዩትን የሚያዩ አይኖች ብፁዓን ናቸው፤

“እላችኋለሁና፣ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነብያትና ነገስታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፣ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ”1

በአዳኛችን ጊዜ መኖር ምን አይነት ሊሆን እንደሚችል ብዙ ጊዜ እገረማለሁ እግሮቹ ስር መቀመጥን? የሱን የማቀፍ ስሜት መሰማትን? ለሌሎችን ሲያገለግል ምስክር መሆንን ማሰብ ትችላላችሁ? እናም ቢሆንም እሱን ካገኙት ብዙዎቹ ሊያውቁት አልቻሉም— የእግዚያብሄር ልጅ እራሱ ከእነሱ መካከል እየኖረ እንደነበረ ለ“ማየት” አልቻሉም

እኛም ራሳችን ልዩ የሆነ ጊዜ ውስጥ ለመኖር ታድለናል የጥንት ነብያት የተመለሰውን ስራ እንደ “ድንቅ ነገር……… አዎን፣ ተአምራቶች እና ድንቅ ስራ”2 አዩ ባለፉት የእግዚያብሄር ስልጣን በነበረበት ጊዜያት በበለጠ ሁኔታ በዚኛው ብዙ ሚሲዮናዊያን ተጠርተዋል፣ ለወንጌል መልእክት ብዙ ህዝቦች ክፍት ሆነዋል፣ እናም በአለም ዙሪያ ብዙ ቤተ መቅደሶች ተገንብተዋል

ለእኛ፣ የኋለኛው ቀን ቅዱሳን እንደመሆናችን፣ በግል ህይወቶቻችን ውስጥ አስገራሚ ነገሮች ሊከሰቱ ይችላሉ እነሱም የራሳችንን የግል መለወጥ፣ ለፀሎቶቻችን የምንቀበላቸው መልሶችን፣ እና በእኛ ላይ በየቀኑ የሚፈሱ የእግዚያብሄር በረከቶችን ያካትታሉ

በወንጌል ታምራቶች ላይ መደነቅ የእምነት ምልክት ነው የእግዚያብሄር እጅ በህይወታችን ውስጥ እና በዙሪያችን ባሉ ሁሉ ነገሮች ውስጥ መኖሩን ማስተዋል ነው የእኛ መደነቅ መንፈሳዊ ጥንካሬንም ያመጣል በእምነታችን መልሕቅ እንድንቆይ እና እራሳችንን በመዳን ስራ ላይ ተሳታፊ ለማድረግ ጉልበትን ይሰጠናል

ነገር ግን እናስተውል ለመደነቅ ያለን አቅም የሚሰበር ነው በረጅም ጊዜያት ውስጥ፣ እንደ ትእዛዛትን በቸልተኝነት መጠበቅ፣ ስንፍና፣ ወይም ድካም ያሉ ነገሮች ይዘልቁ እና በጣም ድንቅ ለሆኑት የወንጌል ምልክቶች እና ታምራቶች ስሜት እንዳይኖረን ሊያደርጉን ይችላሉ

መጽሀፈ ሞርሞን ከእኛ ጋር በጣም የሚመሳሰል፣ የመሲሁን ወደ አሜሪካኖች መምጣት ክስተት፣ ወቅትን ይገልፃል በድንገት የእሱ መወለድ ምልክቶች በሰማያት ላይ ታዩ ሰዎቹ እራሳቸውን ትሁት እስኪያደርጉ ድረስ በጣም ተደንቀው ነበር፣ እና ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ ወደ ጌታ ተለወጡ ከአጭር አራት አመታት በኋላ ብቻ ቢሆንም፣ “ እናም ሰዎቹ እንዚያን ምልክቶች እናም የሰሟቸውን አስገራሚ ነገሮች መርሳት ጀመሩ፣ እናም ከሰማይ በሆነው አስገራሚ ምልክቶች መደነቃቸው መቀነስ ጀመረ፤…እናም ያዩዋቸውን እና የተመለከቱአቸውን በሙሉ አለማመን ጀመሩ”3

ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ ወንጌል ለእናንተ አሁንም ድረስ አስደናቂ ነውን? እስካሁን ማየት፣ መስማት፣ እና መደነቅ ትችላላችሁ? ወይም የመንፈሳዊነት ስሜታችሁ ቀንሷልን? የግል ሁኔታችሁ ምንም ቢሆንም፣ ሶስት ነገሮችን ለማረግ እጋብዛችኋለሁ

መጀመሪያ፣ የወንጌል እውነቶችን ለማግኘት ወይም ድጋሚ ለመለማመድ መፈለግ ላይ በጭራሽ አትድከሙ ፀሀፊው ማርሴል ፕሮውስት እንዲህ አለ “ትክክለኛ የግኝት ጉዞ የሚሰራው አዲስ የቦታ አቀማመጥን በመሻት አይደለም፣ ነገር ግን አዲስ አይኖችን በመያዝ ነው።”4 ለመጀመሪያ ጊዜ የቅዱሳት መፅሀፍት ጥቅስ አንብባችሁ እናም ጌታ ልክ ለእናንተ በግላችሁ እንደተናገራችሁ የተሰማችሁን ጊዜ ታስታውሳላችሁ? ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ምን አልባት መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ከመገንዘባችሁም በፊት፣ የመንፈስ ቅዱስ ጣፋጭ ተፅእኖ በላያችሁ ላይ ሲመጣ የተሰማችሁን ታስታውሳላችሁ? እነኚህ ቅዱስ፣ ልዩ የሆኑ ቅፅበቶች አልነበሩምን?

መንፈሳዊ እውቀት ለማገኘት በየቀኑ መራብ እና መጠማት አለብን ይህ የግል ትግበራ በጥናት፣ በማሰላሰል፣ እና በፀሎት ላይ ይገኛል አንዳንዴ እንደዚህ ለማሰብ ልንፈተን እንችላለን፣ “ቅዱሳት መፅሀፍትን ዛሬ ማጥናት አያስፈልገኝም፤ ሁሉንም ከዚህ በፊት አንብቤአቸዋለሁ” ወይም “ዛሬ ቤትክርስቲያን መሄድ አያስፈልገኝም፤ እዛ ምንም አዲስ ነገር የለም”

ነገር ግን ወንጌል በጭራሽ የማይደርቅ የእውቀት ምንጭ ነው በእያንዳንዱ እሁድ፣ በየስብሰባው፣ በእያነደዳነዱ የቅዱሳት መፅሀፍት ጥቅስ ውስጥ ለመማር እና ለመሰማት አንድ የሆነ አዲስ ነገር አለ በእምነት “ ከፈለግን እናገኛለን” የሚለውን ቃል ኪዳን አንለቅም።”5

ሁለተኛው፣ በግልፅ እና በቀላል የወንጌል እውነቶች ላይ እምነታችሁን መስርቱ የእኛ ግርምት በእምነታችን ዋና መርሆዎች ላይ፣ በቃልኪዳኖቻችን እና ስርአቶቻችን ንፅህና፣ እናም በአምልኮ ትግበራ ላይ መመስረት አለበት።

በአፍሪካ ውስጥ በነበረ የአውራጃ ጉባኤ ጊዜ ስላገኘቻቸው የሶስት ሰዎች ታሪክ አንድ እህት ሚስዮናዊ ተናገረች ቤተክርስቲያኑ ገና ካልተቋቋመበት ነገር ግን 15 ታማኝ አባላት እና ወደ 20 የሚጠጉ ስለቤተክርሰቲያን የሚማሩ ከነበሩበት እሩቅ ተነጥላ ካለች መነደር የመጡ ናቸው እነኚ ሰዎች ከሁለት ሳምንት በላይ በእግር ተራምደዋል፣ ጉባኤው ላይ ለመካፈል እና ከቡድናቸው አባሎች የተገኘውን አስራቶች ማምጣት እንዲችሉ በዝናብ ወቅት ጭቃማ በሆኑ መንገዶች ላይ 300 ማይሎች (480ኪ.ሜ) የሚበልጥ መንገድ ተጓዙ በቀጣዩ እሁድ ቅዱስ ቁርባን የመካፈል እድልን ለማግኘት ሳምንቱን ሙሉ ለመቆየት አቀዱ እና ከዚያ ለመንደራቸው ህዝቦች ለመስጠት የመፅሀፈ ሞርሞን ቅጂዎች የተሞሉ ካርቶኖችን በጭንቅላታቸው በመሸከም ለመመለስ ለጉዟቸውን አቀዱ

እነኚህ ወንድሞች ባሳዩት አስገራሚ ስሜት እና ለእርሷ ሁሌም በቀላሉ የተገኙትን ነገሮች ለማግኘት ከልብ በመነጨ መስእዋታቸው ምን ያህል ተነክታ እንደነበር ምስዮናዊቷ መሰከረች

እርሷ ተገረመች፤ “በአሪዞና አንድ ጠዋት ላይ ብነሳ እና መኪናዬ እንደማትሰራ ባውቅ፣ ከቤቴ ጥቂት ብቻ ወደ ሚርቀው ቤተክርስቲያኔ እራመዳለውን? ወይስ በጣም እሩቅ በመሆኑ ወይም ዝናብ እየዘነበ ስለሆነ እቤት እቆያለሁን?”6 እናስብባቸው ዘንድ እነኚህ ጥሩ ጥያቄዎች ናቸው

በስተመጨረሻም፣ የመንፈስ ቅዱስ አጋርነትን እንድትሹ እና እንድትንከባከቡ እጋብዛችኋለሁ አብዛኞች የወንጌል አስደናቂ ነገሮች እና ታምራቶች በተፈጥሮ ስሜቶቻችን መረዳት አይቻልም “አይን ያላያቸውን፣ ጆሮም ያልሰማው፣...እግዚያብሄር ለሚወዱት ያዘጋጀው” ነገሮች ናቸው።7

መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ሲኖረን፣ መንፈሳዊ ስሜቶቻችን ይቀርፃሉ እናም ያየነውን ታምራቶች እና ምልክቶች እና ምልክቶችን መርሳት እንዳንችል ትውስታችንን ይቀሰቅሳል ለዛ ነው፣ ክርስቶስ ትቷቸው ሊሄድ ሲል፣ የእሱ ኔፊያውያን ደቀመዛሙርት በስሜት እንዲህ ፀለዩ “እናም ይበልጥ ስለሚፈልጉትም ፀለዩ፤ እናም መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጣቸው ይፈልጉ ነበር”8

ምንም እንኳን አዳኝን በራሳቸው አይን ቢያዩትም እናም ቁስሎቹን በራሳቸው እጆች ቢነኩትም፣ በእግዚያብሄር መንፈስ ሀይል ያለማቋረጥ ካልታደሱ በስተቀር የእነርሱ ምስክርነቶች ሊደበዝዙ እንደሚችል ያውቁ ነበር ወንድሞች እና እህቶቼ፣ እነዚህን የከበረ እና እፁብ ድንቅ ስጦታ — የመንፈስ ቅዱስ አጋርነትን የማጣት አደጋ ውስጥ የሚጥል ምንም አይነት ነገር በጭራሽ አታድርጉ ከልብ በሆነ ፀሎት እና በፃድቅ ኑሮ አማካኝነት እሹት

እየተሳተፍን ያለንበት “ እስደናቂ ስራ እና ተአምር” እንደሆነ እመሰክራለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ስንከተል፣ በምልክቶች እና በድንቅ ነገሮችም፣ እናም ከልዩ ታምራቶች ጋር፣ እናም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች፣ እንደ ፈቃዱ እግዚያብሄር ለኛ ይመሰክርልናል።”9 በዚህ ልዩ ቀን፣ የወንጌል አስደናቂ ነገሮች እና ታምራቶች ከእግዚአብሄር ስጦታዎች ሁሉ ታላቅ በሆነው ስጦታው— የአዳኝ የሀጢያት ክፍያ ላይ እንደተመሰረተ ምስክርነቴን እሰጣለሁ ይህ አብ እና ወልድ፣ በአንድ አላማ፣ ለእያንዳንዳችን ያቀረቡልን ፍፁም የፍቅር ስጦታ ነው ከእናንተ ጋር “ ኢየሱስ ባቀረበልኝ ፍቅር ሙሉ ለሙሉ ተገርሜ ቆሜያለሁ...ኦህ፣ አስደናቂ ነው፣ ለኔ አስደናቂ ነው!” 10

ሁሌም የሚያዩ አይኖች፣ የሚሰሙ ጆሮዎች እናም የዚህ አስገራሚ የወንጌል ድንቅ ነገሮችን የሚቀበል ልብ ይኖረን ዘንድ ፀሎቴ ነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ አሜን